cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🌹 የተውሂድ ፋና 🌹

🌹 🌹 🌹 أثر التوحيد

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
143
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

`የትዳር ነገር ========= ቁም ነገሩ «መቼ ታገባለህ?» የሚለው ጥያቄ ሳይሆን «ማንን ታገባለህ?» የሚለው ነው። || የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር፦ «አላህ ሆይ! ከሽበት እድሜዬ በፊት ከምታሸብተኝ የትዳር አጋር በአንተ እጠበቃለሁ»። ﺍﻟﺴﻠﺴﻠﺔ ﺍﻟﺼﺤﻴﺤﺔ (3137) ✔️ኢማሙ ሻፊዒይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ አሉ፦ «ከማምናቸው ጓደኞቼ መካከል አንደኛው እንዲህ ሲል ሰማሁ "ዲኔን ለመጠበቅ ብዬ አገባሁ ነገር ግን በመጥፎ ሚስቴ ምክንያት የእኔም፣ የእናቴም፣ የጎረቤቶቼም ዲን ጠፋ።" ተወገደ»! || ✔️ለአንተ ለእድገትህም ለውድቀትህም ወሳኟ ሚስትህ ናት፣ ሚስትህ በዲኗ እንዲሁም በባህሪዎና በሁሉም ነገር ካማረች ሁሉም ነገርህ ያምርልሃል፣ የአላህን ህግጋት እንዳትዘናጋ ታስታውስሃለች። || ለዛም ነው ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ዱኒያ መጣቀሚያ ናት ከመጣቀሚያወቹ መካከል ደግሞ ሷሊህ ሚስት ናት»።ያሉት በሌላ ዘገባ ላይ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦ ሴት ልጅ ለአራት ነገራቶች ትገባለች:- ➊↝ለመልኳ ➋↝ለገንዘቧ ➌↝ለዘሯና ➍↝ለዲኗ ዲን ያላትን ያልመረጠ እጁ አመድ ይፈስ ብለዋል። ምንጭ:-ሙስሊም (1466) መልካም ሴትስ ማናት? እሷ ማለት አላህ በቁርአኑ ያወሳትና በሱናም መልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓይሂ ወሰለም) የጠቀሷት ናት! ﻭﻗﺎﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻓَﺎﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕُ ﻗَﺎﻧِﺘَﺎﺕٌ ﺣَﺎﻓِﻈَﺎﺕٌ ﻟِﻠْﻐَﻴْﺐِ ﺑِﻤَﺎ ﺣَﻔِﻆَ ﺍﻟﻠَّﻪُ አላህ እንዲህ ይላል፦ «…መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡…» ቅዱስ ቁርኣን ሱራ ኒሳእ (34) || ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:- «ሴት ልጅ አምስት አውቃት ሰላቶቿን ከሰገደች፣ የረመዳንን ወር ከፆመች፣ ብልቷን ከጠበቀች፣ ባለቤቷን ከታዘዘች በምትፈልጊዉ የጀነት በር ግቢ ትባላለች»። (ኢብኑ ሂባን በሰሂህ ዘግበዉታል) «አላህ አንድን ሰው ሲወደው በህይወት መንገዱ ላይ መልካም ሚስትን ያስቀምጥለታል ሚስትህ ወይ የጀነትህ በር ናት አለያም የጀሃነም በርህ ናት ዲኗን አይተህ አግባ»!! ሁላችንንም ከመጥፎ የትዳር አጋር አላህ ይጠብቀን
Show all...
•°♡ ሴት ልጅ ክቡር ናት... ህፃን ሳለች ለወላጆችዋ ጀነትን ታስከፍታልች ሚስት ስትሆን ለባሏ ግማሽ እምነትን ትሞላልች እናት ስትሆን ጀነት በእርሷ እግር ስር ትሆናለች፡፡
Show all...
{قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ} [ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡] (ሱረት ኑር-30) ➧ወንድ ሴትን ማየት እንደማይችለው ሁሉ ሴትም ወንድን ማየት አይቻልላትም ኢብኑል ዓረቢ እንዲህ አሉ:-ለወንድ ልጀ ሴት ልጅን ማየት እንደማይፈቀድለት ሁሉ፡ ለሴትም ልጅ ወንድ ልጅን ማየት አይፈቀድላትም፡ ከእሷ የሚያስበውን አይነት እሷም ከእሱ ያን ታስባለች ምንጭ:-አህካሙል ቁርአን(3-380) ➧አዒሻ ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰው ገባ፡ከዚያም ፊቷን ስትሸፍን ይህ ሰው እኮ ማየት አይችልም አሏት፡ እንዲህ አለች እሱ ባያየኝ እኔ አየዋለሁ አይደል አለች። ምንጭ:- አት ተህሲል(491-17) .•• •⊰✿🌹✿⊱• ••.
Show all...
🌹የልብ መጥበብ በሁለት መንገዶች ይታከማል:— ① አላህን በማጥራት(التسبيح) እና ② በስግደት ( السجود) قال تعالى: { ولقد نعلم أنك يضيق صدرك بما يقولون. فسبح بحمد ربك وكن من الساجدين} አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በእርግጥ እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ሁን። 👇👇👇👇👇 https://t.me/yetwhiedfana
Show all...
🌹 የተውሂድ ፋና 🌹

🌹 🌹 🌹 أثر التوحيد

አስታውስ(ሺ) ☞አንድ ቀን ይመ ጣል አንተ እራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያውለወቁልህ ቀን ☞የተከፈተ አፍ እና አይንህን ሰዎች የሚዘጉልህ ቀን ☞ተራምደህ ከሄድክበት ቦታ ሰዎች ተሸክመው የሚያስወጡህ ቀን ☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን ☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ የሚወልቅበት ቀን ✘✘✘✘✘✘✘✘✘✘ ፌስቡኬ ★Friend request ይላካል ዝም ★አሰላሙ አለይኩም ጭጭ ★ኧረ አናግሪኝ፣ ለምን ዘጋሺኝ? መልስ የለም !!! ማን ይመልስ? እኔ ወደማይቀረው አለም ሄጃለሁ ያ ራህማን !! አጂብ ልብ የሚነካ ታሪክ እባከወን ያንብቡት ¶እናት ከልጇ ሞት በኋላ ያጋጠማት ልዩ ታሪክ¶ .................. ¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶¶ ልጅ በአንድ የዲን ዩንቨርስቲ ተማሪ ስትሆን ልዩ ድምጽም ነበራት፡፡ በዚህም ሁለ ግዜ ለሊት ቁርአን ትቀራ ነበር፡፡ ቂራአቷም እጅግ ያማረ ነበር፡፡ እናት ወደ ክፍሏ ስትሄድ ከልጇ ከፍለ በር ላይ በመቆም ያማረ ቂራአቷን ሁል ግዜ ታዳምጥ ነበር፡፡ በዚህ አየነት ቀናቶች ያልፉ ነበር፡፡ ከእለታት አነድ ቀን ይህች ልጅ ታመመች፡ ቤተሰቦቿም ወደ ሀኪም ቤት ወሰዷት፡፡ በሆስፒታሉም ለቀናት ቆየች፡፡ ማገገም አልቻለችም ህይወቷ በሆስፒታሉ ውስጥ አለፈ፡፡ ቤተሰብ በጣም አዘነ በተለይ እናት በልጇ ሞት እጅጉን አዝናለች፡፡ የመጀመሪያው እናት ለጇን ያጣችበት ቀን የአመት ያክል ረዘመባት፡፡ መሽቶ ወደ ክፍሏ የምትሄድበት ሰአት ላይ እናት እንደለመደችው ከልጇ ክፍል በር ላይ ቆመች ይሄኔ አንድ አስደንጋጭ ነገር ሰማች ከክፍሉ ወስጥ ብዙ ሆኖ ዝግ ባለ ድምጽ ለቅሶ ይሰማል፡፡ ወደ ውስጥ ለመግባት ፈራች፡፡ እስኪነጋ ጠብቃ እናት ሌሊት ከልጇ ቤት ወስጥ የሰማቸውን ለቤተሰብ ነገረች፡፡ ወደ ከፍሉ ገቡ ምንም ነገር የለም፡፡ በሁለተኛው ቀን እናት እንደለመደችው በተመሳሳይ ሰአት ወደ ልጇ ክፍል ስትሄድ ትላንት የሰማችውን ድመጽ በድጋሚ ሰማች የሰማችውንም ለባለቤቷ ነገረችው፡፡ ባለቤቷም ሲነጋ የሰማሽው ምን እንደሆነ እናጣራለን አሁን ተኚ ይላታል፡፡ ጠዋት ላይ ወደ ከፍሉ ሲሄዱ ምንም ነገር የለም፡፡ እናት ግን ድምጹን መስማቷን እርግጠኛ ነበረች፡፡ የሰማችውን ለአነድ ጓደኛዋ ትነግራታለች፡፡ ጓደኛዋም አንድ አዋቂ ሰው ብታማከር የተሻለ እንደሆነ ትነግራታለች፡፡ እናትም አንድ ሸኽ ጋር በመሄድ ስለ ሁኔታው ነገረቻቸው፡፡ ሼኹም በሁኔታው በመገረም በሰአቱ በመገኘት ሁኔታውን ማየት አለበኝ በማለት ተነስተው ሄዱ፡፡ ከዚህ ቀደም ልጅ በቤቱ ወስጥ ትሰራው የነበረውን ሁሉ እናት ለሸኹ ነገረቻቸው፡፡ ልክ ሰአቱ ሲደርስ ወደ ክፍሉ ተጠጉ፡፡ እናት ከዚህ ቀደም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስትሰማው የነበረው የለቅሶ ድምጽ ዛሬ ለሶስተኛ ግዜ ተሰማ፡፡ሼኹ ይህንን ሲሰሙ አለቀሱ እናትም ያ ሸይኽ ምንድንው የሚያስለቅሳቹ ስትል ጠየቀች፡፡ ሸይኹም አላሁ አክበር ይህ እኮ የመላኢኮች የለቅሶ ድምጽ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሁል ግዜ ሌሊት ልጅሽ እያለች ከሰማይ በመውረድ እየተሰበሰቡ ቁርአን ያዳምጡ ነበር አሁን ያንን ድምጽ በማጣታቸው ነው የሚያለቅሱት፡፡ ሱብሀነላህ እርሶ ዘንድ እንዲቀር አይፍቀዱ Share ያርጉት — ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተናገሩ"አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ዘመዶቹ በቀብር ሥነስርአቱ ላይ ሲጨናነቁ አንድ እጅግ ያማረ ቆንጆ ሰው በጭንቅላቱ በኩል ይቆማል።ጀናዛውም እንደተከፈነ ያ ሰው በከፈኑ እና በሞተው ሰው ደረት መሀል ይሆናል።ከቀብር ሥነስርአቱም በህዋላ ቀባሪ ቤተሰቦቹ ወደ ቤት ሲመለሱ ሁለት ሙንከር እና ነኪር የተባሉ ምላኢኮች ወደ ቀብሩ በመምጣት ጀናዛውንና ያንን ቆንጆ ሰው በመለያየት ያንን የሞተውን ሰው በእምነቱ ጉዳይ ብቻውን በጥያቄ ሊያፋጡት ይሞክራሉ ። ሆኖም ያ ቆንጆ ሰው ይናገራል "ይህ ሰው አጋሬም ጋደኛዬም ነው ብቻውንም ልተወው አልችልም። እናንተ እንድትጠይቁት ከተመደባቹ ስራችሁን መሥራት ትችላላቹ እኔ ግን ወደ ጀነት መግባቱን ሳላረጋግጥ ትቼው እልሄድም"። ከዝያም ወደ ሞተው አጋሩ በመዞር እንዲህ ይለዋል "እኔ አንዳንዴ ድምፅህን ከፍ አርገህ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቀስ ብለህ ስታነበኝ የነበርኩት ቁርአን ነኝ ምንም አትጨነቅ፤ ከሙንከርና ነኪር ጥያቄና መልስ በኃላ ምንም ጭንቀት አይኖርብህም"፤ጥያቄና መልሱም ካለቀ በኃላ ያ ቆንጆ ሰው አል ማሉል አላ በተባሉ የጀነት መላኢኮች የተዘጋጀ በመልካም ሽታ የሚያውድ እና ከ ሀር በተሰራ ልብስ የተዘጋጀ አልጋ ያዘጋጅለታል። 2. ረሰል(ሶ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት በቂያማ ቀን በአላህ ሱ.ወ ፊት ስንቆም ከቁርአን የበለጠ ለኛ ሚከራከርልን አይኖርም ከነብይያትም ከ መላኢኮችም በበለጠ። 3. እባክዎን ይህን መልእክት የቻሉትን ያህል ያስተላልፉ። ረሱል (ሶ.ዐ.ወ) እውቀትን ከኔ ለሌላው አስተላልፉ አንድም አረፍተ ነገር ብትሆን እንኩዋን ብለዋል። 4. ይህ መልእክት በ አላህ ፍቃድ በቀጣይ 7 ቀናት ቢያንስ 5 ሚልዬን ሰዎች እንዲዳረስ ዱአ እያደረግን ነው። እባክዎን ይህን መልእክት ለ ቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎትና ላሚያውቅዋቸው ሁሉ በማስተላለፍ ከተትረፈረፈው የአላህ ምንዳ ተጠቃሚ ይሁኑ። *እርስዎ ቁርአንን ሲይዙ ሰይጣን ራሱን ያመዋል። *ሲከፍቱት ይወድቃል። *እያነበቡት ሲያይ ራሱን ይስታል። *ይህንን መልእክት ሊያስተላልፉ ሲያስቡ ላማዳከምና ለማስነፍ ይሞክራል። እኔ አሸነፍኩት ምክንያቱም ለእርስዎ መላክ ችያለሁ። 🌺🌺🌺😊🌺🌺🌺 5. እባክዎን ሸይጣንን ያሸንፉና ይህንን መልዕክት ቢያንስ ለ5 ሰው በ 5 ደቄቃ ውስጥ ያስተላልፉ።
Show all...
أخوة الإسلامية ኢስላማዊ ወንድማማችነት "إنما المؤمنون إخوة فأصلحو بين أخويكم واتقوا الله لعلكم ترحمون" "ምዕመናኖች ወንድማማቾች ናቸው፤በሁለት ወንድሞቻችሁ መካከል አስታርቁ፤ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ።" 🔻ኢስላማዊ ወንድማማችነት አላሁ ሱብሀነሁ ወተአላ ያፀደቀልንና ወንድማማች ያረገንም ከፍ ያለው ጌታ በቅዱስ ቁርዓን ውስጥ ነው። 🔻አላሁ ተአላ በሡረቱል ሁጁራት ላይ ወንድማማች መሆናችንን ከገለፀልን ቡኃላ በሁለት ወንድማማቾች መሀከል እንድናስታርቅ ያዝናል።ይህ በወንድማማችነት መሀከል አለመግባባት ሊከሰት እንደሚችልና ምን ማረግ እንዳለብንም ይጠቁመናል። እኛ ግን ምን አይነት ውሳኔን ነው ምንወስነው ወንድማችንን ማነወር ወይስ ማንቋሸሽ የቱም ቢሆን የቱ ትክክል አይደለም ከቁርዐን አንቀፁ እንደምይረዳውና ልናስተካክል ይገባል። 🔻በጣም የሚገርመው በዚሁ ሱራ ላይ በሱረቱል ሁጁራት ቁጥር 9 ላይ ከምዕመናን የሆኑ ስለ ሁለት ጭፍሮች መገዳደል ካወራ ቡኃላ ነው ቁጥር 10 ላይ"ሙዕሚኖች ወንድማማቾች ናቸው"ያለው ይህ ድንቅ ነገር ነው።እስከ መገዳደል አንኳን ቢደረስ ወንድማማች እንደሆንን ያሳየናል። በኛ መካከል ያለው አለመስማማት እስከ መገዳደል ያደርስ ይሆን?የብዙዎቻችን በፍፁም እንደዛ አይሆንም።ታዲያ ለምን እርስ በርስ እንቧጨቃለን፣እርስ በርስ ለምን እንሰዳደባለን፣እርስ በርስ ለምን ስም እንጠፋፋለን፣ ለምን አንግባባም፣ለምን አንዋደድም ሁላችንም ለዚህ ጥሩ መልስ መመለስ ይኖርብናል!!! 🌟 ሀቢቡና ረሡል ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው እንዲህ ይላሉ፦ "المسلم أخ المسلم" "አንድ ሙስሊም ለሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ነው" 🔻እንግዲህ ሁለቱ መመሪያችን የሆኑት ቃሎች ወንድማማች መሆናችንን አፅድቀዋልና ከፍተኛ ቦታ መስጠት ይኖርብናል እንዲሁም ልንዋደድ እና ልንስማማ ይገባል።አለመስማማቶች ሲከሰቱም ወደ ቁርዐንና ወደ ሀዲስ በመመለስ ችግሮቻችንን መፍታት ይኖርብናል። 🔻እንዲሁም ከቻልን እርስ በርስ ልንረዳዳ እና ልንጠቃቀም ይገባል።ተወዳጁ ነብይ ሙሀመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና፦ "من استطاع أن ينفع أخاه فاليفعل" "ወንድሙን መጥቀም የቻለ አካል ያርገው" 📌ኢስላማዊ ወንድማማችነት ትልቅ ርዕስ ነው በኔ ተነካክቶ ሚታለፍ አይደለምና እዚህ ጋ ላብቃ ወላሁ አእለም!!! ✍ኡሙ ሰባህ... የተለያዩ ኢስላማዊ ፅሁፎች፣ ድምፆች እና ጠቃሚ መልእክቶች የሚለቀቁበት https://t.me/bayushpage ለአስተያየት @abumestura @tofiksani @bayushpagebot
Show all...
ባዩሽ መስጂድ

የተለያዩ ኢስላማዊ ፅሁፎች፣ ድምፆች እና ጠቃሚ መልእክቶች የሚለቀቁበት

https://t.me/bayushpage

ለአስተያየት @abumestura @tofiksani @bayushpagebot

🏷️አላህ ከወደደህ... 🔅አላህ አንድ ባሪያውን ከወደደው፤ የሚሰራውን መልካም ስራ ( ትንሽ እንኳ ብትሆን) ይቀበለዋል፣በጣም የበዛ ወንጀል እንኳ ቢኖርበት ይቅር ይለዋል። 🔅አላህ ግን ይብዛም ይነስ አንድን ሰው የሚወደው፤ 2 ዋና ዋና መስፈርቶች ሲገኙ ብቻ ነው። እነሱም፤ በስራው ላይ ኢኽላስ ሲኖረውና በሁሉም ነገር ነቢዩን ‌‎ﷺ የሚከተል ሲሆን ነው። 🔅የአላህን የተሟላ ውዴታ እናገኝ ዘንድ እኛ እሱን መውደድ፣ መልካም ስምና ባህሪያቱን ማወቅና ማመን፣ ተቆጥረው የማያልቁ የዋለልንን ውለታዎችን ዘወትር ማስታወስ፣ ማመስገንና ለመልካም ነገር መጠቀም፣ የከለከለንን በሙሉ መከልከልና ያዘዘንን መታዘዝ እንዲሁም በሁሉም ነገር የነቢዩን ‌‎ﷺ ሱንናህ መከተል፣ ይጠበቅብናል። 🔅አላህ ሆይ፥ አንተን፣ መልእክተኛህን እና መልካም ስራን የምትወድ ልብ ስጠን! ውዴታህን እኛ ዘንድ በጥም ሰዓት ካገኘነው ቀዝቃዛ ውኃ የሚበልጥና ከፍጥረታትህ በሙሉ የሚቀድም አድርገው! "ኣሚን" ✍🏻 ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ 6/2/1442ዓ.ሂ 👇👇👇👇 https://t.me/yetwhiedfana
Show all...
🌹 የተውሂድ ፋና 🌹

🌹 🌹 🌹 أثر التوحيد

ከፊትና ለመጠበቅ፦ መቼም ሰው ነንና ሁላችንም በራሳችን ላይ ፊትናን እንፈራለን።እኔ አልፈራም የሚል ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም። ከፊትና ለመጠበቅ የመጀመሪያው መንገድ ፊትናን በራስ ላይ መፍራት ነው።ለማንኛውም ለዛሬ እንዴት ከፊትና መጠበቅ እንደምንችል ኡለሞች ያስቀመጡልንን መንገዶች ይዤ ቀርቤያለው።ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና አባባሉም በደንብ አንብቡት... ከፊትና ለመጠበቅ፦ 1/ስሜትን መከተል መተው➡ ስሜታችንን ከሸሪዓ ጋ ሚካሄድ ማረግ 2/ከችኮላ መራቅ/መተው 3/ሸሪዐዊ ዕውቀትን መማር➡ ቁርዐንና ሀዲስን በሰለፎች አረዳድ 4/ፊትና(መኻለፍ/በአስተሳሰብ መለያየት)ሲከሰት በዕድሜም በዕውቀትም ተለቅ ወዳሉ ዑለማዎች መሄድ 5/ሱናን አጥብቆ መያዝ 6/ከፊትና ቦታዎች እና በአጠቃላይ ወደ ፊትና ከሚያዳርሱን ነገራቶች መጠንቀቅና መራቅ➡ነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም"በፊትና ቦታ ላይ ከነቃው ሰውዬ የተኛው የተሻለ ነው"ብለውናል ሚገርመው የተኛውም ከፊትናው ትንሽ ይቋደሳል ቢሆንም ግን ይሻላል። 7/ፊትና ሳይከሰትብን በፊት መከላከሉ ከወደቁበት ቡኃላ ከመውጣት የተሻለ ነውና ቀድሞ መከላከል➡ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ"ፊትና በሰዎች መሀል ከተቀጣጠለች ዑለማዎች እሷን ለማጥፋት ይከብዳቸዋል"ብለዋል 8/በፈትዋ ጊዜ ከሸህዋ መራቅ➡ፈትዋ ስንቀበል ለስሜታችን ቅርብ የሆነውን ብቻ አይደለም መቀበል ያለብን 9/ፈትዋን ስትይዝ ከተሻለው ዓሊም ያዝ ደስ ያለህን ሳይሆን ምክንያቱም ሰዎች እኩል አይደሉም በዕውቀትም ይለያያሉና። 🔻እንግዲህ በጥቂቱ እነዚህን ይመስላሉ ተግባር ላይ ካዋልነው ተጠቃሚ እንሆናለን ብዬ አስባለሁ።አላህ እኔንም እናንተንም ከፊትና ይጠብቀን! ወላሁ አእለም!!! ✍ኡሙ ሰባህ... የተለያዩ ኢስላማዊ ፅሁፎች፣ ድምፆች እና ጠቃሚ መልእክቶች የሚለቀቁበት https://t.me/bayushpage ለአስተያየት @abumestura @tofiksani @bayushpagebot
Show all...
ባዩሽ መስጂድ

የተለያዩ ኢስላማዊ ፅሁፎች፣ ድምፆች እና ጠቃሚ መልእክቶች የሚለቀቁበት

https://t.me/bayushpage

ለአስተያየት @abumestura @tofiksani @bayushpagebot

አላህ ይወፍቀን ጠለሃ ኢብኑ ዑበይደላህ ረድየላሁዐንሁ እንዳስተላለፉት፦ 《ሁለት ሰዎች ወደ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይመጡና በተመሳሳይ ሰዓት ኢስላምን ይቀበላሉ። አንደኛው ዒባዳ ላይ በጣም የተበራታ ሲሆን ደግሞ ሌላኛው ደግሞ ጅሃድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ፤ እናም አንድ ቀን ጅሀድ ላይ ይገደልና ሸሂድ ይሆናል ፤ አንደኛው እርሱ ሌላኛው ከሞተ ከአንድ ዓመት በኋላ ይሞታል። ጠለሃ እንዲህ ይላል "አንድ ቀን በህልሜ ከነዚህ ሁለት ሰዎች ጋር በጀነት በር ላይ ቆሜ ነበር ፤ አንድ ነገር ከበሩ ይወጠና ከመጀመሪያው ሟች ቀጥሎ የሞተውን ሰው ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ድጋሚ ይመጣና መጀመሪያ የሞተውን ግባ ይለዋል ፤ ከዚያም ወደኔ ዞር ብሎ ‘ አንተ ሂድ ተመለስ ያንተ ጊዜ ገና ነው ’ ይለኛል"። ጠለሃ ከዕንቅልፉ እንደተነሳ ስላየው ህልም ለሰዎች ይነግራቸውና ሰዎቹም ይገረማሉ ፤ እናም ይህ ወሬ መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋር ይደርሳል ፤ እሳቸውም ሰዎቹን "ምንድ ነው ያሰደነቃቹ?" ብለው ይጠይቃሉ። ሰዎቹም አንደኛው ጅሀድን አብዝቶ ይሳተፍ ነበር ሸሂድ ሆኗልም ነገር ግን ቅድሚያ ጀነትን እንዲገባ የተደረገው ቀጥሎ የሞተው ነው።"አሏቸው የአላህ መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፤ " ቀድሞ ጀነትን የገባው ሰው ከመጀመሪያው አንድን ዓመት በሕይወት አልቆየምን?" ሰዎቹም አዎን ሲሉ መለሰ የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ አለህሂ ወሰለም ፡ " ረመዳንን አላገኘምን? አልፆመምን? ፤ ይሄን ይሄን ያክል ሰላት አልሰገደምን ?" ሰዎቹም አዎን አሉ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦" ታዲያ በርሱና በዛኛው ሰውዬ መካከል የሰማይና የምድር ያክል በላይ ልዩነት አለ" አሏቸው።》 ኢብን ማጃህ (2/344,346)፤ ሸኽ አልባኒ በሲልሲላ አ‘ሰሂሃ ሰሂህ ብለውታል 👇👇👇 https://t.me/yetwhiedfana
Show all...
🌹 የተውሂድ ፋና 🌹

🌹 🌹 🌹 أثر التوحيد

በአላህ ታገዝ፡፡ ☞እወቅ! ህዝቦች በሙሉ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ እንጂ አይጠቅሙህም፡፡ ☞በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው እንጂ አይጎዱህም፡፡ ☞ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦቹም ደርቀዋል፡፡ ☞እወቅ! የሳተህ ነገር የሚያገኝህአልነበረም፡፡ ያገኘህም ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ ☞እወቅ!!!ድል ከትእግስት ጋር ነው፡፡ ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው፡፡ከከባድም ነገር ጋር ገር ነገር አለ፡፡” 👇👇👇👇 https://t.me/yetwhiedfana
Show all...
🌹 የተውሂድ ፋና 🌹

🌹 🌹 🌹 أثر التوحيد

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.