1 200
Subscribers
No data24 hours
+127 days
+4230 days
Posts Archive
1 201
ከተለያየን ከረጅም ጊዜ በኃላ ከሩቅ አየሁት...
ልቀርበዉ ድፍረት አጣዉ ብቀርበዉ በስንት ልመና ያደበ ልቤ እንዳይረብሸኝ አሁንም የምወደዉ አይኑ የረጋ የመሰለኝን መኖር እንዳያናዉጠዉ ፈራሁ...
ከሩቅ አየሁት!
የመለያየት ህመሙ የሚብሰዉ አሁን ነዉ!!
...ልክ እንዲ እንደድንገት የቢሆን ንፋስ ሲነፍስ.. አሁን እየሮጥኩ ሄጄ ባቅፈዉ ተመኘሁ...መለየት የሰራት እኔን ከወደዳት ብጠይቀዉ ምኔ እንደሚናፍቀዉ የቱ ጋር ትዝ እንደምለዉ ባዉቅ እንደናፈቀኝ እንዳልጠላሁት በነገርኩት.....
ከተለያየን አመታት ተቆጠሩ የቀን እርዝማኔ እንዲህ እንደሆነ አላወኩም!!!
ስንት እኔን አንስቼ ስንት እኔን ጣልኩ?!!?
በእነዚህ ሁሉ አመታት ያልተረሳኝ አይኑ አሁን ካለሁበት አይታይም...
የጊዜ ክህደት እዚህ ጋር ነዉ!
የምንወደዉን ማራቁ...ስንዝር ታህል ይቀርብ የነበረን እንዲህ ከርቀት ማስቀመጡ...
ጊዜ በመዉደድ ላይ ጠባሳ ይጥላል....
.......አይመስልህም???
#vie.. እእእ??
1 201
ብቻ ትናፍቀኛለህ ...
እንደጓጓሁለት የድሮ የማትሪክ ውጤት
እርቦኝ እንደምጎርሰው የመጀመሪያ ጉርሻ
እንደ መፅሀፎቼ ሽታ
እንደ አስቴር አወቀ አዲስ አልበም መውጫ ቀን
እንደ እሁድ ጠዋት ቅዳሴ
እንደ ልጅነቴ ነፃነት
ስደክም ውዬ እንደምተኛው እንቅልፍ
እንዳባቴ ኮራሁቡሽ ቃል
ሊሳኩ እንደተቃረቡ ህልሞቼ
እንደሚሞላልኝ "ግማሽ ቀን" ትናፍቀኛለህ....
#vie 🥀
1 201
....አየህ በአንተ ልክ ልወደው እንደማልችል ገብቶኛል..
አሁንም ስልኬ ላይ ፎቶህ አለ አሁንም ያለፍንበትን መንገድ አስታውሳለሁ.. አሁንም የቆጨኝ ህይወት አለ አሁንም ማስታወሻህ ማስታወሻዬ ብቻ አይደለም ኑሮዬ እንጂ ያንተ ትናንት ዛሬዬን አነቀብኝ
አየህ አንተ አታውቅም...ትቼህ የሄድኩ ይመስልሀል እኔ ግን ይዤህ እሱ ጋር መጥቻለሁ..
አንተ እያለህ የመውደድ ደህንነት አይሰማኝም..
አንተን እንጂ እሱን እንደማላውቀው ስራዬ ያሳብቃል
እሱን እንዳንተ ለመውደድ ልቤ አይፈቅድልኝም
እሱን እንደማቅፈው ሳይሆን አንተን እንደማቅፍህ እያቀፍኩት እንደሆነ ሳውቅ ሴትነቴ ያስጠላኛል..
... #vie¿
1 201
...ልዩ አልነበረም
የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም..
ገፁ ጨረቃን ወይ ድምፁ ቅዳሴን አላስረሳኝም
ቃሉም ሳቁም የሚረሳ!
ማንም ነበረ ለ አለም
ለኔ ግን --- 'ራሱ አለም!♡
#..
1 201
የህይወት ፅንፍ ሞት
የፍቅር ደግሞ ጥላቻ ይመስለኝ ነበር....
የፍቅር ፅንፍ መተው ነው...ትውት ማድረግ....ዝም መባል...መረሳት ወድያ ወዲህ መጎተት ነፍስን ልብን ማሰቃየት ...ቀልብን ከራስ ማኳረፍ...መንፈስን ከእግዜር ማጣላት...
የፍቅር አንፃሩ ጥላቻ አይደለም መተው ነው ት ው ት ማድረግ. . . .
#... 🥀
1 201
ላፈቀረ... ናፍቆት ነው ወይንስ ሞት የተሻለ የሚሆነው...??
በእርግጥ እንደኔ ሁለቱም ሞት ናቸው ልዩነቱ ናፍቆት በጊዜ የሚሽር መሆኑ ብቻ ይመስለኛል...እኔ ናፍቀኸኛል ብዬ ሳላይህ ማደር አይሆንልኝም..ሳላገኝህ ነግቶ ሲመሽ የመቻል አቅም ካለኝ የመናፈቅ ስሜት ላይ አይደለሁም ማለት ነው..
እኔ... ስትናፍቀኝ ብዙ ወረቀቶች ያንተን ስም ከትበው በሰፈሩት ስንኞች ስግስግ ውስጥ ጠረንህ ታምቆ ብዙ ቀን ብዙ ምሽት እስክትመጣ ልቤን ላባብል ከጨረቃ መንደር ተጉዣለሁ..ካልመጣህ ካላየኸኝ ደህና የማልሆንባቸው ሺ ምክንያቶች አሉኝ..አንዳንዴ በአለሜ ላይ ፈጥሬህ እያኖርኩህ ይመስለኛል..በአለሜ ላይ መልካም የሆኑ ነገሮች ሁሉ በአንተ የሚመሰሉ ይመስሉኛል..አንተን ማፍቀር አይደክምም..ተስፋ ማድረግ አይደክምም መጠበቁም አሰልቺ አይሆንም..ለኔ ከባድ የሆነብኝ ናፍቆቱ ነው ሞትን የሚያስንቅ መናፈቅ....
#....
1 201
''ህይወት የምታምረው ከፊት ተስፋ ከኋላም ትዝታ ሲኖራት ነው''.....
ዛሬዬ የተሰራው በሱ ትናንትናዬ ውስጥ መኖር ነው ....ታድያ ዛሬ ባይሆን እንኳ ነገዬ ላይ እንዲኖርልኝ መፈለጌ ስህተት ነው?.....
#....
1 201
ያጣናቸው ሰዎች ከላያችን ላይ ቦጭቀው የሚወስዱብን ነገር አለ።በመሄዳቸው ያጎሉብናል። እነዚህ ጉድለቶች ቀን በገፋ ቁጥር ልብ ላይ ዘልቀው የሚፈጥሩት ህመም በቀላሉ አይሽርም። ወደ ውስጥ በተመለከትን ቁጥር ጎዶሎነታችን ላይ የምንደርስበት ሰዎች አለን። በራሱ ጨለማ ተውጦ የማያውቅ ማነው?.... አመታት ቢያልፉም እንደ አዲስ የምናለቅስለት ሰው አናጣም። ይህ ስቃያችን በጎጇችን ሰላም፤ በመኝታችን ደግሞ እንቅልፍ ይከለክለናል ....
ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?1 201
በህይወትህ ጠባቂ ስትሆን ብዙ ነገር ይገባሀል… በጣም ብዙ ነገር…ግን ከሁሉም በላይ ምን ይገባሀል መሰለህ… ጠባቂ ስትሆን አታማርም…ሁሌም ተመስገን ነው እምትለው! …ምክንያቱም ያ እምጠብቀው ቀን በማመስገን ውስጥ ነው እና እምታገኘው…
#Mis_s... 😊
1 201
. . . . ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን. . . ጨረቃንና ፀሐይን በልቅ ሰማይ ያቆመ. . .ከዋክብቶችን በጠራ ሰማይ የበተነ ሰውን ከአፈርና ከውሃ ቀይጦ የሰራ. . .ነፍስን የሰጠ . . እርሱ የሰማይ የምድር ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን!😊
#...
