en
Feedback
⛺️✟ ቤተ አብርሃም ✟

⛺️✟ ቤተ አብርሃም ✟

Open in Telegram

በአብ ስም🟠በወልድ ስም🟠በመንፈስቅዱስ ስም🟠 አንድ አምላክ አምናለው! አምኜም ጠላቴ ሰይጣንን እክደዋለሁ ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት! ✝ ዜና ቀዳ 29÷13✝ አምላካችን ሆይ እንገዛልሃለን : ለክቡር ስምህም ምስጋና እናቀርባለን። ◍ይህ የቤተ አብርሀም ማህበር ቻናል ነው◍ ►►► @bete_abraham for any comment ▷ @Lulastuareil22

Show more
3 474
Subscribers
+324 hours
+37 days
+330 days
Posts Archive
photo content

photo content

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

​​ ◽️ታቦር አበራ◽️ ታቦር አበራ ምድርን ከደናት ያደመና እንቅልፍ የለንም ታላቅ ነጎድጕድ ሆኗልና አነቃን ለምስጋና ሙሴም የቀደመው ሰዉ  ኤልያስ ኃይለኛው ተገኝተዋል በታቦር ምስክርህ ሆነው እኛም ከገናናው ክብር ያባቱን ቃል ሰምተናል በረዶ ሆኗል ልብሱ እፁብ እፁብ ብለናል አዝ==== ቃል ገብተህልኝ ነበር ልታሳየኝ ክብርህን ንገስ ከሞት ገስግሰህ አይቼሃለሁ አሁን የእሳት ፈረሶች አሉህ ታዋጊው የኔ ጌታ አርሞኒየም ደስ አለው ሲሳራን ስለመታ አዝ==== እጠብቅሃለሁኝ በምታልፍበት ቆሜ መብራቶቼን አብርቼ ነጩን ልብስ ተሸልሜ የዳዊት ልጆ ሆይ ግባ ኢየሱስ ወደቤቴ ብንኤል እልሀለሁ ድናለች ሰውነቴ አዝ==== ሁሉንም ብታከብር ሁሉንም ብትምረው ማነው ቸርነትህን የሚከለክለው ጠዋትም የተጠራ አምሽቶ የገባው ሆነዋል ባለዋጋ ከበዛው ስጦታው አዝ==== የረዳኸው ይናገር ያሰብከው በሕይወቱ አቤኔዘር እያለ ይዘምር ባንደበቱ በደስታዬም ቀን አለህ አይሃለሁ ከጎኔ ከኔጋር አልቅሰሃል አሳዝኖህ ሀዘኔ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

photo content

photo content

photo content

photo content

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

◽️ ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ◽️ ለክብርሽ አለኝ ምስጋና ከትውልድ አንዱ ነኝና ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስለረዳኝ ነው ሳልታክት የምዘምረው ኪዳንሽ ስላገዘኝ ነው በሔዋን መተላለፍ መች ቀረው ምድረበዳ በልጅሽ ቤዛ መሆን አመለጥኩኝ ከፍዳ አልቀረም ከንቱ ሆኖ ነቢያት ትንቢታቸው ተፈጽሟል ድንግል ሆይ መሰላል ሆነሻቸው አዝ==== የሕይወት ውኃ ጠጣው ከማህጸንሽ መንጭቶ ከድካም አሳረፈኝ መዳፎቹን ዘርግቶ በላይ በሰማያት ጫፍ ለከበርሽው እናቴ ጸጋሽን ሊመሰክር ተፈቷል አንደበቴ አዝ==== ወደ እኔ ስትመጪ ዘለልኩኝ በደስታ ነፍሴን በሐሴት መላት የአንደበትሽ ሰላምታ አንቺ ከእኔ ጋር ካለሽ በአንዳች አልሰጋም ቃል አለና በሆድሽ የሚሰጠኝ ሰላም አዝ==== የሕይወት ውኃ ጠጣው ከማህጸንሽ መንጭቶ ከድካም አሳረፈኝ መዳፎቹን ዘርግቶ በላይ በሰማያት ጫፍ ለከበርሽው እናቴ ጸጋሽን ሊመሰክር ተፈቷል አንደበቴ አዝ==== ማርያም ማርያም ስላልኩኝ አትሸበር ጠላቴ ገና ከፍ ያደርጋታል ዜማዬና ቅኝቴ በኤልሳቤት ውዳሴ በገብርኤል ሰላምታ አንደበቴን ሳልሰስት አከብራታለው ገና ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

photo content

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

◽️የአፎምያ እረዳት◽️ የአፎምያ እረዳት ነህ ሚካኤል/2/ ቅሩበ እግዚአብሔር የልዑል ፈጥነህ ድረስልን ስንጠራህ ሚካኤል አዝ==== ፊት ለፊታችን አምላክ ሠደደህ አቀናህልን መንገዱን ጠርገህ የቤንሆርን ምክር አፈረስክ ከልጆችህ ጋር ከነዐን ደረስክ ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን አዝ==== በቃዲስ ክንፍህ ተዘርግቶልን ደመናው በአንተ ተጋረደልን አብረኸን ልትሆን ጌታ የላከህ አንተ ሚካኤል ታዳጊያችን ነህ ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን አዝ==== ሙሴ ሲለየን ደጉ አባታችን ሚካኤል ነበር ከላይ መሪያችን የማንነቱ ጉዞ እስኪያበቃ እጅግ እረዳን የኛ ጠበቃ ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን አዝ==== ሳጥናኤል መክሮን የሀሰት ምክር ሊወስደን ሻተ ሙሴ መቃብር ስለማይጠቅመን አንተ ሠወርከው ምክሩን በታትነህ አስጎነበስከው ከኛ ጋር ነበርክ አርባውን ዘመን እንጠራሀለን ሚካኤል ብለን ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

◽️ ማር ሚካኤል ◽️ ማር ሚካኤል ልበል ማር ሚካኤል ልበልህ (፪) ባርከህ አሳደከኝ በቅኔ በዜማ መዝሙር አልሰስትም አባቴ ለአንተማ ጅማሬ ታናሽ ያልበቃው ብሆንም እንድፀና አውቃለው ከፊቴ ስትቀድም ፍጻሜዬ እንዲያምር እንዲዋብ በቤትህ አበርታኝ ልበርታ አፅናኝ ልፅና ልጅህ ባሕሩን ክፈለው በደረቅ እንዳልፈው እንዳልፈራ አበርታኝ እጄን በእጅህ ያዘው አዝ==== ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደውል በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል በሄድኩበት ሁሉ ከአፌ አትነጠልም የማር ወለላ ነው ሚካኤል የአንተ ስም ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ መውደዴ የእውነት ነው በምልጃህ ተርፌ አዝ==== በሞቱ ቀጠሮ ሰርግ የደገስክለት ምን አለ ባሕራን ስታተርፈው ከሞት ዛሬም ታምርህን ፅድቅናህን አይተው ብዙዎች ይሉሃል ሚካኤል ሙት አንሳው ረዳኤ ምንዱባን በስደት ደጋፊ ከክፉ ከልለህ በድል አሳላፊ አዝ==== አለቱን ከፍለኸው በበትረ መስቀል ከጭንጫው ሰጠኸን ማር እና ጸበል ቀድሞ ለእስራኤል ያኔ እንዳደረከው ያኔ የሰማነውን ዛሬ ሆኖ አየነው የብርሀኑን አምድ ፋና ተከትለን ከቅዱሳን ስፍራ ዛጀርማኤል ደረስን አዝ==== ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደውል በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል በሄድኩበት ሁሉ ከአፌ አትነጠልም የማር ወለላ ነው ሚካኤል የአንተ ስም ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ መውደዴ የእውነት ነው በምልጃህ ተርፌ              ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

◽️ የስሙ ትርጓሜ ◽️ የስሙ ትርጓሜ ማን እንደ እግዚአብሔር ነው የሰውን ወደ አምላክ የአምላክን ወደ ሰው እኛን የሚረዳን ዘወትር በምልጃው የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው[፪]                ከጉድጓድ ተጥሎ ፍፁም ከሚያስፈራው ከተራቡ አናብስት ዳንኤልን ያዳንከው እኛንም ተራዳን ቸል አትበለን ሰይጣን በተንኮሉ ወጥመድ ሳይጥለን አዝ==== የክፉ ሰው ስራው ክፉ ሃሳብ ነውና በቅንነት መንገድ ከቶ አይሄድምና የሞቱን ደብዳቤ ለባህራን ሲሰጠው ሚካኤል አጥፍቶ በደስታ ለወጠው አዝ==== ገና ብላቴና ሳለው አንድ ፍሬ ሰው ሁሉ ሲንቀኝ ምስጋናን ጀምሬ ጸጋዬን አብዝቶ ያበቃኝ ለዚህ ክብር የሚካኤል አምላክ ይመስገን እግዚአብሔር    ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥        

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

◽️ሰማዕቷ አርሴማ◽️ የልቤን የውስጤን ምስጢሬን አዋቂ በደለኛ ልጇን ከአምላክ አስታራቂ ዕንባዬን ፀሎቴን ዘውትር የምትሰማ ወዳጄ ነች ለኔ ሰማዕቷ አርሴማ/2/ ስፍራውን ሲለቅ ሀዘኔ በውስጤ ሰላም ሲሰማኝ የደስታዬ ምክንያት አርሴማ ለኔ አለችልኝ ዘወትር ከጎኔ ሆና እንባዬን የምታብሰው እናቴ ለኔ ልዩ ናት ውለታ አለብኝ ማረሳው አዝ==== ከኔ ጋራ ነች ሰማዕቷ አለች ዘወትር ከጎኔ መጠሪያዬ ነች አርሴማ እንባዬን አባሽ ከአይኔ በዝቶብኝ ሳለ መከራ በህይወቴ ከብዶኝ ፈተና ፀሎቷ ክፋን አርቆ ዛሬም ቆሜአለው በደህና አዝ==== ደጇ እሄዳለው ሁልጊዜ ምስጋናን ይዤ ለክብሯ የፀጋ ስግደት ሰግጄ በክብር ወድቄ ከእግሯ ይታወቀኛል ከውስጤ ያክፋ ጠላት ሲሸሸኝ ኃይልን የሚያደርግ ፀበሏ ታላቅ እምነትን ሲሰጠኝ አዝ==== እግዚአብሔር ፀጋን የሰጣት አዛኝ ላመኗት ምትራራ በእርሷ አየሁ ማዳኑን የአምላክን የጥበብ ስራ ስወጣ ስገባ ሁሌ ባርኪኝ እናቴ እላለሁ ስለምወዳት አርሴማን በስሟ እማፀናለሁ አዝ==== ከኔ ጋራ ነች ሰማዕቷ አለች ዘወትር ከጎኔ መጠሪያዬ ነች አርሴማ እንባዬን አባሽ ከአይኔ በዝቶብኝ ሳለ መከራ በህይወቴ ከብዶኝ ፈተና ፀሎቷ ክፋን አርቆ ዛሬም ቆሜአለው በደህና ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥   ⛺️✞ ቤተ አብርሀም ✞⛺️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ ✥ @bete_abraham ✥ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹✥✥✥🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥