cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Nuniye🥰

Wellcom to my channal Will gate ✨arif tarkoch ✨astemari melktoch ✨meme ✨pic Just JOIN comment in box me @Hayutii

Show more
Advertising posts
499Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

queen ስክራፕ እና የሮዝመሪ ቅባት ስክራፕ የእርድ እና የቡና 150birr ቅባቱ 250 ሙሉ ለሙሉ ተፈጥሮአዊ የሆነ መግዛት ለምትፈልጉ 0984055355 ይደውሉልን free delivery
Show all...
ሻሸመኔ ያላቹይዘዙን
Show all...
wedoch gebuna like adrgulegn🙏
Show all...
<< እብድ ነው ብለው ይሳለቁ ይሆናል። አልያም ከንፈራቸውን መጥተው እዝነት የሚመስል ስሜት መፅውተው ያልፋሉ። ሀሀሀሀ……ምን ተቀየረ? ይኸው ትዝታ የሞለው የጊዜ መጠጥ እየጠጣሁ ነው። ቺርስ! ወቅት ሁሉ ትውስታ፣ ወቅት ሁሉ ትዝታ ሲመሽም ሲነጋ አለሽ እዚህ ቦታ። ሀሀሀሀ…የተለየሺኝ መስሏቸዋል። ይቅርታ አድርጊልኝና መጀመርያ ላይ ከቀደር ጋር ስሟገት እጄ ተሰበረ። ከዛ ወዲህ ሙስበሀ መያዝ አቅቶት ትዝታ ሙሉ ጠርሙስ ጨበጠ። ልቤ እየጋለ ሲያቃጥለኝ ልብሴን አወለቅኩት። ጠሀይ ከትዝታ ስትቀዘቅዝብኝ ኮፍያዬን ጥዬ ጠጉሬን ወደፊት ደፋሁት። መሬቷ እንዳቀፈችሽ ሳውቅ ጫማዬን አሽቀንጥሬ ጣልኩት። አየሽ አይደል እንደ ዛፍ ግንድ በእግሬ ቆንጥጬ የትዝታሽን ማዕድን በመላ አካሌ ሳሰራጨው። ሀሀሀሀ……ትዝታ እየደለቀው ሳቄ በደንብ ይሰማል። እንዴት ነሽ ውዷ? ይኸውልሽ ዱንያ ላይ ሁሉንም ነገር ትቼ ይቺን ወንበር ርስቴ ብዬ ይዣለሁ። ቺርስ! ትዝታ የሞላው የጊዜ መጠጥ እየጠጣሁ ነው። ደግሞ የትዝታ ተንኮል እንጂ አልኮል የለውም አልሰክርም! ሀሀሀሀ…… ደህና ነሻ? ቆይ የሆነ ስንኝ ፅፌልሽ ነበር ላንብብልሽማ። በመጀመርያ እድሉ………ሀሀሀሀ አታስቂኛ። እሺ… …አሁን እንዳታስቂኝ ልጀምር…… የግጥሜ ርዕስ……ሀሀሀሀሀሀሀ …እንዲህ እየሳቅሽብኝማ አላነብም። እንደውም ተዪው…… ስሚኝማ ኒቃብሽን የት ነው ያስቀመጥሽው? እስቲ ስጪኝና ትዝታዬን ልከልልበት! አዪ……ቆይ እንደውም አሁን እንዳታቋርጪኝ ላንብብልሽ…… ቀናት ሁሉ ትናንት፣ ዘመን ሁሉ ድሮ ምኞት ሁሉ ያኔ፣ ነበር ሁሉ አብሮ እኔን የሚቀናኝ መሄድ ኋላ ዞሮ እ……እንዴት ነው ወደድሽው? ሀሀሀሀሀ…ቺርስ! ትዝታ የሞላው የጊዜ መጠጥ እየጠጣሁ ነው። ደግሞ የትዝታ ተንኮል እንጂ አልኮል የለውም አልሰከርኩም። >> (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @Venuee13
Show all...
“በገንዘቦቻችሁ እና በነፍሶቻችሁ በርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከነዚያም ከናንተ በፊት መፅሀፍን ከተሰጡትና ከነዚያ ከሚያጋሩትም ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡” አዎ የሚደርስብን የደረሰባቸው ነው፡፡ ካለንበት ለመውጣት የታዘዝንበት ብልሃትም የታዘዙበት ነው፡፡ (وَإِن تَصۡبِرُوا۟ وَتَتَّقُوا۟ فَإِنَّ ذَ ٰ⁠لِكَ مِنۡ عَزۡمِ ٱلۡأُمُورِ) “ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው” ብሎናል፡፡ [አሊ ዒምራን፡ 186] ፈተናው ሊከብድ ስቃዩ ሊጨምር ይችላል፡፡ ግና መለኮታዊ አዋጁን እንስማ፡ (أَمۡ حَسِبۡتُمۡ أَن تَدۡخُلُوا۟ ٱلۡجَنَّةَ وَلَمَّا یَأۡتِكُم مَّثَلُ ٱلَّذِینَ خَلَوۡا۟ مِن قَبۡلِكُمۖ مَّسَّتۡهُمُ ٱلۡبَأۡسَاۤءُ وَٱلضَّرَّاۤءُ وَزُلۡزِلُوا۟ حَتَّىٰ یَقُولَ ٱلرَّسُولُ وَٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ مَتَىٰ نَصۡرُ ٱللَّهِۗ أَلَاۤ إِنَّ نَصۡرَ ٱللَّهِ قَرِیبࣱ) “በእውነቱ የእነዚያ ከበፊታችሁ ያለፉት (ምእመናን መከራ) ብጤ ሳይመጣችሁ ጀነትን ልትገቡ ታስባላችሁን? መልእክተኛውና እነዚያ ከርሱ ጋር ያመኑት 'የአላህ እርዳታ መቼ ነው?' እስከሚሉ ድረስ መከራና ጉዳት ነካቻቸው፣ ተርበደበዱም፡፡ 'ንቁ! የአላህ እርዳታ በእርግጥ ቅርብ ነው' (ተባሉም፡፡)” [አልበቀራ፡ 214] አዎ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው፡፡ ግና የአላህን ትእዛዝ ማክበር ይጠይቃል፡፡ ፈረጃው ይፈጥን ዘንድ የአላህን ህግጋት እንጠብቅ፡፡ ጌታችን “አላህን ብትረዱ ይረዳችኋል” ይላል፡፡ አላህን መርዳት ማለት ትእዛዙን መጠበቅ እና ክልከላውን መራቅ ነው። ለውጥ ከፈለግን እራሳችንን እንለውጥ፡፡ (إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُغَیِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتَّىٰ یُغَیِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمۡۗ) “በርግጥም አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን (ገፅታ) በነፍሶቻቸው ያለውን (ሁኔታ) እስከሚቀይሩ ድረስ አይለውጥም፡፡) [አረዕድ፡ 11] “እስከመቼ” አትበለኝ፡፡ “የአላህ ውሳኔ እስከሚመጣ ድረስ” እልሃለሁ፡፡ ለመሆኑ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም እስከመቼ ነው ፊርዐውንን የታገሱት? ነብዩ ﷺ እስከመቼ ነው ደናቁራን አጋሪዎችን የታገሱት? ረጋ ብለህ አስተውል፡፡ የያኔው ሰቀቀን ከዛሬ እጥፍ ድርብ የከፋ ሰቀቀን ነው፡፡ የያኔው መፍተሄ የዛሬም መፍተሄ ነው፡፡ ይልቅ እወቅ! “አላህን ጠብቅ ይጠብቅሃል፡፡ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህን ታገኘዋለህ፡፡ ስትለምን አላህን ለምን፡፡ ስትታገዝ በአላህ ታገዝ፡፡ እወቅ! ህዝቦች በሙሉ በሆነ ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ አላህ ላንተ በፃፈልህ እንጂ አይጠቅሙህም፡፡ በሆነ ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ በፃፈው እንጂ አይጎዱህም፡፡ ብእሮቹ ተነስተዋል! መዝገቦቹም ደርቀዋል፡፡” “እወቅ! የሳተህ ነገር የሚያገኝህ አልነበረም፡፡ ያገኘህም ነገር የሚስትህ አልነበረም፡፡ እወቅ!!! ድል ከትእግስት ጋር ነው። ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው። ከከባድም ነገር ጋር ገር ነገር አለ።” ወሶለላሁ ዐላ ነቢይና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም። (ኢብኑ ሙነወር፣ ሐምሌ 28/2007) (ተነካክቶ በድጋሚ የተለጠፈ) የቴሌግራም አድራሻ፦ https://t.me/IbnuMunewor
Show all...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

የመከራውን ጎርፍ በትእግስት ጀልባ እናቋርጠው! ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~~~~ ~ ~ ~ ፈተና የአላህ ሱና ነው። መልኩ ቢለያይም ደረጃው ቢፈራረቅም ማንም የማያመልጥበት የሆነ ወጥመድ። ጌታችን አላህ "ሰዎች አመንን ስላሉ ብቻ ሳይፈተኑ ሊተው ያስባሉን?" ሲል እስትንፋሳችን ዱንያን እስከምትሰናበት ድረስ ከፈተና እንደማናመልጥ እቅጫችንን ነግሮናል። ኧረ እንዲያውም “ከፍርሃትና ከረሃብም በሆነ ነገር፤ ከገንዘቦች፣ ከነፍሶችና ከፍሬዎች በመቀነስም በእርግጥም እንፈትናችኋለን” ሲል አስረግጦ ነግሮናል፡፡ ታዲያ ብልጦቹ ይታገሳሉ፡፡ ሽልማታቸውንም ያፍሳሉ፡፡ ቂሎቹ ደግሞ ይወራጫሉ፣ ምንም ጠብ ላያደርጉ የትእግስትን እድል በማሳለፍ ከሁለት ያጣ ይሆናሉ፡፡ በርግጥ የዋሆች ባያስተውሉትም ፈተና ማለት ቅስማችንን የሚሰብረን ነገር ብቻ አይደለም፡፡ ፈተና ስቃይ እንግልቱ፣ መከራው መአቱ ብቻ ሳይሆን ድሎት ምቾቱም፣ ሁሉም የአላህ ፈተና ነው። ታዲያስ "ከዚያም ከ(ተዋለላችሁ) ፀጋዎች ሁሉ በርግጥም ትጠየቃላችሁ" ማለቱ ምንድን ነው የሚያመላክተን? እንዲያውም ነብዩ ﷺ ከማጣት ይልቅ የማገኘትን ፈተና ሰግተውልናል። ጌታችን በክፉ ከተፈተነው ትእግስትን፤ በበጎ ከተፈተነው ምስጋናን ይጠብቃል። የኛ ነገር ግን ሲበዛ ግራ ነው። ብናገኝ ጥጋባችን መከራ። ብናጣ ምሬታችን ፈተና። ቢደላን ምስጋናውን አናውቅበት፡፡ ቢከፋን ትእግስቱን አንችልበት። በህይወታችን ላይ የሚያጋጥመን እያንዳንዱ ነገር ቢከፋም ቢለማም ሁሉም ከአላህ ነው። ይሄ ከስድስቱ የኢማን ምሰሶዎች የአንዱ መሰረታዊ መልእክት ነው፣ ቀደር። በቀደር ማመን በመርህ ደረጃ ከማስተጋባት ባለፈ በተጨባጭ በህይወታችን ላይ ልናስገኘው የሚገባ አንኳር የሙእሚን መለያ ነው። በቀደር ማመን አማኞችን ጀግና ያደርጋል። "አላህ ከወሰነው ውጭ ምንም አይደርስብኝም" ብሎ የቂን ብሎ የሚያምን አካል የፍጡራን ሴራ አያሸብረውም። ሞራሉንም አይሰብረውም፡፡ የዘወትር መፈክሩ "አላህ ለኛ የፃፈብን እንጂ ፈፅሞ አያገኘንም" የሚለው መለኮታዊ ቃል ነው። በቀደር ስታምን ሰው ጂኑ ከጥንት እስከ ዛሬ ባንድ አብረው ቢዘምቱ አላህ ከፃፈብህ ውጭ ቅንጣት ታክል ምንም እንደማያደርሱብህ ስለምታምን በፍጡር አትሸበርም፣ ከፍጡር አትከጅልም። በቀደር ስታምን አንዴ በተከሰተ ነገር በከንቱ አትብከነከንም፣ በባዶ አትቆዝምም። የሆነውን ላትቀይር ነገር "እንዲህ አድርጌ ቢሆን ኖሮ" እያልክ የቂል ፀፀት ውስጥ አትገባም። ለምን ቢባል "ቢሆን ኖሮ" ነብዩ ﷺ እንዳሉት “የሸይጧንን ስራ ትከፍታለችና፡፡” አላህ አለምን ከመፍጠሩ ከሃምሳ ሺ አመት በፊት የወሰነውን ውሳኔ በቢሆን ኖሮ አትቀይረውምና ለአላህ እጅ ስጥ። “አላህ ቀደረው፣ የሻውንም ፈፀመ” በል። የሙእሚን መታወቂያው ይሄው ነው፡፡ “የሙእሚን ነገሩ አስገራሚ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉ ለሱ መልካም ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለአማኝ እንጂ ለማንም አይደለም፡፡ (ሙእሚን) አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል ይህ ለሱ መልካም ነገር ነው፡፡ ጎጂ ነገርም ቢያገኘው ይታገሳል ይህም ለሱ መልካም ነገር ነው” ይላሉ ውዱ ﷺ፡፡ [ሙስሊም] ነብዩ ﷺ የሚወዱትን ነገር ሲመለከቱ "ምስጋና ለአላህ ይሁን በፀጋው በጎ ነገሮች ይፈፀማሉ" ሲሉ "የሚጠሉትን ሲመለከቱ ደግሞ "በማንኛውም ሁኔታ ምስጋና ለአላህ ይሁን" ይሉ ነበር። እኛ ግን በሚደርሱብን ነገሮች ከትእግስት ይልቅ ብስጭትን፣ ተስፋ መቁረጥን፣ ቀንን መራገምን ምርጫችን የምናደርገው ቀላል አይደለንም፡፡ በሚደንቅ ሁኔታ አላህን እስከማማረር አልፎም እስከመሳደብ የሚደርሱም አሉ፡፡ ሱብሓነላህ! ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! እስኪ የነብዩን ﷺ ታሪክ እናስታውስ። ገና በናታቸው መሀፀን ሳሉ አባታቸውን አጡ። ይቺን ምድር ሲቀላቀሉ አባት አልባ የቲም ነበሩ። ገና የልጅነት ጊዜያቸውን ቦርቀው ሳይጨርሱ እናታቸውን አጡ። እዚህ ላይ ወላጅ አልባውን ሙሐመድን ﷺ አስቡ። አስር አመት እንኳ ሳይሞላቸው አሳዳጊ አያታቸውን አጡ። ትዳር ይዘው ሲኖሩ የጠላት ፈተና እጅጉን በከበደበት ጊዜ መከታ የሆነላቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብን እና ብርታት የሆነቻቸውን ውድ ባለቤታቸው ኸዲጃን በሞት አጡ። ከሰባት ልጆቻቸው ውስጥ ስድስቱ እሳቸው በህይወት እያሉ ነው የሞቱባቸው። ምን ያክል የሀዘን መከራ እንደተፈራረቀባቸው ተመልከቱ። ከሶሐቦቻቸውም ውስጥ እነ ሐምዛን፣ ሙስዐብን፣ ጀዕፈርን፣ ዐብደላህ ብኑ ረዋሐን፣ ሰዕድ ብኑ ሙዓዝን፣ ... በስንቱ ሃዘን ተጎድተዋል? እስቲ ለአፍታ መካ ላይ፣ ጧኢፍ ላይ በሙሽሪኮች የደረሰባቸውን አስቡ። ለመቋቋም በሚከብድ ሁኔታ ክብራቸው ተጠልሽቷል። አካላቸው ተደብድቧል። የሸተተ እንግዴ ልጅ ላያቸው ላይ ተጥሎባቸዋል። ድፍን ሃገር አድሞ ከነቤተሰባቸው በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል። ለስደት ሲወጡ የታወጀባቸውን ዘመቻ አስታውሱ። መዲና ላይ በሙናፊቆችና በየሁዶች፣ የኡሑድ ዘመቻ ላይ ጥርሳቸው መሰበሩን፣ እራሳቸው መድማቱን እናስታውስ እስኪ፡፡ አለም ከተፈጠረች ጀምሮ ካለፉ ፍጡሮች ሁሉ የምርጦች ሁሉ ምርጥ፣ የታላቆች ሁሉ ታላቅ ከመሆናቸው ጋር፣ ከአላህ ዘንድ ከየትኛውም ፍጡር በተለየና በበለጠ የተወደዱ ከመሆናቸው ጋር ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ አስተናግደዋል። ደረጃችንን ከደረጃቸው ፈተናችንን ከፈተናቸው ጋር እናነፃፀር እስቲ! እዚህ ግባ የሚባል ደረጃ አለን? ከዚህ ሁሉ ፈተና አንፃር የኛ ፈተና ምን አለው ወገኖቼ? ወገኔ ሆይ! ምንም ቢደርስ ታገስ! እርግጠኛ ሁን በትእግስት ምንም የምታጣው ነገር የለም፡፡ እንዲያውም ትእግስቱን ከቻልክበት ካሰብከው ትደርሳለህ፡፡ ያለምከውን ታሳካለህ፡፡ ድል ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስ፡፡ “እወቅ ድል ከትእግስት ጋር ነው” ብለውሃል ነብዩ ﷺ፡፡ እርዳታ ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስና ወደ ጌታህ ተመለስ፡፡ (وَٱسۡتَعِینُوا۟ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ) “በትእግስትና በሶላት ታገዙ” እያለ ነው ጌታህ፡፡ [አልበቀራህ፡ 45] ካለህበት ጭንቅ መውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ታገስ፡፡ ይበልጥ በተጨነቅክ ቁጥር ይበልጥ ፍጡርን እየተወክ ይበልጥ በጌታህ ላይ ተስፋህን እየጣልክ ትመጣለህ፡፡ ያኔ እፎይታን ታገኛለህ፡፡ “እፎይታ ወይም ግልግል ከጭንቅ ጋር ነው” ይላሉ መልእክተኛው ﷺ፡፡ ታገስ! በትእግስት የጠላት ውስብስብ ሴራዎች ይበጣጠሳሉ፡፡ ታገስ! በትእግስት እብሪተኛ አንባገነኖች ይፈራርሳሉ፡፡ ታገስ! በትእግስት ደካሞች ድሎትን ይጎናፀፋሉ፡፡ ወገኔ ሆይ እወቅ! በፈተና እኛ የመጀመሪያዎች አይደለንም፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀዋል፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ አይናቸው እያየ ከሚንቀለቀል እሳት ውስጥ ተማግደዋል፡፡ ቀደምቶች በዲናቸው ሳቢያ ከፈላ ዘይት ውስጥ ተነክረዋል፡፡ ቀደምቶች ነፍሳቸው እያለ በስለት ተዘልዝለዋል፣ ተመትረዋል፡፡ ቆስለዋል ደምተዋል፡፡ ይሄ ወደፊትም የማይቋረጥ የጌታችን ሱና ነው፡፡ ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡- (لَتُبۡلَوُنَّ فِیۤ أَمۡوَ ٰ⁠لِكُمۡ وَأَنفُسِكُمۡ وَلَتَسۡمَعُنَّ مِنَ ٱلَّذِینَ أُوتُوا۟ ٱلۡكِتَـٰبَ مِن قَبۡلِكُمۡ وَمِنَ ٱلَّذِینَ أَشۡرَكُوۤا۟ أَذࣰى كَثِیرࣰاۚ)
Show all...
💡የእድሜ_ባለፀጋው_ተጠየቁ! ለመሆኑ እስካሁን ባሳለፉት እድሜ ምን ተማሩ? እሳቸውም መለሱ! 💎 "ይህች ዓለም የአበዳሪ እና የተበዳሪ መነታረኪያ መድረክ መሆኗን፤ መልካም የሠራ የብድሩን መልስ ከፈጣሪው ሳይሆን መልካም ከዋለለት አካል የሚጠብቅባት ዓለም እንደሆነች ተረዳሁ!" 💎"በዳይ ዘግይቶም ቢሆን የእጁን እንደሚያገኝ፣ ተበዳይም የበዳይን መጨረሻ በአይኔ ካላየሁ ብሎ ሲያለቅስ እድሜውን እንደሚፈጅ ተረዳሁ!" 💡"በለሊት የተወነጨፈች ቀስት ኢላማዋን እንደማትስትም ተማርኩ!" 💎"ህይወታችን እኛ ከዝንጋቴ ሳንወጣ በየትኛውም ቅፅበት ሊቋጭ እንደሚችል ተገነዘብኩ!" 💡"መልካም ንግግር፣ ፈገግታ የተሞላ ገፅታ፣ ችሮታ የማይለየው እጅ ካሉን ሃብቶች ሁሉ የላቁ ድልቦች እንደሆኑ ተማርኩ!" ሰናይ ጊዜ!❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity
Show all...