cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Abu Taymiyyah Amir Mohammed

‏قال الإمام الأوزاعي رحمه الله «عليك بآثار من سلف وإن رفضك الناس، وإياك ورأي الرجال وإن زخرفوه بالقول؛ فإن الأمر ينجلي وأنت منه على طريق مستقيم».

Show more
Advertising posts
1 466
Subscribers
+324 hours
-127 days
-3230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

The_Reality_of_the_Salafi_Methodology_Sheikh_Abdullāh_Ad_Dha.m4a47.61 MB
👍 3
አይሁዶች መርየምን በዝሙት መተቸታቸው ከተረገሙበት ውስጥ አንዱ ሁኖዋል። وَبِكُفْرِهِمْ وَقَوْلِهِمْ عَلَىٰ مَرْيَمَ بُهْتَانًا عَظِيمًا በመካዳቸውም በመርየም ላይ ከባድ ቅጥፈትን በመናገራቸውም ምክንያት (ረገምናቸው)፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አን'ኒሳእ 4:156
Show all...
ዒሳ (ኢየሱስ) ፉጥር ነው! አንዳንድ አላዋቂ ክርስቲያኖች ኢየሱስን አምላክ ለማድረግ ተራራን ካልተሸከምን ካልፈነቀልን ይላሉ ድካምን እንጂ አያተርፉም! ከመጢቅሶቸው የቁርኣን አናቅፅቶች መካከል - ወደ መርየም የጣላት ቃል - ከእርሱ የሆነ መንፈስ (ሩህ) በቀላሉ መልስ ለመስጠት እንዲህ ስለ ተባለ አምላክ ነው ማለት ነው? የሚል ጥያቄ እናቀርባላቸዋልን እነሱም *አዎን!* ይላሉ የዚህን ጊዜ ለአደም ዓለይሂ ሰላምም እነዚህን ተጠቅሞዋልና አደምንም አምላክ አድርጉት እንጂ ብለን እኒዛቸዋለን። فَإِذَا سَوَّيْتُهُ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِي فَقَعُوا لَهُ سَاجِدِينَ (ፍጥረቱን) ባስተካከልኩትና በውስጡ ከመንፈሴ በነፋሁበትም ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አል'ሂጅር 15:29 ➹ እዚህ ጋር ለአደም ዐለይሂ ሰላም ነው አገልግሎት የዋለው። إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡ 📘 ቁርኣን ሱራ አሊ ዒምራን 3:59 ➹ እዚህች ጋር አደምም እንደ ዒሳ ዒሳም እንደ አደም ሁለቱም በቃል እንደተገኙ ይገልፃል ቃሉ كن *ይኹን* በሚለው ሲሆን እነሱ ግን كن *ይኹን* የሚለው ቃል አይደለም በቃሉ የተገኙ ናቸው እንጅ። ይህንን ካለን ታዲያ ሩህ ፉጥር አይደለምን? ሩህ ፉጥር ነው። በዚህም ዙርያ አል'ሃፊዝ አቡ ዐብዲሏህ ብን መንዳህ "ፉጥር አይደለችም" በሚል ሰው ላይ ምላሽን በመስጠት አር'ሩህ ወን-ነፍስ የሚልን ትልቅን መፅሀፍ ፅፈዋል። መጅሙዑል ፈታዋ 4/218 ተመልከቱ ለምን ወደ አሏህ ተጠጋ ? ለማላቅ ለክብር ነው። ዒሳ ፉጥር እንደሆነ ከብዙ መረጃውች አንዱን ብቻ እናውሳ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት፡፡ 📘 ቁርኣን ሱራ አሊ ዒምራን 3:47 ➹ እዚህች ጋር *አሏህ የሚሻውን ይፈጥራል* በማለት ለመርየም ዒሳ የተፈጠረ ፉጥር መሆኑን እንደተገለፀላት በግልፅ አስቀምጦታል። 🖋 አቡ ተይሚያ
Show all...
አሏህ ለመኖሩ (abt Existence) የመጀመሪያው መረጃ ፊጥራ (innate/inspection) ነው እንጂ ፍጥረታ ዓለሙ መኖሩ የመጀመሪያው አይደለም። - ይህም ርዕስ በአህሉ ሱናህዎችና በአሻዒራዎች መሀከል የልዩነት ርዕስ ሆኖዋል።
Show all...
👍 2
አደም ዐለይሂ ሰላም የነበሩባት ገነት ዘውታሪ ገነት ናት ወይስ ምድራዊ ገነት ናት? - ለአደም በሰማይም በምድርም ያሉ ሁሉም መላእክቶች ሰገዱላቸው ወይስ በምድር ያሉት ብቻ? - እውን ጅብሪል ሚካኢልም ከሰጋጆች ውስጥ ነበሩን? - አደም ዐለይሂ ሰላም የነበሩባት አሁንም የምትገኝ ዘውታሪ ገነት ነበረች? ወይም ምድራዊ ገነት ሁኖ ለሱ (ለአደም) አሏህ የፈጠራት ነበረች? - ከሰማይ ወደ ምድር ወረዱ ወይስ ከምድር ወደ ምድር እንደ በኒ ኢስራኢሎች ወረዱ? 📌 መልስ ምስጋናዎች በአጠቃላይ ለአሏህ የተገቡ ናቸው። ለአደም ሁሉም መላእክቶችን አሰግዶለታል በዚህ ጉዳይ ከፍ ባለው ጌታች ቃል መሰረት በቁርአን ውስጥ በግልፅ ተቀምጦዋል። فَسَجَدَ الْمَلَائِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ መላእክትም መላውም ተሰብስበው ሰገዱ፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አል'ሂጅር 15:30 * الْمَلَائِكَة * የታወቀ የብዜት (plural) ስም (noun) በአሊፍ እና በላም (ل) ከተገነባ ጠቅላይነት ያሲዛል። እንዲሁ "ሁሉም መላእክት አልሰገዱም በምድር ያሉ መላእክት ነው የሰገዱት" ያለ አካል በእርግጥም ቁርኣንን በውሸትና በቅጥፈት መልሶዋል [አልተቀበለም]። እንዲህ [1] አይነት ንግግር የሙስሊም የአይሁዶችም የነሷሯዎችም ንግግር አይደለም በል እንዲያውም እነዚያ መላእክትን መልካሚቷ ነፍስ ሸያጢንን የመጥፎው'ዊቷ ነፍስ የሚያደርጉ (የሚሉ) የኢ-አማኝ ፈላሲፋዎች ንግግር ነው።..... ይህም [2] ንግግር የቀራሚጣዎች የባጢኒያዎች እንዲሁም የነሱን የጥመት ጎዳና የተጓዙ ሰዎች ንግግር ነው። አሏህ በቁርኣን ላይ ባወሳው ላይ የሙስሊሞች የአይሁዶች የነሷሯዎችም መንገድ በስግደት ከታዘዙት ውስጥ አንድም ከሸያጢን አነበረም ነገር ግን አባታቸው ኢብሊስ ታዞ ነበር እምቢም አለ አመፀም። ከፊል ሰዎች ኢብሊስን ከመላእክቶች ጋር በመታዘዙ ከመላእክቶች መደቡት ከፊሎች ደግሞ ከጂኖች ምክንያቱም ለሱ ነገዶችና ዘሮች አሉትና ነገር ግን ከእሳት (ኢብሊስ) ተፈጠረ መላእክት ደግሞ ከብርሀን ተፈጠሩ። እውነታው እሱ ከመሰረቱና ከምሳሌው አንፃር ሳይሆን ከገፅታ አንፃር ከእነሱ ጋር ነበረ። ለአደም ከመስገድ ከመላእክቶች አንድም አልወጣም (አልቀረም) ጅብሪልም ሚካኢልም ሌሎችም ቢሆኑ። አደም እና ባለቤታቸው ያረፉባት የነበረችው ገነት ሰለፎችና አህሉ ሱናህዎች ዘንድ ዘውታሪ ገነት ናት። እሷ ምድራዊ ገነት ናት በሕንድ ወይም በጂዳ የምትገኝ ወይም ከዚህም ውጭ ሌላ ያለ አካል እሱ ከፈላስፎችና ከአቆልማሚዎች ወይም ከእነሱ ወንድሞቻቸው ከአህሉል ከላም ከሙብተዲዖች ነው። ይህንን የሚናገረው ከፈላስፎች ከሙዕተዚላዎች ነው። ቁርኣንና ሀዲስ በዚህ ንግግር ላይ ምላሽ ይሰጣል እንዲሁም ቀደምት ህዝቦች ይህ ንግግር ባጢል በመሆኑ ላይ ይስማማሉ። ከፍ ያለው እንዲህ አለ:- وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡ وَقُلْنَا يَا آدَمُ اسْكُنْ أَنتَ وَزَوْجُكَ الْجَنَّةَ وَكُلَا مِنْهَا رَغَدًا حَيْثُ شِئْتُمَا وَلَا تَقْرَبَا هَٰذِهِ الشَّجَرَةَ فَتَكُونَا مِنَ الظَّالِمِينَ «አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትኾናላችሁና» አልንም፡፡ فَأَزَلَّهُمَا الشَّيْطَانُ عَنْهَا فَأَخْرَجَهُمَا مِمَّا كَانَا فِيهِ ۖ وَقُلْنَا اهْبِطُوا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ وَلَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَاعٌ إِلَىٰ حِينٍ ከርሷም ሰይጣን አዳለጣቸው በውስጡም ከነበሩበት (ድሎት) አወጣቸው፡፡ «ከፊላችሁም ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ» አልናቸው፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አል'በቀራ 2:34-36 በእርግጥም ጥራት የተገባው ጌታችን ከፊሉ በከፊሉ ላይ ጠላት ሆኖ ሳለ በመውረድ ላይ እንዳዘዛቸው ገለፀ ይህም በምድር እንዳልነበሩ ግልፅ ያደርጋል ቀጥሎም وَلَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَاعٌ إِلَىٰ حِينٍ "ለናንተም በምድር ላይ እስከ ጊዜ (ሞታችሁ) ድረስ መርጊያና መጣቀሚያ አላችሁ" ይህ እነሱ በምድር ላይ እንዳልነበሩ ግልፅ ያደርጋል በል እንዲያውም ወደ ምድር ወረዱ በምድር ላይ የነበሩ ቢሆን ኖሮ ወደ ሌላ ምድር በተዘዋወሩ ነበር እንደ ሙሳ ህዝቦች። قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ (አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡ «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡ قَالَ فَاهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَاخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ الصَّاغِرِينَ ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አል'አዕራፍ 7:12-13 قَالَ اهْبِطُوا بَعْضُكُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ ۖ وَلَكُمْ فِي الْأَرْضِ مُسْتَقَرٌّ وَمَتَاعٌ إِلَىٰ حِينٍ (አላህ) « ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ» አላቸው፡፡ قَالَ فِيهَا تَحْيَوْنَ وَفِيهَا تَمُوتُونَ وَمِنْهَا تُخْرَجُونَ «በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ» አላቸው፡፡ 📗 ቁርኣን ሱራ አል'አዕራፍ 7:24-25 - በመጨረሻም አደምና ሙሳ በተከራከሩ ጊዜ ሙሳ ከገነት አስወጣህን አሉ እንጂ ከምድር አስወጣህን አለማለታቸው ያቺ ገነት ዘውታሪዋ ለመሆኖ መረጃ ነው። 📌 هل الجنة التي سكنها ادم هي جنة الخلد 📚 መጅሙዑል ፈታዋ ጁዝእ 4 ላይ ቁጥር 345-349 مجموع فتاوى الجزء الرابع 345 ------------------------------- [1]. ሁሉም መላእክት አልሰገዱም የሚለው [2]. ሁሉም መላእክት አልሰገዱም የሚለው በግርድፉ የተተረጎመ 🖋 አቡ ተይሚያ
Show all...
👍 3
🔖የፍስልስጤ ወንድም እህቶቻችን ስንቶቻችን ነው በዱአ የምናስታውሳቸው? 👉አደራ የሚደርስባቸው ግፍና መከራ ልክ እንደራሳችን ህመም በመቁጠር በዱአ እናስታውሳቸው = t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Show all...
4_5792171141376257856.mp31.96 MB
👍 5
ስለ ሴቶች ፈተና አስፈሪ ታሪክ ታሪኩን የሚነግሩን አብዳህ ኢብኑ አብዱልሃኪም እንዲህ ይላሉ “በድብቅ ወደ ሮማውያን ምድር ዘመትን። በዘመቻውም ላይ አንድ ወጣት ተጎዳኝቶን ነበር። ከኛ ውስጥ ከሱ የተሻለ ቁርአን የሚቀራ ከሱ የተሻለ የፊቅህ እውቀት የነበረው ከሱ የተሻለ ስለ ፈራኢድ የሚያውቅ አልነበረም። ቀኑን ፁሞ የሚውል ለሊቱን ሲሰግድ የሚያድር ኣቢድ ወጣት ነበር። የኛ ሰራዊት በአንድ ምሽግ ውስጥ ለቀናት ሰፍረ። ይህ ወጣት ሁል ግዜ ለሊቱ ሲመሽ ለመስገድ ጌታውን ለማናገር ከምሽጉ ይወጣል። አንዲት ክርስቲያን ሴትም ከምሽጉ ጀርባ ሁና ትመለከተው የሚቀራውንም ቁርአን ታደምጥ ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን ወጣቱ ከእኛ ዞር ብሎ ወደ ምሽጉ አቅራቢያ ሌላ እንዳንሰፍርበት በተከለከልነው ምሽግ ውስጥ ሰፈረ። ወደልጅቷም ይመለከት ጀመር እሷም ከምሽጉ ጀርባ ሁና ትመለከተው ያዘች። ልጅቷ አላህ ከፈጠራቸው ፍጥረቶች እጅግ ውብ ነበረች። ከማማሯ የተነሳ ፀሀይ በፊቷ ላይ የምትጓዝ ትመስላለች። ወደ ምሽጉ ቀረብ ብሎ ያስተውላት ጀመር።ከጠላት ምሽግ ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ የጠላት ቀስቶች እንዳይወድቁበት ሰጋን። በየግዜ ይህን ያደርግ ጀመር። ይህንን ነገር ማዘውተር ባበዛ ግዜ ፍቅር ላይ ወደቀ ራሱን መቆጣጠር እስከማይችል ድረስ ልቡ በሷላይ ተንጠለጠለ። አንድ ቀን ራሱን አደጋ ላይ ጥሎ በሮማን ቋንቋ “ በምን መንገድ ነው የማገኝሽ?” ሲል ጠየቃት። እሷም “ ክርስቲያን ስትሆን” ስትል መለሰችለት። ልጁም "በአላህ እጠበቃለሁ!” ብሏት ጥሏት ሄደ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ተመልሶ ወደሷ በመምጣት እንዲህ አላት “ በሶላቴ ውስጥ እና ቁርአንን በማነብ ግዜ ባንቺ ተጠምጃለሁ (ሃሳቤ ያለው ካንቺ ጋር ነው)። በምን መንገድ ነው ላገኝሽ የምችለው?”። እሷም “ ክርስቲያን ሁን በሩንም እንከፍትልሃለን ከምሽጉም እናስገባሃለን እኔም ያንተ እሆናለሁ” አለችው። (አሁን ግን በአላህ እጠበቃለሁ የሚለውን ቃል አንደበቱ መናገር አልቻለም። ልቡ በፍቅሯ ታውሯል አንደበቱ ተሳስሯል። ፍቅር በሚሉት ሃይል ተማርኳል። የምትለውን ከመቀበል ውጭ ምርጫ አልነበረውም።) ያለችውን አድርጎ ወደ ምሽጋቸው ገባ፤ ከእርሷ ጋር ሆኖ ከፊትለፊቱ መስቀሉን ለብሶ ካልሆነ በቀር አናያቸውም።" አስከትለውም እንዲህ ይላሉ “ዘመቻችንን በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ሆነን አጠናቀቅን። ከመካከላችን ያለው ሰው ሁሉ ያንን ወጣት ከወገቡ ተወልዶ ክርስትናን እንደተቀበለ አድርጎ ያየው ነበር። ከግዜያት በኋላ በሌላ ቡድን ተመልሰን መጣን። በአጠገቡ አለፍን። ከክርስትያኖች ጋር ከምሽጉ በላይ ይታያል። እገሌ ሆይ የምትቀራው ቁርአን ምን ሰራ?! ያሁሉ መልካም ስራ ስገደት ፆምህ ወዴት ገባ ምን ሰራ?” ብለን ጠየቅነው። እሱም “እወቁ እኔ ቁርአንን ሙሉ በሙሉ እረስቻለሁ። በፍፁም ከዚህች አንቀፅ ውጭ رُّبَمَا يَوَدُّ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْ كَانُوا مُسْلِمِينَ ذَرْهُمْ يَأْكُلُوا وَيَتَمَتَّعُوا وَيُلْهِهِمُ الْأَمَلُ ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ {እነዚያ የካዱት (በትንሣኤ ቀን) ሙስሊሞች በኾኑ ኖሩ በብዛት ይመኛሉ፡፡ ተዋቸው ይብሉ፤ ይጠቀሙም፡፡ ተስፋም ያዘናጋቸው፡፡ በእርግጥም (መጥፎ ፍጻሜያቸውን) ያውቃሉ፡፡} በፍፁም ምንንም ከቁርአን አንቀፅ አላስታውስም። ” አለን። እኛም እንዲህ አልን“ ይህ ሰው በእውቀት ላይ አላህ ያጠመመው ሰው ነው።” ከዛም አብዳህ ቢን አብዱረሂም እንዲህ ይላሉ፡- “እኛ ልጁን አናግረን ዘወር እንዳልን ብዙም ሳንሄድ አንድ ጥቁር ነገር ወደኛ ሲመጣ ተመለከትን። ያቺ ሴት ነበረች ወደ ካሃድያን ምሽግ ልጁን ያስገባችው ሴት። ወደሷም ዞርንና “ይህ ልጅ ከእምነቱ ፈተንሽው (ከሃዲ አደረግሽው) አልናት። እሷም “በአላህ እምላለሁ፣ (የሚያነበው ቁርአን ማርኮኝ) የሚያነበውን ለመስማት ብቻ ነው ወደሱ ስመለከት የነበረው፣ የሚያነበውን (ቁርአን) ለመስማት ስል ነበር ያገባሁት። እሱ ግን የሚያነበውን ሁሉ በአንድ ጊዜ ረሳው፣ ስለዚህም ከእሱ ምንም ሳልጠቀም ቀረሁ። አሁን ከእናንተ ውስጥ እሱ ሲያነበው የነበረውን (ቁርአን) የሚያነብ አለን?” ብላ ጠየቀችን ለእርሷም ተነበበላት። እርሷም “ወላሂ ይህ ያ በእውነት ስሰማው የነበረው ነገር ነው” አለች። እስልምናን ተቀብላ ከእነርሱ (ከሙስሊሙ ሰራዊት) ጋር ሙስሊም ሆና ተመለሰች እርሱም ምሽጉ ላይ መስቀሉን ለብሶ ከክርስትያኖች ጋር ኖረ። ልቦናን እንዳሻው የሚጠለባብጥ ጌታ ጥራት ይገባው። የታሪኩ ምንጭ ኢብኑል ጀውዚ "ታሪኩል ሙሉክ ወ ኡመሚሂም" ከሚለው ኪታባቸው አቡበክር አል-በይሃቂ "ሹአቡል ኢማን" ከሚለው ኪታባቸው 🖊 Abdulkerim Husen https://t.me/AntiDoubts/
Show all...
👍 6
ቅደመ-ውሳኔ ተከታታይ ት/ት ክፍል 1 - የቅድመ-ውሳኔ ትርጉሙ 📌 ኢማም አን'ነወዊይ እንዲህ አሉ :-
ትርጉሙም (ቀደር) አሏህ ነገራቶች አስቀድሞ ወሰነ እንዲሁም እሷ በተወሰ ጊዜ በተወሰነ ገፅታ እንደምትከሰት ያቃታል (ያውቃታል) እሱ በወሰናትም ሁኔታ ትከሰታለች።
📗 ሸርህ አን'ነወዊይ ዓላ ሙስሊም 1/154 🎙 አቡ ተይሚያ https://t.me/AntiDoubts/
Show all...
9.55 KB
👍 1
የጁምኣ ኹጥባ በወንድም ነጃ ሰኢድ(በኢብኑ አባስ መስጅድ )   ሶብር በሚል ርዕስ መሳጭ እና አስተማሪ ምክር
Show all...
በወንድም ነጃ .amr1.67 MB
👍 1
በውዱ ወንድማችን ነጃ ከብዙ የግቢ ቆይታወቻችን በመጨረሻ ያስተላለፈል መሳጭ የሆነ የኹጥባ መልዕክት ''ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም በሚል ርዕስ'' የቀረበልንን ልብ የሚነካ ተግሳጥ ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።
Show all...
2024_07_05_12_41_30.mp319.38 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.