cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

EPC- library(TMS ቤተመጻሐፍት )

የሚያነብ ሰው ከመሃይምነት ግርሻት ተላቆ ከሰው ጋር መግባባት ይችላል። አላማችን 1. አንባቢ ትውልድ መፍጠር ፣ 2. የመማር ማስተማር ሒደት የሚደግፉ 👉text መፅሐፎች 👉ልብወለድ መፅሐፎች 👉 ቴክኖሎጂ መፅሐፎች 👉 ሪሰርቾችን 👉የቴክኒክና ሙያ TTLM&OS 👉 ልዩ ልዩ መፅሐፎችን በpdf ማቅረብ ሁሌም ለንባብ ባህል መጎልበት እንተጋለን

Show more
Advertising posts
198Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ችግር! የእምቅ ብቃትህ ብቸኛ መውጫው ቀዳዳ! “ያልገደለኝ ነገር ሁሉ ያጠነክረኛል” ይላል ምንጩ ያልታወቀ የከረመ አባባል፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለማለፍ ፈቃደኛ እስካልሆንክ ድረስ የብቃትህን ጥግ ሳታውቀው ታልፋለህ፡፡ የሰው አቅሙና ብቃቱ የሚወጣው በሚያልፍበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች አሁን ከድሮው ሕይወታቸው የተሻለ ኑሮን እየኖሩና የአሁኑ ዘመን ከበፊቱ በብዙ እጥፍ እየበለጠ እንኳን፣ “ድሮ ቀረ!” ሲሉ የሚደመጡት የበፊቱ አስቸጋሪ ዘመን በጊዜው ፈትኗቸው ቢሆንም እንኳን ተደብቆ የነበረውን እምቅ ብቃታቸውንና ድብቅ ብርታታቸውን እንዳወጣው ያውቃሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ዛሬ የሆኑትን የሆኑት፣ ዛሬ የሚችሉትን የቻሉት፣ ዛሬ የገባቸው ነገር የገባቸው . . . ከእነዚያ ፈታኝ፣ ነገር ግን ድንቅ አመታት የተነሳ እንደሆነ ውስጣቸው ያውቀዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥማቸው የበለጠ እያዳበሩ የሚሄዱት “ችሎታ” ከዚያ ሁኔታ፣ ስፍራ፣ ግንኑነት … የመሸሽን ችሎታ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ግሩም የሆኑ “የሽሽት ባለሞያዎች” ወደመሆን ያድጋሉ፡፡ የስራና የትምህርት ዘርፍ ከበድ ሲላቸው እየለወጡ ውስጣቸው ግን ሳይለወጥ፣ የትዳር ሕይወት ችግር ይዞ ሲመጣ የትዳር ጓደኛን እየቀየሩ ባሪያቸው ግን ሳይቀየር፣ መንደር፣ ሰፈርና ሃገር አልመች ሲላቸው እየለወጡ አመለካከታቸው ግን ሳይለወጥ እንደነበሩ ይኖራሉ፡፡ ምን ያህል አስገራሚ ብቃት እንዳለህ ማንም ሰው አያውቀውም፣ አንተው ራስህ እንኳን በቅጡ አታውቀውም፡፡ ይህንን ብቃትህን የሚያወጣው ጉዳይ “ችግር” ይባላል፡፡ ይህ ችግር የሚባል ነገር በሁለት ይከፈላል፣ 1) አስፈላጊ ችግርና፣ 2) አላስፈላጊ ችግር፡፡ አስፈላጊው ችግር የተለመደውን የሕይወት መስክ ይዘህ ስትጓዝ በተመሳሳይ ሁኔታ የሚያልፍ ሰው ሁሉ የሚጋራው ችግር ነው፡፡ ይህንን ችግር ከመሸሽ ይልቅ ስትጋፈጠው የውስጥህ ብቁ ማንነት ይወጣል፡፡ አላስፈላጊ ችግር በእኛው የጥበብ ጉድለትና የተሳሳተ ውሳኔ የሚመጣው አይነት ችግር ነው፡፡ ይህን ችግር ሽሸው፣ እንዳይከሰትም የምትችለውን ሁሉ አድርግ፡፡ ሆኖም፣ አንዴ ከተከሰተ ግን ከስህተትህ ተማር፣ ውጤቱንም ተጋፈጥ እንጂ ለመደባበቅና ለመሸሽ አትሞክር፡፡    ዛሬ የምታልፍበት ችግር ነገ በብዙ ብቃት የምትወጣበት አስገራሚ እድል እንጂ ዛሬ የምትደክምበት ሁኔታ እንዲሆን አትፍቀድለት፡፡
Show all...
Cut off point by Ahmed (2008) Step #1: Compute the overall mean score for the items of that variable of interest Step #2: Make cutoff points using a calculator (Maximum- Minimum / n). How? In case of a five-point Likert scale, you may, for example, have assigned the value (1) for Strongly Disagree, (2) Slightly Disagree, (3) Neutral, (4) Slightly Agree, (5) Strongly Agree. So in order to make cutoff points, you've to do this simple math, as per the formula stated above: (5-1/3). Upon calculation you will get this value (1.33), right! This is the interval value. * "Maximum" refers to the highest score of the given Likert scale (5, in our example) * "Minimum" refers to the lowest (1) * "n" refers to the number of CATEGORIES you intend to create Step #3: Do the math for the three categories (Low, Mid & High). How? Just add up the score of your interval value to the three category, as in the following: Low (1 - 2.339), Mid (2.34 - 3.669) High (3.67 - 5) Step #4: Interpret the results according to the above assigned values.
Show all...
በሥራ ቃለ-መጠይቅ / Interview/ ወቅት አብዛኛው ኩባንያዎች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ላስተዋውቃችሁ !! የክረምት መዳረሻዎች እና ወራቶች ላይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የተማረ የሰው ኃይል ለሕዝብ የሚያስረክቡበት ነው። ዘመኑ የውድድር መንፈስ የተጠናወተው ነውና ራስን ማዘጋጀት የብልህ ሰው መለያ ነው። በሥራ ቃለ መጠይቅ /Interview/ ላይ በብዛት የሚጠይቁ ጥያቄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል። እነሱም:- 1ኛ. ራስዎን ያስተዋውቁን? (Please introduce yourself to know who you are?) ይህ ጥያቄ ቀላል ቢመስልም፤ ብዙዎች ገና ከጅምሩ ስህተት የሚሰሩበት ነው። ብዙዎች የሕይወት ታሪካቸውን ያወራሉ። የጥያቄው አይን ግን በሥራ (በትምህርት) ሕይወት ላይ ስለቆያችሁበት ማንነት፣ የት/ት ደረጃ፣ የስራ ልምድ ካላችሁ ስለ ልምዳችሁ፣ ስላስመዘገባችሁት እና ስለ ሰራችሁት ጥሩ ሥራዎች፣ ጀማሪ ተቀጣሪ ከሆናችሁ ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ስለ ነበራችሁ መልካም እንቅስቃሴዎች ወይም ስለ ሰራችሁት የመመረቂያ ጥናት (Research) ወይም ፕሮጀክት በመዘርዘር እራሳችሁን ማስተዋወቅ ነው። በንግግራችሁ ወቅት ለጠያቂው የመጀመሪያ ምርጫው እንድትሆኑ ጠቃሚ ነገሮች ላይ ትኩረት አድርጉ። የዘር ሀረግ እየቆጠሩ፣ በትውልድ ቦታ እየከለላችሁ ጥያቄውን እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ። ለዚያውም በዚህች ጎጠኛ ዓለም ላይ ተሳታፊ ሆኖ ጎጥ መቁጠር ተገቢ አይደለም። 2ኛ. ስለዚህ የሥራ ማስታወቂያ እንዴት መረጃ አገኙ? (How did you got an information about this vacancy?) ይኸም በተደጋጋሚ ይጠየቃል። የዚህ ጥያቄ ዓላማው ድርጅቱን ምን ያክል እንደምትወዱትና እንደምትፈልጉት ለማወቅም ጭምር ነው። በመሆኑም መልሳችሁ "የድርጅቱን ድረገጽ እከታተል ስለነበር ከዛ ላይ አገኘው"፣ "ከጋዜጣ ላይ"፣ "ከማስታወቂያ ቦርድ ላይ" በማለት በትክክል መልሱ። ለመልሶቻችሁ ውበት ብላችሁ የሌለ ነገር ከጠቀሳችሁ ውሸታም ያስብላችኋል። 3ኛ. ስለ መስሪያ ቤታችን ምን ያውቃሉ? (Have any knowhow about this organization?) ለቃለ መጠይቅ ፈተና ከመቅረባችሁ በፊት ስለ መስሪያ ቤቱ የምስረታ ዘመን፣ ተልዕኮውን (Mission)፣ አላማውን እና ስፋቱን (Scope and Objective)፣ ራዕዩን (Vision)፣ የምርት ውጤት (Final Output) አስቀድመው ለማወቅ እና እርሰዎ ለአላማው መሳካት የሚያደርጉትነ አስተዋጽኦ ለማካተት ይሞክሩ። ይህንን መረጃ ከድረገጽ እና ከተለጠፉ ታፔላዎች ማግኘት ይቻላል። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ለሥራው ትኩረት መስጠትን ያመለክታል። 4ኛ. ለምን እዚህ መቀጠር ፈለጉ? (Why did you want to be employee in this company?) በምንም ምክንያት "ሥራ ዕድል ስለፈጠረልኝ፣ ደሞዝተኛ ለመሆን፣ ሥራ ላለማጣት" የሚሉ ነገሮችን እንዳትመልሱ። በምትኩ አግባብነት ያላቸውን መልሶች ለምሳሌ ያህል ቀርበዋል። እነሱም:- ~ "በመስሪያ ቤቱ ባሉት ዘርፍ/ዘርፎች ላይ ብሳተፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደማበረክት ስላመንኩኝ" ~ "መስሪያ ቤቱ የላቀ እንቅስቃሴዎችን እያስመዘገበ በመሆኑ እኔም የበኩሌን ድርሻ በመወጣት ሀገሬን እና መስሪያ ቤቱን ማሳደግ ስለምፈልግ፡፡" ~ መስሪያ ቤት የሚሰጠውን አገልግሎት በመጥቀስ "እንደዚህ ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎች ላይ መሆን ታላቅ እርካታን ስለሚሰጠኝ።" ብለው መልሱ። 5ኛ. ለመስሪያ ቤቱ ምን አይነት አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ብለው ያምናሉ? (If you will be employed, what role do you believe that you may pay for company?) በመስሪያ ቤቱ የምሰራ ከሆንኩ፤ በቡድን እንቅስቃሴ ውስጥ የቡድን አንድነትን ማጠናከር (Team Work)፣ የክህሎት ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን ማመቻቸት (Skill Building Trainings)፣ የሥራ ልውውጥ ማድረግ (Experience Sharing)፣ አዳዲስ ጥናቶችን ከመደበኛ ሥራዬ ጎን ለጎን በመስራት (Researches and Projects)፣ ደንበኞችን በአክብሮት እና በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ (Respect and Legality for customers) እና መሰል ነገሮችን በማድረግ ለመስሪያ ቤቱ እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደምታበረክቱ ተናገሩ። 6ኛ. ጠንካራ ጎኖዎ ምን ምንድናቸው? (What are your strength?) የምትፈልጉትን ምኞት ሳይሆን እውነተኛ ጥንካሬዎቻችሁን መስክሩ። ከምትወዳደሩበት የሥራ መደብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሙያዊ ጥንካሬዎችዎን ብታስቀድሙ የተሻለ ነው ፡፡ 7ኛ. የዚህን ድርጅት ራዕይ እና ተልእኮ ያውቃሉ? (What are vision and missions of this organization?) ይህን ጥያቄ ለመመለስ አስቀድሞ መዘጋጀት ይጠበቅባችኋል። እየተወዳደራችሁበት ያለውን የድርጅቱን ራዕይ፣ ዓላማ እና ተልእኮ አስቀድማችሁ በሚገባ ማወቅ አለባችሁ። ይህንን መረጃ በድርጅቱ ድረገጽ፣ በተሰቀሉ ባነሮች ላይ፣ በታተሙ በራሪ ወረቀቶች ላይ፣ በድርጅቱ የውስጥ ግድግዳዎች ላይ ስለሚገኙ ፈጽሞ ሳታውቁ እንዳትገቡ ይመከራል። ምንም መረጃ ባታገኙ እንኳን ገና ራዕይ እና ተልዕኮ ያልረቀቀላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በራስዎ ከመመለስ ይልቅ የቅርብ ሰዎችን አፈላልጎ መጠየቅ ተገቢ ነው። 8ኛ. ስለ ድርጅቱ ምን ምን ያውቃሉ? (What knowhows do you have about this organization?) እያንዳንዱ ድርጊት የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። ይህም ጥያቄ ድርጅቱን ለማወቅ እና የድርጅቱ ሰራተኛ ለመሆን ካላችሁ ጉጉት አንጻር ምን ያክል እንደተጓዛችሁ የሚያመላክት ስለሆነ ሰፋ ያለ መረጃዎችን በማሰባሰብ ምላሽ መስጠት ተገቢ ነው። ለዚህ መልስ ለመስጠት ቢያንስ መቼ እንደተመሰረተ፣ ማን እንደመሰረተው (ባለቤቱ ማን እንደሆነ)፣ የት እና በምን ያክል መነሻ ገንዘብ (Capital) እንደተመሰረተ፣ ስንት ቅርንጫፎች እንዳሉት፣ ዋና መስሪያ ቤቱ የት እንደሆነ፣ ምን ምን አይነት አገልግሎቶች እንደሚሰጥ፣ ምን ያክል የገንዘብ ሃብት እንዳለው፣ ምን ያክል ሰራተኞች እንዳሉት፣ ምን አይነት የእድገት ፍጥነት እንዳለው እና የመሳሰሉትን ማወቅ ይኖርባችኋል። እነዚህን ካወቃችሁ የድርጅቱን ማንነት መግለጽ ትችላላችሁ ማለት ነው። 9ኛ. በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸው መርሆች እና እሴቶች ምን ምን ናቸው? (What are values and principles expected from one organization?) በአብዛኛው እነዚህ ነገሮች፤ ለሁሉም ድርጅቶች ተቀራራቢ የሆነ ይዘት ቢኖራቸውም እንደ ድርጅቱ ባህርይ እና ይዘት ሊለያዩ ስለ ሚችሉ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን እሴቶች እና መርሆች አፈላልጎ ማወቅ ተገቢ ነው። ከእነዚህም ውስጥ ሃቀኝነት (Integrity)፣ የደንበኞች እርካታ (Customer Satisfaction)፣ የሰራተኞች እርካታ (Employees Satisfaction)፣ ታማኝነት (Honesty)፣ የቡድን ወይም የኅብረት ሥራ (Team Work)፣ የህዝብን አደራ መወጣት (Public Trust)፣ ትህትና (Humility)፣ ፈገግተኛ መሆን (Simplicity)፣ አንድነት (Unity)፣ ደስተኛነት (Happiness)፣ ነጻነት (Freedom)፣ ግልጸኝነት (Articulate)፣ ፍቅር ዋና ዋናዎቹ ናቸው። #ሼር_ማድረግ
Show all...