cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የመንፈስ ፍሬዎች ❤️ 🕊 🙏

👉በዚህ ቻናል በቅዱሱ መፅሐፋችን ለይ 📖ገላ 5÷22 ሰፍረው ስለ ምናገኛቸው የመንፈስ ፍሬዎች ማለትም ስለ :- ❤️ፍቅር 😁ደስታ 🕊ሰላም 🙏ትዕግሥት ✋ቸርነት 😍በጎነት ✝እምነት 🤗የውሃት፥ 🙊ራስን መግዛት በፅሁፍ እንደሁም ደግሞ በድምፅ እንማማራለን እንዲሁም :- 🗣በተለየ ሁኔታ በተለየ ቀን የበደላችሁን እንዱሁም የበደላችሁትን ሰው በይቅርታ ልባችሁን ከጥላቻ ወደ ፍቅር ከጨለማ ወደ

Show more
Advertising posts
1 475
Subscribers
-124 hours
-37 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

እህቴ 👸 ሆይ አርአያሽ (ሮል ሞዴልሽ) ማነች ⁉️ 👉አስተዋይ ሴት እንድትሆኝ ሁሌ ፀልይ አንች የ ቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ልጅ ነሽ😘 💖ድንግል ሆይ ልደትሽ በረከታችን ነው!!! 💖ድንግል ሆይ የልደትሽ ቀን ሙላታችን ነው!!! 💖የእመቤታችን የልደቷ በረከት ይደርብን! \ ምልጃዋ ሀገራችንን ይጠብቅልን ሕሙማንን ይፈውስልን!!! 🌹የተወለድንበትን ቀን ከምንረግምበት ፈተና ሁሉ እግዚአብሔር ይሠውረን! 🙏 ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን። 🙏ሰናይ ቀን💚💛❤️🕊️🕊️🕊️ 🙌ቀናችንን ባርክልን የፍቅር አምላክ ነህና ፍቅርን አድለን የሰላም ባለቤትም አንተ ነህና ለሀገራችንም የቀደመ የማይናወፅ ሰላሟን አንተ አድላት ሰናይ ቀን ወዳጆቼ🙌 ✍የአብስራ ተስፋዬ @yeabm 💚  •✥• @Etelawyan •✥•  💚 💛  •✥• @Etelawyan3 •✥•💛 ❤️  •✥• @Etelawyan •✥• ❤️
Show all...
👍 3 2
አይዞሽ              አንቺ ከመኖሪያሽ ተነስተሽ ወደ አንድ ከተማ በመኪና ስትጓዢ ለዓይን ያማረሽን ለምላስ የጣመሽን ምግብ ቋጥረሽ ትጓዣለሽ። እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ወጥተው የሲና ምድረ በዳን ሲያልፉ የቋጠሩት ምሳና እራት አልነበረም። በማያርሱበት በማይዘሩበት በማያጭዱበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ ጎራ ብለው የሚበሉበት ሬስቶራንት በሌለበት፣ የታሸገ ምግብ የሚገዙበት ሱፐርማርኬት ባልኖረበት ምድረ በዳ ላይ እግዚአብሔር መናና ድርጭት እየመገበ መራቸው። ከመሀላቸው አንዳች የተራበ አልነበረም። እግዚአብሔር መሪ የሆነበት ህይወትና ጉዞ በጉድለት ሳይሆን በበረከትና በጠል የተመላ ነው። ወዳጄ አምላክሽ እስራኤልን በምድረ በዳ የመገበ፣ እውር አሞራን የሚቀልብ፣ ድንጋይ የተጫነውን ትል የማይረሳ፣ ትንሿን ትንኝ ሳይዘነጋ የሚመግባት ጌታ ነው።  አንቺንማ ሞቶልሽ እንዴት ይረሳሻል ርቦሽ እንዴት ይጨክንብሻል በፍፁም!        ምድረ በዳ በሆነ የህይወት ቀጠና ብታልፊ፣ ዘርተሽ የማታጭጂበት ሰርተሽ የማታተርፊበት፣ ቀድተሽ የማትጎነጪበት ሁኔታ ላይ ብትሆኚ እንኳ በሚያስፈልግሽ ሁሉ መለኮታዊ እጁን ይገልጥልሻል።            ምድረ በዳ ነው ብሎ ሰው ሲጨነቅ በምድረ በዳ አንቺን ለመርዳት የማይከለክለው ጌታ የበረከቱን ጠል ያዘንምልሻል። በሲና ምድር እስራኤላውያን ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሰዎች ለጉብኝት አልፈዋል፣ ሀገር አቋርጠው ሄደዋል ያቋርጡ እንጂ መና አልበሉም ከአለት ውኃ አልጠጡም የጠጡት በእግዚአብሔር ያመኑት እስራኤላውያን ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ሰው በሚራብበት ዘመን ትጠግቢያለሽ፣ ሰው በሚጠማው ዘመን ትረኪያለሽ፣ በሚሞትበት ዘመን በህይወት ትኖሪያለሽ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ያዘጋጃል!    "እናት ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ታበላለች እግዚአብሔር ግን ከሞትም ቀስቅሶ ይመግብሻል።" በአንዳች አትጨነቂ እግዚአብሔር ያዘጋጃል።   🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊 መልዕክት፣አስተያየት፣ ጥያቄ፣ ጥቆማ በ  @Yeabm 🕊//ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር //🇪🇹 @Etelawyan 🇪🇹 @Etelawyan3 🇪🇹 @Etelawyan 🇪🇹                  
Show all...
👍 3
ያሰባችሁት ባይሆንም ያሰበላችሁ ሆኗል ይደመጥ 🦻🦻🦻‼️ 🎤የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm
Show all...
👉ልባሟ እህቴ 😍 በፍቅር ስለፍቅር ነውና በደንብ አድምጪኝ 🙏 ►ዓይን ያለ ፍቅር ካየ ምን አገባኝ ይላል። : ►ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ : ►ምላስ ያለ ፍቅር ከወጣ ይሰብራል። : ►እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል። : ►እግር ያለ ፍቅር ከሄደ ድልድይ ♡የተሰጠን የእድሜ ገደብ እንኳንስ ለፀብ ለፍቅርም አይበቃምና አምላክ ከወረት ፍጹም የጸዳ ንጹሕ ፍቅር ለሁላችንም አብዝቶ ያድለን!(አሜን) 🎤የአብስራ ተስፋዬ @Yeabm 📩 ይሄን ፖስት ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አርጉ ቻናሉንና ግሩፑንም አስተዋውቁ @Etelawyan 🇪🇹 @Etelawyan3 🇪🇹 @Etelawyan 🇪🇹
Show all...
👍 2
✨የምትመች ረዳት✨ 👸ሔዋን (ሴት) የእግዚአብሔር መልካምነት ማሳያ ናት እንዲህ ነው እንግዲህ የሴትነት አፈጣጠር የምትመች ረዳት ለመሆን ተሰርታለች እርሷ ሙላት ናት 👉ለደከመ ብርታት 👉ለደበዘዘው ፍካት 👉ላዘነው መፅናኛ  👉ራእይን አጋዥ 👉ከግብ አድራሽ 👉ታማኝ መካሪ የፅሎት ሴት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተፈጥራ በጎደለበት ገብታ ሂወትን በእግዚአብሔር መልካምነት የምታስውብ የነፍስ ጌጥ ናት :: 🎙የአብስራ ተስፋዬ ለማንኛውም ጥያቄ ሃሳብ እና አስተያየት 📥 @yeabm
Show all...
እቴጌ ጣይቱ(ወለተ ሚካኤል)በንጉሡ ትእዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዛ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ማቴዎስና ከቀሳውስቱና መነኮሳቱ ከንጉሡ ሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክም ጋር ወደ ጦርነቱ የተጓዘች ጀግና ልባም እና የሴትነት ልኬት የሆነውን ብልህነትን የታደለችዋ ንግስት ሀይማኖተኛ ብቻ ሳትሆን ፀሎተኛ ከሆነችው የሀገር ባለውለታ ከተናገረችው መሀል :- 👸🗣“እኔ ሴት ነኝ፡ ጦርነት አልወድም፤ ነገር ግን ሀገሬን እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን እመርጣለሁ፡፡ ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ! እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር አስጥቶ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ ለአፈሩ ክብር ለብሶ እሱ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ! ሂድ! የኢትዮጲያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው ፡፡ 👉እናም የዛሬው ትውልድ ሆይ እኔም ይሄን እልሀለሁ 🛡ታሪክ መስራት ቢያቅተን ታሪክ እንጠብቅ ⚔ አድዋ ብዕሩ ደም🩸፣ ወረቀቱ መሬት ሆኖ የተጻፈ  ማንም ሊያጠፋው የማይችል ደማቅ የነጻነትና የአሸናፊነት ታሪክ ነው  ክብር ለጀግኖች አያቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ፤ ደማቸውን አፍሰው  ነጻ ሀገር ላስረከቡን ፡፡ ክብር በአደዋ ለተሰዉ ጀግኖች ሰማዕታት ይሁን። በዘር በሽታ ታመን ከአድዋ ድል እሳቤ ርቀን፣ አባቶቻችን አንድ ያደረጓትን ኢትዮጵያ አንሰን ከማሳነስ ወጥተን ለዚህ ታላቅ ድል መሰረት የሆነችውን ሀገርን ፊደል ቀርጻ፣ የስነጽሁፍ ስርዓት ቀምራ፣  መጻፊያ መከተቢያ ብዕር ቀርጻ፣ ቀለም በጥብጣ፣ ብራና  ፍቃ፣ መጽሀፍ ጽፋ ደጉሳ ታሪክን የጠበቀች ቅድስት ቤተክርስቲያንን 👉ብታከብራት አክብረዋት እንደከበሩት ትከብራለህ 👉አጠፋታለሁ ብለህ ካሰብክ ደግሞ አጠፋታለሁ ብለው ተነስተው እንደጠፉት ነገስታት ትጠፋለህ ሰው በሰውነቱ በወደደበት ሰርቶ፤በፈቀደበት ወልዶ ከብዶ የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለማየት ያብቃን ። 🛡ታሪክ መስራት ቢያቅተን ታሪክ እንጠብቅ ⚔ አድዋ ብዕሩ ደም🩸፣ ወረቀቱ መሬት ሆኖ የተጻፈ  ማንም ሊያጠፋው የማይችል ደማቅ የነጻነትና የአሸናፊነት ታሪክ ነው  ክብር ለጀግኖች አያቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ፤ ደማቸውን አፍሰው  ነጻ ሀገር ላስረከቡን ፡፡ ክብር በአደዋ ለተሰዉ ጀግኖች ሰማዕታት ይሁን። በዘር በሽታ ታመን ከአድዋ ድል እሳቤ ርቀን፣ አባቶቻችን አንድ ያደረጓትን ኢትዮጵያ አንሰን ከማሳነስ ወጥተን ለዚል ታላቅ ድል መሰረት የሆነችውን ሀገርን ፊደል ቀርጻ፣ የስነጽሁፍ ስርዓት ቀምራ፣  መጻፊያ መከተቢያ ብዕር ቀርጻ፣ ቀለም በጥብጣ፣ ብራና  ፍቃ፣ መጽሀፍ ጽፋ ደጉሳ ታሪክን የጠበቀች ቅድስት ቤተክርስቲያንን 👉ብታከብራት አክብረዋት እንደከበሩት ትከብራለህ 👉አጠፋታለሁ ብለህ ካሰብክ ደግሞ አጠፋታለሁ ብለው ተነስተው እንደጠፉት ነገስታት ትጠፋለህ ሰው በሰውነቱ በወደደበት ሰርቶ፤በፈቀደበት ወልዶ ከብዶ የሚኖርባት ኢትዮጵያን ለማየት ያብቃን። ✨‟ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሶሙ፡ ወተሣሐሎሙ! ወለነኒ መሐረነ ወዕቀበነ እምኲሉ ስሕተት፡ ወእምተመውዖ ለጸላኢ!” 👉(አቤቱ ነፍሳቸውን አሳርፍ፡፡ ይቅርም በላቸው፡፡ እኛንም ማረን፡ ከስህተት ሁሉ እንዲሁም በጠላት ከመሸነፍ ጠብቀን፡፡)                                   አሜን!🙏 🔸የልዳው ሰማዕት፤ የፋርሱ ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ምልጃው በረከቱ ጠብቆቱ አይለየን ።             👉 የካቲት 23/06/16 አድዋ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ❤ ✍ የአብስራ ተስፋዬ   @yeabm
Show all...
👍 4
የኔ ውድ እህት ዛሬ ምልጃዋን ፍቅሯን የምታመፀኛት እመአምላክ እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን እኮ ጌታሽ ፈጣሪሽ እናቱን የመረጠው ከሴቶች መካከል ነው አንቺስ ሀገሩን ከሞሉት ሴቶች የተመረጠችዋ ልባም ሴት 😍 መሆን አትፈልጊም 🤔 ከፈለግሽስ ይህቺን የምትመረጥ ከሴትም ሴት ልባም ሴት የሆነችዋን ለመሆን ምን እያደረግሽ ነው ⁉️ መልሱን ለአንቺ ተውኩት ግን ይሄን አድምጪው ✍ የአብስራ ተስፋዬ   @yeabm
Show all...
2
አድነኝ ለምትሉት እግዚአብሔር ያድናችሁ፤   👉 ድረስልኝ ለምትሉት እግዚአብሔር ይድረስላችሁ፤   👉 ለጨነቃችሁ፣ መሄጃው ግራ ለገባችሁ ሁሉ እግዚአብሔር መፍትሔ ይስጣችሁ፤    👉እንባ የቀንና የለሊት ምግብ የሆናችሁ እግዚአብሔር በቃ ይበላችሁ፣ ደስታ ይሁናችሁ፤     👉ነፍሳችሁ ቅርቃር ውስጥ ገብታ ተስፋ ለራቃችሁ እግዚአብሔር በምስራች ወደናንተ ይምጣላችሁ በፍቅር 🥰 የምታምሩበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበረቁበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንላችሁ እርሱ እውነተኛ ቸር እረኛ አባት እንደሆነን ሁሉ እኛም እውነተኛ በጎች ልጆቹ እንድንሆን በፍቅር በምህረቱ ይርዳን 🙏 ✍ የአብስራ ተስፋዬ   @yeabm Join and share 💚💛❤️ @Etelawyan3 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️ 💚💛❤️ @Etelawyan 💚💛❤️      
Show all...
🙏 5👍 1
“ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።”— ኤርምያስ 31፥3       እርሱ ወረት የለበትም አወኩሽ ናኩሽ፤ ሰጠሁሽ ሰለቸሁሽ፤ አጣሽ ነጣሽ፤ ከሳሽ ገረጣሽ ሳይል በጽኑ ፍቅር ይወድሻል ። ከእለታት አንድ ቀን ፍቅሩ አያልቅም፤ በዘለዓለም ፍቅር ይወድሻል። እናም የኔ ልባም 😍 እህት አምላክሽን ዘወትር እንዲህ በይው      አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ በአንተ ብቻ እንደተወደድኩ ልቅር ቸር ጠባቂ እረኛ እንደሆንከኝ እኔም ከመልካም እና ታማኝ አንተን ደስ ከሚያሰኙት ወገን ደምረኝ አባት እንደሆንከኝ ልጅህ ልሁን ያንተ ፍቅር ጉድለት የለውም መጥላት በማይችል ፍቅር ወደኸናልና ተመስገን ። አሁንም ምህረት ቸርነትህን ከእኔ አታርቅ 🙏 በፍቅር 🥰 የምታምሩበት በይቅርታ 🙏 የምታሸበረቁበት ሰናይ 😁 ቀን ይሁንላችሁ እርሱ እውነተኛ ቸር እረኛ አባት እንደሆነን ሁሉ እኛም እውነተኛ በጎች ልጆቹ እንድንሆን በፍቅር በምህረቱ ይርዳን 🙏 ✍ የአብስራ ተስፋዬ   @yeabm
Show all...
🥰 4👍 1