cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Andemta media-አንደምታ ሚዲያ™

Andemta media ሀገራዊ ወቅታዊ መረጃዎችን፣ ዜናዎችና እይታዊ ዳሰሳዎች የሚሻገሩበት የሁላችን ቤት ነው!! ያልተረጋገጠ መረጃን አናጋራም። ስለ እውነት እንሰራለን። መረጃዎችንና አስተያየቶችን @Andemta24 ያድርሱን!

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

2015 ዓ/ም ገባባባባባባ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ‼️
Show all...
የአሸባሪውን ወረራ በመመከት በዱር በገደሉ መስዋዕትነት እየከፈላችሁ ለምትገኙ  ጀግኖች፣ ቤተሰቦቻችሁ የአሸባሪውን ወረራ ለመመከት ከጎናችሁ ለራቁ የጀግና ቤተሰቦች፣ ለጥምር ጦሩ  ደጀን ለሆናችሁ ሁሉ በያላችሁበት እንኳን አደረሳችሁ!  ቀጣዩ ዓመት መስዋዕትነታችሁ ፍሬ የሚያፈራበትና በዓልን በሰላም የምታከብሩበት ይሁንልን!
Show all...
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ2015 ዓ/ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን!! መልካም በዓል!!
Show all...
Sudan ሱዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር በምትወዛገብባት አቢዬ ግዛት በተመድ ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ስር ተሠማርተው ለነበሩ 247 ኢትዮጵያዊያን ሰላም አስከባሪዎች የፖለቲካ ጥገኝነት ሰጥታለች ሲል ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። ወደ አገራችን አንመለስም ብለዋል የተባሉ 649 የትግራይ ብሄር ተወላጆች የሆኑ የቀድሞ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኢትዮጵያዊያን በገዳሪፍ ግዛት ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ዘገባው ጠቅሷል። የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች በሱዳን ጥያቄ ከአቢዬ ግዛት ሲወጡ ከ550 በላይ የትግራይ ብሄር ተወላጅ ናቸው የተባሉ  ሰላም አስከባሪዎች ሱዳን ውስጥ ስለመቅረታቸው ሚያዝያ ላይ ተዘግቦ ነበር።(wazema)
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በሰደድ እሳት በርካቶች ከመኖሪያቸው እየተፈናቀሉ ነው በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት በርካቶች ከመኖሪያ ቤታቸው መፈናቀላቸው ተነግሯል። በሰደድ እሳቱ እስካሁን በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ከ100 በላይ መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውም ተነግሯል። አልአይን የሰደድአማርኛ እንደዘገበው በእሳቱ ቃጠሎ ምክንያት በርካቶች መኖሪያቸውን ለቀው እየተሰደዱእንደሆነ ተመላክቷል።
Show all...
የመረጃ ቲቪ ስርጭት ተቋረጠ። በወቅታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የመረጃ ቲቪ ተቋርጧል። ከምንጮች ለመረዳት እንደሞከርነው የሳተላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ የተቋረጠው በገንዘብ ችግር መሆኑ ተገልጿል። በቀጣይ ገንዘቡን በማፈላለግ በመክፈል ወደ አየር ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ምጮቻችን አሳውቀዋል።
Show all...
ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ተጨማሪ ውሳኔ‼️ የደሴ ከተማ አስተዳደር ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በከተማው ልዩ ልዩ  ክልከላዎችን በማስቀመጥ የተቀመጡ ህጎችን እያስተገበረ ይገኛል። እነዚህ ህጎች እንደተጠበቁ ሆነው በተጨማሪ ከነሀሴ 30/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆኑ ተጨማሪ ክልከላዎችን ያስቀመጥን መሆኑ ታውቆ ህዝቡ ተባባሪ እንድሆን እንጠይቃለን። 1ኛ- የመከላከያ አባል ሳይሆን የመከላከያን የደንብ ልብስ መልበስ ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባል ሳይሆን የልዩ ኃይሉን የደንብ ልብስ ለብሶ በከተማው ውስጥ መንቀሳቀስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። የመከላከያም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይል አባል ሳይሆን የደንብ ልብሱን ለብሶ ሲንቀሳቀስ የተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል ። 2ኛ- ከደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅር ውጭ ተፈናቃይ በመሆን የመጥታችሁ በከተማው በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው ፡፡  3ኛ- ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የጥምር ጦሩን ስም ማጠልሸት ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ የተገኘ  በህግ ተጠያቂ ይሆናል ። ለዚህም የከተማው ማህበረሰብ አሉባልታዎችን በተለያዩ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገጥ ወይም ጥላቻ ለማሳደር የሚሰሩ ኃይሎችን ለፀጥታ ሀይሉ  ጥቆማ እንዲያደርጉ  እናሳስባለን፡፡ 4ኛ- ፀጉረ ልውጥ የሆነ ሰው በምናገኝበት ሰአት ማህበረሰባችን በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል። 5ኛ- በከተማችን የሚገኝ ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ  በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት። 6ኛ- ማንኛውም አካል ከመንግስት አደረጃጀት ውጭ ለጦርነቱ በሚል ገንዘብ መሰብሰብ ፈፅሞ የተከለከለ ሲሆን ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ አካል ሊኖር አይገባም ። ሆኖም መንግስት ወጣቱንም ፣ ባለሀብቱን ፣ መንግስት ሰራተኞችና አመራሮችን ወዘተ በማሳተፍ የራሱን የመንግስት አደረጃጀት ተጠቅሞ ለጥምር ጦሩ የሎጅስቲክ ድጋፍ በዓይነትም ሆነ በገንዘብ በህጋዊ ደረሰኝ ከህዝቡ እየሰበሰበ ጥምር ጦሩ ውስጥ እየተሳተፈ ለሚገኝ ማንኛውም ኃይል ይጠቀምበት ዘንድ ያስረክባል።  7ኛ- በማንኛውም ሰዓት ታርጋ ቁጥር የሌለው ተሽከርካሪ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር ውሎ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ።      ©የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት @Andemtanews24
Show all...
ከወልድያ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ‼️ የከተማውን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ ከተማ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የሰዓት እላፊ ገደብ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ክልከላዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎችን አስተላልፏል። 1.  ከፀጥታ መዋቅሩ ውጭ በከተማችን በየትኛውም ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ 2.  ከተፈቀደላቸው የመንግስት የፀጥታ አባላት ውጭ የሰራዊቱን አልባሳትን መልበስ የተከለከለ ነው፡፡ 3. ሀሰተኛ ወሬ በመልቀቅ የከተማውን ማህበረሰብ የሚያውኩ አሉባልታዎችን በሚዲያዎችና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በማሰራጨት ህዝቡን ማዋከብ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ 4.  በከተማችን የሚገኙ የራያና ቆቦ ከተማ ተፈናቃዮች ውጭ ሌላው አካል ወደ መጣበት አካባቢ እንዲመለስ በጥብቅ እናሳስባለን 5. በከተማችን የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ባንክ ቤት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ ካፌና ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ተቋማት እና የመሳሰሉትን መዝጋት ፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ 6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ለፀጥታ ስራ ትብብር ሲጠየቅ የመተባበር ግዴታ አለበት። ነገር ግን ተሸከርካሪን የሚሸሽግ፣ የሚያሸሽ፣ ሆን ብሎ ተበላሸ በሚል ላለመተባበር ጥረት የሚያደርግ ግለሰብ እና ድርጅት ተጠያቂ ይሆናል። 7. የመኖሪያ ቤትና የመኝታ አልጋ የሚያከራይ ግለሰብ የተከራዮቻችሁን ማንነት የመለየትና የታደሰ መታወቂያ ስለመያዛቸው የማረጋገጥ ግዴታ ሲኖርባችሁ አጠራጣሪ ጉዳይ ሲኖር ለጸጥታ አካል ሪፖርት የማድረግ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በግልፅ እናሳስባለን 8. ፀጉረ ልውጥ ሰው የሚያገኝ ግለሰብ በቅርቡ ለሚገኝ የፀጥታ አካል የመጠቆምና የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል 9.  ከነሀሴ 29/2014 ዓ.ም ጀምሮ የቀበሌ መታወቂያ መስጠት የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን። 10.  ማንኛውም የመንግስት እና የግል ታጣቂ አካባቢውን በብሎክ አደረጃጀት ውስጥ በመካተት በየደረጃው ያለ የፀጥታ አካላት በሚሰጠው ስምሪት አካባቢውን የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለበት 11.  አግባብነት የሌለው የዋጋ ንረት መፍጠር፣ በሸቀጦችና በግብርና ምርቶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ ጨምሮ ህዝቡን ማስቃየት፣ በማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ መገኘት በህግ ያስጠይቃል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች ማንኛውም አካል የማክበርና ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ ያለበት መሆኑንና ይህን ውሳኔ የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንደሚወስድ በአጽእኖት እናሳውቃለን፡፡                                       የወልድያ ከተማ አስተዳደር  የፀጥታ ምክር ቤት ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም ወልድያ
Show all...
ራያ ግንባር ✔ከራያ ግንባር 1,500 ምርኮኞች ዛሬ ወደ ተዘጋጀላቸው ቦታ ተጓጉዘዋል። ✔የወራሪ ኃይሉን ከፊል ተዋጊውን ትናንት ሌሊቱን ወደ ሌላ ግንባር ማዘዋወሩ ታውቃል። ✔በወርቄ አቅጣጫ አሁንም ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ✔ግራካሶ ተራራን የሃይል ስምሪት ቦታ አድርገውታል ✔ወልዲያ ከተማ ሙሉ የባንክ አገልግሎት ተጀምሯል።
Show all...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ውሳኔ አሳለፈ‼️ ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
Show all...