cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Huruta Fellowship official™

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
[ክፍል 1] የሚለውጥ ብርሃን || በአገልጋይ ታምራት ገብሬ [part 1] Changing Light Amharic Teaching With Tamrat gebre

ሠላም የዚህ ቻናል ቤተሰዎች በመጀመሪያ እንኳን ወደ እዚህ ቻናል በሰላም መጣችሁ:: በቤተክርስቲያናችን የሚካሄዱ ፕሮግራሞችን በዚህ ቻናል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በመቀጠል ስለ ቤተ-ክርስቲያናችን አመሰራረት እና አመጣጥ ማወቅ ለምትፈልጉ ከታች አጠር ተደርጎ የተጻፈውን ጹሁፍ እንድታነቡ በጌታ ፍቅር እንጋብዞታለን:: የቤተ-ክርስቲያናችን ቋሚ ፕሮግራሞች • ዘወትር እሁድ ከ03:30 - 06:00 ድረስ የአምልኮ እና የአንድነት ጊዜ • ዘወትር ማክሰኞ ከ10:30 - 02:30 ድረስ የትምህርት እና የሀይል ጊዜ • ዘወትር እሁድ ከ10:30 - 01:30 ድረስ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት እና የፀሎት ጊዜ • ዘወትር አርብ ከ03:30 - 07:30 ድረስ የፀሎት እና የፈውስ ጊዜ • የወሩ መጨረሻ እሁድ የጌታ ራት • የወሩ መጨረሻ ሳምንት የፆምና የፀሎት ሣምንት • ዘወትር ማለዳ ከ12:00 ጀምሮ የማለዳ ፀሎት በእነዚህ ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት ፀጋን እንዲካፈሉ በጌታ ፍቅር እንጋብዞታለን:: ባሉበት ቦታ ሆነው የፀሎት አገልግሎት ለማግኘት በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች መጠቀም የምትችሉ መሆኑንን እንገልፃለን:: +251921295181 +251900623469 አስተያየት ወይንም ሀሳብ ካሎት በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ሊያደርሱን ይችላሉ +251-114432284 ስለ ቤተ-ክርስቲያኒቱ የኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ ወንድማማች ቤ/ክ የሣሪስ አጥቢያ ጎፋ ከነበረችው ከመጀመሪያ አጥቢያ ለአባላቱ በቦታ ርቀት እና ህብረትን ከማጠናከር አንፃር እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ሰኔ 21 1984ዓ.ም ፍቃድን በማግኘት በሣሪስ ተመሠረተች፡፡ በዚህ መሠረት ሐምሌ 1 1984 ዓ.ም የማምለኪያ ቦታን በመከራየት 30 የሚሆኑ አባላትን በመያዝ የመጀመሪያውን የአምልኮ ፕሮግራም እሁድ ሐምሌ 5 1984 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ በነበረውም የአምልኮ ጊዜ በወንድም ላቀው ተሰማ የእግዚአብሔር ቃል የተሠበከ ሲሆን በተጨማሪም የሽማግሌዎች ቦርድን በመወከል ወንድም በዛብህ በልሁ የሳሪስ አጥቢያ ተብላ እንድትጠራ እንደተወሰነ ገልፀው ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመቀጠልም እግዚአብሔር በሰጠው ራዕይ መሠረት አገልግሎቱ እየቀጠለ እና የአባላቱም ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የቦታ ለውጥ ለመደረግ ተወሰነ፡፡ በዚህ መሠረት በቁጥር መቶ(100) የሚሆኑ አባላትን በመያዝ በ1990 ዓ.ም የራሱዋን ቦታ በማግኘት አዲስ የማምለኪያ ቦታ ልትሰራ ችላለች፡፡ አሁንም በእግዚአብሔር ፍቃድና ቤተ-ክርስቲያን በተሰጣት ፀጋ መሠረት በዚሁ 480 ካ.ሜ በሚያህል በራሱዋ ቦታ ላይ አምስት መቶ ስልሣ(560) የሚያህሉ አባላትን በመያዝ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሠጣትን ሀላፊነት እየተወጣችና እየፈፀመች ትገኛለች፡፡ የጠቅላላ አባላት ቁጥር 540 ወንድ፡-175 ሴት፡-365 The Present Saris Branch of ECBC had been found in Gofa area until sene 21-1989 E.c. Due to some factors such like un suitableness of the area and so as to consolidate unity, The change in location become crucial hence, the current branch found around saris was established hamlea 5 1984 e.c hence the current branch found around saris was planted following successful travel to attain the required license in the same year. If the end of course of diligence to solve those factors, It was possible to launch the 1st day the Sunday weekly program in 5 hamlea 1984. On the starting day , the word of God was preached by M.r Lakew Tessema. And M.r Bezabeh belihu Who was from ECBC Board, the verification of the name of the church to be “Saris Branch” and some other derails of ECBC. Following that based on the vision, which have been Sourced from God the service continued and was why change in location was essence. Thanks to lord; since the church, with 100 members was able to attain a new 480m2 place, with no rent, load to construct its own shelter. Laying on the will and Grace of God the church is still found, with 540 members performing its responsibility given from God. #Ethiopian_Protestant_teaching #Tamrat_Gebre #Amharic_teaching

Show all...
የሮሜ መልዕክት ጥናት መግቢያ ክፍል 1

Evangelist Yared Tilahun: Introduction to the Book of Romans - Part 1

በሁሩታ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የተዘጋጀ የፊልጵስዮስ መፅሀፍ ማጥኒያ ወረቀት ስለተዘጋጀ እንድትጠቀሙበት በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን!!!!!
Show all...
ሰላም ውድ የፌሎ ልጆች በመጀመሪያ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ እያልን ሰኞ በ2/5/14 ዓ.ም ልዩ የገና በዓል ፕሮግራም ከቀኑ 9:30 ሰአት ጀምሮ ስለተዘጋጀ እንድትገኙ እንጠይቃለን፡፡ በእለቱም - የፀሎት - የአምልኮ - የአርት - የቃልና ሌሎች ፕሮግራሞችም ስለተዘጋጁ እንድትገኙ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።
Show all...
የልደቱን ባለቤት የሚመለከት ነገር እያደረግን ፣ የልደቱን ጌታ እናክብር። https://telegra.ph/የማን-ልደት-ነው-10-23-2
Show all...
የማን ልደት ነው?

(ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ)/ መንፈሳዊ መጽሐፍት / መንፈሳዊ ወግ / መንፈሳዊ ግጥም ሚሚዬ ልደቷ እየተቃረበ መምጣቱ ተደጋግሞ ተነግሯታል። የዘንድሮዉ ለየት ባለ ሁኔታ በትልቅ ድግስ እንደሚከበርላት ስለተነገራት ደስታዋ ወሰን አልነበረዉም። ወሬዋም አሳቧም እርሱዉ ሆኗል። ቤተሰብም ዝግጅቱን አጧጡፎታል። እንዳይደርስ የለም ከብዙ ጥበቃ በኋላ ‘የሚሚዬ ልደት’ ቀን ደረሰ! በማለዳ የቀሰቀሳት የዝግጅቱ ግርግር ሲሆን ይህ ሁሉ ለእርሷ መሆኑ ገርሟት በደስታ ከአልጋዋ ዘልላ ወረደች። እኩለ-ቀን ሲሆን ቤቱና ግቢዉ በታዳሚዉ ተሞላ። ፈንጠዝያዉ ቀጠለ፡- ይበላል፣ ይጠጣል፣ ይጨፈራል፣ ይሰከራል፣ ይሳቃል። በፈንጠዝያው መጨረሻ ግን ‘የሚሚዬ ልደት’ ማጠቃለያ ኬክ መቁረስ በመሆኑ አመሻሹ ላይ የልደቱ ኬክ ሊቆረስ ተዘጋጀ። ሆኖም ግን በዚህ ወሳኝ ጊዜ ሁሉንም ሰዉ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ተፈጠረ። ኬኩን ቆራሿ ሚሚዬ በአካባቢዉ ስትፈለግ ልትገኝ አልቻለችም። የሚያስገርመዉ ነገር በግርግሩ መሃል ባለልደቷ ለካ ተረስታ ነበር። ከጠዋት ጀምሮ ያስታወሳትም ያያትም ሰዉ አልነበረም። አሁን ግን ከመኝታ ቤቷ እስከሰፈር ድረስ ፍለጋዉ ቀጠለ። ከብዙ ዉጣ ዉረድ ብላ ባለልደቷ ሚሚ ሰፈር ውስጥ ከሌሎች ልጆች ጋር እየተጫወተች ተገኘች። እንደዋና ባለጉዳይ ወግ ያለዉ ልብስ ያለበሳት እንኯ አልነበረም፤ የለበሰቻትም የሌሊት ልብስ አቧራ ለብሳለች። የሚሚዬ ወላጆች በቁጣ ተሞልተዉ “በልደትሽ ቀን አዋረድሽን!” የሚል የጩዀት ዝናብ ያወርዱባት ጀመር። ልጃቸዉ ያቀረበችዉን ብርቱ ጥያቄ ግን የሚመልሱበት የሞራል ብቃት አልነበራቸዉም። የልጅ ዓይኖቿን ወደላይ እቅንታ እየተመለከተች፡- “እኔኮ ልደቱ የእኔ መስሎኝ ጠዋት በደስታ ነበር የነቃሁት። ትኩረት የሚሰጠኝና የሚያለብሰኝ ከማጣቴም በላይ የምታደርጉትን ሁሉ ዝም ብዬ ስመለከት ልደቱ የእናንተ መስሎኝ ነዉ ለመጫወት…

ፊልጵስዩስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ ⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ ¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
Show all...
“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” — ኢሳይያስ 9፥6
Show all...
ሁላችንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን በማወቅ ራሳችንን " እግዚአብሔርን የሚያስከብር ህይወት እየኖርኩ ነው ??" ብለን በመጠየቅ ክርስቶስን ወደ መምሰል እንደግ !!!! Spiritual Education Office Fellow!!!!
Show all...
ሮሜ 12 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። ² የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
Show all...