cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

guzo wede jenet

ጉዞ ወደ ጀነት አላማው 🌎 ዳእዋዉን ተደራሽ ለማድረግ ነው የተለያዩ የነቢያት ታሪክ ሶሂህ ቡሀሪ ሀዲሶች የሶሀቦች ታሪክ ስለ ጤናዎ መረጃ እዚህ ቻናል ላይ ያያችሁትን ማንኛውም ስተት እንድትነግሩን በአላህ ስም እንጠይቃለን እንዲሁም ገንቢ ሀሳቦን ያጋሩን ሁሌም ከጎናችን ላላችሁ ሁሉ አላህ ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። ለአስተያየትዎ @asiye9 @Asutii5

Show more
Advertising posts
368
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
የጁምዓ ቀን ሱናዎች•° 1 ገላን መታጠብ። 2. ሽቶን መቀባባት (ለወንድ) እና መዋብ። 3. ሲዋክን መጠቀም። 4. የክት ልብስ መልበስ። 5. በጊዜ መስጂድ መጓዝ። 6. በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ። 7. መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር። 8. ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየተል መስጂድን መስገድ። 9. ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ። 10. ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ። 11. ሰደቃን ማብዛት። 12. ሱረቱል ከሕፍን መቅራት። 13. ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ። 14. በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋትን በብዛት ማውረድ።      የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ "መልካምን ነገር ያመላከት የሰሪውን ያህል ምንዳ ያገኛል።       http://t.me/guzo5
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
00:19
Video unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
የዑመር ኢብኑልኸጣብ (ረዐ) 20ምርጥ ምክሮች፤ . 1. ‹የምትጠላውን ሰው ተጠንቀቅ፤› 2. ‹ብልጥ ሰው የእለት ስራዎቹን ከራሱ ጋር ይተሳሰባል፡፡ 3. ‹የዛሬን ስራ ለነገ አታሳድር፡፡› 4. ‹ከሰዎች ጥያቄ ተነስተህ አስተሳሰባቸውን መለካት ይቻላል፡፡› 5. ‹ለሌሎች ዳዕዋ በምታደርግበት ወቅት እራስህን አትርሳ፡፡› . 6. ‹ከዱንያ ትንሽን ብቻ ስትፈልግ ይበልጥ ነፃነትን እያገኘህ ትሄዳለህ፡፡› 7. ‹ወንጀል አለመስራት ከፀፀት ይሻላል፡፡› 8. ‹ታጋሽ ሁን፤ ትዕግስት የእምነት ምሶሶ ነችና፡፡› 9. ‹አሏህን ፈሪ መሆን እድለኛነት ነው፤ ከዚህ ውጭ ያለው እድለቢስ መሆን ነው፤› 10. ‹ወደ አኺራ የሄዱ ሰዎችን ንግግር ጠብቁ፤ እነርሱ የተናገሩት አሏህ እንዲናገሩ ያገራላቸውን ብቻ ነውና፡፡ . 11. ‹አሏህን ፍራ፤ እርሱ ሁሌም ህያው፤ ከርሱ ውጭ ያሉ ሁሉ ጠፊ እና አላቂ ናቸውና፡፡ 12. ‹ጥፋቴን በነገረኝ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡ 13. ‹እውቀትን ገብያት፤ ከዚያም ለሰዎች አስተምር፡፡› 14. ‹የተከበርክ፣ ታማኝ እና እውነተኛ ሁን፡፡› 15. ‹ትምክህተኛ ምሁር አትሁን፤ ትምክህተኛነት እና እውቀት አንድ ላይ አይሄዱምና፡፡ . 16. ‹ለዚህች አለም ፍቅር ያለው አዋቂ ባየህ ግዜ እውቀቱ አጠራጣሪ መሆኑን ተረዳ፡፡› 17. ‹ትንሽ አውርቶ ብዙ በሚሰራ ሰው ላይ የአሏህ እዝነት ይውረድ፡፡› 18. ‹ታማኝነት ማለት በምትሰራው፣ በተናገርከው እና በምታስበው ነገሮች ልዩነት አለመኖር ማለት ነው፡፡ 19. ‹የሰው ልጅ ምንም እንኳ እንደ ቀስት ቀጥ ያለ ስራ ቢሰራ ተቃውሞ አያጣውም፡፡› 20. ‹አዕምሮህ እንዲሰፋ ከፈለግክ፤ ከፈሪሀ አሏሆች ጋር ተቀመጥ፤› ለወዳጆችዎ ሼር በማድረግ ያካፍሉ http://t.me/guzo5
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ልታገባ ስታስብ ..... አንድ ልጅ ለአባቱ እንዲህ ሲል ያማክረዋል። ልጅ:- አባዬ ላገባ አስቢያለው አባት:- ይቅርታ በል ልጅ :- እንዴ አባዬ ምን አጠፋሁ አባት :- ይቅርታ በል አልኩህ ልጅ :- አባዬ ጥፋቴን ንገረኝና ከዛ ይቅርታ እጠይቃለው አባት:- እኔ የምልህን አትሰማም እንዴ ይቅርታ በል አልኩህ ልጅ :- እሺ ይቅርታ አባት :- አዎ ልጄ ልታገባ ስታስብ ሳታጠፋ ይቅርታ መጠየቅን መልመድ አለብህ። አዎ ልታገባ ስታስብ ያለ ጥፋትህ ይቅርታ መጠየቅን መልመድ አለብህ። ካልሆነ ትዳር በእልህና በአልሸነፍ ባይነት የሚመራ ጥምረት አይደለም። ሁለታችሁም አልሸነፍ ባይነት ከተቆጣጠራችሁ ፍቅራችሁ ይሻክራልና ልክ እንደተጋባችሁ ለሚስትህ እንዲህ በላት። «ሀቢብቲ እኔ ስናደድ አንቺ በረድ በይ እሺ! ምንም ያክል ጥፋቱ እኔ ጋር ቢሆንም ተሸነፊልኝ» አንቺም እንዲህ በይው «ሀቢቢ ህይወቴን ካንተ ጋር እስከ ጥግ መሄድ ስለምፈልግ እኔ ትክክል ነኝ ብዬ አስቤ በንዴት ድርቅ ካልኩብህ ተሸናፊ ሁነህ አረጋጋኝ! በፍቅርህም ገስፀኝ» አሏህ ደስ የሚል ሐያትን ይለግሳችሁ 𝓱𝓪𝓯𝓾 ቻናል:- t.me/lemuslimuaehte
Show all...
ለሙስሊሟ እህቴ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ بسم الله الرحمن الرحيم በቻናላችን ዲናዊ እውቀቶች ስለሒጃብ ማብሪራያዎች ስለ ትዳር ምክሮች እናንተን ያዝናናል ያስተምራል የምንላቸው በአላህ ፍቃድ ለናንተ እናደርሳለን። ከናንተ ሚጠበቀው join ማረግ ነው። @lemuslimuaehte for any comment 👇 @fitayebot