cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሐብተማርያም 🙏

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! የዚህ ቻናል ዋና አላማ መዝሙራት እየተለቀቁ እንድናጠናበት እና የወጣቱን የመዝሙር እውቀት መጨመር ነው!!! የደቂቀ አቡነ ሐብተ ማርያም መንፈሳዊ ማሕበር Contact us at: @Elchapo_ET

Show more
Advertising posts
6 147
Subscribers
-524 hours
-517 days
-22330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✝️ማኀሌታይ ያሬድ✝️ አንተ ባለቅኔ አንተ ባለዜማ ድጓ ፆመ ድጓ የሰማህ ከራማ የግእዝ የእዝሉ የአራራይ ቀማሪ የድፋት የቅናት የጭረት ፈጣሪ ያሬድ ማኅሌታይ የእግዚአብሔር ዘማሪ ከጥበባት ሁሉ ጥበብ የምስጋና ከመላእክት ሰምተህ ተቀኝተሀልና ወጥተን ተከተልንህ ልጆችህ ለዜማ በመዝሙር ልንወርሳት ታላቋን ከተማ     አዝ===== ነብርም ዥንጉርጉር ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ ዜማህም ውበቷ ጸሎቷ ሃሌሉያ የመቅደሱ ጌጥ ነህ የሃገር ግርማ ሞገስ ነፍስ ያለመልማል ቅኔ ዜማ ሲፈስ አዝ===== መቅደሱን ወረሰ ሰማያዊ ፀጋህ የካህናቱን ልብ በዝማሬ ሞላህ ልብ እየሰቀለ ሰማይ እየነካ ዜማህ ምድርን ጥሶ ጸባዖት አንኳኳ
በዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 3🥰 1
✝️ግንቦት✝️ ሐሙስ ግንቦት 1 - ቅድስት ልደታ - የተወለደችበት ቅዳሜ ግንቦት 3 - ቅዱስ ፋኑኤል - በመሪ እና በዓለም ባንክ ረቡዕ ግንቦት 7 - ጠሮ ሥላሴ - ቅዳሴ ቤቱ እሁድ ግንቦት 11 - ቅዱስ ያሬድ -  የተሰወረበት ጎተራ አጎና ሰኞ ግንቦት 12 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ፍልሰተ አፅማቸው                       - ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ - በአማላጅነቷ እልፍ ነፍሳት ከሲዖል ያወጣችበት መታሰቢያ እለት ማክሰኞ ግንቦት 13 - ቅዱስ እግዚአብሔር አብ - ቅዳሴ ቤቱ በአዲሱ ገበያ እና በኮዬ ፈጪ እግዚአብሔር አብ(ጎጆ አርሴማ) ረቡዕ ግንቦት 14 - አቡነ አረጋዊ ወገብረ ክርስቶስ - ገብረክርስቶስ ከጫጉላ ቤት ወጥቶ የመነነበት መታሰቢያ እለት አርብ ግንቦት 16 - ቅድስት ኪዳነምህረት - ፈረንሳይ ጉራራ - ቅዳሴ ቤቷ ሰኞ ግንቦት 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ጎሮ - ቅዳሴ ቤቱ                       - አቡነ ዓብየ እዝጊ - በብስራተ ገብርኤል - በዓለ እረፍታቸው ረቡዕ ግንቦት 21 - እመቤታችን - በደብረ ምጥማቅ ለአህዛብ ሳይቀር የተገለጠችበት መታሰቢያ በዓል ቅዳሜ ግንቦት 24 - ቁስቋም ማርያም - እንጦጦ                          - ቅዱስ ዮሴፍ - ንፋስ ስልክ                           ስደት የጀመሩበት መታሰቢያ እለት ሰኞ ግንቦት 26 - አቡነ ሃብተማርያም - በዓለ ልደታቸው ማክሰኞ ግንቦት 27 - የመድኃኔዓለም በዓል ጎተራ አጎና በሚገኘው በቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን  እና ለገሀር በሚገኘው ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን ይከበራል(በዓሉም ኢህአዴግ 1983 በገባ ሰዓት ጎተራ አካባቢ በነበረ ከፍተኛ ፍንዳታ የአካባቢው ምዕመን እና የሌላ እምነት ተከታይ ሳይቀር በቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን  ተሰባስቦ በመድኃኔዓለም ታምር በቅዱስ ያሬድ ምልጃ የዳነበትን መከራውን ያለፈበትን እለት መታሰቢያ በማረግ ሁሌም በያመቱ ግንቦት 27 ታቦተ ዕጉ ወጥቶ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ቅዱስ ቂርቆስ የሚወጣበትም ምክንያት ተመሳሳይ ነው። ረቡዕ ግንቦት 28 - ቅዱስ አማኑኤል - ቅዳሴ ቤቱ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
ሐብተማርያም 🙏

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! የዚህ ቻናል ዋና አላማ መዝሙራት እየተለቀቁ እንድናጠናበት እና የወጣቱን የመዝሙር እውቀት መጨመር ነው!!! የደቂቀ አቡነ ሐብተ ማርያም መንፈሳዊ ማሕበር Contact us at: @Elchapo_ET

👍 11 1
✝️ልደታ ለማርያም✝️ ልደታ ለማርያም ስምሽ ስንጠራ መላ አካላታችን ለመለመ አፈራ/2/ ከገነት የፈለቅሽ ልዩ መአዛችን የቃላችን ቃና ናርጎስ ወዛችን በጉዛችን ሁሉ ስምሽን አስከትለን እንቅፋት ሳይነካን/2/ ከእርስቱ እንገባለን     አዝ===== ቃልኪዳን እንዳለ ስምሽን ለጠራ ዘወትር ይድናል ከክፋ መከራ ልደታ ለማርያም ስምሽን ስንቅ አድርገን ምን አለ ያጣነው/2/ አንቺን ተስፋ አድርገን     አዝ===== በወንጌል አጸዶች ዙርያሽን ተከበሽ የዜማ አውአፍ ቀን ከሊት ሲቀኙሽ የዘካርያስ እጣን ምድርን ያሻተተ ነፍሳችን ተነጥቆ/2/ ካንቺ ሊኖር ሻተ     አዝ===== እንደምን ያለ ክብር እንዴት ያለ ግርማ የጥበብ መገኛ የዜማ አውድማ የሚዘራ ወንጌል ከደጊቱ መሬት ሰላሳና ስልሳ/2/ የመቶ ፍሬው አዝ===== በእናት ፊት ማደግ ሰቆቃ የለበት ሳይጠይቁት ሰጪ የልብ አውቃ እመቤት ስምሽን ለመጥራት ለዚህ ያበቃሽን ድንግል ማርያም ሆይ/2/ ከቁጥር አታጉዲይን
በዘማሪ ዘሩባቤል ሀብታሙ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 4 2
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" ሉቃ 24፣5      እንኳን ለዚህ አበቃን መልካም በዓል ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 8 2
✝️ትንሣኤከ ለእለ አመነ✝️ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/        የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/     አዝ===== የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ አዝ===== ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/
በዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 5🥰 1
✝️ተናገር አለኝ✝️ ተናገር አለኝ መስክር ተናገር አለኝ ዘምር ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ ሰላም አውጥቶ ካስገባ ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ ሆሳዕና ልበል መድኃኒት ከፍ በልልኝ የኔ አባት ተጠምተኸ እኔ ረካሁ ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ     አዝ===== እጆቹን እዩት በእምነት ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት በዚያ ታትሞ ውበቴ እየሱስ ለኔ ብርታቴ ከማንም በላይ ከምንም ለኔ ልዩ ነው ዘላለም ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ እኔስ በረታሁ በአምላኬ     አዝ===== የእሾህ አክሊሉ በራሱ ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ ሞቴን ገድሎታል አባቴ ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ ሰው የመሆኔ ምስጢሩ የማይለወጥ ነው ፍቅሩ የገባኝ እውነት በምድር ላይ ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ     አዝ===== ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ ተራበ ውዴ መድኃኔ ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ ወሰን የሌለው ምሕረቱ ለዚህ ደግነት ውለታ ምን ይከፈላል ለጌታ
በዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 4 4🥰 1
✝️ቸር አገልጋይ ማነው✝️ ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ  የታመነ መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ /2/ ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው     አዝ===== ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ     አዝ===== ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ አዝ===== ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል
በዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
4👍 2
✝️በወርቅ  ቀለም ተጽፈሻል✝️ በወርቅ ቀለም ተጽፈሻል ድንግል ሆይ ለኔ ተሸጥተሻል አከብርሻለው እመቤቴ ተስፋ ጽዮን ነሽ ለሕይወቴ        ተሰናክዬ እንዳልወድቅ ዘይት መብራቴ እንዳያልቅ ሁኚልኝ ድንግል ንጹህ ዋጋ በሩ በእኔ ላይ እንዳይዘጋ            አዝ===== የቆመ መስሎት የወደቀ የክብሩን ስፍራ የለቀቀ ሲቀና አየሁት አንቺን ይዞ በትር ምልጃሽን ተመርኩዞ            አዝ===== እንዳልቀርብሽ ተራቁቼ የጌታን ክብር እረስቼ ቀድመሽ ውጪልኝ በጉዞዬ ልጅሽ ነውና አላማዬ አዝ===== ምልጃሽ ካቀናው ጉልበቴን ከባረከልኝ ሕይወቴን ብጽይት እላለሁ ዘወትር ስላንቺ ይክበር እግዚአብሔር
በዘማሪት ጽጌረዳ ጥላሁን
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 7
✝️የልቤን በልቤ ይዤ✝️ የልቤን በልቤ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው የሆዴን በሆዴ ይዤ ከፊትሽ ቆሜአለው ካለኝ ነገር ሁሉ አንቺን መርጫለሁ እናቴ ሆይ ስሚኝ አማልጅኝ እላለሁ ግራኝ ቀኝ ህይወቴ በሾህ ታጥሮብኛል በፊት በኋላዬ መሰናክል በዝቷል እኔስ ያለ ምርኩዝ ጉዞዬ ከብዶኛል እመ አምላክ ደግፊኝ እጄ ተዘርግቷል /2/     አዝ===== ቆሜ ስራመድ ጤነኛ እመስላለሁ የውስጤን ጎዶሎ እኔ አውቃለሁ ድንግል ሆይ ቅረቢኝ አይዞህ ልጄ በይኝ የጭንቀቴን ካባ አውልቀሽ ጣይልኝ /2/     አዝ===== እናት ያለው ሰው ፍጹም አይተክዝም አንድ ቀን ይስቃል አልቅሶም አይቀርም ሀዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ በደስታ ልዘምር በቀረው ሕይወቴ /2/ አዝ===== አሁን ጎዶሎ በውስጤ አለና ድንግል ሆይ ቅረቢኝ ዛሬም እንደገና ለዚች ለትንሿ ለጥቂቷ እድሜ እንደከፋኝ አልኑር ቀና አርጊኝ እናቴ /2/
በዘማሪ ዲያቆን ልዑል ሰገድ ጌታቸው
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
👍 4
✝️ሚያዚያ✝️ ሰኞ ሚያዝያ 7 - ቅዱስ እያቄም - እረፍቱ - በኮተቤ ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን ረቡዕ ሚያዚያ 9 - አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ  እረፍታቸው - በቤተል ሚካኤል ቤተክርስቲያን በቀበና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን - በወይራ ሰፈር ቅድስት አርሴማ ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ሚያዝያ 15 - መጥምቁ ዮሐንስ - አንገቱ ለ15 ዓመት ያስተማረችበት መታሰቢያ በዓል - በቤላ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ማክሰኞ ሚያዝያ 22 - ቅዱስ ዑራኤል - ቅዳሴ ቤት ጎፋ መብራት ሀይል ረቡዕ ሚያዝያ 23 - ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ እረፍቱ እሁድ ሚያዝያ 27 - ቸሩ መድኃኔዓለም በ 6 ኪሎ ምስካየ ኃዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ብቻ ረቡዕ ሚያዝያ 30 - ቅዱስ ማርቆስ - በዓለ እረፍቱ -በ6 ኪሎ ቅዱስ ማርቆስ ማሳሰቢያ ሚያዝያ 22 እና ሚያዝያ 23 ሕማማት ላይ ስለዋለ ለሌላ ጊዜ ተላለፏል። ሚያዝያ 27 ደግሞ ትንሣኤ ስለሆነ በጌታ በዓል ላይ ሌላ በዓል አይከበርም እና እሱም ለሌላ ጊዜ ተላለፏል። ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ሐብተ ማርያም⛪️🙏🏾 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ ✥ @habtemaryam26 ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Show all...
ሐብተማርያም 🙏

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!! የዚህ ቻናል ዋና አላማ መዝሙራት እየተለቀቁ እንድናጠናበት እና የወጣቱን የመዝሙር እውቀት መጨመር ነው!!! የደቂቀ አቡነ ሐብተ ማርያም መንፈሳዊ ማሕበር Contact us at: @Elchapo_ET

👍 7