cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

⚜⚜ኤማንዳ!⚜⚜🇪🇹

#በኤማንዳ 💡ሀሳብ እና አስተሳሰብ 💡 --ደስታ እና ስኬት --ራስን-ማበልፀግ እና ራስን-መለወጥ --መንቃት እና መነቃቃት ሌላም ሌላም ብዙ ሀሳቦች ይዳሰሳሉ! ስር ነቀል ሁለተናዊ የህብረተሰብ ለውጥ ለማምጣት #ኤማንዳ ይሰራል! ይቀላቀሉ ያተርፉበታል! ለየትኛውም ፤ አስተያየት ፤ @Emanda_way_bot ይጠቀሙ፡፡ ጥያቄ፤

Show more
Advertising posts
368Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ይቻላል! የይቻላል አዎንታዊ አስተሳሰብን ማዳበር ይቻላል፡፡ የ Positive psychology ባለሙያዎች ይህንን ሂደት “Learned Optimism” የሚል ስያሜ ሰጥተውታል፡፡ ያለፈ ጊዜያችን መጪውን ጊዜ እንዳይወስን መወሰን አስፈላጊ ነው፡፡ ውድቀታችሁ የወደፊት ስኬታችሁን እንዳይወስን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ “ምን እባክህ ከዚህ በፊትም እኮ ሞክሬ አልሆነልኝም! አሁን ምን የተለየ ነገር ይኖራል ብለህ ነው?” የምትሉ ከሆነ ያለፈ ውድቃታችሁ እስር ቤት ውስጥ አሁንም በገዛ ፈቃዳችሁ ለመኖር ወስናችኋል ማለት ነው፡፡ ጥቂት እውን መሆን ያላቻሉ ህልሞቻችሁን ብቻ መሠረት አድርጋችሁ ዓላማ ያለው ሕይወት ከመጓዝ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ ዓለም በብዙ አዳጋች ሁኔታዎች የተሞላች ነች፡፡ እነዚህ እንቅፋቶች መንገድ ላይ ሲያጋጥሟችሁ ወድቃችሁ አትቅሩ፡፡ በክረምት ወራት ጭቃ በየቦታው ይኖራል፡፡ አንድ እና ሁለት ቀን ወድቃችሁ ስለቆሸሻችሁ ወይም ስለተጎዳችሁ ወይም ሰው ስለሳቀባችሁ “ከዚህ በኋላ ከቤቴ ንቅንቅ አልልም” አትሉም መቼም፡፡ ቁም ነገሩ ከዚህ በፊት የወደቃችሁበትን ምክንያት ማወቅ እና ዳግመኛ ላለመውደቅ ጥንቃቄ አድርጎ ጉዞን ወደፊት መቀጠል ነው፡፡ ሴሊግማን አዎንታዊ መሆንም ሆነ አዎንታዊ የሆኑ ነገሮችን ማግኘት ሕይወትን ከምንረዳበት ዘዴ (Explanatory Style) ጋር የተያያዘ ነው ይላል፡፡ ይህ ዘዴ ራሳችንን እና ዓለምን አእምሮአችን ውስጥ የምንተረጉምበት መንገድ ነው፡፡ ይህንን እይታችንን፣ አረዳዳችንን፣ አተረጓጎማችንን አወንታዊ ማድረግ መቻል በየትኛውም ዘርፍ ቢሆን አንድ የስኬት መንደርደሪያ ነው፡፡ ነጋሽ አበበ (ሳይኮሎጂስት እና ፀኃፊ) @melkam_enaseb
Show all...
No caption is needed
Show all...
ህይወታችን ላይ ትልቅ በጎ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ 10 አመለካከቶች! 1. ራሴን ለመውደድና ለመቀበል ሰዎች እስኪወዱኝና እስኪቀበሉኝ አልጠብቅም። 2. ትክክለኛውን ነገር አደርጋለሁ እንጂ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት አልሞክርም። 3. ትችቶች እንዲያስተምሩኝ እንጂ እንዲሰብሩኝ አልፈቅድም። 4. እኔ በስህተቶቼ define አልደረገም። 5. ስህተቶቼን ከስኬቶቼ በላይ አግዝፌ አላይም። 6. ሰዎች ሁሉ እንደኔ እንዲያስቡ አልጠብቅም። 7. የማልቀይራቸውን ሀቆች እቀበላለሁ። 8. ሰዎች እንዲያማክሩኝ እንጂ እንዲወስኑልኝ አልፈቅድም። 9. በማልቀይረው ትላንት ላይ ሳይሆን ባለኝ ዛሬ ላይ አተኩራለሁ ። 10. ደስታዬን ለነገ አልቀጥርም። ባለኝ ረክቼ ዛሬ ሀሴት አደርጋለሁ። ኤርሚያስ ኪሮስ (ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)
Show all...
JACK MA በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነው “ጃክ ማ” ሲሆን 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት አለው። ጃክ ማ እንዲህ ይላል፡- ‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም! አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው። ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው። ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት  መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል! እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል? በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’ ይላል ጃክ ማ። እውነት ነው እኛም አገር ያለው ነባራዊ እውነታ ይሕ ነው። ምክንያቱም ተቀጥረህ በምታገኘው የወር ደመወዝ ሀብት፣ ጥሪት፣ ቤት እና ራስህን ለውጠህ ሌላ ሰው መርዳት አትችልም። እርግጥ ነው የወር ደመወዝ ሲኖርህ የምትፈልገውን ማድረግ ባትችልም በገቢህ ልክ መኖርን ትለምደዋለህ። ለማንኛውም በሥራ ፍለጋ ጊዜ ከማባከን በትንሹም ቢሆን የግል ስራ የምትጀምሩበትን የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል። (Getu Temesgen) @melkam_enaseb
Show all...
7⃣ ዐይን-ገላጭ የጃፓኖች የሕይወት ጭብጥ! 1⃣ IKIGAI ፨ በሕይወት ውስጥ ዓላማህን ድረስበት። ፨ ሰርክ ማለዳ የመንቃትህን ምክንያት እወቅ። ፨ አስፈላጊነትህን (ለዓለም)፣ ጥንካሬህን፣ ዝንባሌህን የተወዳጀ የሆነ ነገር አስስ። ይሄ ነው ለሕይወትህ ትርጉም የሚሰጣት። 2⃣ SHIKITA GA NAI ፨ መለወጥ የማይቻልህን ነገር ተወው፣ ልቀቀው። ፨ ካንተ ቁጥጥር ውጪ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን እና ያም ያለ መሆኑን ተረዳ። ሂድ እና መቀየር በምትችለው ነገር ላይ ትኩረት አድርግ። 3⃣ WABI-SABI ፨ በጎዶሎነት ውስጥ ሠላምን አግኝ። ፨ ራስህ እና ሌሎችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ ምንም ነገር ፍፁም አለመሆኑን ተገንዘብ። ፨ ለእንከን-የለሽነት ከመትጋት ይልቅ ሕይወትን ልዩ በሚያደርጋት ጎዶሎነት ውስጥ ደስታን አጣጥም። 4⃣ GAMAN ፨ በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ። ፨ ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት-ብስለትህን እና ራስ-ገዝነትህን አሳይ። ፨ ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ። 5⃣ OUBAITIORI ፨ ራስህን ከማንም ጋር እንዳታወዳድር። ፨ ሁሉም የተለየ ጊዜ-ቤት እና ልዩ ጎዳና አለው። ፨ ራስህን በሌላው ለመለካት ከመሞከር ይልቅ በራስህ መሻሻሎች ብቻ ማተኮርህ አስፈላጊ ነው። 6⃣ KAIZEN ፨ ሰርክ በሁሉም የሕይወትህ ክፍል ውስጥ መሻሻሎችን ፈልግ! ፨ ጥቃቅን ለውጦች እንኳ መጠራቀም ችለው በጊዜ ሂደት ውስጥ ግዙፍ ለውጥ ያመጣሉ። 7⃣ SHU-HA-RI "ተማሪዎቹ ሲዘጋጁ መምህሩ ይገኛል። ተማሪው የምር ዝግጁ ሲሆን ግን መምህሩ ይሰወራል።" ―Teo Te Ching 👉 (እንዴት) ስለመማር እና በዘዴው ስለመጠበብ ማወቂያ መንገድ ነው። ከዕውቀቱ ለመድረስ ሶስት ደረጃዎች አሉት። ፨ SHU: የአንዱን አዋቂ (master) ትምህርት በመከታተል መሰረቶቹን መቅሰም! ፨ HA: ከአዋቂው የተቀሰመውን ትምህርት ከሙክረት በማዋሃድ የተግባር ልምምድ መጀመር። ፨ RI: ይሄ ደረጃ የሚያጠነጥነው ፈጠራዎች ላይ እና ትምህርቶቹን በተለያዩ መስኮች የመተግበር ችሎታ ላይ ነው። ውብ ቅዳሜ❤️ @EthioHumanity @EthioHumanity @EthioHumanitybot
Show all...
የሰውን ልጅ ነፃ የሚያደርገው እውነት በአብዛኛው ለመስማት የማይፈልገው የእውነት ክፍል ነው !              -- Herbert Agar -- >>ጥርጣሬ እውነትን መፋቅ አይችልም! በሆነ ነገር ላይ ፍርሃት ካደረብህ ስለነገሩ በቻልከው ልክ ተማር ዕውቀት ፍርሃትን ያሸንፋል !               -- Edmund Burke -- ለስልጣን ብቁዎች የማይፈልጉት ናቸው !                       -- Plato -- የአለም ህዝብ በሙሉ አንገቱን አርዝሞ ወደ ገደል ቢጓዝ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዘው እንደእብድ ይቆጠራል !            -- Thomas S Eliot -- ¤¤¤-------//------¤¤¤ @motivate_youngsters ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ  ካሎት @Emanda_way_bot አለሎት
Show all...
**ተስፋ😭 መቁረጥ😭 ፈለኩ😭** አይኖቼ በዕንባ ተሞልተው ልቤ በሀዘን ሲቃ ተይዞ መሸነፍ እጅ መስጠት ፈለኩ!!!!! የለፋውበት ሁሉ ገደል ሲገባ መኖር ሲያስጠላኝ ከዚህ ሁሉ ችግር ከዚህ ሁሉ ሀዘን መች ይሆን የምገላገለው ብዬ ተመኘው! በሰው መሀል የተከበብኩ ብቸኛ የውስጤን የማወራው ሀዘኔን የሚጋራኝ ከጎኔ አጋር የሌለኝ በጓደኛ ብዛት የተበሸበሽኩ ብቸኛ ነኝ!!! ትልቁ ችግሬ "የሁሉ ነገር ፈላጭ ቆራጭ እኔ መሆኔን መረዳቴ ነው!!" ይሄን ባልረዳ ኖሮ የሽንፈቴን ምክኒያት በሌሎች ሰዎች አመካኝ እና እራሴን አታልል ነበር! እውነታው ስለማውቀው ግን የሽንፈቴም የድሌም ባለቤት እኔ መሆኔን ስለማውቀው ግን በሰው ማሳበብ አልቻልኩም!!!! የጀግና ጀግንነት የሚለካው በጦርነት ነው!!!!! በሰላሙ ጊዜ'ማ ሁሉም ጀግና ነው። ለዚህ ነው ጦርነት ጀግና ይፈጥራል የሚባለው!!!! እኔም ከራሴ ጋር እየተዋጋው ነው!!! የተስፋ ቁረጥ አቆርጥም ግብ ግብ!!! ምንም እንኳን ከኮሶ የመረረ ቢሆንም ዛሬም አፈር በልቼ አፈር ልሼ ለውጊያ ተነስቻለው!!!ጦርነቱን እስከማሸንፍ ድረስ አያልቅም!!!! ህይወትን ባፍጢሙ እስከምደፋው ድረስ ጦርነቱ አይቆምም!!! ህይወት ብቻ ሳትሆን እኔም ከባድ ነኝ!!!! ደና አድርጌ አበሻቅጣታለው!!!!!
Show all...
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" (ኢሳይያስ 9:6) ________________________ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!
Show all...
ካሸነፍክባቸው ጨዋታዎች ይልቅ በተሸነፍክባቸው ጨዋታዎች ብዙ ትማራለህ። ምርጥ ተጫዋች ከመሆንህ በፊት በርካታ ጨዋታዎች መሸነፍ አለብህ!      -- Jose Raul Gapablanca -- ምንጊዜም ሁለቴ አዳምጥ መጀመሪያ ምን እንደተነገረ ቀጥሎ ማን እንደተናገረ ! ለመለወጥ ፈቃደኛ ካልሆንክ ለማማረር መብት የለህም!                         -- Mark Twain -- ጥሩ ውሳኔ የሚመጣዉ ከልምድ ነው። አብዛኛው ልምድ ደግሞ ከመጥፎ ውሳኔ የሚመጣ ነው!                         -- Will Rogers -- የአዕምሮ ሰላም ያለው ሰው ራሱንም ሆነ ሌሎችን አይረብሽም!                  -- Epicurus --
Show all...
🔸የራስህን ህይወት በፍፁም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክንያቱም የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን ፣ 🔹 ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው ሚሆነው።ሁለቱም ውጤቶች መጥፎ ናቸው። 🔸ሲለዚህ ወዳጄ ራስህን ከራስህ ጋር ብቻ ነው ማወዳደር ያለብህ።እመነኝ ያኔ ሰላምህን ታገኛለህ።
Show all...