884
Subscribers
+324 hours
+77 days
+1230 days
Posts Archive
Get All The Textbooks And Teacher's Guides you need based on the new curriculum at
https://t.me/+Nf6Q0lTl_pkzYjE0
የአዲሱን ስርዓተ - ትምህርት መጽሀፍ በአንድ ላይ
KG 1 KG 2 KG 3
GRADE 1 GRADE 2 GRADE 3
GRADE 4 GRADE 5 GRADE 6
GRADE 7 GRADE 8 GRADE 9
GRADE 10 GRADE 11 GRADE 12
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
ALL IN ONE ALL IN ONE
ALL IN ONE ALL IN ONE
Start unlocking your full potential now!
ውድ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ይህ ማስታወሻ በፈተና ወቅት ይጠቅማችኋል በትኩረት ይነበብ።
😃😃😃😃😃😃😄😄😄
ውድ ወላጆች !
በፈተና ወቅት በተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ውጥረት እና መጨናነቅ ለመቀነስ ይህንን ምክር በማስገንዘብ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን።
☝️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች
📙 ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው።
👉ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤
👌 ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።
☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡
👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አለመሆኑን መረዳት
☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጁ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን
☝️ ከጓደኞቻችን ወይም ከወላጆቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ እርማት እንድናረግም ያግዘናል።
☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል።
👉ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤
👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።
👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።
👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር::
👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤
👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።
👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።
👉በተደጋጋሚ ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ።
👉ወቅቱ የፈተና ወቅት በመሆኑ ተማሪዎች እንደየ እድሜያቸው እና የክፍል ደረጃቸው ይህን ማስታወሻ እንዲጠቀሙበት እናሳስባለን
