OPTIMUM CRYPTO
Open in Telegram
📚 ይሄ Official Airdrop እና የ Crypto News በ አማረኛ የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Show more661
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
🗣የ 200 MB ሽልማት ከ ንስር Academy (@Neser_Academy)
🤔እስኪ Weekend በማስመልከት አብረን ፈታ እንበል🤩
👨👨👦👦የ አመቱ ምርጥ ጀማ የቱ ነው? የመለያ ግዜው ደርሷል😊
👉ሁላችሁም እስቲ ከ ትምህርት ቤት ጀለሶች ጋር በጀማ ያላችሁን Picture😎 @Neser_Academy_bot ላኩልን ብዙ Like ሚያገኘው Picture የ 200 MB ተሸላሚ ይሆናል።🔥
➡️ውድድሩ ለ ሶስት ቀን ማለትም እስከ እሁድ ድረስ ይቆያል🥳
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
🔰ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ[የቀጠለ]
©በቀሰም Academy ( ) ተዘጋጅቶ የቀረበ
*⃣ፕረዘንት ለማድረግ ምን ብለን እንጀምር ❓
ዳስተር /Eraser ከተቀመጠበት ለማንሳት ረጋ ብላችሁ እየተረዳመዳችሁ Hello my classmates ፡
Hello dear our ......(Subject) teacher;
ዳስተሩን አንስታችሁ ቦርድ እያጠፋችሁ ንግግራችሁን ሳታቋርጡ ቀጥሉ
Here we are going to see about ..........(your lesson topic)
e.g Here we are going to see about philosophy .....ቦርድ ላይ ቀን ካልተፃፈ ፃፉ ...about philosopy ስትሉ ቦርድ ላይ ከድምፃችሁ እኩል ፅፋችሁ ጨርሱ
ወደ ተማሪዎቹ ዞር ብላችሁ
So if you are ready ,let's began.Philosophy means ....
So here we go.Philosophy means.... የሚል skeleton ተጠቅማችሁ ወደ ፕረዘንቴሽናችሁ መግባት
🔰ፕረዘንቴሽ ስናቀርብ ማድረግ ያለብን ነገሮች!
1⃣ ሰዓት አጠቃቀም
❓የተሰጣችሁን ሰዓት በዓግባብ ካልተጠቀማችሁበት ማለት የምትፈልጉትን ሃሳብ ሳትናገሩ ወደመቀመጫችሁ ትሸኛላችሁ!ስለዚህ ጊዜ ለመቆጠብ ፦
1)አንድ ነገር እየደጋገማችሁ ለማስረዳት አትሞክሩ።
2) ለተማሪዎች ኖት ለመፃፍ አትሂዱ!ኖት ከመፃፍ ይልቅ ትናንት ባሳየኋችሁ ምሳሌ መሰረት draft ያደረጋችሁትን Outline በBullet & numbering ቦርዱን አሸብርቁት!
3) ጊዜ ለመቆጠብ ከፈለጋችሁ በምታወሯቸው ቃል ማህል እንደ ባለስልጣን ' እእእ...' እያላችሁ ንግግር አታቆርፍዱ! ሳዓት ያልቃል ፤ ንግግራችሁ ይደብራል ፤ ነጥባችሁንም ያስጎምዳል!
2⃣ ቦታ አጠቃቀም
ሙሉ ቦታ ለመጠቀም ብላችሁ እንደ Dance chirography መድረኩን አትፈንጩበት!
ከመድረኩ ቀኝ ረድፍ ላይ መቆም ካለባችሁ ቆሙ ፤ በግራ መልኩ መሆን ካለባችሁ እንደዛው አክት አርጉ!ዘና በሉና
❗️Warning : calculation ከሆነ ቦርድ ላይ የምትሰሩት ተማሪዎችን ሳትከልሉ ፤ ራሳችሁን ከቦርዱ ወደ ዳር ገለል አርጋችሁ ማቀጣጠል ይኖርባችኋል!
❗️THINK 'BOUT DIS : ቦታ አጠቃቀም ላይ ጎበዝ ካልሆናችሁ የመድረኩ ማህከል ላይ ሁኑ!በግራም በቀኝም ፤ በማህልም ረድፍ ያሉ ተማሪዎች ትኩረታችሁን አይነፍጓችሁም!
3⃣የሰውነት እንቅስቃሴ አጠቃቀም!
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ''በቃል ለቃል ምልልስ'' ጊዜ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ሃሳባችንን በ 30% ጭማሪ ቀላል እና ግልፅ ያረጉታል።ስለዚህ የሰውነት እንቅስቃሴያችሁ እንደሚከተለው ይሁን!
✅ የእጅ እንቅስቃሴ አጠቃቀም
1)እጃችሁን ከጭንቃላታችሁ በላይ አታወራጩ!...የሚመለከታችሁ ሰው ይደክመዋል)
2) ነገሮችን በተለመዱ የእጅ መልክቶችን ለመግለፅ ሞክሩ!...ለምሳሌ
መሮጥ ከሆኑ ቃሉ እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲረጡ እጃቸውን እይደሚያረጉት ማሳየት ...
3) እጃችሁን ኪሳችሁ አታርጉ!...የጋጣወጥ ባህሪ አላችሁ ተብሎ ይታሰባልና
4) እያወራችሁ ሳለ እጃችሁን አትፈትጉ። የእጃችሁን ጣቶች ለማንቋቋት አትሞክሩ!እንደዛ ስታረጉ ሰው አይኑቹን እጃችሁ ላይ ያረጋል!ያኔ ድንብርብራችሁ ይወጣል!
5) አደራ እየፃፋችሁ የምትሳሳቱት ነገር ካያችሁ በእጃችሁ አታጥፉ!ምምህሩ እና ተማሪዎቹ ለናንተ ያላቸው ቦታ ይቀንሳል!ለምን አንድ ፊደል አትሆንም ከተሳሳተች በዳስተር አጥፉ!
✅ የእግር እንቅስቃሴ አጠቃቀም!
1).በተለይ ሴቶች 😡ጭነታችሁን በአንድ እግራችሁ ላይ አታርጉ!ቆፈጠን በሉ! የተመጣጠነ አረማመድ ይኑራችሁ!ላንዴ እንኳን ዘንበል የሚል አቋቋም እንዳይኖራችሁ!
✅ የጭንቅላት እንቅስቃሴ አጠቃቀም
1) ይሄ እንኳን ብዙ አይጠፋችሁም ፤ ራስ በመነቅነቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው!
4⃣የአቀራረብ ዘዴ
1). ተማሪዉን የሚያሳትፍ ከባቢ ፍጠሩ!
ለተማሪዎች ስታስረዱ ጥያቄ ጠይቋቸው ፣ መልሳቸውንም እየሰማችሁ የተነቃቃ audience ያዙ!መምህሩ አሪፌ እንቅስቃሴ ሲያይ ደስ ይለዋል!
2).ፕረዘንቴሽን ማቅረብ ከጀመራችሁበት second አንስቶ ለ አንዴ እንኳን ወደ መምህሩ እንዳታዩ!
አንዳንድ ደግ መምህር አለ ልክ ዞር ብላችሁ ስታዩት ራሱን እየነቀነቀ ልክ መሆናችሁን እየነገረ የሚያበረታታችሁ!
ሌሎች ግን መስመር ሊያስቷችሁ ነው ሚፈልጉት!በዛላይ አስረዱ የተባላችሁት ተማሪዎችን እንጂ መምህሩን አይደለም!
3.) ፕረዘንት ስታረጉ ልክ እንደመምህሩ ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች አርጉ!
የሚረብሽ ካለ ከክፍል አሶጡ ፤ የሚንጫጫ ካለ ተቆጡ!
4.)የተለየ ፈፈግታ ወይም መሽኮርመም አታሳዩ!ሙዳችሁ ይጠፋባችኋልና
5.) ሁሉንም ተማሪ በዓይ ለመጎብኘት ሞክሩ!ይህ ካልተመቻችሁ !ደስ በሚል ሁኔታ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ያሉ ቀና ተማሪዎችን መርጣችሁ ከነሱ ጋር የአይን ንግግር አርጉ!
...........Done !
❓ለመሆኑ Presentation ላይ ልዩ ቄንጦች ምንድናቸው?
የሚከተሉትን ቄንጦቾ ስትጠቀሙ በእርግጥ ክላሱ ሁሉ እናንተን ለማየት ይናፍቃል!
❗️Warning ፡ አንዳንድ ቄንጥ የማይወድ ወግ አጥባቂ መምህር አለ!ቦታ ለይታችሁ ተጠቀሙ ቄንጦቹ ፦
🔰 እያስተማራችሁ እያለ በእጃችሁ የያዛችሁትን ረጅም chalk ከዳሯ ላይ በጣታችሁ ሽርፍ በማድረግ ሽራፊዋን ወደ ምድር በንቀት መወርወር ....😎
🔰 ኮት ነገር አጥልቃችሁ ከነበር አሁን በንግግር ላይ ሳላቹ ኮታችሁን አውልቃችሁ ....chair lay ጣል ማረግ😎😎
🔰የሆነ diagram አንስታችሁ እያወራችሁ ከቦርዱ ራቅ በሉና ...ድንገት ከፍ ባለ ድምፅ ....ተመልአቱ እዛ መሃል ያለውን ነገር ብላችሁ እጃችሁን መሰንዘር.... ህዝቤ ከዛን ሰፍ 😎
🔰የኮት ቁልፍ መፍታት (በተለይ ሳንቃ ደረት ላላችሁ ወንዶች)
ገልፃ እያረጋችሁ ጀነን ባለ መልኩ የኮት ቁልፍ ቀስ ብላችሁ ፈታ ማረግ
❌አንዳንድ ተማሪ ቄንጥ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ነገር ግን ስግጥና የሆኑ ቄንጦች በ presentstion
🚫 አንገት ማሸሻት.......
🚫 ፀጉር በአንድ ጣት ማከክ....
❤️ልብ በሉ : አንዳንድ ተማሪ አለ present እያረጋችሁ ጥያቄ ጠይቆ ግራ ሊያጋባችሁ ሚፈልግ !ስለዚህ ማንም ተማሪ ቢሆን ጥያቄ ለመጠየቅ እጁን ካወጣ ስጨርስ መልስልሃለው በሉት!በኋላ ላይ ወላ ሊረሳው ይችላል!
❤️ልብ በሉ: Present አርጋችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከተማሪዎች እንዲሁም ከመምህሩ ጥያቄ ይነሳባችኋል!ይህን ጊዜ ተማሪዎች እንዲሳተፉ እድል መስጠት ብልጥነት ነው!
👨💻This is all about!
🔗SHARE
🔰ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ
Part - 1
➡️ያልተዘራ ሊበቅል እንደማይችል ሁሉ እኛም ያልተረዳነው ነገር ለሰው ለማስረዳት ስለማንችል!በቅድሚያ Present ስለምናደርገው ነገር አሪፍ ዝግጅት ሊኖረን ይገባል!
1⃣ስለምታቀርቡት ርዕስ በደምብ ተዘጋጁ
*⃣ ከዚህ በፊት በዛ ርዕስ ላይ የወጡ ሃሳቦችን እዩና በራሳችሁ አረዳዳ ለመተርጎም ሞክሩ!
ለምሳሌ ፤When rate of background and forward reaction become equal ,equilibrium state is carried out.''
የሚል ነገር ካያችሁ ለመሸምደድ አትሞክሩ ።የሸመደዳችሁት ነገር ፕረዘንት እያረጋችሁ ቢጠፋ 🐵 ነጥብ ተበላችሁ So.... ሃሳቡን ተረዱና በራሳችሁ አባባል ተርጉሙት :-
'' Equilibrium is a state of reaction in which rate of backward and forward reaction become equal.''
ምናልባት ቃል በቃል ላይገጥም ይችላል!ነገር ግን ዘዬ በሉት ከመግባባት አያግዳችሁም!ስለዚህ በራሳችሁ አገላለፅ ግለፁት።
2⃣ ለምታቀርቡት ነገር አፅተዋፆ (Out line ) አዘጋጁ !
አዎን የምታቀርቡትን ሁሉንም ነገር ወረቀት ላይ መፃፍ የለባችሁም ከዛ ይልቅ Outline ተጠቅማችሁ ነገሩን በአሪፍ ፍሰት ጀምራችሁ መቋጨት።
ለምሳሌ ፥ ስለ መንኮራኩሮች present አርጉ ብትባሉ።sequence ጠብቃችሁ የሚከተለውን Outline ልታወጡ ትችላላችሁ
✔️ SPACESHIPS
1⃣Introduction OF SPACESHIPS
a) dictionary definition of SPACESHIPS
b)History of Spaceships
2⃣SPACESHIPS on today's world
a) the level where they are been now(
b) their pro's and Con's
C)......
3⃣ Conclusion
a)the future destiny of SPACESHIPS
b)Summary about SPACESHIPS
3⃣ክላስ present ከማረጋችሁ በፊት ተለማመዱ
አሪፍ አርጋችሁ ከተዘጋጃችሁ በኋላ ለጓደኞች , ወይም ብቻችሁን ብቻችሁን ስትሆኑ ፕረዘንት በማረግ ተለማመዱ!ይህ ያለባችሁን ጉልበት ፉንትው አርጉ ያሳያችኋል!
❗️Warning : መስታወት ፊት በጭራሽ አትለማመዱ ፣ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ መስታወት እያየ የሚለማመድ ሰው በርዕሱ ይዘት ላይ ሳይሆን በአኳሁኑ ፤ በቄንጥ አወጣጡ እና በቁንጅናው ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ስለሚገፋፋ ቀልብ ይሰርቃል!
4⃣ ዝግጅታችሁን ቶሎ ጨርሱ!
መምህሩ እንድታዘጋጁ ያዘዛችሁ ቀን ወዲያውኑ ተዘጋጅታችሁ ጨርሱ!ካልሆነ
ቴንሽን + plus ቴንሽኝ
መንገድ ላይ ፕረዘንቴሽን😂
5⃣ በሁኔታዌች አደንግጡ !
ከናንተ ቀድመው ያሉ ተማሪዎች present ሲያረጉ ሙሉ ትኩረታችሁ እነሱ ላይ ይሁን። በረጅሙ እየተነፈሳችሁ ለመረጋጋት ሞክሩ።ልክ መምሩ እንደጠራችሁ ፈታ ብላችሁ ንግግራችሁን መጀመር!
*⃣እንዴት ፕረዘንት እናርግ
እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን አየን።እስኪ አሁን ደግሞ እንዴት Present ማድረግ እንዳለብን እንይ 😊
1⃣አደራችሁን ስትጀምሩ
Dear our teacher, dear my classmates first of all I would like to say thank you for giving me this golden chance!😤አትበሉ!Highschool የመረረን ነገር 🤮🤮
ይህን ካላችሁ መምህሩ Yared Negu 16th derivative መሆናችሁን ያውቃል☹️!Golden chance 🤮በዚህ አሽቃብጣችሁ ማርክ ለማግኘት የፈለጋችሁ ስለሚመስለው ጉድፍ ይፈልግባችኋል!
ተማሪዎች እራሱ በጣም ይንቋችኋል!አሪፍ ፊት አታገኙም!ሁሉም ሰው ሲሰግጥባችሁ ድንብርብራችሁ ይጠፋል!
❓ካዲያ ምን ብለን እንጀምር
................to be continued!
Part - 2 Coming Soon...
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
🔰ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ
❓ስንቶቻችሁ ናችሁ Presentation አቅርቡ ተብላችሁ ፤ በፍርሃት🥶ምክንያት ሳታቀርቡ ቀርታችሁ ማርክ የተጎመዳችሁ? ስንቶቻችሁስ ትሆኑ እውቀቱ እያለቹ በፍራቻ ምክንያት ከተማሪዎች ፊት ለፊት ማለት የምትፈልጉት ነገር ሳትሉ የምትገቡ?
❓ለራሳችሁ ምርጥዬ አርጌ ነው ፕረዘንት ያረኩት ብላችሁ?ያልጠበቃችሁት ማርክ ተሰቷችኋል😳❓
🔰እንግዲያውስ ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ እና ሚስጢር ይዘንላችሁ ከተፍ አልን?😊
ከ 100👍 በኋላ ጠብቁን! ያልጠበካችሁት ነገር ያስገርማችኋል
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
🔰ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ
❓ስንቶቻችሁ ናችሁ Presentation አቅርቡ ተብላችሁ ፤ በፍርሃት🥶ምክንያት ሳታቀርቡ ቀርታችሁ ማርክ የተጎመዳችሁ? ስንቶቻችሁስ ትሆኑ እውቀቱ እያለቹ በፍራቻ ምክንያት ከተማሪዎች ፊት ለፊት ማለት የምትፈልጉት ነገር ሳትሉ የምትገቡ?
❓ለራሳችሁ ምርጥዬ አርጌ ነው ፕረዘንት ያረኩት ብላችሁ?ያልጠበቃችሁት ማርክ ተሰቷችኋል😳❓
🔰እንግዲያውስ ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ እና ሚስጢር ይዘንላችሁ ከተፍ አልን?😊
ከ 👍100 በኋላ ጠብቁን! ያልጠበካችሁት ነገር ያስገርማችኋል
Law of Attraction?😝
Coming soon...
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
➡️Difference Between Resistance and Resistivity
🤜Understanding the difference between resistance and resistivity is certainly an important part of learning physics.
🤌Furthermore, an important difference between resistance and resistivity has to do with the flow of free electrons. Also, resistance is an aspect that opposes the flowing of free electrons.
👉In contrast, resistivity is any material’s property that tells the resistance of the material with a particular dimension.
▶️Understanding the difference between resistance and resistivity will certainly help you in dealing with more complex topics of electricity.
⏩Definition of Resistance
Resistance refers to a measure of opposition to the flow of current in an electrical circuit. Furthermore, the measurement of resistance takes place in ohms.
Moreover, the symbolization of resistance takes place by the Greek letter omega (Ω). Also, the naming of resistance was after a German physicist Georg Simon Ohm (1784-1854).
⏩Definition of Resistivity
One can certainly define resistivity as a measure of the resistance of a specific material of specific size to electrical conduction.
➕One can also say that resistivity refers to as the volume resistivity or specific electrical resistance, even though such terms are not in popular usage.
#Update
በዚህ አመት 152ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን እንደሚቀላቀሉ ተገለፀ።
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152ሺ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።
ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።
በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።
የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287ሺ 223 ናቸው።
የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
😊ውዴ እኔ አዳም ነበርኩ ፣ ካዲያ ቸሩ ፈጣሪዬ ብቸኝነቴን አይቶ ነው አንቺን የሰጠኝ።ከዛን ጊዜ ጀመሮ ነው እንግዲ ከጎኔ መሆን የጀመርሽው ።ክብርት ሆይ አንቺ ምንም እንኳን አንቺ ያልሽን ሰምቼ ፣ ከ መልካሚቱ ገነት ብወጣም ፣ አቤልን የመሰለ ልጅ ሰተሺኛል።እመቤቴ የህየወትን ፅዋ ተጠምቼ የነበር ቢሆንም ፣ ዳግም ባንቺ ንፅህና ምክንያት ምህረትን አጊንቼ ጥሜን ቆርጫለሁ🙏።
❤️የኔ እናት አንቺ ባቶልጂን ኖሮ ፣ ዛሬ እኔ እንዴት መኖር ይቻለኛል❓አባቴ አንቺን ባያገኝ እኔ አልኖርም ነበራ ❗️ዉዷ እህቴ እኔን ታናሽ ወንድምሽን ተንከባከበሽ ስላሳደግሺን አመሰግናለሁ፣ ውለታሽን መቼም አረሳዉም።ውዴ ለኔ አንቺ ማለት መቼም የማረሳሽ የ ትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነሽ፣ አብረን ያጠናንባቸው ፣ የተመካከርንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ አይረሱኝም❗️ዉዴ ፈጣሪ ሲል ፣ ቀኑም ሲደርስ ጣትሽ ላይ ቀለብት አስርልሻለሁ።በፍቅር በ ደስታ አብረን እኖራለን።💞
ዉዴ ዛሬ ቀንሽ ነው ፣ ያንችን መኖር በህይወቴ ዋጋ እንዳለው ልነግርሽ ፈልጋለሁ። እንድትጎጂ አልፈልግም ፣ ለጠብቅሽ ሁሌም ዝግጁ ነኝ።መልካም የሴቶች ቀን😊።
✳️የኔ ሴት ሁሌም አብሬሽ ነኝ !
©QesemAcademy
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
Colligative Properties
🤝Part-4🤝
4⃣Osmotic Pressure
⚡️Osmotic pressure is the pressure required to stop a solvent from flowing across a semipermeable membrane. The osmotic pressure of a solution is proportional to the molar concentration of the solute. So, the more solute dissolved in the solvent, the higher the osmotic pressure of the solution.
🔥The van’t Hoff equation describes the relationship between osmotic pressure and solute concentration:
Π = icRT
where
Π is osmotic pressure
i is the van’t Hoff index
c is the molar concentration of solute
R is the ideal gas constant
T is temperature in Kelvin
🤚THE END✋
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
Colligative Properties
🤝Part-3🤝
3⃣Vapor Pressure Lowering
👉Vapor pressure of a liquid is the pressure exerted by its vapor phase when condensation and vaporization occur at equal rate. The vapor pressure of a solution is always lower than the vapor pressure of the pure solvent.
🤜The way this works is that the solute ions or molecules reduce the surface area of the solvent molecules exposed to the environment. So, the rate of solvent vaporization decreases. so the new equilibrium has fewer solvent molecules in the vapor phase.The solute particles stabilize the solvent molecules, stabilizing them so they are less likely to vaporize.
🤌Raoult’s law describes the relationship between vapor pressure and the concentrations of the solution:
PA = XAPA*
where:
PA is the partial pressure exerted by component A
PA* is the vapor pressure of pure A
XA is the mole fraction of A
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
Colligative Properties
🤝Part-2🤝
...The formula for freezing point is:
ΔT = iKfm
where:
ΔT = Change in temperature in °C
i = van ‘t Hoff factor
Kf = molal freezing point depression constant or cryoscopic constant in °C kg/mol
m = molality of the solute in mol solute/kg solvent
2⃣Boiling Point Elevation
🤜The boiling point of a solution is higher than the boiling point of the pure solvent. As with freezing point depression, the effect is directly proportional to solute molality. For example, adding salt to water increases the temperature at which it boils (although not by a lot).
Boiling point elevation may be calculated from the equation:
ΔT = Kbm
where:
Kb = ebullioscopic constant (0.52°C kg/mol for water)
m = molality of the solute in mol solute/kg solvent
Part-3 & Part-4 Coming soon
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
Colligative Properties
🤝Part-1🤝
In chemistry, colligative properties are characteristics of chemical solutions that depend on the number of solute particles compared to solvent particles, not on the chemical identity of the solute particles.The four colligative properties are
1⃣freezing point depression
2⃣boiling point elevation,
3⃣vapor pressure lowering and
4⃣osmotic pressure
The 4 Colligative Properties
1⃣Freezing Point Depression
👉Freezing points of solutions are lower than freezing points of pure solvents. The depression of the freezing point is directly proportional to solute molality.
The effect works in other solvents besides water, but the amount of the temperature change varies by solvent.
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረገውን መግለጫ ተከትሎ በርካታ የተማሪዎች ወላጆች ልጆቻቸው ኮሌጅ እንኳን ገብተው መማር እንዳይችሉ ወደ ግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግቢያ ነጥብ እጅጉን ከፍ ማለቱን በመቃወም መንግስት ለልጆቻችን የወደ ፊት እጣ ፈንታ ሲል በመግቢያ ነጥብ ላይ ማስተካከያ ያድርግ ሲሉ ጠይቀዋል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠር መማር የተነፈገ ወጣት በማምረት የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ አይቻልም ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ መንግስት ፍትሃዊ ፈተና ማስፈተን ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራ ዘንድም ጠይቀዋል።
©Addis_News
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
📊የዩኒቨርሲቲ ማለፊያ ነጥብ ከ 400 በላይ ሊሆን ይችላል⁉️
እንግዲ ብዙዎች የ ዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ማለፊያ ነጥብ ክፍ ከውትሮው ክፍች ሊል እንደሚችል እየተነበይዩ ይገኛሉ። ለዚህም ምክንያት አላቸው።
1️⃣ በዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ቁጥር ክፍ ያለ ነው 599,003። ከ አለፈው አመት ተፈታኞች ጋር ሲነፃፀር በ የ 200,000 ተማሪዎች ጭማሬ አለው ።ካዲያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የዩኒቨርቲዎች መቀበል አቅም 150,000 የተማሪዎችን ቀጥር ብቻ ነው።ካዲያ ምን ያክል ተማሪ ያልፍ ይሆን።
2️⃣ በዘንድሮ አመት ፈታናዎች ተሰርቀው ወተዋል። ፈተናው ከመጀመሩ በፊት በ ቀናት ልዩነት ፈታናዎች እየተለቀቁ ASSIGNMENT ነው ወይስ ፈተና ነው በሚያስበል ደረጃ ተማሪዎች በቤታቸው ፈተናዉን ሰረተው ፣ ክላስ ዉስጥ የሸመደዱተን መልስ ሲደቀድቁ ነው የከረሙት። የሚያሳዝኑት ግን አይናቸውን እስኪቃጠል በ ሃቀኝነት ለመስራት የሞከሩ ምስኪን የደሃ ተማሪዎች ነበሩ።
3️⃣ በፈተና ጊዜ Internet አልተዘጋም ነበር፣ የ ድህር ገፁን ለማቋረጥ ተሞከረ እንጂ Intrnet አልተዘጋም ነበር።አሁን ጥያቄው ስንቶች ናቸው ስለ VPN Service የማያዉቁት።
📊በዛም ሆነ በዚህ የዘንድሮ የ 12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ማለፊያ ነጥብ ከ 400 በላይ እንዳይሆን ተሰፋ እናርግ።ከሆነ ግን ሁኔታዎች የሚያመሩበትን መንገድ መገመት ይከብዳል።
©Qesemacademy
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
እስቲ የንስር Academy ቤተሰቦች ነጥባቹን ሳትዋሹ ንገሩን?
>550 - 15
👍👍👍👍👍👍👍👍 28%
500 - 550 - 4
👍👍 7%
450 - 500 - 13
👍👍👍👍👍👍 25%
400 - 450 - 7
👍👍👍 13%
350 - 400 - 5
👍👍 9%
300 - 350 - 5
👍👍 9%
<300 - 5
👍👍 9%
👥 52 people voted so far.
Ayu's Therapy
🤷♂️ነጥብ ተመለሰ አልተመለሰ ብላችሁ ለምትሸበሩ የተዘጋጀ Therapy
😎Part - 2😎
©በ ንስር Academy
(@Neser_Academy)
🙏በመጀመሪያ ስለጠፋው ይቅርታ🙏
4️⃣እራሳችሁ አበልፅጉ(Self Improvement)😇
👉አዕምሮን ሊያነቃቁ የሚችሉ አንዳንድ ምርጥዬ የሆኑ ፅሁፎችን ፤ ቪድዮችን እና Audiobookችን በየጊዜው መከታተል አለባቹ።
Ayu እነዚህን ከ የት እናገኛለን ብላቹ ለምጠይቁኝ🤷♂ ደግሞ ከታች የዘረዘርኳቸውን የማህበረሰብ አነቃቂ አሰልጣኞችን(Motivational Speakers)🎤ተከታተሉ:-
⭐️MANYAZEWAL ESHETU
➡️በመጀመሪያ ለሱ ያለኝን ክብር መግለጽ እፈልጋለው
👨ይህ ሰው በጣም ብዙ የሆኑ ችግሮችን አሳልፎ ነው ዛሬን የደረሰው ስለሱ ማውራት ከጀመርን አንድ ቀን እራሱ አይበቃንም፨
📱Social media-Telegram,Tiktok & Youtube ላይ "Manyazewal eshetu" ብላቹ ፈልጉ
🤝እሱን በአካል ማግኘት የምትፈልጉ ደግሞ የሱን Seminar መታደም ትችላላቹ።
ዘወትር እሁድ ጠዋት ከ3:00 እስከ 6:00
እንዲሁም ሰኞ ማታ ከ12:00 እስከ 2:00
-
ቦታ: ቦሌ በአለምሲኒማ
መግቢያ :-100 ብር
☀️INSPIRE ETHIOPIA(ዳኒ & ስነ)
▶️እነዚህ ሁለት ሰዎች Professional Life Coach ናቸው ፤ እመኑኝ እነሱን ብትከታተሉ ታተርፉላቹ🤗
📱Social media :-Telegram,Youtube & Tiktok
👨💻በ አካል ለማግኘት የ online "Zoom" ስልጠና ስላላቸው ከፍላቹ መሰልጠን ትችላላቹ👩💻
⚡️አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ(መልካም ወጣት)
⏩ይህ ሰው ለ ኢትዮጽያ ከፍታ ከሚለፋ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው።🙏
✍የሱን ቪድዮዎች ለማየት የግድ ፕሮቴስታንት መሆን አይጠበቅብህም
😎Positive Thinker መሆን ከፈለክ YONI🥰 ምርጥ መፍትሄ ነው።
Social Media :-Youtube(Marsil Tv)
✨ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
👌ይህ ኡስታዝ ለ ትውልድ ለውጥ ከሚሰሩ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው።
👍ከምንም በላይ ደግሞ የውስጥ ፅዳት ላይ ከ ኡስታዝ አቡበክር ናስር😘 ጋር የሰሩትን ቪድዮ ብታዩ በጣም ይጠቅማችኋል።
Social Media :-Youtube(Alif media)
🤙እነኝን አነሳን እንጂ እነ አብይ ይልማ ፣ የ Tiktok influencerኦች እና ብዙ ብዙ አሉ!አቦ እንዲህ አይነቶቹን ሰዎች ፈጣሪ ያብዛልን 🙏🙏🙏
5⃣Gym & Workout🏋♂
🥱ጠዋት ወይም ማታ ላይ ለ 45 ደቂቃ Dumpbell ብትገፉ ወይም ብትሮጡ🏃♂ ውጤቱን ለማየት ሁለት ወር አይፈጀባቹም💪
🧔♂ከዛ በኃላ ጀለሶችክ ግብዳው እያሉ ይጠሩካል ፤ አንቺም ሸንቃጣዋ🙍♀ መባል ትጀምሪያለሽ ከምንም በላይ ደሞ ጠዋት ጀምበር ስትወጣ ማየት እራሱ ትልቅ Energy ነው።🌞
6⃣ተሰጦቻችሁን አዳብሩ☀️
🥇የትኛውም Talent ሊደበቅ አይገባውም። እናንተም፡-
👨🎨የ ስዕል ተሰጦዎቹን ብታዳብሩ አንድ ቀን ሀገር ታስጠሩ ይሆናል
📝የግጥም ተሰጦ ያላቹ በትክክል ብታዳብሩት አንድ ቀን የራሳችሁን መጽሃፍ ትጽፉ ይሆናል
⚽️የ እግርኳስ ተሰጦ ያላቹ ደግሞ Training ላይ በርቱ እነ LEO MESSI😍,Cr7 & others ተሰጥኦዋቸውን ከ ልፋት ጋር በማቆራኘት ነው እዚ የደረሱት። ብዙ ግዜ እግርኳስ ከ ትምህርት ጋር አይሄድም ይባላል ይህ 100% የተሳሳተ ነው 🙅፤ እንዴት የሚለውን ሌላ ግዜ እንመለስበታለን።
7⃣አንብቡ📗
📚ብዙ አንብቡ ብዬ አላስጨንካቹም ነገር ግን አሪፍ የሚባሉ መጽሐፎችን መርጣቹ ብታነቡ ምርጥዬ ይሆናል።
🤔እንደኔ ብታነቡ ብዬ የምመክራቹ መጽሐፎች
🤜ATOMIC HABITS &
🤜THE SECRET የናንተ ፍላጎት ከሆነ POST እናረጋቸዋለን ፤ መቼም ለናንተ ማንሆነው ነገር የለም😍
✍ Aዩ ነበርኩኝ✍
👊የዛሬውን በዚው አበቃን በሚቀጥለው እስክንገናኝ PEACE🖐
ንስር Academy ❗️
🦅ከፍ እንደ ንስር!
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
📚JOIN: @Neser_Academy
📚JOIN: @Neser_Academy
╚════════════╝ ⇲
ሰሞኑን ፈተና ስላለኝ ለ ትንሽ ጊዜ Post ላላደርግ እችላለው🙏
ይቅናክ - 68
👍👍👍👍👍👍👍👍 95%
😢 - 8
👍 11%
👥 71 people voted so far.
