cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Kingdom Christian Media

ትላንትን ለዛሬአችን ዛሬን ለነጋችን ነገን ለዘላለማችን !! በኢትዮጵያ የክርስቲያኑ ማህበረሰብ መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት በተገቢ ሁኔታ ለመሙላት አላማ አድርጎ የተነሳ አገልግሎት ነው።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
529
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#አዲስ ምዕራፍ ! #New Beginning ! የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዓሊ እንኳን ደስ አሎት እያልን መልካም የስራ ዘመን ይሆንሎ ዘንድ እንመኛለን !!! Kingdom Christian Media _______________ አብራችሁን ተጓዙ ‼️‼️ https://t.me/KingdomChristianMedia https://t.me/KingdomChristianMedia https://t.me/KingdomChristianMedia ⚠️ያግኙን = @KCMcrew @KCMcrew @KCMcrew
Show all...

#Kingdom_christian_media በኢትዮጵያ የክርስቲያኑ ማህበረሰብ መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት በተገቢ ሁኔታ ለመሙላት አላማ አድርጎ የተነሳ አገልግሎት ነው ። _______ ከወገንተኝነት በፀዳ መልኩ ወደናንተ የተከበራቹ ተከታታዮቻችን መረጃዎች በብቁ ሁኔታ ለማድረስ እንተጋለን። _______ የትላንት የቤተ ክርስቲያን ታሪክን ለዛሬ እንድንጠቀም የዛሬ ተግባራችንን ለነገ እንድናፀና ነገን ለዘላለም እንድንሰዋ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ህይወታችንን ሊያሳድጉ እና ሊያበረታቱን የሚችሉ መረጃዎችን በጥራት ለማቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰን ወደናንተ መተናል። ______ #ዜናዎች_በጠራ_አቀራረብ #የበሰሉ_Documentary's _______ ከያለንበት፣ በያለንበት ሆነን ወንጌልን በእንድ ልብ አብረን እናፍጥን !!! ________ አብራችሁን ተጓዙ ‼️‼️ https://t.me/KingdomChristianMedia https://t.me/KingdomChristianMedia https://t.me/KingdomChristianMedia ________ ⚠️ያግኙን = @KCMcrew
Show all...

#ሰላም_ሰላም ✋🤚 ዘንድሮ ወደ #ወልቂጤ _ዩኒቨርስቲ የተመደባቹ አዲስ ተማሪዎች #እንኳን_ወደ_ወልቂጤ_ዩኒቨርስቲ_ተቀላቀላችሁ እያልን የመግቢያ ቀናችሁ ሰኔ 28&29 መሆኑን አውቃቹ እንድትዘጋጁ እያሳወቅን እኛ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት መሪዎች እና ተማሪዎች እናንተን ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማንኛውም መረጃ በነዚህ ስልኮች በመደወል ስለ ህብረታችን እና ስለ ግቢው መረጃ መውሰድ ትችላላችሁ። #ወልቂጤ_ዩኒቨርስቲ ለደረሳቸው ሁሉ ይህ መረጃ እንዲደርሳቸው share አድርጉ 〽️WKU Fellowship leaders(main campus) 📱0932533711 #frew Telegram- @OperationEzra 📱0941226894 #Dibora Telegram- @Diiborah 📱0934944167 #kaleb Telegram- @Calietb 📱0934285545 #bereket 📱0935537153 #ephrem 📳Facebook -Wolkite University Evangelical Christian Student Fellowship 🔗Link - https://m.facebook.com/Wolkite-University-Evangelical-Christian-Student-Fellowship-725291340838797/?ref=opera_speed_dial&_rdr #This_is_our_Fellowship -------------------------- #የመንግስቱን_እሴቶች_መኖር #Living_the_kingdom_values @wkuevacsf @wkuevacsf
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

የኢትዮጵያ ቃለ ህይውት ቤተ ክርስቲያን አስቸኳይ የጸሎት ጥሪ አቅርባለች
Show all...
በሊባኖስ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ! (የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄ/ፅ/ቤት ቤይሩት - ሊባኖስ) በቤይሩት ወደብ ዛሬ የተከሰተው ፍንዳታ ጋር ተያይዞ እስከ አሁን ወደ 10 የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ሪፖርት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ፍንዳታው በተከሰተበት አካባቢ መንገዶች እና ህንጻዎች የፈራረሱ ሲሆን ከፍንዳታው እስከ በ10 ኪሎሜትር ርቀት ደግሞ ብዙ ህንጻዎች መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በመሆኑም ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ዜጎች በተቻለ መጠን በቤታችሁ እንድትቆዩ ይመከራል ፤ ከቤት መውጣት የግድ ከሆነም ከቤት ከመውጣታችሁ በፊት መረጃዎችን እንድታጣሩና ጥንቃቄ እንድታደርጉ፤ እንዲሁም በሚከተሉት መልኩ ራሳችሁን እንድትጠብቁ ቆንስላ ጽ/ቤቱ ያሳስባል ፡- 1. ፍንዳታው ከተከሰተበት አካባቢ ራሳችሁን እንድትጠብቁና እንድትርቁ፣ 2. የአገሪቱን የዜና አውታሮች እንድትከታተሉ፣ መረጃዎችን እንድትለዋወጡ፤ 3. ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መግለጫዎችን እንድትከታተሉና እንድትተገብሩ፤ 4. በተቻለ መጠን ከመኖሪያ ቤታችሁ አካባቢ እንድትቆዩ ወይም ብዙ እንዳትርቁ፤ 5. ከቤት ስትወጡ የሞባይል ስልኮቻችሁን ቻርጅ እንድታደርጉ ይመክራል፤ ከዚህ ጋር ለተያያዙ ለድንገተኛ እና አስቸኳይ ጉዳዮች ብቻ በስልክ ቁጥሮች 71463074 ወይም 70696193 ወይም 81952182 ይደውሉ፡፡ ፈጣሪ ከሁላችን ጋር ይሁን፣ ይጠብቃችሁም! #SHARE #ሼር
Show all...
​ዜና ክርስቲያን 👇👇👇👇👇 የኢየሱስ ድንቅ ስራ አለም አቀፍ ቤ/ክ መስራች እና ባለ ራዕይ ሐዋሪያው እስራኤል ዳንሳ በየካቲት 16፣ 2012 ዓም የወንጌል አማኝ አገልጋዮችን በመሰብሰብ የይቅርታና የጉብኝት ጊዜን በማዘጋጀት "ቃሉን እማራለሁ፣ ዘይት ሆነ ማንኛውም ነገር ከዚህ በኋላ በየትኛውም በ JW ቤተክርስትያን በፍፁም አይሸጥም። የኢትዮጲያ እና የኤርትራ ቅዱሳን ስለ ወንጌል ብዬ እናንተን ያሰናከልኳችሁ ነገር ይቅርታ አድርጉልኝ? ማናቸውንም ነገር ስለ ወንጌል ብዬ ነው ያደረኩት። እኔ ፍፁም አይደለሁም የሰው ልጅ ነኝ፤ ጥፋቴን አምናለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ?" ብሎ በጉባኤው በፊት ተንበርክኮ የኢትዮጲያ እና የኤርትራ ቅዱሳንን ይቅርታ ጠይቋል። ምንጭ፦ክርስቲያን ፖስት ለፈጣን ክርስቲያናዊ ዜና እና መረጃ በተጨማሪምለአስተማሪ ፁሁፎች 👇👇👇👇👇 @crowntalk 👇👇👇👇👇 @Aklilcrown ልታገኙን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን
Show all...
ከመልካም ንግግሮች ዓምድ 👇👇👇👇 ከዘማሪ በረከት ተስፋዬ 👇👇👇👇 ትኩረት ላዳዲስ ነፍሳት 👇👇👇👇 አሰላ ከታዪ የወንጌል ከዋክብቶች አንዱ የሆነው ፖስተር ታዬ ታከለ (ጋሽ ታዬ) ስለ ወንጌል መገረፍ፣ መገደል፣ መደብደብ፣ መታሰር እና ኢየሱስ ብሎ መስበክ ወንጀል በነበረበት ዘመን ጋሽ ታዬ የኢየሱስ ስም በመጥራት የታመኑ የእምነት አባት ነበሩ። ጋሽ ታዬ በልጅነቴ በአሰላ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት ያስተማሩኝ የእግዚአብሔር ቃል ልረሳዉ አልችልም። ታዲያ ጋሼ ታዬ ሲያስተምሩን እኔ በጣም አስቸጋሪ ልጅ ነበርኩ። ነገር ግን ጋሼ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ከሚመልሱ ጎበዝ ተማሪ አንዱ እኔ ነበርኩ ስለዚህ ይወዱኝ ነበር። ጋሽ ታዬ ግራ ገባቸዉና "በርከት የተባለዉ ልጅ ህፃናቱን እንዳላስተምር በጣም ይረብሸኞል እንዳላባርረዉ ጉብዝናዉና ችሎታዉ ያሳሳኞል። ምን አይነት ጉድ ነው?"አሉና ያደረጉት ነገር አንድ ነዉ እሱም ቅፅል ስም ማውጣት ነበር። "ጉዱ ካሳ" ብለዉ አወጡልኝ። ከዚያም የአሰላ ከተማ ቅዱሳን መንገድ ላይ ሲያገኙኝ "ጉዱ ጉዱ"ይሉኝ ጀመር። ጉዱ የአሰላ ስሜ ሆኖ ቀረ። አሁን ላለዉበት መንፈሳዊ ህይወቴ ከወላጅ አባቴ ቀጥሎ ትልቅ ስፍራ አላቸው። ጋሽ ታዬ እጅግ በጣም ጌታን የሚወዱና የሚፈሩ አባት ነበሩ። በአገልግሎት እና በወንጌል ስራ የማይቀልዱ በዚህ ጉዳይ ኮስታራ ነበሩ። እኔ ከአሰላ ከተማ የወጣዉት 1992 አ/ም የ11 አመት ልጅ ሆኜ ነበር። ቤተሰቦቼን ለመጠየቅ አሰላ ስመላለስ ሳገኛቸዉ ያበረታቱኝም ነበር። ከሰባት አመት በፊት ጋሼ ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ስልኬ ላይ ደወሉልኝ እንዲ አሉኝ ጋሽ ታዬ ጉዱ እኔ አቤት ማን ልበል ጋሽ ታዬ እኔ ነኝ ታዬ ነኝ እኔ እንዴ ጋሽ ታዬ አባቴ ደና ነህ አባቴ ጋሽ ታዬ ደና ነኝ ንተ እንዴት ነህ የአክብሮት ሰላምታዬን እና ፍቅሬን እየገለፅኩላቸዉ መደወላቸዉ በጣም ደነቀኝ አና እንዲ አልኩዋቸዉ እኔ እና ጋሽ ታዬ ምን ልታዘዝ ? አልኩ የሚሉኝን ለመስማት በመጓጓት ጋሽ ታዬ እኔ ምንም አላዝህም ነገር ግን የምነግርህ ነገር አለኝ በረከት ምን መሰለህ የጌታ መምጫዉ ጌዜ ቀርቧል። ሰአቱ ደርሷል እኔ ስራዬን ጨርሻለዉ። ነገር ግን በጣም ብዙ ትራክቶች አሳትሜያለዉ ነገ አውቶቢስ ተራ አስጭኜ ወደ አሰላ እሔዳለዉ ከዛም ወደገጠር ወንጌል ስርጭት እወጣለዉ ሩጫዉን ጨርሻለዉ። ልጄ በረከት እባክህን የጌታን ስራ አደራ ለጓደኞችህም ንገራቸዉ። አሉኝ ከዛም ቻዉ ተባብለን ስልኩ ተዘጋ። እኔ ግን ግራ ገባኝ አንደኛ ጋሽ ታዬ ደዉለዉልኝ አያዉቁም ሁለተኛ ሩጫዉን ጨርሻለዉ የምትለዋ ሀረግ ግራ አጋባችኝ። ነገር ግን ይህንን ባወሩኝ በሶስተኛዉ ቀን ጋሽ ታዬ ወደ ጌታ ሄዱ ተብሎ ተነገረኝ በጣም ደነገጥኩ የነገሩኝን ቃላት ማሰላሰል ጀመሩርኩ። ከሁሉ ነገር ልቤን የነካኝ ወደ ጌታ ከመኼዳቸዉ አራት ወይም አምስት ቀን በፊት ያሳተሟት ትራክት ትደንቀኝ ነበር። የጋሽ ታዬ የመጨረሻ ስራ የነበረችዉ ትራክት ስንት ሰዉ ጋር ገብታ ይሆን ስንት ሰዉ አድና ይሆን?እሱን ለስራዉ ባለቤት ለሸላሚዉ ጌታ ተዉኩለት። ጋሽ ታዬ ወደ ጌታ እንደሚሄድ እንዳወቁት ከንግግራቸዉ ያስታዉቅ ነበር። ታዲያ እኚህ አባት ወደጌታ መሄዴ ነዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም እስከመጨረሻዉ ድረስ ለጌታቸዉና ለአዳዳስ ነፍሳት ያላዉን ፍቅር አሳይተዉ አልፈዋል። በቤተ ክርስቲያናችን የማትረሳ አንድ የአምልኮ ስርአት አለች እሷም የመባና የፍቅር ስጦታዋ ጌዜ ናት። ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስለሆነ የስርአቱን መርሀ ግብር ጠንቅቄ አውቃለዉ የመባና የፍቅር ስጦታዋ ጊዜዋን የረሳ የቤተ ክርስቲያን መሪ አላዉቅም። የነፋሳትን ጥሪ ሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያናት መሪዎች በጣት ሚቆጠሩ ናቸዉ። ለአገልግሎት ስዘዋወር በአብዛኛዎቹ ቤተ ክርስቲያናት አዳዲስ ነብሳት ሲጋብዙ (ሲጠሩ) አላይም። በጣም የሚገርማቹ አንዳንዶቹ ጋር ምን አየዉ መሰላቹ የመድረክ መሪዉ እስኪ ከኢትዮጵያ ውጪ የመጣቹ እጃችሁን አዉጡ ይልና ሰዎች ይቆማሉ ከዛም የመድረክ መሪዉ እቱ ከየት ወንድም ከየት ነዉ?እያለ ይጠይቃል እነሱም ከአሜሪካ፣ ከካናዳ፣ ከአዉሮፖ እና ወዘተ እያለ በየተራ ካስጨበጨበን በዃላ እስኪ ደሞ ዛሬ ገና ወደ ኢየሱስ የመጣቹ ጌታን የማታዉቁ ሳይል ፕሮግራሙ ያልቃል። የአዳዲስ ነፍሳት ፍቅር የሌላቹ ቤተ ቤተክርስቲያናት እባካቹ ተመለሱ። የእግዚአብሔር የልብ ትርታዉ አንድ ግለሰብ ነዉ። ወንጌል ተሰብኮ ነፍሳት አለመጥራት ማለት ሰርግ ቤት ሰዉ ጠርቶ ምግብ አንሰጥም እንደማለት ነዉ። ትኩረት ላዳዲስ ነፍሳት አበቃዉ ዘማሪ በርከት ተስፋዬ ለፈጣን ክርስቲያናዊ ዜና እና መረጃ በተጨማሪምለአስተማሪ ፁሁፎች 👇👇👇👇👇 @crowntalk 👇👇👇👇👇 @Aklilcrown ልታገኙን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን
Show all...

ዜና ክርስቲያን 👇👇👇👇 ዓለም አቀፋዊ የመጋቢያን ሥልጠና ማዕከል ከኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ያዘጋጀው ሥልጠና በቤተ ክርስቲያኒቱ የኩሪፍቱ ማዕከል ከየካቲት 1 - የካቲት 5 2012 ዓ.ም ባሉት ቀናት ተካሄደ፡፡ በዚሁ ሥልጠና የሦስተኛ ዓመት መርሃ ግብር ላይ መጋቢ አል እና ሜሪ፣ መጋቢ ፒጄ እና ሪሼል የተባሉ ከአሜሪካን አገር የመጡ አገልጋዮች ሥልጠናውን የመሩ ሲሆን ሥልጠናው የወንጌል ተልዕኮ ተኮር ማኅበረሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት በሚል ርዕስ ዙሪያ ተካሂዷል፡፡ በዚህ የሥልጠና መርሃ ግብር የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ሥልጠናውን እንደካፈሉ የሚደረግ ሲሆን በነበሩ መርሃ ግብሮች ላይ አገልጋይ መሪዎች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር መጥተው መሠልጠናቸው ሥልጠናውን የተለየ እና የበለጠ ስኬታማ እንዳደረገው በመርሃ ግብሩ መዝጊያ ላይ ተወስቷል፡፡ ምንጭ;-ethiopian Kale Heywet Church Communication ለፈጣን ክርስቲያናዊ ዜና እና መረጃ በተጨማሪምለአስተማሪ ፁሁፎች 👇👇👇👇👇 @crowntalk 👇👇👇👇👇 @Aklilcrown ልታገኙን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን
Show all...

ዜና ክርሰቲያን 👇👇👇👇 ዘማሪ ዮሐንስ በላይ እና ዘማሪ አቤነዘር በቅርቡ በጋራ የሰሩትን የመዝሙር ቪዲዮ ሊለቁ ነው።ዘማሪ አቤነዘር በቅርቡ ከዘማሪት ኤደን እምሩ ጋራ እንዲሁ በጋራ ደራሽ የሚል የመዝሙር ቪዲዮ መልቀቁ የሚታወስ ነው። ለፈጣን ክርስቲያናዊ ዜና እና መረጃ በተጨማሪምለአስተማሪ ፁሁፎች 👇👇👇👇👇 @crowntalk 👇👇👇👇👇 @Aklilcrown ልታገኙን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን
Show all...