cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዳይኦርቶሲስ ( DCM )Surafel Amaha

“...በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” — 1ኛ ጢሞ.3÷15 For more information 👇👇👇👇👇👇👇 @SurafelAmaha76 @SurafelAmaha76

Show more
Advertising posts
249Subscribers
No data24 hours
+17 days
+530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የተገኛችሁበትንና የክርስቶስን ፍቅር እያሰባችሁ በዚህ ምሽት ጌታን ባርኩ!! 👉የእግዚአብሔር ፍቅር የመኖራችን ምክንያት ነው!!
Show all...
3
የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ! አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡ • ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡ • አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?” • ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ” • አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ” • ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ) • አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?” • ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል” • አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ” ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡ ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታያችሁ አትጠብቁ፡፡ በሚታያችሁ መጠን ተራመዱ፡፡ የሚታያችሁን ያህል ስትራመዱ፣ ከመራመዳችሁ በፊት ያልታያችሁን ማየት ትጀምራላችሁ፡፡ ሁሉንም ነገር እስከምታውቁ አትጠብቁ፡፡ በምታውቁት ልክ ስራን ጀምሩ፡፡ በምታውቁት እውቀት መጠን ስራን ስትጀምሩ፣ ያንን ከመጀመራችሁ በፊት ያልነበራችሁ ልምድና እውቀት ወደ እናንተ ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ሰው እስኪቀበላችሁ አትጠብቁ፡፡ የሚቀበሏችሁ ላይ በማተኮር ተሰማሩ፡፡ በሚቀበሏችሁ ላይ ስታተኩሩና ደስተኛ ስትሆኑ፣ ቀድሞ የማይቀበሏችሁ ሁሉ እናንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ የጠየቃችሁት ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ፡፡ የተሰጣችሁን ተቀበሉና በዚያ በመጀመር የምትችሉትን አድርጉ፡፡ በተሰጣችሁ በጥቂቱ የምታደርጉት ጥረትና የምታከናውኑት ነገር የቀረው እንዲለቀቅላችሁ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡ አትቀመጡ! የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ! https://t.me/Dreyob 👇👇👇join👇👇👇 https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ! አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡ • ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡ • አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?” • ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ” • አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ” • ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ) • አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?” • ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል” • አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ” ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡ ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታያችሁ አትጠብቁ፡፡ በሚታያችሁ መጠን ተራመዱ፡፡ የሚታያችሁን ያህል ስትራመዱ፣ ከመራመዳችሁ በፊት ያልታያችሁን ማየት ትጀምራላችሁ፡፡ ሁሉንም ነገር እስከምታውቁ አትጠብቁ፡፡ በምታውቁት ልክ ስራን ጀምሩ፡፡ በምታውቁት እውቀት መጠን ስራን ስትጀምሩ፣ ያንን ከመጀመራችሁ በፊት ያልነበራችሁ ልምድና እውቀት ወደ እናንተ ይመጣሉ፡፡ ሁሉም ሰው እስኪቀበላችሁ አትጠብቁ፡፡ የሚቀበሏችሁ ላይ በማተኮር ተሰማሩ፡፡ በሚቀበሏችሁ ላይ ስታተኩሩና ደስተኛ ስትሆኑ፣ ቀድሞ የማይቀበሏችሁ ሁሉ እናንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡ የጠየቃችሁት ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ፡፡ የተሰጣችሁን ተቀበሉና በዚያ በመጀመር የምትችሉትን አድርጉ፡፡ በተሰጣችሁ በጥቂቱ የምታደርጉት ጥረትና የምታከናውኑት ነገር የቀረው እንዲለቀቅላችሁ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡ አትቀመጡ! የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Show all...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

💉💉  በልካችን እንኑር💉💉 “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።”   — ማቴዎስ 5፥16   👉👉ክርስትና በልብ ከማመን ቢጀምርም የልብ ብቻ ሆኖ አይቀጥልም ። በሰወች ሁሉ ፊት የማይገለጥ መልካም ስራ ፣ በጨለማው መንግስት ላይ የማይሰለጥን ብርሀን በእኛ ዘንድ የለም ። ጌታን ለመከተል በወሰንበትና የእግዚአብሔር ልጆች በሆንንበት ቅጽበት የአለም ብርሀን ሆነናል ።       “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።”                                 ማቴዎስ 5፥14 👉👉ይህ ቃል በክርስቶስ የሆንነውን እንጂ ወደፊት የምንሆነውን የሚናገር ክፍል አይደለም ። በዳግም ውልደት የኢየሱስን ብርሀን ተካፍለናል ፣ ያለ እኛ ስራና ትጋት በመወለድ ብቻ የአለም ብርሀን ሆነናል ።                     ከክፍሉ የምንረዳው ትእዛዝ “ብርሀን ሁኑ ” የሚል ሳይሆን “ ብርሀናችሁን አብሩ ” የሚል ነው ። በዘመናችን የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዳለን የተገለጠ ነው ። በክርስቶስ የሆንነውን ሳይሆን ፡ የራሳችንን ፍላጎትና ረሀብ ለመግለጥ የምንተጋበት ፣ በራሳችን ፅኑ ሩጫ የተጠመድንበት እንደሆነ በብዙ ይታያል ። “በአብዛኛው”።   👉👉  መልካሙ ስራችን ሲገለጥ እኛ አስረጂዎች ሳንሆን በእያንዳንዱ ቤት የሚገለጥ ፡ የተቀበልነው የህይወት ነፀብራቅ በግልፅ መታየት ይጀምራል ። 👉👉በዚህም እኛ ሳንሆን እራሱ እግዚአብሔር ይከበራል ። 👉ምክንያቱም በእኛ የሚገለጥ የትኛውም መልካም የሚባል ህይወትም ሆነ ተግባር ባለቤቱ እሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ። 👉እኛን ያየ እግዚአብሔርን ያከብራል፣ከክፉ ስራው እንዲመለስ እድል ይሆናል ። 👉በጨለማው ላይ የሚበራ ብርሀን ባለቤቶች አይደለንም ። ነገር ግን እኛው እራሳችን... ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ ”                       ኤፌሶን 5፥8 ተብሎ እንደ ተፃፈ ፦ በጨለማ የነበርን ሳይሆን ጨለማ የነበርን ፣ በዛም መንግሥት ውስጥ እንደሚገባና እንደ ማንነታችን የምንመላለስ ፣ የጨለማው መንግስት የሚረካብን ትጉ ሰራተኞች ነበርን። 👉አሁን ደግሞ የማንነት ለውጥ ፣ የመንግስት ለውጥ በማድረግ...           “...አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤”                           ኤፌሶን 5፥8 እንደተባለ ፦ የሆንነውን በትውልድ ሁሉ ፊት ልንገልጥ ፣ “ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤...”   — ዮሐንስ 8፥12...  እንዳለና በህይወቱም እንደ ገለጠ ፡ በእኛ ያለውን ህይወት ልንገልጥ ተጠርተናል ።  👉👉ትውልድ ሁሉ ኢየሱስን በእኛ ውስጥ ሊያይ ይናፍቃልና ካንቀላፋንበት መንቃት ይሁንልን!!! 👉👉ብርሀን ከሆንን በኋላ ለጨለማው ብርታት የምንተጋበት እድሜ አይኑረን!! 👉👉የደከምን ፣ በክርስቶስ የሆንነውን ለመግለጥ አቅም ያነሳን ብንኖር ዛሬ ከፍ የሚያደርግ ፣ ከድካም የሚያወጣ ፀጋ ይለቀቅልን!!   👉👉ጨለማን ድል የማይነሳ ብርሀን የለምና በተራራ ላይ እንዳለች ከተማ በሁሉም ፊት እንታይ ! 👉👉እግዚአብሔር በእኛ መልካም ስራ መከበር ይፈልጋልና እንደ ብርሀን በጨለማው ሁሉ ላይ እንገለጥ!!    📢📢 የማብራት አመት ይሁንልን📢📢         ✒️✒️✒️ ሱራፌል አምሀ                          15/01/2016      👇👇👇👇 join 👇👇👇👇                      https://t.me/Diorthosis          https://t.me/Diorthosis      https://t.me/Diorthosis
Show all...
ዳይኦርቶሲስ ( DCM )

“...በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” — 1ኛ ጢሞ.3÷15

👍 2
🔔🔔🔔ቢያንስ 5 ወንጌል እንዲሰሙ ለምትፈልጓቸው ሰወች ያጋሩ ። 🙏🙏🙏 👉የምትከተለው ፍጻሜህን ይወስናል!! 👉የምትከተለው ማን እንደሆነ ደግሞ ኑሮህ ይናገራል!! እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ብሎ ያዘጋጀው የዘላለም ህይወት እንጂ ገሀነም እሳት የለም ። የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ገሀነም እሳት ለሰይጣን የተዘጋጀ መሆኑን ነው። “በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።” ማቴዎስ 25፥41 🔥🔥🔥 ሁላችንም እንደምናውቀው ሰው እግዚአብሔርን ከመበደሉ በፊት ሰይጣን ከመላእክት አለቃነት የእግዚአብሔርን ክብር በመመኘት ወድቋል። ገሀነም እሳት ለዲያብሎስና በሰአቱ ለተከተሉት መላእክት ለዘለአለም የቅጣት ቦታ ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ። የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክ ተፋጥሮ ዘመኑን ሁሉ በምድር ያሉትን ሁሉ እየገዛ ህያው ሆኖ እግዚአብሔርን እያመለከ እንዲኖር የፈጠረው ቢሆንም ፤ በራሱ ምርጫ ለዘላለም ህያው ሆኖ ከሚያኖረው ይልቅ ፥ ፍጻሜው ጥፋትና የገሃነም ፍርዳኛ የሚያደርገውን የስህተት ቃል ፡ በጣፈጠ መርዝ ከሰይጣን ተቀበለ። እግዚአብሔር ከሰጠው መመርያ ይልቅ ሰይጣን የሰጠውን ተከተለ ። በዚህም ፍፃሜው የተከተለው (ሰይጣን) የሚገባበት ሊገባ ግድ ሆነ ። ስለዚህ እግዚአብሔር ከወሰነለት ርቆ ፍጻሜው እደተከተለው ዲያብሎስ ሆነ። እግዚአብሔር ማንንም ለገሀነም እሳት አልፈጠረም ! እግዚአብሔር በባህሪው ፍቅር ነው እንጂ ፡ በዘመናት መካከል የተማረው አይደለም ። ሲፈጥረንም ለዘላለም ህይወት እንደነበር ፤ ዛሬም በእኛ ላይ ያለው እቅዱ ያው ነው። ለእኛ ያለውን ፍቅር ለመራዳት ቀራንዮን ማሰብ በቂ ነው ። ዳግመኛ የሰው ልጅ የሚከተለውን መርጦ ዘላለሙን እንዲወስን የመጨረሻውን እድል ልጁን መስዋዕት በማድረግ አዘጋጅቷል። ብዙዎች ግን ተከፍሎላቸው ከፍለው ለመዳን ይጥራሉ ። እግዚአብሔር ግን በልጁ የተከፈለውን ቢል እንጂ በእኛ የተከፈለ አይቀበልም ።“ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤” ዮሐንስ 1፥12 በአዳም ውድቀት የገባንበት የእዳ አዘቅት ኢየሱስን አስከፍሏል። ይህ ክፍያ ቅንጦት ሳይሆን የእኛ የሀጥያት እዳ በዚህ እንጂ በሌላ በምንም ሊወራረድ ስለማይችል የተከፋለ ነው ። እግዚአብሔር የሰው ልጆች መዳን ያዘጋጃው መንገድ ኢየሱስ ነው ። ከዚህ መንገድ ጋር የሚስተካከል ፥ ወደአብ ሊያደርስ የሚችልና በአብ ፊት ለመቆም ድፍረት የሚሆን ምን ልናዘጋጅ እንችላለን? ማዘጋጀት ከቻልን እሰየው ። ነገር ግን ዛሬም ድረስ ሰይጣን ተከታዮቹን ለማብዛት የተለመደ የውሸት ስብከቱን ቀጥሏል ። የማይቻልን ትችላለህ፣ የማይሆነውን ይሆናል እያለ ያስታል። እግዚአብሄር ከዘረጋው ስርአት ውጪ ክብር የለም ፣ ስኬት የለም ፣የዘላለም ህይወት የለም ። “ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም። 1ኛ ዮሐንስ 5፥12 የመጀመርያው ሰው አዳም እንደተሳሳተ ዛሬም የመጨረሻ የመዳን መንገድ የሆነውን ኢየሱስን ስተን ከዘላለም ህይወት እንድንጎድል ይተጋል ። መንቃት ፣ መዘጋጀት ፣ በእግዚአብሔር የተዘጋጀውን ብቸኛ መንገድ መቀላቀል አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ። “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” ዮሐንስ 14፥6 እግዚአብሔር ማንንም ወደገሀነም አይመራም ። ነገር ግን ምርጫችን ፍጻሜያችንን ይወስናል። ለመዳን ያዘጋጃልንን ኢየሱስን ከተከተልን የእግዚአብሔር ምርጫ ወደሆነውና አለም ሳይፈጠር ወደ ተዘጋጀው የዘላለም ህይወት እንገባለን ። እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።”ዮሐንስ 6፥47 “ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።” ማቴዎስ 25፥34 🔥🔥🔥 እንቢ ካልንም ሳይጣንን ልንከተል ወስነናል ማለት ነው ስለዚህ እሱን ተከትለን እሱ የሚደርስበት አለመድረስ አይቻልም ። ✒️✒️✒️ሱራፌል አመሀ https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis
Show all...
ዳይኦርቶሲስ ( DCM )

“...በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” — 1ኛ ጢሞ.3÷15

🔥<<<የፈራነው ሳይሆን ከጌታ የሰማነው ነጋችንን ይወስነዋል>>>🔥 ዘፍ.26 ³ በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፤ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።⁴ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤⁵ አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።⁶ ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ።⁷ የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፤ እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ፤ የዚህ ስፍራ ሰዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፤ እርስዋ ውብ ነበረችና።      🔔ብዙ ግዜ የብዙዎቻችን ድክመት ነው ብዬ አስባለሁ። ቀደም ብሎ እግዚአብሔር በይስሀቅ ህይወት ሊፈጽመው ያቀደውን በዝርዝር ነግሮታል። “እንደሚያበዛውና ይህን ምድር እንደሚያወርሰው ።” ከዛም ላቅ ያለው የተስፋ ቃል በዚህች ምድር ተቀመጥ የሚለው ነው። ነገር ግን በራሱ መንገድ  ኑሮውን ማደላደል ፈልጓል። ይስሀቅ ስለ ሞት ማሰብ በሌለበት ቦታ ስለሞት እያሰበ ነው ። ለዚህም  ህይወቱ እንድትቀጥል በውሸት ሚስቱን እህቴ ናት አለ።    👉ሁኔታውች ብዙ ግዜ የእግዚአብሔርን ቃል ትተን የራሳችንን ጥበብ እንድንከተል ያደርጉናል።    👉 እግዚአብሔር መብዛትን ባየበት ቦታ እኛ ሞትን እንቃኛለን ።     👉ከየትኛውም አስጨናቂ ሁኔታ ፤ ቀድሞ የሰማነው የእግዚአብሔር ድምፅ ያሻግረናል!!     👉ይስሀቅ በርብቃ ምክንያት ልሞት እችላለሁ ባለበት ስፍራ ፤ ከፈራቸው ሰወች ይልቅ በርትቷል፣እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ተባርኳል ፣ በርሀብ ዘመን ዘርቶ መቶ እጥፍ አጭዷል ።    👍ከየትኛውም ተጽእኖ ይልቅ ቀድሞ የሰማችሁት የእግዚአብሔር ድምፅ ላይ ጽኑ!!እርሱ የህይወታችን መልህቅ ነውና!! ተባረኩ                               🖋🖋🖋ሱራፌል አማሀ Join 👇 👇👇👇 https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis https://t.me/Diorthosis
Show all...
ዳይኦርቶሲስ ( DCM )

“...በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” — 1ኛ ጢሞ.3÷15

   የእግዚአብሔር ሀሳብ እና የሙሴ ትህትና     በሙሴ ህይወት የተመለከትናቸው ያልተደገሙ ተአምራት የሙሴን የአገልግሎት ከፍታ በሚገባ የሚያመለክቱ ናቸው ።       ሙሴ ምንም እንኳን በብዙ ግፊት ወደ ግብጽ ቢሄድም ተልእኮውን ከተቀበለበት እስከ ፈጸመበት የ40አመት ጉዞ እግዚአብሔርም እንደመሰከረለት ፍጹም ትሁት ነበር ። በግብጽ ከነበሩት ጠንቋዮች የላቀ ተአምራት ቢያደርግ የሚኮራ አልነበረም ፣ በፈርኦን ፊት ቆሞ ቤተ መንግስትን እስኪንጥ ድረስ የእግዚአብሔርን ክንድ ቢገልጥ አይመጻደቅም፣ በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ግልጽ ልዩነት እስኪታይ ድረስ የእግዚአብሔርን ክንድ ቢገልጥ እራሱን አይኮፍስም ፣ ውሀ እንደ ግርግዳ ቆሞ እያየ '' እኔ '' ብሎ ወደራሱ አያመለክትም ። የሙሴ ህይወት ብዙ የሚያስተምረን ቁም ነገር ቢኖርም ለዛሬ ግን ልቤን የነካኝን የሙሴን የትህትና ጥግ ላካፍላችሁ ።      “እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ከአንተ ጋር ስነጋገር ሕዝቡ እንዲሰሙ፥ ደግሞም ለዘላለም እንዲያምኑብህ፥ እነሆ በከባድ ደመና እመጣልሃለሁ አለው። ሙሴም የሕዝቡን ቃል ለእግዚአብሔር ነገረ።”   — ዘጸአት 19፥9       ይህ ክፍል በግልጽ የሚናገረው እግዚአብሔር ለሙሴ በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነትን እንዲያገኝ ያሰበውን ሀሳብ የሚያወሳ ነው።       እግዚአብሔር ህዝቡ በሙሴ እንዲያምን ፣ እውጥቶ በሜዳ እንደማይጥላቸውና እግዚአብሔር ያለው ቦታ እንደሚያደርሳቸው እንዲተማመኑ ፈልጓል ። ለዚህም '' ...በከባድ ደመና እመጣልሀለሁ...'' በማለት የአሁኑ መገለጥ ህዝቡ ሁሉ በሙሴ  እንዲያምኑ መሆኑን ያስረዳል ።        ብዙ ታምራቶች ታይተዋል ነገር ግን በተገለጡት ተአምራት ሳይሆን ፤ በተገለጠ እግዚአብሔር የሙሴ መመረጥ በህዝቡ ልብ እንዲታተም ያስፋልጋል ። ይህ ትልቅ እድል ይመስላል እራስን ከፍ ለማድረግ ። በሰወች አንቱታን ለማግኘት ከዚህ የተሻለ አጋጣሚ ምን ይገኛል ? ያህዌ ሙሴን ሊያስተዋውቅ ሰው ሁሉ እያየው በደመና ሲገለጥ ፣ ከዚያም አልፎ ..ድሮ ''ተናገረኝ'' ብሎ መልዕክት የሚያመጣ ሙሴ ዛሬ ግን ህዝብ ሁሉ እየሰማ ታላቁን አምላክ ሲያወራው መስማት ። ይገርማል!!  አብሶ በእኛ ዘመን እንዲህ ያለ እድል ቢገኝ ምን እንዳምንሆን አላውቅም ። ምክንያቱም ትንሽ የመለኮት እሳት በጉባኤያችን ስትገለጥ የብዙዎቻችን አራማመድ ሲቀየር ፣ ስማችን ለራሳችን አልጥም ብሎን ሜጀር ማይነር ስንል፣ የመለኮትን ዙፋን ለመጋራት ሲዳዳን ተመልክተናል።       ምንም እንኳን እግዚአብሔር የተገለጠበት አላማ ይሄ ቢሆንም ሙሴ ግን ከዚህ አስፈሪ እና ባለብዙ ግርማ ከሆነ የመለኮት መገለጥ ለራሱ ክብርን ለማትረፍ አልሞከረም ።  “ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።”   — ዘኍልቁ 12፥3   የሙሴ አንዱ የትህትና ጥግ ይሄ ነበር 👉እግዚአብሔር እንደተናገረ በህዝቡ ሁሉ       ፊት ተገለጠ !! 👉በጣም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ነበር 🔥🔥ህዝቡ ሁሉ በፍርሀት እንኪንቀጠቀጡ ድረስ የእግዚአብሔር ክብር የሚያስፈራ ነበር።    ዘጸአት 20 ¹⁸ ሕዝቡም ሁሉ ነጐድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ።           👉ድምጹን ለመስማት አቅም ስላልነበራቸው ...     ዘጸአት 20 ¹⁹ ሙሴንም፦ አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ እንዳንሞት ግን እግዚአብሔር አይናገረን አሉት።            ሙሴ በዚህ ሰአት ምን መለሰ ? ''እኔ ማለት''ብሎ እራሱን ከማሳየት ይልቅ የተገለጠውን እውነተኛ አምላክ ማሳየትን መርጧል ። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር መገለጥ ሙሴን ህዝቡ እንዲያምነው ፣ በፍጹም ልቡ እንዲቀበለው ቢሆንም ፤ ሙሴ ግን ህዝቡን ወደ ልኡሉ አመለከተ።       ዘጸአት 20 ²⁰ ሙሴም ለሕዝቡ፦ እግዚአብሔር ሊፈትናችሁ፥ ኃጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ ይሆን ዘንድ መጥቶአልና አትፍሩ አለ።     👉 ይሄ ሞኝነት ሳይሆን ትህትና ነው ።     👉ሙሴ ያገኘውን እድል አላበላሸም፤          ነገርግን :-       ✔የመክበሩን ምክንያት አከበረ ፣       ✔የከፍታውን ምንጭ ከፍ አደረገ ፣       ✔የሰው ሁሉ ትኩረት ሊሆን የሚገባውን አሳየ እንጂ። 👉 በህይወታችን እግዚአብሔር ከከበረ           በውጭ ማክበር አይከብደንም! 👉በግል እግዚአብሔርን ካየነው እራሳችንን ለማሳየት አቅም እይኖረንም! 👉የጸጋ ስጦታ መንፈስ ቅዱስን በመግለጥ ቤተ ክርስትያንን ለማነፅ ፡ ከዛም እየሱስን ማክበር እንጂ ግቡ ፤ እኛን የመግለጥና የማክበር አላማ የለውም ።   “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል።”  1ኛ ቆሮንቶስ 12፥7      🙏  በዘመናችን ከእግዚአብሔር በተቀበሉት እግዚአብሔርን የማይጋርዱ ፣ ይልቁንም አጋጣሚዎችን ሁሉ እሱን ለማክበርና ለማሳየት የሚጠቀሙ ሀያላን ይነሱልን !!      🙏 እንደተቀበለ ሰው የሚመላለሱ፣ ለራሳቸውም ለቤተ ክርስቲያንም የሚበጀውን የሚያዩና ዝቅ ብለው የሚሮጡ ይብዙልን!!!             የጌታ  ሰላም ይብዛላችሁ🙏🙏                      🖋🖋🖋ሱራፌል አማሀ 👇👇👇👇👇Join👇👇👇👇👇                  https://t.me/Diorthosis           https://t.me/Diorthosis           https://t.me/Diorthosis
Show all...
ዳይኦርቶሲስ ( DCM )

“...በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።” — 1ኛ ጢሞ.3÷15