cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ህይወትን በግጥም

👉በዚ ቻናል ውስጥ ታዋቂና የግጥም ተሰጥዖ ያላቸው ግን በተለያየ ምክንያት መውጣት ያልቻሉ እንቁ ገጣምያኖች የሚገኙበት ምርጥና ብቸኛው ህይወትን በግጥም ቀለል አርጎ የሚገልጽ የግጥም ቻናል ነው! አንዳንድ ወጎችም ይኖሩናል😉 👉ግጥም እንዲለቀቅላቹ ምትፈልጉ @klete and @Poemday ላይ መላክ ትችላላቹ #Share & #like

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
162
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስሚኝ!! መውደዴን ለመግለፅ ቃላቶች ቢያጥሩኝ አይቼሽ ለማውራት ፊትሽ ቢያስፈራኝ አሁን ፍቅር ጥሎኝ እግርሽ ላይ ብወድቅም የዛሬን አያርገውና እንዲህ አልነበርኩም ውዴ ስሚኝ ልንገርሽ... ቃላት ከሚደረድር ከሸንጋዩ ሰው ፍቅር ፍቅር እያለ ከሚለፈልፈው እያየ የሚወድሽ ድፍረት ለነፈገው እሱ ይበልጣል ከሁሉም በልቡ የያዘው ✍ ተፃፈ በእዮብ ተሾመ© 02/09/2013 E.c 07:33A.m @poemday
Show all...
ስሚኝ!! መውደዴን ለመግለፅ ቃላቶች ቢያጥሩኝ አይቼሽ ለማውራት ፊትሽ ቢያስፈራኝ አሁን ፍቅር ጥሎኝ እግርሽ ላይ ብወድቅም የዛሬን አያርገውና እንዲህ አልነበርኩም ውዴ ስሚኝ ልንገርሽ... ቃላት ከሚደረድር ከሸንጋዩ ሰው ፍቅር ፍቅር እያለ ከሚለፈልፈው እያየ የሚወድሽ ድፍረት ለነፈገው እሱ ይበልጣል ከሁሉም በልቡ የያዘው ✍ ተፃፈ በእዮብ ተሾመ©
Show all...
​​እኔ ምልሽ ውዴ አንቺን በመውደዴ ባውቶብስ ፌርማታ ባቡር ተጠበቀ ሌባው እየኮራ ፖሊስ ተደበቀ ጥርስ ያለው አይስቅም ድዳሙ እየሳቀ ለነገሩ ይሁን ቀን ነግቶ ይመሻል እንኳን ሌላው ቀርቶ አንቺም የኔዋ ጉድ የኔን ልብ ሠርቀሻል።
Show all...
እመስላለሁ አይደል ? (አብርሀም ሙሉ ሰው) እመስላለው አይደል? ፣ደስ እንደተሰኘ አጥቶ እንዳገኘ ህልሙን እንደነካ በልቶ እንደጠገበ፣ ጠጥቶ እንደረካ… "ተስማምተው ይመስል፣ ነፍስና ስጋየ" ድብቁን እንደሰማ፣ ሚስጥሩን እንዳየ የመኖር ብዥታ፣ እንደሆነለት ግልፅ የሀሳቡ ሞልቶ፣ እንደያዘለት ቅርፅ… እመስላለሁ አይደል ? የጨበጠው መልካም፣ የረገጠው ቀና ለምለም የሆነለት፣ የህይወት ጎዳና ውሀው ወይን ሆኖ፣ ያሰከረው አይነት እርካታን እረክቷት፣ ያቆመ መመኘት ፍቅር ያሰጠመው፣ መውደድን የሚጠልቅ ሁሉንም የሚያውቅ ፣በሁሉም ሚታወቅ እመስላለሁ አይደል ? እመስላለሁ አይደል ? ፣ያማረበት ለብሶ ጆሮው መርዶ ያልሰማ፣ አይኑ ያላየ ለቅሶ እስኪ መልሱልኝ ፣እመስላለሁ አይደል ? መታገል ያልጣለው፣ ያቆመው መታደል! .
Show all...
እንኳን አደረሳችሁ 🙏❤🙏 📖📖📖 የገነት በሬነህ _______ ለኔ ለደካማ ክፋት ለወረረኝ በሰው ደም ለቆሸሽኩ ምህረት ማይገባኝ በዝሙት በርኩሰት ገላዬ ላደፈው ቅንጣት ሀዘኔታ በውስጤ ለሌላው ተንኮል ለማሴረው ለጨኳኟ ነብሴ ሁሌም ኗሪ ለሆንኩ ለሟይሞላው ኪሴ አንተ ግን ተሰቀልክ ደምክን አፈሰስክ የኔን በደል ትተህ ለእኔ ተከሰስክ እኔ ድኜ ባንተ እኔ ድኜ ባንተ ዳግመኛ ተነሳህ ሞትህ ድል አድርገህ ከቶ ምን ሊሳንህ የገነት በሬነህ በዳዳ coffee
Show all...
✟✞ ትንሳኤ ለኔ ነሽ ✟✞ አዳም ቢበድልም በምኞት ስህቱ ለምድር ቢሰጥም ሔዋን ብትስትም እምነቷን ለስህተት ፈቅዳ ብትሰጥም ቆይ ግን እንደምን ባለ መልክ ምን በሆነ ሁኔታ እንዴት የሰው ፍጡር ማሰብ የተሰጠው ማወቅን ያወቀው፣ እባብ ያስተዋል የማወቅን እውቀት ጥበብ ያልተሰጠው። መሳቱንስ ይሳት ይህን ስህተት ሊያርም ቢወርድ ከመንበሩ፣ እጅጉን ይከፋል በርን እያንኳኳ ግባ እሚለው አቶ ከደጃፍ ማደሩ። በጥፊ ሲመታ በባርያ መዳፍ ላይ በደም መልክን መሳል፣ የተካደው እውነት ለካደው ሐሰት ሲል ከመስቀል ላይ መዋል፣ ምን አይነት ፍቅር ነው ምን የሚሉት መንደድ ምን ይሉት ስቃይ ነው ምን የሚሉት መውደድ ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ስሞ ላሸመተው አላውቀውም ብሎ ሶስት ጊዜ ለካደው የዶሮዋን ጩኀት ሰምቶ ላለቀሰው ወንጀለኛን ፈቶ ንፁሁን ላሰረው እስኪ ልጠይቅሽ ምን አስገድዶት ነው፦ መራራን የጠጣው? ሀሞት የቀመሰው? አንቺ የይሁዳ ምስል ዲናር ብታስበልጭ ፍቅሬን ችላ ብለሽ፣ ልረሳሽ አልችልም አላውቃትም ልልሽ። አንቺን በማለቴ ቁጥሩ ማይታወቅ ጅራፍ ቢያርፍብኝም የመረረን ሀሞት ምላሴ ቤቀምስም የረሳሽው ጅራፍ ስንዝር የመረረው ሀሞት ስፍር ቢያስክደኝም እኔነቴን ላያከስመው ያንቺን ፍቅር ከክናፍርሽ ስር ያለውን ውብ ጠለል ቢጠማም ከንፈሬ ደጅሽ ሲመላለስ ሚስማር ቢወጋውም ቢንሻፈፍም እግሬ ከድንግሏ እናቱ ከስጋዋ ስጋን ነስቶ ተዋህዶ ሊያድነኝ ከመጣ ህመም መከራዬን ሊቀበለኝ ወዶ እኔን ከመሰለ ስጋን ከለበሰ ለፍቅር ተዋርዶ እኔ እርሱን ልመስለው ይገባል ልገልጠው ያያ የእውነት ፍቅሩን የእውነት ልኖረው አንቺ እኔን ብጠይኝ ምራቅ ብተፊብኝ በጥላቻሽ ጅራፍ እጥፍ ብትገርፊኝ ግራዬ እያልኩሽ ጎኔን ብትወጊው በደሜ ማህተም ቃሌን ሰጥሻለው እኔን የመሰለኝ ለወጉት ጥላቻን ሲሰጥ ስላላየው፣ ዕፅፍ ወድሻለሁ ፍቅር ለፍቅርሽ ስል ነፍሲን እሰጣለው። ትንሳኤ ለኔ ነሽ ፦ ካለሁበት ፅልመት ሳይሽ እምመለስ፣ መግነዝ ሳላስፈታ ከደጅሽ ላይ ምደርስ፣ በር ሳልቀበቅብ ልብሽ ላይ ምገለጥ፣ ሳጣሽ ግን አንቺ ልጅ ሲኦል ነው ምቀመጥ። ✍ ዮላ ቀን 23:08:2013 ዓ/ም ሰዓት 04:15
Show all...
አጣጥለህ አትነሳ (አብርሃም ሙሉ ሰው) አጣጥለህ አትነሳ ያንዱን ውድቀት፣ አትደገፍ ጥረህ ፣ግረህ ፣ሰርተህ እለፍ አሊያ አንደኛ ብትወጣ... አያጠግብህ የሚበላ፣ አያረካህ የሚጠጣ አያምርብህ የሚለበስ በሰው ልፋት፣ አንተ ስትደርስ ያለ ቦታህ ስትሰየም፣ ያለ ጊዜህ ስትገኝ ያለእውቀትህ ስትሞገስ፣ ያለ ሞያህ ስትቀኝ ውጭህ ሙላት፣ ውስጥህ ባዶ ስኬት አይባልም የራስን መካብ፣ የሌላውን ንዶ!፡፡ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
Show all...
#የጠቢብ ቃል! (ሚካኤል አስጨናቂ) . #ባህር ዳር ተኝቼ ሳልሞቅ ጠሀይቷን አየር ላይ በርሬ ሳልጎበኝ ምድሪቷን ቁርሴን አዲሳ ' ባ ምሳዬን ፓሪስ ላይ እንዲህ ተዝናንቼ ድሎት ተድላ ሳላይ በቆንጆዎች ጉያ ስራቸው ሰምጬ ብኖር ነው ደስታዬ ዓለሜን ቀጭቼ እያልሁ አስብ ነበር ! አቤት የኔ ነገር ... ዳምኖ ይሄ ቀኔ ... ሰፍኖበት ፅሞና ከሎሬቱ ቅኔ.. . አንዷን እመዝና ምነው እመብርሀን ኢትዮጵያን ዘነጋሻት? ቀኝሽን ረሳሻት ... ? እያልሁ ሳልዘምር ... ስንኙን ሸምድጄ በቃል ሳልደረድር በዝናብ ሳልተኛ በሬን ዘጋግቼ ብልጭልጭ መኪና ሳልሾፍር ገዝቼ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ህንጣ ሳልገነባ እልፍ ሎሌ ኖሮኝ ታጅቤ ሳልገባ ይሄ ህይወት ነው ወይ... አሁን የኔ ኑሮ ? እያልኩ አስብ ነበር ያ...ኔ በፊት ድሮ ይሄ ታሪኬ ነው ሌላ ነው ዘንድሮ ! ዛሬ ... ከመጥሀፍ ትንቢት አንዲቷን ቆንጥሬ ገላልጬ ባየው ... ይሄ ስንዝር ገላ ድሎት አበጃጅቶት ወዘና ቢያጠምቀው ዝናው ባህር አልፎ የአዳም ዘር ቢያውቀው በስልጣን በውበት ሁሉ ቢያዳንቀው አሸርጋጅ አጎንባሽ ዙሪያውን ቢያጅበው ጠቢቡ ሰለሞን አበክሮ እንዳለው ሁሉም ከንቱ ... ከንቱ ... የከንቱ ከንቱ ነው !
Show all...
የሚወድ ይጽናና! - በገበያ ዓለም ውስጥ... ብርቱ በመፃጉዕ በሚታዘልበት ነፍስ ባሞሌ ጨው በሚለወጥበት፤ ያጸና አንድ ሲገኝ መንፈሱን እንዳ'ለት ተመስገን ነው ማለት! ፍትህና ሰላም በደኅና አይጠላም - ብሎ ከኅሊናው መክሮ... የራሔልን ዋይታ ከሚፈጥሩት ተርታ፤ ከበደለኞች ሰልፍ መራቅ የመረጠ ክፋትን በለጠ። ፍትሕ ናት ገናና ሰላም ናት ገናና የሚወድ ይፅናና! ለተከታይ መንጋ - ሰው ጀርባ ለቆመ ውበት ወደዚህ ናት - ብሎ የጠቆመ እምነት ወደዚህ ናት - ብሎ የጠቆመ፤ ገሚሱ ጣቱ ላይ - ወጥቶ ቢንጠለጠል በገሚሱ ደግሞ - ግብሩ ቢብጠለጠል፤ ከሰልፍ ባሻገር - ዐይኑን ገልጦ ያየ ልቡን ከፍቶ ያየ ከነፍሱ ተስማማ- ከመንጋ ተለየ! ውበት ናት ገናና እምነት ናት ገናና የሚወድ ይፅናና! የኖረ እንኳ ቢኾን - ገድሎ፣ ዘርፎ፣ ዋሽቶ ሞት ጽድቅን እንዳይቀድም - ሥርየትን ሽቶ፤ ልቡን ወደ ምህረት - ካለ የመለሰ ራሱን ፈወሰ! ምሕረት ናት ገናና የሚወድ ይጽናና! ያግኝም ይጣትም ሽልማት ቅጣትም፤ ታግኘው ትጣውም ክስረቱም ዕጣውም፤ ከማግኘት ከማጣት- ከርሱም ከርሷም ይልቅ (ከእኔም ካንቺም ይልቅ) (ከኹላችን ይልቅ) ፍቅር ነው ገናና የሚወድ ይፅናና! በገበያ ዓለም ውስጥ... ብርቱ በመፃጉዕ በሚታዘልበት ነፍስ ባሞሌ ጨው በሚለወጥበት፤ ያጸና አንድ ሲገኝ መንፈሱን እንዳ'ለት ተመስገን ነው ማለት! ጭቁን መች ይዝላል? ያነሳል ይጥላል፤ ድሮ ቀረ ይላል አዲስ ዘመን ይላል፤ ትዝታ ያኝካል ተስፋ ያመነዥካል፤ ጨቋኝ መች ይዝላል? ያነሳል ይጥላል፤ በትግል ይነግሣል በትግል ይፈርሳል፤ እንትን ኹለት ይላል እንትን ኻያ ይላል፤ የሻገተ ልቡን በምላሱ ያጥባል የነጠፈ አንጎሉን በሽንገላ ያልባል። ለመንፈስ መታወክ - ተስፋ እንደሚቸረችር፣ ታሪክ የሚሸቅጥ ሐርነት ምን እንደኹ፣ መታደስ ምን እንደኹ- አልተረዳም በቅጥ። የየግለሰቡ የየነፍሱ እውነት የየራሱ ጥበብ፣ የየራሱ ኪነት፤ ሐርነት ገናና ነጻነት ገናና የሚወድ ይጽናና! በአምልኮ አደባባይ - በትምህርት ገበታ ጥላቻ እየፀናች - በርዕዮት ተፈትፍታ፤ በራዲዮን ልሳን - በቴሌቪዥን መስኮት ቂም እየተዘራ - በቀል ሲኮተኮት ቀጥፎ ሞት ለማትረፍ - አዳሜ ሲራኮት፤ በገበያ ዓለም ውስጥ... በገበያ ዓለም ውስጥ... ብርቱ በመፃጉዕ በሚታዘልበት ነፍስ ባሞሌ ጨው በሚለወጥበት፤ ያጸና አንድ ሲገኝ መንፈሱን እንዳ'ለት ተመስገን ነው ማለት! እንዲህ ዐይነቱ ሰው - ስም ቢቀርበትም - ስም ቢወጣለትም እውነት ነፍሱ አትሞትም! እውነት ናት ገናና! የሚወድ ይጽናና! ------------------------- መስፍን ወልደተንሳይ ሰኞ- መስከረም 1- 2004 (ክብ ልፋት መድብል)
Show all...
እኔው_ሞኛ_በሱራፌል_ጌትነትሱራ_ቢራቢሮ.mp31.00 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.