cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በጎ ለውጥ(Jijjrrama) Book for all life

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ ! https://t.me/book9954 Book

Show more
Advertising posts
698Subscribers
+124 hours
+67 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

25 ጠቃሚ አባባሎች!! 1. አንተ ጠንክረህ በዝምታ ስትሰራ ፣ ስኬትህ ጮኾ ይናገራል፡፡ -ፍራንክ ኦሽን 2. በሕይወትህ ከዚህ በፊት ያልነበረህ አዲስ ነገር ለማግኘት ከፈለክ፣ አዲስ ሰርተኸው የማታውቀው ስራ ለመስራት መፍቀድ ይኖርብሀል፡፡ -ቶማስ ጄፈርሰን 3. ትክክለኛ ሕይወት የሚጀምረው የምቾት ቀጠና ሲያልቅ፡፡ -ዶናልድ 4. አንተን ሁለት ነገሮች ይገልፁሀል ፡፡ የመጀመሪያው ምንም የሌለህ ጊዜ የምታሳየው ትዕግስት ሲሆን ሁለተኛው ሁሉም ሲሟላልህ የምታሳየው ጠባይ ነው፡፡ -ኢማም አሊ 5. በምድር ላይ ትልቁ አስደሳች ነገር ሰዎች አትችልም ያሉህን ሰርተህ ማሳየትህ ነው፡፡ -ዋልተር ባግሆት 6. ወንዝ ድንጋይ ቦርቡሮ የሚገባው ሀይለኛ ስለሆነ ሳይሆን ያለማቋረጥ ስለሚፈስ ነው፡፡ -ጂም ዋትኪንስ 7. ህልምህን ለመፈፀም ብዙ ጊዜ በመውሰዱ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጊዜ ስለሚበር አርቀህ ያየኸው ህልም በፍጥነት መፈፀሙ አይቀርም፡፡ -አርል ኒተንጋል 8. ሰዎች በምታቅደው እቅድ ካልሳቁ ወይም ካልተገረሙ እቅድህ ትንሽ ነው ማለት ነው፡፡ -አዚም ፕሪሚጂ 9. ለመጀመር ትልቅ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ትልቅ ለመሆን መጀመር አለብህ፡፡ -ዚግ ዚግላር 10. ደስተኛ የሆነ ሕይወት ለመኖር ከፈለክ ከሁኔታና ከሰዎች ጋር ሳይሆን ከአላማና እቅድህ ጋር ተጣበቅ፡፡ -አልበርት አንስታይን 11. አንተ የምርጫህ ውጤት እንጂ በአንተ ላይ የሚደርሱት ነገሮች ውጤት አይደለህም፡፡ -ካርል ጉስታቭ 12. ባለትላልቅ አእምሮ ሰዎች በሃሳብ ላይ ይወያያሉ ፣ መካከለኞች በ ድርጊት / ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ባለትናንሾች ቁጭ ብለው ሰው ያማሉ፡፡ -ሪያኖር ሮዝቪልት 13. እስካልቆምክ ድረስ በምንም ዝግታ ብትጓዝ መድረስህ አይቀርም ፡፡ -ኮንፊሺየስ 14. ችሎታ ያለው ሰው ምንም ስራ እስካልሰራ ድረስ ችሎታ በሌለው ጠንካራ ሰራተኛ ይበለጣል ፡፡ -ቲም ኖትኪ 15. ከውድቀት ይልቅ ጥርጣሬ የነገ ህልምን ይገላል፡፡ -ሱዚ ካስም 16. እውቀት ብቻ አይበቃም ተግባራዊ ካልተደረገ በስተቀር ፣ ፍቃደኛነት ብቻ አይበቃም ካልተሰራ በስተቀር፡፡ -ብሩስ ሊ 17. የዛሬ አመት በዚህ ሰአት ምናለ ምናለ ከአመት በፊት በጀመርኩ የምትላቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ -ካረን ላንብ 18. ጀማሪዎቹ ለመስራት ከሞከሩት ጊዜ በላይ አለቃቸው ብዙ ጊዜ ወድቋል፡፡ -ስቴፈን ማክክሬን 19.ብዙ ጊዜ ላለመስራት የምትተዋቸው ስራዎች በውስጣቸው ብዙ እድልን የያዙ ናቸው፡፡ -ሮቢን ሻርማ 21. መተንፈስ እንደምትፈልግ ያህል ለስኬታማ ሕይወት ጥልቅ ፍላጎት ካለህ ይሳካልሀል፡፡ -ኤሪክ ቶማስ 22. ፊትህን ወደ ፀሀይ ስታዞር ጥላህ ከኀላህ ይወድቃል፡፡ -የማዎሪ አባባል 23. 99% የሚሆኑ ሰዎች ሀሳብህን ከተጠራጠሩህ ፣ እጅጉን ስተሀል አልያም ታሪክ ልትሰራ ነው፡፡ -ስኮት ቤልስካይ 24. ፈፅሞ አትድከም ምክንያቱም አሁን እጅግ ከባድ የሆነብህ ስራ ከጥቂት ጊዜያት በኀላ ለሌላ ስራ መሟሟቂያ ይሆናል፡፡ -ያልታወቀ ሰው 25. ሕይወት ልክ እንደ ካሜራ ነች ፡፡ የምትፈልገውና ጠቃሚ ነገር ላይ ስታተኩር ሌሎቹ የማያስፈልጉት እየደበዘዙ ይሄዳሉ፡፡
Show all...
በመጠን ኑሩ! ፨፨፨////፨፨፨ በመጠን ኑሩ አትብሰክሰኩ። አለምን ካልገዛው፣ ምድርን ካልተቆጣጠርኩ፣ መሪ ካልሆንኩ፣ ህንፃ ላይ ህንፃ፣ ንብረት ላይ ንብረት ካልጨመርኩ ብላችሁ አትጨነቁ። ጭንቀታችሁ ለመኖር እንጂ የሚጠፋ ንብረት ለመገንባት አይሁን፣ መብሰልሰላችሁ ፈጣሪያችሁን ስላስቀየማችሁ እንጂ ምድራዊ ካባን ለመደረብ አይሁን። አስቀድማችሁ ትገዙት ዘንድ የታደላችሁ ንፁህ ህሊና መኖሩን አስቡ። ለህሊናችሁ በመኖር የምድርን ጥፋትና በደል ተጠየፉ፣ በእግዚአብሔር መልካም መንገድ እየተጓዛችሁ እራሳችሁን አድኑ፣ የሚያኮራችሁን ማንነት ፍጠሩ። መጠናችሁን አውቃችሁ ተራመዱ፣ ልኬታችሁን ተረድታችሁ ኑሩ። አዎ! በመጠን ኑሩ በብዙ አትርፉ፤ በጥቂቱ አስተውሉ በመጥንቃቄ ወደፊት ተጓዙ። ዋናውን ይዛችሁ ስለምን ለትርፉ ትብሰለሰላላችሁ? አንኳሩን አግኝታችሁ ስለምን ለተጨማሪው እንቅልፍ ታጣላችሁ? እናንተ ካልኖራችሁ የማይኖር እንጂ እናተ ሳትኖሩ የሚኖር ነገር አይሰጣችሁም። የምትገነቡት ንብረትና ዝና እንኳን የእናንተ ጥገኛ ነው፤ የምታፈሩት ንብረትና ተከታይ እንኳን ከእናንተ ቦሃላ ዋጋ የለውም። ዋናዎቹ እናንተ ናችሁ፤ ዋናው ጉዳይ መኖራችሁ፣ ምድር ላይ መመላለሳችሁ፣ በሰላም በጤና ማምሸት ማንጋታችሁ ነው። ስለዋናው ማመስገናችሁን አትርሱ፣ ስለትርፉም ብዙ አትጨነቁ። እግዚአብሔር ያለው ሲሆን ይሆናል፣ ፈጣሪ የፈቀደውም በጊዜው ይከናወንላችኋል። አዎ! ጀግናዬ..! ሩቅ ስታልም የቅርቡ እንዳይርቅህ ተጠንቀቅ፣ የተሰቀለውን ለማውረድ ስትጥር በኪስ ያለው እንዳይደፋ ተጠንቀቅ። ምኞትህን ልክ አብጅለት፣ ለሃሳብህ ገደብ ይኑርህ፣ ህልምህ እስኪያጠፋህ አትጋፈጠው። ብልሆች ለሃሳባቸው ገደብ ያበጃሉ፣ ጠቢባን ግን ሃሳባቸው በእራሱ ገደብ አለው። ያዙኝ ልቀቁኝ የምትልለት ነገር ለህይወትህ ምንያክል እንደሚያስፈልግህ አስቀድመህ ተረዳ። ለሃሳብህ ልኬት፣ ለተግባርህ ገደብ፣ ለጭንቀትህም ፈር አብጅለት። ለማን ብለህ ነው ለሚያልፍ ችግርና ፈተና ብለህ ልብህ ላይ የማያልፍ ጠባሳን የምታስቀምጠው? ለማን ብለህ ነው መቀየር ስለማትችለው ታሪክህና ስለማይመለከትህ የሌሎች ሰዎች ጉዳይ ስትጨነቅ የምትገኘው? ህይወትህን መጥን፣ በማያገባህ አትግባ፣ አጉል ተስፋ ለሰውም ሆነ ለእራስህ አትስጥ፣ በመጠን ኑር ደስታህንም ለእራስህ ፍጠር። ውብ ምሽት ይሁንልን!
Show all...
ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች እና የአእምሮ ጤና፦ - የታዳጊ ልጆች እድሜ (ጉርምስና) ልዩና ወሳኝ ጊዜ ነው:: አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ለውጦቹም ከፍተኛ ናቸው። - በዚህ ጊዜ ላይ ለድህነት፣ ለጥቃት (አካላዊም ፆታዊ) መጋለጥ እዚህ ዕድሜ ላይ ላሉ ልጆች ለአእምሮ ጤና መታወክ የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል:: አጋላጮች፦ ▫️የአቻ ግፊት ▫️አካባቢያዊ ተጽዕኖዎች ▫️አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት ▫️የቤት ውስጥ ሰላም መጓደል ▫️የማንነት ጥያቄ ▫️የሚዲያ ተጽዕኖ ▫️ከፍላጎት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች የተወሰኑት ናቸው። - በተለይም የአዕምሮ እድገት ውስንነት፣ የተለያዩ የነርቭ ችግሮች፣ የቅርብ ቤተሰብ ድጋፍ የሌላቸው ታዳጊ ልጆች/ወጣቶች ደግሞ የበለጠ ለአዕምሮ ጤና መታወክ የተጋለጡ ናቸው። ከስሜት ጋር የተያያዙ ችግሮች፦ * ከልክ በላይ ጭንቀት * የስሜት መዋዠቅ * ድባቴ፣ ራስን ማግለል አልፎም *በህይወት መቆየት አለመፈልግ የባህሪ ችግሮች፦ ° ትኩረት ማጣት፣ ° ለነገሮች መቸኮል፣ ° የፀባይ ለውጥ መኖር የአመጋገብ ችግር፦ ➡ ውፍረት እንዳይመጣ ከሚል ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ችግር ነው። የስነ-ልቦና ቀውስ፦ • ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ያደርጋል። • ራሳቸውን በተለያዩ ሱሶች ይጎዳሉ። • ከማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድርበታል። - ይህ እንዳይሆን ምን እናድርግ? ▪️ቤተሰብ ልጆቹ በሰውነታቸው ላይ ለውጥ እየተካሄደ እንደሆነ በመረዳት ለልጆቹ ከምን ጊዜውም በላይ ቅርብ መሆን አለበት። ▪️ራሳቸውን በተለያዩ ዓይነት ስራዎቸ(እንደ ስፖርት ያሉ ነገሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ)፣ የመፍትሄ ሰዎች እንዲሆኑ፣ በጤነኛ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ  በማድረግ ሁሉም ሰው የድርሻውን ማድረግ አለበት።
Show all...
ቶማስ ሳንካራ ማነው?   በርካቶች አፍሪካዊው ቼጉቬራ ነው ይሉታል። በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 2.5 ሚሊዮን ህጻናትን የማጅራት ገትር፣ የወባና የኩፍኝ ክትባቶችን እንዲወስዱ ማድረግ አስችሏል። 13% ድረስ ተንኮታኩቶ የነበረውን የትምህርት ዘርፍ በ4 ዓመታት ብቻ ወደ 73% ሽቅብ አስመንጥቋል። መሬትን ከባላባቶች ነጥቆ ለገበሬዎች በመስጠት የስንዴ ምርትን በሄክታር 1700 ኪ.ግ ተነስቶ 3800ኪ.ግ በሄክታር ማፈስ አስችሏል። በስልጣን በቆየባቸው ጥቂት ዓመታት ብቻ በርሃማነትን ለማጥፋት 10 ሚሊዮን ዛፎችን ያስተከለ፣ የውጭ እርዳታን በተመለከተ የአገሩን ዜጎች የሚመግባችሁ ከላይ ይታዘባችኋል አርፋችሁ በአገራችሁ አምርቱም ያለ ቆፍጣና መሪ ነበር። የአገሩን ስም ከ The Republic of Upper Volta ወደ Burkina Faso የቀየረ። Burkina faso ትርጉሙ የቀና ሰዎች አገር ማለት እንደሆነ ልብ ይሏል። ምስጋና ለእርሱ አመራር ይሁንና በ3 ወራት ውስጥ ብቻ 35000 ቡርኪናፋሶዊያን ማንበብ እና መፃፍ እንዲችሉ አድርጓል። ሌላም ሌላም በርካታ ጀብዶች…
Show all...