Nibras Tube ~ ኒብራስ ቲዩብ
Open in Telegram
የፈለከዉን ያክል ኑር ሟች ነህ። ያሻሀውን ዉደድ ትለየዋለህ። የፈለከዉን ስራ ትመነዳዋለህ። ጠባቧ ዱንያ ለሙስሊሙ እስር ቤት ናት። አላህ ሰፊዉን ጀነት የምንወርስ ያድርገን። በዚህ ገፅ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ብቻ ይለቀቃሉ። ሼር ማድረግ እንዳይረሳ። ለማንኛውም መረጃዎች እና ጥያቄ በ @NibrasTube ልታገኙኝ ትችላላችሁ።
Show more2 925
Subscribers
No data24 hours
-127 days
-8630 days
Posts Archive
እኛ ሙስሊሞች የማሪያም እና የኢየሱስ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም!!
ወዳጅ ወዳጅን ይወዳል ያከብራል እንጂ አያነውርም አይሳደብም።!እኛ ሙስሊሞች ማሪያምንም ሆነ ኢየሱስን አንድም ቀን ሰድበናቸው አናውቅም።አንሰድባቸውምም። ሀይማኖታችንም በስድብ አያዘንም።
ኢየሱስ የአሏህ መልዕክተኛ ነብይ እንጂ ጌታ አይደለም ማለት በፍፁም ኢየሱስን መስደብ አይደለም።ማሪያም የጌታ እናት አይደለችም ይልቁንስ አሏህ በተዓምሩ ያለ አባት እንዲወለድ ያደረገው የነብዩ ኢየሱስ እናት ናት ማለት በጭራሽ ማሪያምን ማነወር ወይም መስደብ ማለት አይደለም።
በል እንደሁም እኛ ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች የበለጠ ማሪያምንና ኢየሱስን እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን።
ስለምንወዳቸውና ስለምናከብራቸውም ነው እናንተን ክርስቲያኖችን ተዉ ድንበር አትለፉባቸው! አታምልኳቸው።ያልሆኑትን ሆኑ ብላችሁ አትቅጠፉባቸው የምንለው።!
ባለፈው ሰሞን አንድ እፎይ የተባለ ባለጌ ሰው ውዱን ነብያችንን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለምን መሳደቡ ይታወቃል።
በዚህም የተነሳ ሙስሊሞች ይህ ሀይማኖትን ከሀይማኖት ሊያጋጭ የሞከረው ግለሰብ በህግ ተይዞ ተገቢ ፍርድ ማግኘት አለበት በማለታቸው አንዳንድ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይህ ባለጌ ሰው እኛን አይወክልም ብለው ተባብረው ለህግ እንዲቀርብ ማድረግ ሲገባቸው ጭራሽ አደባባይ ወጥተው እኛም እፎይ ነን።ከእፎይ በፊት እኛን ብለው መጮህ ጀመሩ!
ይህም ብቻ አይደለም እነ አሕመዲን ጀበልን፣አቡ ሐይደርንና ሌሎች ኡስታዞችንም ሀይማኖታችንን ተሳድበዋል።ማሪያምን ኢየሱስን ተሳድበዋልና እነሱም ህግ ፊት ቀርበው መጠየቅ አለባቸው ብለውም ተናገሩ።!
ከላይ እንዳልኳችሁ እኛ ሙስሊሞች የማሪያምና የኢየሱስ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም።አይደለም እነዚህን ምርጥ የአሏህ ባሪያ የሆኑትን ማሪያምንና ኢየሱስን ልንሰድብ ቀርቶ ሌላን ነገር እንኳን የሚያመልኩ አማለክቶቻቸውን እንዳንሰድብ የሚከለክል ሀይማኖት ነው ያለን አል-ሐምዱሊሏህ!
አስቡት እንግዲህ አሕመዲን ጀበልና አቡ ሐይደር እነሱ እንደሚሉት ኢየሱስን ተሳድበዋል ከተባለ እንዴት እስከዛሬ ለምን ዝም አሉ?! ያልሆነውን ሆነ ብላችሁ የምትከሱ እውነት ከተሳደቡ እንዴት ዝም ልትሉ ቻላችሁ?!
ሀይማኖታችሁን ማሪያምንና ኢየሱስን መጽሀፍ ቅዱሳችሁን እንደፃፉት ፀሃፊዎቻችሁ መምህሮቻችሁ የበለጠ ማን የተሳደበ አለ?!
ምክንያቱ ይታወቃል ግርግር ለሌባ እንደሚባለው ነው።የእፎይ ጉዳይ ትኩረት እንዳይሰጥና ሌላ አጃንዳ ለመክፈት የታሰበበት ሴራ እንጂ ሌላ አይደለም።
አንዳንዶች ደግሞ የንፅፅር ስራ ሀይማኖታዊ ክርክርም መቆም አለበት ብለውም እየተናገሩ ነው።ጉድ ነው ምን ያለበት ነው ዝላይ አይችልም አሉ።!
ለነገሩ እውነታቸው ነው አሏህን፣ነብያችንንና ኢስላምን በተሳደቡ ለማነወርና ለማንቋሸሽ በሞከሩ ቁጥር ወደ ኢስላም የሚጎርፈው ሰው ቁጥር እየበዛ ነው።አል-ሐምዱሊሏህ!
በዚሁ አጋጣሚ በንፅፅር ዳዕዋ የምትንቀሳቀሱ ወንድሞች፣እህቶች፣ኡስታዞች ትልቅ ጅሃድ ላይ ናችሁና በርቱ በርቱ አሏህ ይጨምርላች እላለሁ።
ንፅፅር ይቅር ካላችሁም ምንም ችግር የለም።ግን አንድ ምክር ልምከራችሁ ክርስቲያን ወገኖች ሆይ! መጽሀፍ ቅዱሳችሁን እያንዳንዱን ክፍል በደንብ አንብቡት።አንዳንድ ቦታ መዝለል አይቻልም።ባይሆን ስታነቡ ያልገባችሁን መምህሮቻችሁን በግልፅ እንዲመልሱላችሁ ጠይቋቸው። ያኔ በራሳችሁ ጊዜ ትሰልማላችሁ ኢንሻአሏህ!
አሁንም ቢሆን ፍትህ ውዱን ነብያችንን የተሳደበውን ወንጀለኛ በውስጣችሁ ከመደበቅ አጋልጣችሁ ለህግ እንዲቀርብ አድርጉ ነው የምንለው።!
ሼር ሼር እያደረጋችሁ!
✍ወንድማችሁ:- አቡ መርየም
የቴሌግራም ቻናል=
👉 t.me/AbuMeryemNeja 👈
"الله أكبر، الله أكبر، الله أكبر، لا إله إلا الله، الله أكبر، الله أكبر، ولله الحمد، الله أكبر كبيرًا، والحمد لله كثيرًا، وسبحان الله بكرة وأصيلًا، لا إله إلا الله وحده، صدق وعده، ونصر عبده، وأعز جنده، وهزم الأحزاب وحده، لا إله إلا الله، والله أكبر."
