cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቅኔ ለእግዚአብሔር

አምልኮእና ቅኔ የሚገባው የሁሉም ነገር አስጀማሪ ለሆነው ለእራሱ ግን አስጀማሪ ለሌለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው።በዚህ ቻናል የተለያዩ መዝሙሮች በተለያዩ ቋንቋ ያገኛሉ።you are blessed

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
155
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ትህትና 👉ትህትና ወንበር እያለ አፈር ላይ መቀመጥ አይደለም።😓 👉ትህትና የእግዚአብሔር ቃል ነህ የምልህን ነኝ አይደለህም የምልህን ደሞ አይደለሁም ማለት ነው 👉ትህትና የእግዚአብሔር ቃል ተሰጥቶሀል የሚልህን ተሰጥቶኛል አልተሰጠህም የምልህን አልተሰጠኝም ማለት ነው። 👉ትህትና ለሚቀድምህ ለምበልጥልህ ካንተ ለምልቅ ቅድምያ ቦታ ክብር መስጠት አይደለም ይህማ ሰውዬው ያለበት ቦታ ስለሚያስገድድህ ታረጋለህ። 👉ትህትና ግን ለምትበልጠው ለምትቀድመው ሰው እራስህን ማስገዛት ነው። @truegospell @truegospell #ይቀላቀሉን 👆👆
Show all...
Elohim 👉የተረገዘ ሁሉ 👉አይወለድም የተፎከረ 👉ሁሉ አይፈጸምም 👉ጌታ ካለው ግን አንዳች 👉❤️አይቀርም ❤️👈 @Truegospell @Truegospell
Show all...
Elohim ከራስህ አትሽሽ! (“እይታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) ራሳችንን በማንቀበልበት ጊዜ ሳናስበው ራሳችንን ጥለን ወደ ሌላኛውና የእኛ ወዳልሆነው ማንነት እንድንሄድ ይገፋፋናል፡፡ በዚህ አይነት ተጽእኖ ውስጥ እንድንወድቅ የሚያደርጉን ሁኔታዎች በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡ እነዚህ “ጥሪዎች” መነሻቸው በውስጣችን የሚገኘው ተቀባይነት የማግኘትና ራስን የመቀበል ስነ-ልቦናዊ ፍላጎት ነው፡፡ በውስጣችን ያለውን የመወደድና ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ለማሟላት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ ይቃጣናል፡፡ ሳናስበውም ራሳችንን ማለቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ገብቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ እንዳይሆን በውስጣችን ያሉትን ስነ-ልቦናዊ ፍላጎቶች በማወቅ ትክክለኛ የመፍትሄ መንገድ መፈለግ አለብን እንጂ ራስን ባለመቀበል ስቃይ ውስጥ መማቀቅ የለብንም፡፡ የሚከተሉትን ከራሳችን እንድንሸሽ የሚያደርጉንን ስውር ስነ-ልቦናዊ ምክንያቶች እንመልከት፡፡ 1. ተቀባይነት ፍለጋ አንዳንድ ሰዎች ቤተሰባቸውን ለማስደሰት፣ ልባቸውን የሳበው ፍቅረኛ እንዲቀበላቸው፣ እንዲሁም በአንድ ቡድን ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት ራሳቸውን ለመለወጥ ሲጣጣሩ ይታያሉ፡፡ የዚህ አይነቱ ራስን የመለወጥ ሙከራ ግን መጨረሻው ድካምና “ራስን ማጣት” ነው፡፡ ብቸኛው መፍትሄ ራስን ተቀብሎና ሆኖ መኖር ነው፡፡ 2. ዘመናዊነትን ፍለጋ የዘመኑን ፋሽን፣ የዘመኑን ቁመናም ሆነ የዘመኑን የንግግር ዘይቤ ሁሉ ተከታትለንና አውቀንበት መኖር ብንችል መልካም ነበር፡፡ ሁኔታው ግን ያን ያህል ቀላል አይደለም፡፡ “ዘመናዊ ሰው መስዬ ካልታየሁ ተቀባይነት አላገኝም” ከሚለው ማለቂያ የሌለው የውስጥ ጥማት ከሚመነጭ ትግል መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡ 3. ስኬታማ መስሎ የመታየት ጥማት አንዳንድ ሰዎች በተለያዩ የኑሮ ዘርፎች ስኬታማ መስሎ ለመታየት የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ስኬት ግን የታይታና የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን ሂደትና የኑሮ ዘይቤ ነው፡፡ የስኬት መነሻው መሆን ያለበት በመጀመሪያ ራስን ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በመቀጠልም ባመኑበት ጎዳና ወደ መሰማራትና ራስን ወደ ማሻሻል ሊያድግ ይገባዋል፡፡ @truegospell @Truegospell 👈 share &join @Truegospell @Truegospell @truegospell
Show all...
Elohim #ዋጋህ_እንደ_ቦታህ_ነው!! ከእለታት ባንዱ ቀን አንድ ታዳጊ አባቱን፤ @truegospell “የህይወት ዋጋው ስንት ነው?” ሲል ጠየቀው፡፡ አባትም መልስ በመስጠት ፈንታ ልጁን እንዲህ ሲል አዘዘው፡፡ “እንካ ይህንን የድንጋይ ቁራጭ...ወደ ገበያ ውሰደው " @truegospell "ሰዎችም ዋጋውን ከጠየቁህ በጣቶችህ ሁለት ቁጥርን ብቻ አሳያቸው እንጂ ምንም አትናገር” አለው፡፡ ልጁም ድንጋዩን ወሰደ፡፡ ወጥቶም በገበያ መሃል ቆመ፡፡ አንዲት ሴትም መጣች፡፡ @truegospell “ይህ ድንጋይ ዋጋው ስንት ነው? ብትሸጥልኝ ወስጄ ግቢዬ ውስጥ አስቀምጠዋለሁ” አለችው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳያት፡፡ እሷም አለች “ሁለት ብር? እወስደዋለሁ!!” @truegospell ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ በገበያ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ አባትየውም አለው @truegospell “አሁን ደግሞ ድንጋዩን ይዘህ ወደ ሙዚየም ሂድ ዋጋውን ሲጠይቁህም ሁለት ጣቶችህን አሳይ” @truegospell ልጁም ወደ ሙዚየም ወጣ፡፡ ገዢም መጥቶ ዋጋ በጠየቀው ጊዜ ሁለት ጣቶቹን አሳየው፡፡ ገዢውም “ሁለት መቶ ብር? እወስደዋለሁ!” አለው፡፡ ልጁም በድንጋጤ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ያጋጠመውንም ለአባቱ ነገረው፡፡ @truegospell አባትየውም ተናገረ፡፡ “አሁን ደግሞ በመጨረሻ ድንጋዩን ይዘህ ወደ የከበሩ ማዕድናት መሸጫ ሂድ ለባለቤቱም አሳየው” @truegospell አለው፡፡ ልጁም ሄደ ለሱቁም ባለቤት አሳየው፡፡ የሱቁ ባለቤት በመገረም @truegospell “ይህ እኮ አለም ላይ እጅግ ውድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች አንዱ ነው” አለ፡፡ “ከየት አገኘኸው? ስንትስ ትሸጠዋለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ምንም ሳይናገር ሁለት ጣቶቹን አሳየ፡፡ @truegospell የሱቁም ባለቤት አለ.... “ይህንን ድንጋይ በሁለት መቶ ሺህ ብር እወስደዋለሁ፡፡” @truegospell ልጁም በመገረም እየሮጠ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያጋጠመውን ለአባቱ ነገረው፡፡ @truegospell አባትየውም “ልጄ አሁን የህይወትህ ዋጋ ተገልጦልሃል” አለው፡፡ @truegospell አየህ የመጣህበት ቦታ፣ ዘርህ፣ ሃይማኖትህ፣ የቤተሰቦችህ ሃብት፣ የተወለድክበት ቦታ ልዩነት አይፈጥርም፡፡ @truegospell ዋናው ራስህን የምታስቀምጥበት ቦታ፣ ራስህን የምታገኝበት የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ልዩነቱ ያለው ራስህን ለመሸከም በምትመርጥበት መንገድ ነው፡፡ ህይወትህን ሙሉ የሁለት ብር ድንጋይ ዋጋ ስትሰጠው ኖረህ ይሆናል፡፡ ህይወትህን ሙሉ የኖርከው ዋጋህ ሁለት ብር ብቻ እንደሆነ በሚያስቡ ሰዎች ተከበህ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ውድ የሆነ የከበረ ድንጋይ በውስጡ ይዟል፡፡ @truegospell ልዩነቱም ያለው ውስጣችን ያለውን የከበረ ድንጋይ አይተው ዋጋ በሚሰጡን ሰዎች መሃል መገኘትን ስንመርጥ ነው፡፡ ራሳችንን በገበያ ወይም በከበሩ ማዕድናት ሱቅ የማስቀመጥ ምርጫው አለን፡፡ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ያለውንም ውድ ዋጋ ለማየት ምርጫው የኛው ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም የከበረ ዋጋቸውን እንዲረዱ ማድረግ እንችላለን፡፡ አብረህ የምትውላቸውን ሰዎች በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ ይህ በህይወትህ ልዩነትን ይፈጥራልና !! @truegospell @truegospell @truegospell 👈#share&#join @truegospell @truegospell
Show all...
Elohim # በመንፈስ # መመላለስ + አንድ ክርስቲያን አደገ የሚባለው በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ ሲጀምር ነው። ሮሜ 8, ገላ 2 ፡20 , 3፡1-6, 5፡16,24-25, ቆላ 3፡9-10, ኤፌ 4፡23-24, ኤፌ 5፡18, ሮሜ 12፡2, 13፡14, 2ቆሮ 3፡ 18..... + እግዚአብሔር ወደ ክርስትና ሕይወት ሲያመጣን እኛ እንድንኖር ሳይሆን ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኛ እንዲኖር ነው። + እግዚአብሔር አባትን ማየት የሚቻለው በልጁ በኢየሱስ ክርሰቶስ በኩል እንደሆነ ሁሉ እንደዚሁም ክርስቶስን ማየት የሚቻለው መገለጡ በሆነችው በቤተክርስቲያኑ (በቅዱሳን ሁሉ ) በኩል ነው። + በመንፈስ መኖር ማለት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር በመሆን እኛ በራሳችን ማድረግ የማንችለውን መንፈስ ቅዱስ በእኛ ማድረግ እንዲችል መታመን ወይንም ደግሞ ጌታ አንድ ነገር እንድናደርግ በጠየቀን ጊዜ እርሱ የሚፈልገውን በእኛ ሆኖ እንዲያደርግ ወደ እርሱ መመልከት እና እርሱን ተስፋ ማድረግ ማለት ነው። + መንፈሳዊ ድልን የምንቀዳጀው በየእለቱ ራሳችንን ለመለወጥ በምናደርገው ቁርጠኛ ውሳኔ ሳይሆን ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ ስናስገዛ ብቻ ነው። + እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ማየት የሚፈልገውን ፍሬ ለማፍራት መንገዱ ሃይማኖታዊ እና ሰዋዊ ጥበብን መጠቀም ሳይሆን በመንፈስ መኖር ብቻ ነው። + በእምነት የእግዚአብሔር ፀጋ እኛነታችንን እንዲወርስ እያስረከብን ስንመጣ መንፈስ ቅዱስ እኛን በሀጥያት ላይ ድል ነሽወች እና የአምላክ(የክርስቶስ) ሕይወት መገለጫዎች ያደርገናል። + መንፈስ ቅዱስ እኛን በድል ሕይወት ለማኖር የሰብዓዊ ኃይል ጥረት እና ርዳታ አያስፈልገውም ጌታ ኢየሱስ የድሉ ባለቤት እና ምንጭ ነው። ሮሜ 8, ገላ 2 ፡20 , 3፡1-6, 5፡16,24-25, ቆላ 3፡9-10, ኤፌ 4፡23-24, ኤፌ 5፡18, ሮሜ 12፡2, 13፡14, 2ቆሮ 3፡18..... ፀጋ እና ሰላም ለሁላችን ይብዛ። @truegospell @truegospell @truegospell 👈 join & share
Show all...
ውድ መንፈሳውያን 👉ኃጢአትን አታስቡት 👉ካሰባችሁት አትናገሩት 👉ከተናገራችሁት አታድርጉት 👉ካደረጋችሁት አትድገሙት “ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።” — ሮሜ 6፥6 “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።” — ገላትያ 2፥20 ቆላስይስ ምዕራፍ 3 ሙሉውን አንብቡት @slehiywet @tsegabecha
Show all...
Elohim ትልቅ የሆነውን 🎤 አስቴር አበበ ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x) ከፍታውን ፡ ተመኝቶ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ ያለ ላፍታ ፡ ማን ፡ ተመቸው ፡ ማን ፡ ተደላደለ ወርዷል ፡ ወደ ፡ ቦታው ፡ እርሱ ፡ ወዳዘዘለት ልክን ፡ ማወቅ ፡ እያለ ፡ ኋላ ፡ ከመዋረድ በዕውቀቱ ፡ ልቀት ፡ ማንስ ፡ ገለጠው እንኳንስ ፡ የእርሱን ፡ ጥግ ፡ ጫፉን ፡ ማን ፡ ነካው ሁሉም ፡ ከታች ፡ ሆኖ ፡ ይመለከተዋል የእጁ ፡ ስራ ፡ ሁሉ ፡ ሲያደንቀው ፡ ይኖራል ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x) ደጋግሞ ፡ ቢፎክር ፡ ቢጨምር ፡ ቀረርቶ ልቡን ፡ አጥፍቶታል ፡ ከሰማያት ፡ ወርዶ ዝም ፡ ብሎ ፡ ያለ ፡ ልክ ፡ ታዞ ፡ በመስቀል ፡ ላይ የአብን ፡ ጥም ፡ አርክቷል ፡ ሆኗል ፡ ለአለም ፡ ሲሳይ ግድግዳው ፡ ፈረሰ ፡ በመሀከል ፡ ያለው ሰውን ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ለይቶ ፡ ያቆየው ፍቅር ፡ መሀል ፡ ገብቶ ፡ ሁሉን ፡ አንድ ፡ አረገ ጠላትም ፡ አፈረ ፡ ለሁሌ ፡ እጁን ፡ ሰጠ ከቶ ፡ አልደፍርም ፡ አንደኛ ፡ ልለው ሁለተኛ ፡ ሆኖ ፡ ማን ፡ ተከተለው ሁሌ ፡ ብቻውን ፡ ሚመለክ ፡ ትልቅ ሚጨምር ፡ ክብር ፡ ከትላንቱ ፡ ይልቅ (፪x) ትልቅ ፡ የሆነውን ፡ ከፊቴ ፡ አስቀድሜ መቼ ፡ አንገቴን ፡ ደፋሁ ፡ መች ፡ ሄድኩ ፡ አቀርቅሬ የተማመንኩበት ፡ ኩራቴ ፡ ሆኖኛል ትላንቴ ፡ ይመስክር ፡ ሰልፌን ፡ አሸንፏል ፤ ሰልፌን ፡ አሸንፏል (፪x) @Truegospell @Truegospell 👈join & @Truegospell share @truegospell
Show all...
መዝሙር 136 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ² የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ³ የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁴ እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁵ ሰማያትን በብልሃት የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁶ ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁷ ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁸ ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ⁹ ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁰ ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹¹ እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹² በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹³ የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁴ እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁵ ፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁶ ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁷ ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁸ ብርቱዎችንም ነገሥታት የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ¹⁹ የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ²⁰ የባሳንን ንጉሥ ዐግን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ²¹ ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ²² ለባሪያው ለእስራኤል ርስት፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ²³ እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ ²⁴ ከጠላቶቻችንም እጅ አድኖናልና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና ²⁵ ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ²⁶ የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። በተጨማሪም 1ዜና 16:34-36 መዝ 103-2 መዝ 106-1 አንብቡት የመኖራችን ሚስጥር የሆነው እግዚአብሔር ቸር ነውና ምህረቱም ለዘላለም ነውና አመስግኑት። መልካም Life!!! @tsegabecha @tsegabecha
Show all...
ፍቅሩን የገለጠው እንዲህ ነው👆👆 @tsegabecha @tsegabecha
Show all...
tamu.mp34.12 MB
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ወደፊትም አይኖርም። @tsegabecha @tsegabecha
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.