cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

All in one

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
324
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ ብርጭቆ ወተት አንድ ቀን በትምህርት ቤት ውስጥ ለመቆየት ክፍያ ለመክፈል ከቤት ወደ ቤት ዕቃዎችን የሚሸጥ አንድ ምስኪን ልጅ አንድ ቀጭን ሳንቲም ብቻ ቀረው በጣም ተርቧል ፡፡ በሚቀጥለው ቤት ምግብ ለመጠየቅ ወሰነ ፡፡ ሆኖም አንዲት ቆንጆ ወጣት በሩን በከፈተች ጊዜ ነርቭ አጣ ፡፡ ከምግብ ይልቅ ውሃ እንዲጠጣ ጠየቀ ፡፡ የተራበ ይመስላል ትልቅ ብርጭቆ ወተት አመጣችለት ፡፡ እሱ በጣም በዝግታ ጠጣው ፣ ከዚያም “ስንት እዳ አለብኝ?” ምንም ዕዳ የለብህም ”ስትል መለሰች ፡፡ እናቴ ለደግነት ደሞዝ በጭራሽ እንዳንቀበል አስተምራናለች ፡፡ እርሱም “ከዚያ ከልቤ አመሰግናለሁ” ይላል ፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያች ወጣት ሴት በጠና ታመመች ፡፡ የአከባቢው ሐኪሞች ግራ ተጋብተዋል ፡፡ በመጨረሻም ወደ ትልቁ ከተማ ላኳት ፣ እዚያም ብርቅዬ በሽታዋን ለማጥናት ልዩ ባለሙያተኞች ተጠሩ ፡፡ ለምክክሩ ዶ / ር ሆዋርድ ኬሊ ተጠርተዋል ፡፡ የመጣችበትን ከተማ ስም ሲሰማ አንድ ያልተለመደ ብርሃን ዓይኖቹን ሞላው ፡፡ ወዲያው ተነስቶ ወደ ሆስፒታሉ አዳራሽ ወደ ክፍሏ ወረደ… ከዚያን ቀን ጀምሮ ዶ / ር ኬሊ ለጉዳያቸው ልዩ ትኩረት ሰጡ ፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ ውጊያውን አሸነፈ ፡፡ ዶ / ር ኬሊ ለቢዝነስ ጽ / ቤቱ የመጨረሻውን ሂሳብ እንዲፀድቅለት እንዲያሳውቅ ጠየቁ ፡፡ እሱ ተመልክቶ ከዚያ በጠርዙ ላይ አንድ ነገር ጽፎ ሂሳቡ ወደ ክፍሏ ተላከ ፡፡ ሁሉንም ለመክፈል ቀሪ ሕይወቷን እንደሚወስድ እርግጠኛ ስለነበረች እሱን ለመክፈት ፈራች ፡፡ በመጨረሻም ፣ እሷ ተመለከተች ፣ እና አንድ ነገር ከሂሳቡ ጎን ላይ ትኩረቷን ሳበ ፡፡ እነዚህን ቃላት አነበበች “በአንድ ብርጭቆ ወተት ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል” (የተፈረመ) ዶ / ር ሆዋርድ ኬሊ ፡፡ Kindness coasts nothing be kind ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ መልካም ቅን ደግ እያሰብን እያደረግን እምንውልበት ብሩህ ቀን ይሁንልን 😍🙏
Show all...
በዝምታ እንፍሰስ በአድልዎ ሚዛን በግፍ ችሎት #ተሰይመን_ሳንፈርድ® ለአሽቃባጮች አሸርግደን #ከማስመሰል_ሳንዛመድ® ለሆድ ብለን ርቀን ከእምነት #ቁልቁል_ሳንወርድ® ቃል አምቀን ከርችመን አንደበት #በዝምታ_እንዋደድ® አይሆንም ካልሽ ካልመሰለሽ ይቅር #ምን_ይደረግ_እቱ® ባልተሟሸ አእምሮ ባልሰከነ መንደር #ጩኸት_መጎተቱ® የእኛ ድምፅ ነጥሮ ሲመለስ ግርግር #የገደል_ማሚቱ® እንቅጩን ልንገርሽ ከሆነ አይቀር #ለአብሮነት_ስምረቱ® የአሽቃባጭ አፍ ካጋለው ቧልታ #አጨብጭበን_ከማራገፍ® እንገለል ከኳኳታ ከጫጫታ #ከጆሮዋችን_እንታቀብ® ፍቅር እናጣጥም በከርሞ ትዝታ #ህይወታችን_ታብብ® ዝም ብለን እንፍሰስ ወደ እፎይታ #ወንዙ_አጠገብ® ከወረት ጦስ ከጥላቻ እንፋታ #በአንድነት_እንሰብሰብ® የቆሸሽንበትን የዘመን ሻጋታ #በእምነት_ጅረት_እንታጠብ® በይቅርታ ከፍታ ፣ በዝምታ ፣ በፀጥታ ። #በመዋደድ_እንዝነብ® ከሎሬቱ ውቅያኖስ የተቀነሰ ነቁጣ ነጥብ መልካም ና የሰከነ ቀን ተመኘሁላችሁ 🙏 ከወደዱት share በማድረግ ያግዙን @a2jaedu
Show all...
ሕሊናህን ጥለቅበት፤ አዕምሮህን ስመጥበት! ሰው’ነትህን እንድታወጣበት፣ ምንነትህን እንድታውቅበት፣ ሰው ሆነህ እንድትበቃበት፡፡ ሕሊና ለሰው ልጅ የተሰጠ ክቡር ድንቅ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ድንቅ ስጦታውን ለበጎ የሚጠቀመው ግን በጣም ኢምንት ነው፡፡ አንዳንዱ የሕሊናውን ሃይል ባለመረዳቱ በሆነ ባልሆነው ትርኪምርኪ ነገር ያባክነዋል፡፡ ጭንቅላቱን በማይረባ ነገር እየሞላ ሚሞሪውን የሚያጨናንቅ ቀላል ቁጥር የለውም፡፡ በትርኪምርኪና በግብስብስ ሕይወት ነፍሱን ያጨናነቀ ሺ ነው፡፡ መንፈሱን አጉድሎ፣ ነፍሱን አጎሳቁሎ፣ ስጋውን አደልቦ ውስጠቱን ዘንግቶ፣ ሕሊናውን ረስቶ ከራሱ ጋር ተኮራርፎ የሚኖር፤ ለራሱ እንኳን የማይበጅ ዓመለ ቢስ ቤት ይቁጠረው፡፡ አንዳንዱ ያላደለው ደግሞ ማሰቢያውን ለክፉ ነገር ብቻ ይጠቀምበታል፤ አዕምሮውን የተንኮል ፋብሪካ የሚያደርግ፤ ከገዛ አዕምሮው ክፋትን ብቻ የሚያመርት እጅግ ብዙ ነው፡፡ አብዛኛው ደግሞ ከማሰቢያው ጋር ሳይተዋወቅና አዕምሮውን ምንም ሳይጠቀምበት ከእናቱ ማህፀን ይዞት እንደወጣ ይዞት መቃብር ይወርዳል፡፡ ሕሊናው ሸክም ሆኖበት ከሸክሙ ያልተገላገለ ጭንቅላቱን በራሱ፤ አዕምሮውን በጫንቃው ተሸክሞ ይዞት የሚዞርም እልፍ ነው፡፡ ሰው አዕምሮ ባይኖረው ምን ይሆን ነበር? ከዚህ በላይ ሊከፋ ይችል ይሆን? አዕምሮ እያለው እንኳን አዕምሮውን የማይጠቀምበት በበዛበት ዓለም ሕሊና ባይኖረው ደግሞ ምን እንደሚሆን ለመገመት እጅግ ይከብዳል፡፡ አይ…. ሰው ማሰቢያ ባይኖረው እንደዚህ ሊከፋ አይችልም ብሎ የሚያስብ አይጠፋም፡፡ አሃ ሰው ማሰቡ ነው ክፉ እንዲሆን ያደረገው እንዴ? ብለን ብንጠይቅስ ምን ይሆን የምናገኘው መልስ፡፡ አንድ ጀርመናዊ ፈላስፋ፡- ‹‹ማሰብ ያማል›› ብሏል፡፡ ምን ማሰብ ይሆን የሚያሳምመው? ደግ ማሰብ ወይስ ክፉ ማሰብ? ነው ወይስ ማሰብ በጠቅላላ ራስ ያዞራል? ፈላስፋው ማለት የፈለገው እንደገባኝ ከሆነ መልካም ማሰብ ከባድ ነው፤ ክፉ ማሰብ ግን ቀላል ነው፡፡ አዕምሮ የሚጠይቀው ለሰው ሁሉ የሚጠቅመውን ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰውን የሚጎዳ ነገር ማሰብ እጅግ ቀላል እንደሆነ አፅንኦት ለመስጠት ይመስለኛል ‹‹ማሰብ ያማል›› ያለው፡፡ አዎ ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡ ቅንነትም ሆነ ደግነት እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይደለም፡፡ ደግነትን ለመውለድ፤ ቅንነትን ለመገላገል በእውነትና በፍቅር ማማጥ ግድ ይላል፡፡ ምጥ ደግሞ ህመም አለው፡፡ ሕመሙ ግን ከወሊድ በኋላ የሚቆምና በደስታ የሚለወጥ ነው፡፡ ቅንነት ዕውቀት፤ ፍቅር ጥበብ፣ ደግነት ችሎታ መሆኑ የማይገባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገር ሲያስቡ ያማቸዋል፡፡ ሕመማቸው እንደምጡ ሲወልዱ የሚገላገሉት አይደለም፡፡ የነሱ ጤንነት መታመም ነው፡፡ ጤንነት የሚሰማቸው ክፉውን ሲዘሩ ብቻ ነው፡፡ አዎ በሱስ ለሚሰቃይ ሰው ህመሙ የሚሰማውና የሚብስበት የሱሱን ምሱን ሲያጣ ነው፡፡ ጤነኛ የሚሆነው የለመደውን ሲያገኝ ነውና፡፡ የሰው መበደል ደስ የሚያሰኛቸው፤ የወገን መሳደድ፣ የደሃ መታረድ፣ የምስኪኖች መጎሳቆል ነፍሳቸውን የሚያረካው ደግ ማሰብ የማይችሉና በጎ ማየትም ሆነ መስማት የማይሹ በተንኮል ወረርሽኝ የተያዙ፣ በዘረኝነት የታመሙ፣ በጎጥ የተለከፉ፣ ሕሊናቸውን የሸጡ እርኩሳን ሰዎች ናቸው፡፡ አዎ የዚህ ሁሉ መግፍኤ መነሻው አዕምሮን ሙሉ በሙሉ መጠቀም ያለመቻል ነው፡፡ ትክክለኛውን ሰውነቱን ፈልጎ ያላገኘ የማይጠቅመውን አውሬነቱን ይወዳጀዋል፡፡ ሰውነቱን የተረዳ የሌላውን ሰውነት ይረዳል፡፡ በራሱ ሕይወት ውስጥ የጠለቀ በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ ጥልቅ ማለት እንደሌለበት ዕውቀት ያገኛል፡፡ ሌላው ወደራሱ ሕይወት ይሰምጥ ዘንድ ነፃ ፈቃድ እንዳለው ይረዳል እንጂ በማያገባው በሌላ ሰው ሕይወት ባህር ውስጥ ዘው ብሎ አይገባም፡፡ ከአዕምሮው ጋር የተግባባ አዕምሮውን ይስላል፤ በሣለው አዕምሮ ባህሪውን ይሞርዳል፣ ስሜቱን ይገራል፡፡ የሚቀርፅ ሕሊና በራሱ ተሰርቶ የተዘጋጀ (Ready-made) አይደለም፡፡ ገንቢ ሕሊና ቀድሞውኑ በመልካም አስተሳሰብ የታነፀ ነው፡፡ አንተ ሕሊናህን በወጉ ካልሰራኸው አንተን እንደአዲስ አይሰራህም፡፡ እንዲሰራህ ልትሰራው ይገባል፡፡ እንዲያውቅህ ልታውቀው ግድ ይላል፡፡ ወደውስጡ ስትጠልቅ ይዘህ የምትወጣው ራስህን ነው፡፡ ወደባህሩ አንተነትህ ስትሰምጥ የምታገኘው ሰውነትህን ነው፡፡ ብልህ ሰው አዕምሮውን ይሠራል፤ በሰራው ሕሊና እየተመራ የሕይወት ኮምፓሱን ያስተካክላል፡፡ ወዳጄ ሆይ…… ወደሕሊናህ እልፍኝ ጎራ በል፡፡ ውስጣዊው ዓለምህን ብቅ በልና ጎብኘው፡፡ ያልተጎበኘ ማንነት፣ ያልተስተናገደ ምንነት ትርጉም የለውም፤ ማን ይሁን፣ ምን ይሁን አይታወቅም፡፡ የሌሎች ባሪያ ይሆናል እንጂ የራሱ ተገልጋይ አይሆንም፡፡ ከራስ ጋር መጠፋፋት እውን የሚሆነው ከራስ ጋር በወጉ ባለመተዋወቅ ነው፡፡ የደግነት፣ የፍቅርና የቅንነት ባላንጣ፤ የመተባበርና የአንድነት ጠላት የሚሆኑ ሰዎች ከራሳቸው ጋር የተጠፋፉ፤ ሰውነታቸውን የዘነጉና መልካሙን ሁሉ ከሕሊናቸው ጓዳ አውጥተው በክፉ የተኩ ናቸውና፡፡ ለማንናውም በስንኝ ልሰናበትህ………… ………………. ሰው መሆንን አስተምረው! (እ.ብ.ይ.) ሕሊናህን ጥለቅበት፤ አዕምሮህን ስመጥበት! ሰው’ነትህን እንድታወጣበት፣ ምንነትህን እንድታውቅበት፣ ማንነትህን እንድትሰራበት፣ ሰው ሆነህ እንድትበቃበት፡፡ ልቦናህን ዝለቅበት፤ መንፈስህን ርቀቅበት፣ ስሜትህን እንድትገዛበት፤ ዓለምህን ተመራምረህ፤ አንተነትህን ዝመትበት፣ ኖረህ እንድትረካበት፤ መልካም ፍሬ እንድታፈራበት፤ አውቀህ እንድትፀድቅበት፡፡ ነፍስያህን አነጋግረው፣ ውስጠትህን መርምረው፣ ጭንቅላትህን አማክረው፣ አንተነትህን ንገረው፣ ሰው መሆንን አስተምረው፡፡ ………… ቸር ጊዜ!
Show all...
Late make this photo our profile
Show all...
"መፍራት ችግር የለውም ፣ ማልቀስ ምንም ችግር የለውም ፣ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል ፡፡ ግን ተስፋ መቁረጥ አማራጭ መሆን የለበትም ሁሌም ይናገራሉ ውድቀት አማራጭ አይደለም ይላሉ ፡፡ አለመሳካት አንድ አማራጭ መሆን አለበት ምክንያቱም ባይሳካሎት ከወደቁበት ይነሳሉ እና እርስዎ የሚሄዱበትን እንደገና ይመርጣሉ ፡፡ ያ ሰው እንዴት ጠንካራ ነው አለመሳካት አማራጭ መሆኑን የተረዳ ግን ግን መተው በጭራሽ አማራጭ አይደለም" ☝️ የቻናላችን የሳምንቱ ምርጥ ሃሳብ 💚ውብ አሁን💚 ┄┄┉✽̶»̶̥ ͜͡ ❀🌼❀ ͜͡»̶̥✽̶┉┄ @a2jaedu
Show all...
እንዳትወጣ የሚጎትቱህ ብዙዎች ናቸው! _________________________ ምቀኝነት አይደለም፤ ምቀኝነት የሚመስል ግን ካለማወቅ የሚመጣ ባህሪ ነው። አንዳንዴ እራሳችንን ለመለወጥ እናስብና ሌሎችን ማሳመኑ ዳገት ይሆንብናል። ከሱሰኝነት ለመላቀቅ ብንወስን፤ ሱስ ውስጥ የተዘፈቁትን ጓደኞቻችን ጥለን መሄዱ ይከብደናል፤ እኛ ብንለውጥ ጓደኝነታችን ይቀራል ብለን ስለምናስብ። _________________________ እረጅም አመታትን በሌብነት የኖረ ሰው ስራው ጸጽቶት ቢለውጥ እንኳ፤ ማህበረሰቡ አያስለውጠውም። ሁሌም እንደሌባ ስለሚታይ፤ አለመታመኑ ለመለወጥ ካደረገው ትግል በላይ ይከብደዋል። ሱስን እና ሌብነትን እንደምሳሌ ወሰድኩኝ እንጂ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ውስጥ ብንሆንም፤ እራሳችንን እንዳንለውጥ የሌሎች ተጽዕኖ ከባድ ነው። _________________________ የሚገርመው ደግሞ እራስን ለመለወጥ ሲታሰብ ትልልቆቹ እንቅፋቶች የምንቀርባቸው ስዎች መሆናቸው ነው። ምቀኝነት አይደለም፤ ዋና ምክንያታቸው የለመዱትን ማንነታችንን ማጣት ስለማይፈልጉ ነው ። “ምነው እንደድሮህ አይደለህም?” እያሉ ለውጣችን ስህተት እስኪመስለን ደረስ ይሞግቱናል። _________________________ ለምሳሌ ሁሌም አብረሃቸው የማይረባ ነገር እየሰራህ ጊዜህን ስታባክን የሚያውቁህ የቅርብ ጓደኞችህ፤ የጊዜን ዋጋ አውቀህ ጊዜህን በአግባቡ መጠቀም ስትጀምር “ምነው ተለውጥክ፤ በጣም ኮራህ፤ እንደድሮ አይደለህም” በማለት ለውጥህ ስህተት እንደሆነ ይነግሩሃል። _________________________ እንዳልኳችሁ ምቀኝነት አይመስለኝም፤ አዲሱን ማንነትህን ለመቀበል ስለከበዳቸው ብቻ ነው። ማርከስ ጋርቬይ ለጥቁሮች ነጻነት ሲታገል ከነጮች በላይ ጥቁሮችን ማሳመን እዳ ሆኖበት ነበር። _________________________ የምነቀርባቸው እና የምናውቃቸው ሰዎች ሁሌም ለለውጣችን እንቅፋቶች መሆናቸው አይቀርም፤ አውቀው በክፋት የኛን መልካም ነገር ላለማየት ብለው ሳይሆን፤ ስንለወጥ የለመዱትን ማንነታችንን እንደሚያጡት በመስጋት አልያም ለኛ የተሻለው ነገር እነሱ የሚያስቡት ነገር ስለሚመስላቸው ነው። ይህንን የሚያስረዳ ድንቅ አባባል ከማከስ ጋርቬ መጽሃፍ ላይ ቀንጠብ አድርጌያለው። _________________________ “we are like crabs in a barrel. That none would allow the other to climb over, but on any such attempt all would continue to pull back into the barrel the one crab that would make the effort to climb out” _________________________ “እኛ ማለት በጎድጓዳ ገንዳ ውስጥ እንዳለን ነፍሳቶች ነን፤ ማናችንም ሌላው ከገንዳው እንዲወጣ አንፈልግም፤ እንደው ጥሮ ግሮ እራሱን ከገንዳው ለማውጣት የሞከረ ካለም፤ ከጫፍ ሲደርስ ሌላው ተባብሮ ወደታችን ይጎትተዋል” _________________________ እውነት ነው፤ እኔ በበኩሌ ገንዳውን እንደህይወት ልምድ ወይም ባህሪ እወስደዋለው። ብዙ ሰዎች በድሮ ባህይሪያችን ወይም ልምዳችን ለምደውናል፤ እራሳችንን ለማሻሻል ከገንዳው ለመውጣት ስንታገል ይጎትቱናል። _________________________ እንዳልኳችሁ እኔ በምቀኝነት አይመስለኝም ባለማወቅ እንጂ። ውሳኔው እንግዲህ እዚህ ላይ፤ ነጻነትህን የሚሰጥህ የመረጥከውን ጎዳና የሚቀበልልህ ካለ እሰየው፤ ሊያስቆሙህ የሚሞክሩት ግን ያንተ ለውጥ ስህተት ሆኖ ሳይሆን (መልካም ለውጥ እስከሆነ ድረስ) የነሱን መንገድ መከተል ስላቆምክ ነውና አያሳስብህ። _________________________ ጓደኛ እና ቤተሰብ መስዋት ሊከፈልላቸው የሚገቡ ነገሮች እንደሆኑ አምናለው፤ ነገር ግን የአላማችን እንቅፋት እንዲሆኑ መፍቀድ የለብንም። ስንት ስኬታማ ሰዎች ናቸው በስተመጨረሻ ሲመሰክሩ “ቤተሰቦቼ እንድሆን የሚፈልጉት ነገር ሌላ ነበር፤ ከቤተሰብ እና ወዳጅ ደጋፍ አላገኘሁም” ብለው የሚመሰክሩት። _________________________ በእርግጠኝነት አላማናችንን የማይደግፉት ብዙዎች ናቸው፤ በተለይ የምናውቃቸው እና የምንቀርባቸው ሰዎች። ነገር ግን አላማችን እውን ከሆነና ስሩን ከሰደደ ማን ሊያቆመን ይችላል? ሌሎች እንዲወዱን ብቻ ብለን የማንፈልገውን ኑሮ መኖር የለብንም!!! _________________________ @a2jaedu
Show all...
ኢንተርፕርነር ሺፕ ማለት ምን ማለት ነው? _____________________________ ኢንተርፕርነር ሺፕ /የስራ ፈጠራ / ፅንሰ ሀሳብ የተጀመረው ለ 18ኛው ክፍለ ዘመን (1700 ዎቹ ) ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ቢዝነስ አስተሳሰብ ሲቀነቀን እስከ አሁን እስካለንበት የ21ኛው ክ/ዘመን ደርሷል፡፡ ብዙዎች ይህንን ፅንሰ ሃሳብ ከግል ስራ ፈጠራ (በግል ስራ መጀመር) ጋር የሚያያይዙት ሲሆን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ደግሞ ከዚህ ባለፈ ተጨማሪ ትርጉም እና ትንታኔ ይሠጡታል፡፡ _____________________________ አንድ አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ኢንተርፕርነር (ስራ ፈጣሪ) ማለት ከዚህ በፊት ያልተጀመሩ / ያተሞከሩ/ ትርፋማ ስራዎች ለመጀመር የሚደፍር እና ሊከተሉ ለሚችሉ ኪሳራዎች ሃላፊነት ለመውሰድ የሚደፍር ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ገበያ የሚቀርብን ሰው ስራ ፈጣሪ /ኢንተርፕረነር) በማለት ይበይናሉ ፡፡ አንድ አንድ ግለሰብ ኢንተርፕረነር ነው የሚያስብለው አዳዲስ ምርቶች እና ምርት ሂደቶችን በማስተዋወቅ ሰፊ የገበያ ድርሻን ለማግኘት የሚሞክር ነው ሲሉ በርካታ የመስኩ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ _____________________________ ይህ በእንዲህ እያለ በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በመሰረታዊነት በአንድ ነገር ላይ ይስማማሉ፤ አንድ ሀገር ምጣኔ ሃብት ለማሳደግ እንዲሁም በርካታ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ሁነኛው መንገድ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕርነርሺፕ) መሆኑን። ከእንደኛ ዓይነት ሀገራት ( እያደጉ ባሉ ሀገራት) አዳዲስ እና ጀማሪ የስራ ዘርፎች በስራ እድል ፈጠራ፣ በገቢ እድገት እንዲሁም በድህነት ቅነሳ በኩል ለሃገሪቱ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ በእነዚህ ሀገራት ያሉ መንግስታት ለእነዚህ አዳዲስ የስራ ዘርች ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ አንዳንድ ግለሰብ ስራ ፈጣሪ የሚያሰኙት መሰረታዊ ባህሪያት _____________________________ በአለማችን ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች ከተለያየ ይህ ህብረተሰብ ክፍል የተገኙ፣ የተለያዩ ዘር፣ እምነት፣ሃይማኖት፣ ፆታ እና የእድሜ ክልል ቢኖራቸውም እነዚህን መሰረታዊ ባህሪያት ግን ይጋሯቸዋል፡፡ የፈጠራ ችሎታ _____________________________ አዳዲስ ምርቶችን አገልግሎቶች እና የአሰራር ስልቶችን ማስተዋወቅን የሚያካትት ሲሆን የፈጠራ ችሎታ በስራ ላይ ለሚገኙ ምርቶች እና አገልግሎቶች መሻሻል አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ባህሪ በመጠየቅ፣ በመማር እና ምርምር ከማድረግ ማዳበር ይቻላል፡፡ ቁርጠኝነት፡- _____________________________ ይህ የስራ ፈጣሪዎች ባህሪ በተለየ ሁኔታ እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው ባህሪ ነው፡፡ ስራ ፈጣሪዎች ከሌላው በበለጠ ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው ሃሳቦቻቸው እና የአሰራር እቅዳቸው ከተግባር ጋር ሲጣመር ቁርጠኝነት ይባላል፡፡ ፅናት፡- _____________________________ ጠንካራ ፍላጎትና አላማን ይዞ እስከ ስኬት መዝለቅ የፅኑ ሰዎች መለያ ነው፡፡ ይህም ሲባል በጥንካሬ ያለማቋረጥ ላስቀመጡት ዓላማ በትጋት መስራት እና ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች እጅ አለመስጠት ማለት ነው፡፡ በርካታ ሙከራዎች ባይሳኩ እንኳን እስኪሳካ መማርና ለስኬት መድረስ የስራ ፈጣሪዎች ዋነኛ መገለጫ ባህሪ ነው፡፡ ለለውጥ ዝግጁነት _____________________________ ገበያው በሚፈልገው መልኩ አካሄድን በማድረግ እና ለአዳዲስ ሃሳቦች አዕምሮን ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡ የገበያውን እውነታዎች በመረዳት ተለዋዋጭ የገበያ እቅዶችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ ይህም ለአንድ አዲስ የስራ ፈጣሪ ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡ መሪነት _____________________________ ተገዢ የሚሆኑበት ሕግ በማዘጋጀትና እና ግልጽ የሆነ ግብን በማስቀመጥ ወደ ስኬት የሚያደርስ ልዩ ክህሎት ነው፡፡ ጠንካራ ፍላጎት፡- _____________________________ ይህ ባህሪ የአንድን ስራ ፈጣሪ እስከ መጨረሻው እንዲፀና የሚደርገው ሲሆን ሌሎችንም በስራው ለማሳመን የሚረዳ ነው፡፡ በራስ መተማመን ፡- _____________________________ ይህ የእርግጠኝነት ባህሪ ሲሆን ጥርጣሬን ከሕሊና በማስወገድ አንድ ፈጣሪ ሙሉ አቅሙን ስራው ላይ ብቻ እንዲያው ያስችለዋል፡፡ በራስ መተማመን የሌሎች ሠዎችን ትችት እና አስተያየት ያለምንም የአቋም ለውጥ ለመቀበል ያስችላል፡፡ _____________________________ #ሼር# @a2jaedu
Show all...
የጭንቀት ምንጮች ምንድን ናቸው? _______________ የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡- አካላዊና ስነ ልቦናዊ ምንጮች፡፡ እነዚህም የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡- _______________ •- በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና • -የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት • -ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር • -መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ… • -ለአዳዲስ ነገሮች መዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ • -የትራፊክ መጨናነቅ • -ከፍተኛ ድምፅ • -ህመም _______________ •- ክፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜ • -አካላዊ ህመም፣እንቅልፍ ማጣት፣ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይ የሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው ቲምና ፔተርሰን (Timm and Peterson) የተባሉ ምሁራን በተለይ በሥራ አካባቢ የጭንቀት ምንጮች የሚላቸውን እንደሚከተለው ይዘረዝራሉ። _______________ • -ውጤታማ ያልሆነ ተግባቦት (Communications) • -አግባብነት የጎደለው የመስሪያ ቤት አሰራር • -ከመጠን በላይ የሆነ የመረጃ ብዛት • -ወጥ ያልሆነ የሥራ አስኪያጆች ወይም የመሪዎች ባህሪ •- ከመጠን ያለፈ የስራ ብዛት ወይም ጫና • -አዲስ ሥራ መግባት • -የግል ችግሮች • -ጭንቀትን የሚዘሩ ግለሰቦች- በንግግራቸው ሁሉ ጭንቀት የሚፈጥር ወሬን የሚያወሩ (Stress carriers ይባላሉ) _______________ •- የ ድርጅቶች ደሞዝ፣ፖሊሲ እና የስራ አካባቢ(working conditions) _______________ •- የሥራ ቦታዎች ከፍተኛ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ፣ ከፍተኛ ብርሃን ወይም ድንግዝታ ለጭንቀት መነሻዎች እንደሆኑ በፃፉት መፅሃፍ ላይ ይገልፃሉ፡፡ የጭንቀት ውጤቶች ምንድናቸው? _______________ •- የሰውነት ድካም • -ከፍተኛ የራስ ምታት •- ብስጭት • -የምግብ ፍላጎት መዛባት • -የማስታወስ ችሎታ መቀነስ • -ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem) • -ከማህበራዊ ህይወት መገለል • -የ ደም ግፊት መጨመር • -ትንፋሽ ማጠር • -የወሲብ ፍላጎት መቀነስ • -የእንቅልፍ መዛባት • -የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት ወዘተ ከእነዚህም በተጨማሪ ጭንቀት የልብ ህመምን፣ የቆዳ ችግርን(skin disorders) እና ሜታቦሊዝምን (በሰውነታችን ውስጥ የሚካሄዱ ኡደቶችን)የማዛባት አቅም አለው ተብሎ ይታመናል፡፡ በተጨማሪም ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡ ጭንቀት ስነልቦናዊ ችግር ነው ቢባልም አካላዊ ተፅእኖን ይፈጥራል፡፡ ጭንቀትን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብን ? _______________ ___________ ጭንቀትን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብን ? _________________________ ከላይ የተጠቀሱት ምሁራን ለጭንቀት መላ ይሆናሉ ያሉትን መፍትሄዎች እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፡- _________________________ ለአፍታ ዞር ይበሉ፡- ጭንቀት ከፈጠረብዎ ሁኔታ ወይም ሌላ ምንጭ ዞር ይበሉና የማሰቢያና የማሰላሰሊያ ጊዜ ይውሰዱ፡፡ _________________________ ያውሩት፣ይናገሩት፡- ለቅርብና ለሚያምኑት ሰው የጭንቀትዎን ስሜት ይናገሩ፡፡ ባወሩ ቁጥር ይቀልልዎታል፡፡ ወጣ ብለው የሚወዱትን ይጫወቱ፡- የእግር ጉዞ ያድርጉ፣ ደረጃዎችን ወደ ላይና ወደ ታች ይውጡ፡፡ አንዳንዴ እጅ ይስጡ፡- ለምሳሌ እርስዎና ባለቤትዎ ወይም አለቃዎ “ይሄ ነው ትክክል ያኛው ነው ትክክል ” እያሉ ሙግት ከገቡና ጉዳዩ ብዙ ለወጥና ተፅዕኖ የማያመጣ ከሆነ ችላ ይበሉት፤ አንዳንዴ እያወቁ ይተውት፡፡ _________________________ ለሌሎች መልካም ነገር ያድርጉ፡ -በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ሲገቡና ሃዘን ውስጥ ሲሆኑ ችግረኞችን በመርዳትና ልገሳ በማድረግ ይሳተፉ፤ ቀለል ይልልዎታል፡፡ በአንድ ጊዜ አንድን ነገር ይስሩ፡- ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለመስራት መሞከር ጭንቀትን ስለሚያባብስ እንደ ስራዎቹ ጠቃሚነትና አስቸኳይነት ቅደም ተከተል በማሲያዝ በአንድ ጊዜ አንድን ነገር ይስሩ፡፡ _________________________ የታላቁን ሰው ፍላጎት አድብ ግዛ ይበሉት፡- አንዳንዴ የራስዎንም ሆነ የሌሎች ሰዎችን ችግር በሙሉ ራስዎ መፍታት እንደሚችሉ ማሰብዎ “በውስጥዎ ያለው የሃሰተኛው ትልቅ ሰው urge of superman” ምክር ነውና አድብ ግዛ ይበሉት፡፡ እርስዎ የሁሉንም ሰው ችግር ፈቺ አይደሉም፡፡ ትችትን መቋቋም ይለማመዱ፡- አንዳንድ ሰው ትንሽ ትችት እንቅልፍ ትነሳዋለች፡፡ በተጨማሪም ሌሎችንም ከመተቸት ይቆጠቡ። ቶማስ ፍሬድማን የ “ The world is flat” ፀሃፊ በዚህ አለም አንድ መንደር በሆነችበት ግሎባላይዜሽን ዘመን ለትችት ቆዳህን አወፍር (Make your skin thick) ብሎ ይመክራል፡፡ ለሌሎች ራስህን አስገኝ፡- ሰዎች ሲፈልጉህ ተገኝላቸው፡፡ _ ብቻ መርጦ ማየት(Filtering)፣ ይህንን አስቦ ነው ብሎ ያለምንም ማስረጃ ድምዳሜ ላይ መድረስ (Mind reading)፣ሰዎችን መተቸትና መውቀስ (Blaming)፣ለራስ ስያሜ መስጠት ለምሳሌ ደካማ ነኝ፤ዋጋ ቢስ ነኝ ወዘተ ማለት (Labeling) አግባብ ላልሆኑ አስተሳሰቦች ምክኒያት ናቸው ይሉናል፡፡ _____________________ የ ABCDE ቴክኒክን ተንትነን ለማየት እንሞክር Antecedent(Activating event, Stimulus)፡ ይህ ማለት ጭንቀትን የሚቀሰቅሰው ሁኔታ ወይም ነገር ነው(ተንኳሽ እንበለው)፡፡ _____________________ ይህ ተንኳሽ የኛን ምላሽ (Response) ይጠይቃል። ለምሳሌ ከስንት አንድ ቀን ቀጠሮ ብናረፍድ ጭንቀት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት ጭንቀትን የሚፈጥርብን ጉዳይ ማርፈዳችን ነው ማለት ነው፡፡ _____________________ Belief-our cognition about the situation፡- ይህ እንግዲህ ስለ ተንኳሹ ያለን ሃሳብና እምነት ነው፡፡ ለምሳሌ ማርፈዴ ያለኝን ተቀባይነት ያሳጣዋል፣ በምንም አይነት ምክኒያት ቢሆን ማርፈድ አሳማኝ አይደለም ወዘተ የሚል እምነት ማለት ነው፡፡ _____________________ Consequences-the way that we feel and behave፡ ይህ ውጤት ነው - ጭንቀታችን፡፡ ይህ ምን ባህሪ ይፈጥራል? ቶሎ ለመድረስ አላግባብ ጣልቃ እየገባን መኪናችንን መንዳትን፣ በእጃችንም በአንደበታችንም የተንቀረፈፈ የመሰለንን ሾፌር መስደብ፣መቆጣት፤ ከአስፋልት ወጥቶ በእግረኛ መንገድ መንዳት ወዘተ ማለት ነው፡፡ _____________________ እዚህ ላይ አልበረት ኤሊስ ይሞግታሉ “ያስጨነቀን ማርፈዳችን ነው ወይስ ስለ ማረፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው?” አሳቸው እንደሚሉት፤ ውጤቱን የፈጠረው ማርፈዳችን(stimuls ) ሳይሆን ስለ ማርፈድ ያለን አስተሳሰብና እምነት ነው ባይ ናቸው፡፡ _____________________ Dispute is the process of challenging the way we think about situa
Show all...
Feeling sorry for yourself and your present condition is not only a waste of energy but the worst habit you could possibly have” dale carngie “እራስህን እንደምስኪን መቁጠሩና አሁን ላለህበት ሁኔታ ስለራስህ እያሰብክ መቆዘሙ አቅምህን የሚያባክን ብቻም ሳይሆን፤ ለማስወገድ የሚከብድ  እጅግ መጥፎ ባህሪም ጭምር ነው።” ዴል ካርኒጊ እርግጥ ነው  ከልጅነታችን ጀምሮ በህይወታችን ላይ የሚያርፈው የሌሎች ሰዎች አስተዋጽዎ ቀላል አይደለም። ነፍስ ካወቅን ጀምሮ ግን ህይወታችንን በራሳችን ቁጥጥር ስር የማድረጉ አቅም አለን። ይህ አቅም  ነፍስ መዝራት የሚችለው ግን  በራሳችን ላይ የተስተካከለ አመለካከት ሲኖረን በቻ ነው። የሚከተሉት ነጥቦች እራሳችንን ከተበዳይነት  ስሜት እንድናወጣ የሚረዱን ነጥቦች ናቸው- – የዛሬው ህይወትህ የነገውን ማንነትህን ሊገልጸው አይችልም– “If you treat an individual as he is, he will remain how he is. But if you treat him as if he were what he ought to be and could be, he will become what he ought to be and could be.” -Johann Wolfgang- ሰውን አሁን ባለለበት ሁኔታ አልያም ባለፈው ህይወቱ ከዳኘነው፤ ሊሆን የሚችለውን ማንነቱን ወይም ያለውን አቅም  ማየቱ ይሳነናል። አንዳንዴ የማይገልህ በሽታ ይበልጥ ያጠነክርሃል ይባላል። ያሳለፍናቸው መከራዎች እና ፈተናዎች ጥንካሬዎቻችን እንጂ ማነቆዎቻችን ሆነው ቀሪው እድሜያችንን የታሪካችን እስረኛ ሊያደርጉን አይገባም። ትልቁ በቀል የግል ስኬትህ ነው– “The best revenge is massive success” -Frank Sinatra- ወደታችን የጎተቱህን መበቀል የምትችለው ከፍ ብለህ ስትገኝ ብቻ ነው። በቀል ስል አይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ የሚሉት አይነት በቀል ሳይሆን፤ መልካም በቀል ነው። ምናልባት ሰዎች ትላንት በተለያየ መልኩ ጎድተውህ ይሆናል። ሁለተኛ እንዲጎዱህ የምትፈቅድላቸው ግን የበደላቸውን ትዝታ ይዘህ ስትኖር ነው። “እንዲህ ባይሆን ኖሮ……” እያልን በትላንት ላይ ስንቆዝም ዛሬ መፍትሄውን እንደያዘ ከፊታችን ይጠፋል…… እራስህን እንደ ምስኪን መመልከቱን አቁም– አንድ አንድ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ሌሎች ያደረጉባቸውን በደል ሲያስቡ ለመፍትሄ የሚሆን ጊዜ ያጣሉ። እራስን እንደምስኪን ወይም እንደ ተበዳይ መቁጠር በራስ የመተማመንን ስሜት ከማጥፋቱም በላይ በራሳችንም ሆነ በሌሎች ላይ የለንንን እምነት እንድናጣ ያደርገናል። እንደውም ሌሎችን በጥርጣሬ እንድንመለከት የሚይደርገን ትልቁ ምክንያትም  ይህ ነው።  ለውስጥህ ሰላም መደፍረስ በዙሪያህ ያሉትን ነገሮች መውቀሱን አቁም- “Stop blaming outside circumstances for your inside chaos.” -Steve Maraboli – የደፈረሰን ኩሬ ከውጪ ሆኖ ሊያጠራው የሚችል ምንም ነገር የለም። የደፈረሰ ኩሬ ሊጠራ የሚችለው መማሰሉ ሲቆም ብቻ ነው። የሰው ልጅም ሰላም እንዲህ ነው በውጪ ሃይል ሳይሆን በውስጣዊ መረጋጋት የሚሰክን መንፈስ ነው። እራሳችንን እንደምስኪን ወይም ተበዳይ ስንቆጥር የውስጣችንን ሰላም በትዝታ ማማሰያ እያደፈረስን መሆኑን እናስታውስ።  አየሩን መለወጥ ካልቻልክ አለባበስህን አስተካክል- “You must take personal responsibility. You cannot change the circumstances, the seasons, or the wind, but you can change yourself. That is something you have charge of.” ― Jim Rohn–  እንደሰው አቅማችን ውሱን ነው። በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ የመለወጥ አቅሙ የለንም። ጸሃይዋ ለምን እንዲህ ሞቀች ብለን ከጸሃይ ጋር ሙግት አንገጥምም፤ ሙቀቱን ለመከላከል ዣንጥላ እንይዛለን እንጂ። ሲበርድም እንደዛው። ቀዘቀዘ ብለን ከብርዱ ጋር አይንጣላም፤ ልብስ እንደርባለን እንጂ። ይህ ህግ ለጸሃይ እና ለብርድ ብቻም ሳይሆን ለሁሉም ነገሮች ይሰራል። ሌሎችን ወይም የሌሎችን አስተሳሰብ የመለወጥ አቅም የለንም ልክ የዝናቡን መጠን የጸሃዩን ሙቀት መወሰን እንደማንችል ሁሉ። ስለዚህ እራሳችንን ከሌሎች ቀንበር ለማላቀቅ ይህ አመለካከት ወሳኝ ነው፤ አቅም ያለን እራሳችንን ላይ ብቻ ነው። @a2jaedu
Show all...