cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አገልጋይ ጆን official page🇪🇹🇪🇷

በዚህ ቻናል በየእለቱ የቃል ስንቅ አዳድስ እና ቆየት ያሉ መዝሙሮች እናም የተለያዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ። 😒አይኔን አንስቼ ከሰው ላይ፣😔 ሀዘኔን ረሳው ኢየሱስን 😳ሳይ😁 ለአስተያየታችሁ http://t.me/hiyaw_kal

Show more
Ethiopia4 559AmharicThe category is not specified
Advertising posts
1 643
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአዕምሮ ቅኝት (Mind Set) አንዳንድ ሰዎች የማይሳካላቸው እንዲሳካላቸው ስለሚሰሩ ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ራሳቸው ስኬት ስለሆኑ ሁልግዜ ይሳካላቸዋል፡፡ ይህ የህይወት መርህ ነው፡፡ ስኬት፣ ከስኬት አስተሳሰብ ነው የሚጀምረው፡፡ ለዚህ ነው እግዚያብሔር አብርሃምን የብዙዎች አባት ነህ ብሎ ያሳመነው፡፡ ሲያምን ነገሩ ሆነ፡፡ አብርሃም የብዙዎች አባት ነኝ ብሎ ሲያምን፣ ምንም ልጅ አልነበረውም፡፡ ስለዚህ አብርሃም በሁለት ሀሳብ መሀል ተወጠረ (በግዜው በሚያየው ሁኔታና እግዚያብሔር ነህ ባለው)፡፡ አባታችን አብርሃም በአይኑ የሚያየውን ትቶ እግዚያብሔር ያለውን አመነ፡፡ ለዚህ ነው አብርሃምም እግዚያብሔርን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት የተባለው፡፡ “አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”   — ዘፍጥረት 15፥6 “መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።”   — ሮሜ 4፥3 መጀመርያ ራሳችንን ማሳመን ነው ቁልፉ፡፡ በመጀመርያ ስእሉ ላይ ስሩ፡፡ ስኬታማ እንድትሆኑ አስተሳሰባችሁ (Your mind set) የስኬት መሆን አለበት፡፡ ማመንና በጭንቅላት መስማማት ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ እምነት እግዚያብሔር እንደሚያደርገው ማመን ሳይሆን፣ እግዚያብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ እንዳደረገው፣ ያደረገውም ለእኛ እንደሆነ መቀበል ነው፡፡ እግዚያብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ሁሉን ነገር (ፅድቅ፣ ፈውስ፣ ብልፅግና፣ ስኬት ወ.ዘ.ተ.) የዛሬ 2000 ዓመት ሰርቶ ጨርሷል፡፡ ዛሬ ተነስቶ የሚያደርገው አዲስ ነገር የለም፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው እንደ አባታችን አብርሃም በስጋዊ ዓይናችን ነገሩን ባናየውም፣ በእምነት ተቀብለን የራሳችን ማድረግ ነው፡፡  እግዚያብሔር የሆነን ሰው መቀየር ከፈለገ አስተሳሰቡን ነው የሚቀይረው፡፡ ድህነት ከአስተሳሰብ ነው የሚጀምረው፡፡ ባለጠግነትም እንዲሁ ከአስተሳሰብ ነው የሚጀምረው፡፡ ሀብታም ሰው ሀብቱን የሚስበው በአስተሳሰቡ ሲሆን፣ ድሀም ሰው ችግርን የሚስበው ስለ ችግር እያሰበ ወይንም ትኩረቱን ችግር ላይ በማድረግ ነው፡፡ ኢየሱስ እጥረት ወይንም ችግር አስቦ አያውቅም፡፡ ይህ የአዕምሮ ቅኝት ነው፡፡ አዕምሮአችን የተቃኘበትን ነገር ወደ ህይወታችን እንስባለን፡፡ የተቀበልነው ሁኔታ ኑሮአችን ይሆናል፡፡   በመጀመርያ ደረጃ ባለጠጋ ናችሁ! መፀሀፍ ቅዱስ ባለጠጋ ተደርጋችኋል ይላል፡፡ ይሄንን እውነታ ተቀበሉት፡፡ ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛችሁ ስትቀበሉ መፅደቃችሁን እንደተቀበላችሁት፣ እግዚያብሔር ናችሁ ያላችሁን ይሄንንም እውነት ተቀበሉት፡፡ አሁን ያላችሁበት እውነታ እንደዛ ባይሆንም እንኳ፣ ባለጠጋ ወደመሆን የምትመጡት ቃሉን ስትቀበሉት ነው፡፡ “ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።”   — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥5-6 “በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።”   — 2ኛ ቆሮ 9፥11 “የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።”   — 2ኛ ቆሮ 8፥9 የሆናችሁትን ነገር ለመሆን ስትሞክሩ አይሳካላችሁም፣ ልክ ቻርሊ ቻፕሊን ራሱን አስመስሎ ለመተወን ተወዳድሮ እንደተሸነፈው ማለት ነው፡፡ ይሄ ማለት አማኝ ሆነን አማኝ ለመሆን ስንሞክር፣ ስኬታማ ሆነን ስኬታማ ለመሆን ስንሞክር፣ ወይንም ባለጠጋ ሆነን ባለጠጋ ለመሆን ስንሞክር አይሳካልንም፡፡ ባለጠጋ ሆናችሁ ስትሰሩና ባለጠጋ ለመሆን ስትሰሩ ይለያያል፡፡ ባለጠጋ ሆናችሁ ስትሰሩ ለእርካታ ወይንም ሰዎችን ለማገልገል/ለመጥቀም ሲሆን፣ ባለጠጋ ለመሆን ስትሰሩ ለትርፍ ነው የምትሰሩት፡፡ በአጠቃላይ የአዕምሮ ቅኝታችሁ ሊሆን የሚገባው፣ መፀሀፍ ቅዱስ ስለእናንተ እንዳለው ነው፡፡ ይህም ምንም ነገር ብሰራ እበለፅጋለሁ፤ እኔ ስኬት ነኝ፤ እኔ አካባቢ ያለ ነገር ሁሉ ያድጋል፤ ይለመልማል፤ ተባርኬያለሁ፤ የእኔ ህይወት ወደ ፊት እና ወደ ላይ ነው፤ እግዚያብሔር ደረቁን ስፍራ ያለመልማል፤ እኔ አንድ ስራመድ እግዚያብሔር 1000 ያደርገዋል ………
Show all...
"ኦርቶዶክስ ማለት ንፁህ ማለት ከሆነ ስህተቶችን ከማረም ይልቅ አትናገሩኝ ማለት አያስኬድም።' ፦ መሪጌታ ሙሴ መንበሩ! ገድለ ተክለ ሃይማኖት የተባለው መፅሃፍ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል የሚናገር ሲሆን በደብረ ሊባኖስ ገዳም አሳታሚነት ለንባብ የበቃ የገድል መፅሃፍ ነው። ይህ የገድል መፅሃፍ እንዲህ ይላል፦ 1ኛ. አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቁጭ ብለው ሳሉ ስጋ የለበሰ ሰይጣን ከባህር ወጣና የተክልዬ ደቀ መዝሙር ውስጥ ገባ፤ 💠 መሪጌታ ሙሴ፦ ሰይጣን መንፈስ ነው፤ መንፈስ ደግሞ ስጋ ለባሽ አይደለም፤ ስጋ ለባሽ ከሆነ ደግሞ ስጋ እንደለበሰ ሌላ ስጋ ለባሽ ውስጥ ሊገባ አይችልም። ይህ የመጀመሪያው ኑፋቄ ነው። 2ኛ. አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ሰይጣኑን አማተቡበትና ሸሼ፤ ተከትለውም(🏃🏃🏃) ያዙት (🙊)፤ ሰይጣኑ እፁ ስለወደቀበት ሃይሉ ደከመ፤😂 💠መሪጌታ ሙሴ፦ ሰይጣን ሰይጣንነቱ በእፅ (በእንጨት ወይም በእፀ መሰውር) አይደለም፤ ይህ ገድል የተፃፈው በደብተራ እንደሆነ ያሳያል፤ ይሄ ሁለተኛው ኑፋቄ ነው። 3ኛ. ተክልዬ ሰይጣኑን ከያዙት በኋላ ገረዙት (✂)፤ 🙊 💠መሪጌታ ሙሴ፦ በመጀመሪያ ሰይጣን መንፈስ ነው፤ መንፈስ ደግሞ ወንድም ሴትም መሆን አይችልም፤ መፅሃፉ ግን ተክልዬ ሰይጣንን ወደ ወንድ ፆታ (👨) ቀይረው እንደገረዙት ይገልፃል። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው። 4ኛ. ሰይጣን ከተገረዘ በኋላ ምንኩስናን ተቀብሎ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ በክርስቶስ የተመረጠ ክርስቲያን ሆነ።😂 ማን? ሰይጣን!😂 የሙት አመት መታሰቢያ/ ዝክርስ የለው ይሆን?🙄 💠መሪጌታ ሙሴ፦ ሰይጣን ሰው ሆኖ ወደ ክርስቲያንነት ሊለወጥ አይችልም፤ ማንም ሰው ሰይጣንን የመለወጥ አገልግሎትም አልተሰጠውም። 🙏 መልዕክት! ፩.) ኦርቶዶክስ ማለት ንፁህ ማለት ነው፣ እውነት ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ኑፋቄዎችን ከአስተምህሮቶቿ ማስወገድ አለባት። እኛ የቅዱሳንን ገድል እናከብራለን፤ ነገር ግን በቅዱሳን ገድል ስም የሚፃፉ ኑፋቄዎችን በመፅሃፍ ቅዱስ እየመዘንን ልንለይ ይገባናል። ፪.) ትውልዱን በማለባበስና በመሸፋፈን ልናሳምነው አንችልም፤ እኛ ብንደብቀው ራሱ ገዝቶ ማንበብ የሚችል ትውልድ ነው ያለው (💪)። ያ ትውልድ ደግሞ ከውስጥም ይጠይቃል፤ ከውጭ ያለውም ይነቅፋል። ይህ ሲሆን ስህተት የሆነውን ስህተትኑቱን አምኖ ከማስወገድ ፋንታ "አንገቴን እሰጣለሁ፡ አንገት እቆርጣለሁ፤ ጦርነት እከፍታለሁ" ማለትን ምን አመጣው? ስህተታችንን ታቅፈን ጦርነት ብንከፍት ምን እናተርፋለን? ፫.) ኦርቶዶክስ ሆኖ ጦርነት የሚጎስም ካለ እንደ አርዮስ መወገዝ ያለበት ነው፤ ኑፋቄያችንን እስካላረምን ድረስ መነቀፋችን ይቀጥላል፤ ገና ከዚህ በላይ የሚያስነቅፈን መዓት ኑፋቄ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አለ። አባቶች በመፅሃፍ ቅዱስ መሰረት ሊለዩት ይገባቸዋል።🙏
Show all...
እኛም "የቅድስት አርሴማ ታምራቷ፣ ጸሎቷና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን!" እንበልን? እምነትን በተመለከተ በተሳሳተ አካሄዳቸው ቅር እየተሰኘሁም እንደ ሰው ከሚያሳዝኑኝ ግለሰቦች መካከል አንዱ ዶ/ር ወዳጄነህ ማሓረነ ናቸው። ዶክተሩ ይሁነኝ ብለው በመረጡት የሕይወት መንገድ የመጓዝ ፣ የሚስማማቸውን እምነት የመከተልና የመስበክ መብት ቢኖራቸውም ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ቀናዒነት ለመግለጽ ሲሉ ወንጌላውያኑን የሚያሳጡበት ሸፍጥ ግን ነፍሴ ትጸየፈዋለች። የዛሬዋ ተረኛ ማሳቀያ ደግሞ ቅድስት አርሴማ ናት። ስለ ቅድስት አርሴማ የሚተርኩ ድርሳናት ቅድስቲቱ ፣ ሂርፕሲም (አርሜኒያዊት)፣ አርብሲማ ወይም አርሴማ ተብላ እንደምትጠራ፣ ውበቷና ግርማ ሞገሷ እጹብ ድንቅ ስመሆኑ፣ ሮማዊ መሰረት ያላት ሰማዕት እንደነበረች ያትታሉ። እርሷና የእምነት ባልንጀሮቿ በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት የሚጋፋ ተግዳሮት በመጣባቸው ጊዜም ስለ ሃይማኖታቸው የሕይወት ዋጋ በመክፈል የሰማዕትነትን አክሊል እንደተቀዳጁ ያወሳሉ። ዶ/ር ወዳጄነህ መሓረነ ከአንድ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ሰሞነኛ ቃለ ምልልስ ስለ እርሷ የሚተርኩትም ይኼንኑ ነው። ልዪነቱ እርሳቸው ስለ ቅድስት አርሴማ ውበት፣ ስለ ግርማዋ አስፈሪነት፣ ስለ ንጽህናዋ፣ ስለ እምነቷ ጽናት ሲተርኩ በእርሷ ዘመን ኖረው የሚያውቋት መምሰሉ ብቻ ነው። እኚህ ሰው እውነቱንም ተረቱንም አጣፍጦ መናገርን ተክነውበታልና የሀገሬው ንጉሥ በአርሴማ ውበት ተማርኮ ለጋብቻ በጠየቃት ጊዜ "እኔ የኢየሱስ ሙሽራ ነኝ ላንተ አልገባም" ብላ አሻፈረኝ ስለማለቷ ሲያወሩ አፍ ያስከፍታሉ። ይኼ ሁሉ ባልከፋ ነበር። የዶ/ር ወዳጄነህ ነጥብ ግን እንዲህ ዓይነቷ የክርስቶስ ባሪያ ስለምን ተጠላች የሚል ጥያቄ ማጫር ነው። አርሴማን ይጠሏታል ተብለው የሚጠረጠሩት ደግሞ የፈረደባቸው ወንጌላውያን አማኞች ናቸው። "ኢየሱስ ክርስቶስን ወድዶ አርሴማን መጥላት አይቻልም!" ማለታቸውም ማስጠንቀቂያ የሚያነጣጥረውም ወደ እነርሱ (ወደ እኔ) ነው። እኔም ብሆን ከዚህ ቀደም በዶ/ር ወዳጄነህ አገላለጽ "የእርሱ ሙሽራው ነኝ" ያለችው ቅድስት አርሴማ ኖራ በማትጠየቅበት ሁኔታ የኢየሱስ ዕለተ ቀን ላይ ኩዴታ ( መፈንቅለ ዕለተ ቀን)😀 እንድታካሂድ ስለመደረጓ ጽፊያለሁ። የአርሴማን እንደ አምላክ መመለክ ከመቃወም ውጩም እርሷን የሚጠላት ወንጌላዊ አማኝ ይኖራል ብዬም አልገምትም። ታሪኳን ያነበቡ ወንጌላውያን ታሪኩ አሳማኝ ሆኖ ካገኙት አርዓያነቷን በምሳሌነት ከማንሳትና እንደ እህታችን ከመቁጠር በስቲያ ለእርሷ ያለንን ፍቅር ለመግለጽ "የቅድስት አርሴማ ታምር፣ ጸሎቷና በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን!" ብለን ወደ እርሷ የመጸለይ ግዴታ የለብንም። ሌሎች ሲያደርጉት መቃወምም አርሴማን መጥላት አይደለም። ይልቁኑስ ዶክተር ወዳጄነህ የኦርቶዶክስ ወዳጅ ነኝ ካሉ በወር አንድ ቀን ኢየሱስ በስሙ የሚጠራበትን ቀን ስለምን በአርሴማ እንደተነጠቀ መጠየቅ አለባቸው።😁 ምክንያቱም እስከቅርብ ዓመታት ድረስ በስድስት ኢየሱስ ነበራ!😀አሁን ላይ የትኛውም ኦርቶዶክሳዊ በአንድ ልደታ፣ በሁለት ባታ፣ ...እያለ ቆጥሮ ስድስት ላይ ሲደርስ "አርሴማ" እንጂ "ኢየሱስ" እንደማይልም የተረጋገጠ ነው። እናም "የኢየሱስ ሙሽራ ነኝ" ብላ ስለ እርሱ መስዋዕትነት እንደተቀበለች የሚተርኩላት አርሴማ በነቁ ኦርቶዶክሳውያን ጭምር የኢየሱስ ተቀናቃኝ ተደርጋ እየተሳለች መሆኗንም መናገር አለባቸው።
Show all...
1ኛ ሳሙኤል 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁶ እርስዋም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታ ሆይ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በአንተ ዘንድ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ። ²⁷ ስለዚህ ሕፃን ጸለይሁ፤ ²⁸ እግዚአብሔርም የለመንሁትን ልመናዬን ሰጥቶኛል፤ እኔም ደግሞ ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል።
Show all...
#ከብረው_ይቆዩኝ 📖 ዘጸ 33: 12-23 - ሰው የሚሞላው በእግዚአብሔር ክብር እንጂ በሀብትና በንብረት አይደለም። - የሰው ልጆች እርካታ እግዚአብሔር ነው። - የእግዚአብሔርን ህዝብ ልዩ ያደረገው የእግዚአብሔር አብሮነት ነው። - አጓጉል እርካታ ከእግዚአብሔር አይደለም። - እግዚአብሔር  ሙሴን ህዝቡን ይዞ እንዲወጣ አዘዘው፤ ሙሴም በእግዚአብሔር  ፊት ምገስ አግኝቶ ነበርና ሙሴ ህዝቡን  ይዘህ ውጣ ባለው ጊዜ  አንተ አብረህን ካልወጣህ ከዚህ አታውጣን አለው። - እግዚአብሔርም በፊቴ  ሞገስ ስላገኘህ ያልከውን  አደርጋለሁ ሲለው የሙሴ ጥያቄ፤ እግዚአብሔር  የጠየቀውን እንደሚያደርግለት ቃል ቢገባለትም የልቡ መሻት ግን የእግዚአብሔር  ክብር ስለነበር ክብርህን አሳየኝ  አለው። ስለዚህ ፦ 1:- እኛም ሁልጊዜ  እግዚአብሔር  የቱንም  ያህል የምንፈልገውን ነገር በህይወታችን ቢያደርግልን የእኛ የሁልጊዜም  ፍላጎታችን ክብሩን ሁሌም  ማየት ይሁን። ሁሌም በህልውናው በመገኘቱ  ከብረን መቆየት ይሁንልን። 2፡- ቁ. 19-23 ያለዉ  ሀሳብ እኛ በክርስቶስ እግዚአብሔርን ማየት ሆኖልናል፤ ያለገደብ እግዚአብሔርን ማወቅ ሆኖልናል፤ ስለዚህ በዚህ  አመት በእግዚአብሔር  መገኘት  በክብሩ ውስጥ እለት  እለት  መቆየት  እንዲሆንልን የእግዚአብሔርን  ክብር  በመጠማት ከብረን እንቆይ። @yekal_sink
Show all...
ተባረኩበት
Show all...
ዘጸአት 15 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹³ በቸርነትህ የተቤዠሃቸውን ሕዝብህን መራህ፤ በኃይልህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ አገባሃቸው። ¹⁴ አሕዛብ ሰሙ፥ ተንቀጠቀጡም፤ በፍልስጥኤም የሚኖሩትን ምጥ ያዛቸው። ¹⁵ የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብን ኃያላን መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ። ¹⁶ አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሃትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በክንድህ ብርታት እንደ ድንጋይ ዝም አሉ። @yekal_sink
Show all...