cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Sel Fkr

ፍቅርን💓 የመሰለ ምን አለ! 🚩 አስተማሪ እና አዝናኝ ገጠመኝ እዚ ይገኛል 🔴 የፍቅር ጉዋደኛ ፣ ❣ወርቃማ የሆኑ የፍቅር አባባሎች ፣ ❣አጫጭር የፍቅር ታሪኮች ፣ ❣ፆታዊ ምክሮች ፣ 👉የፍቅር ደብዳቤ ለመጻፍ 👉የልደት መልካም ምኞት 👉የፍቅር ጥቅሶች 👉ሌሎችም 🎵 Join@sle_fkll Contact @Babayeeeeeeeeeeee

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
234
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከተራራው ላይ ክፍል አስራአምስት የመጨረሻው ክፍል (ፉአድ ሙና) . ‹‹ባጎረስሽኝ ጉርሻ፣ ረሀብ ከሰመ፣ በደጉ ስብዕናሽ፣ ችጋር ተፈፀመ፡፡ አንቺን አምኛለሁ!›› *** ሚቾዬ እሁድ በጠዋት ቀሰቀሰችኝ፡፡ እኔ በእንቅልፍ አሳብቤ ለመቅረት ሳስብ ነበር፡፡ አልሆነልኝም፡፡ ቱታ ሱሪ በባለኮፍያ ቱታ ጃኬት ለበስኩ፡፡ የሰፈሬ ሰዎች እንዲለዩኝ አልፈለግኩም፡፡ ትንሱዬን ይዘን መሄድ ስለማንችል ሚቾ አትሄድም፡፡ መኪናዬን አስነስቼ ቤተል አደባባይ ስደርስ ሀፍሷ ጋር ደወልኩኝ፡፡ ‹‹ኡሚ›› የሚል ፅሁፍ ያለበት አረንጓዴ ፒፕስ አባያዋ ላይ እንደደረበች እየተፍለቀለቀች መጣች፡፡ ፈገግ እንዳልኩ ‹‹መኪና አልያዝሽም እንዴ?›› አልኳት፡፡ ‹‹ይዣለሁ ሰጥቻቸው ነው፡፡ እየተጫወትን እንድንሄድ ነው …… ያው የኔ እንግዳ ነህ ብዬ ነው፡፡›› መኪናዬ ውስጥ ከጎኔ ተቀምጣ መንገድ ጀመርን፡፡ ወደኔ ተመቻችታ እየተቀመጠች ‹‹ሚስትህ አልደበራትም አይደል?›› አለችኝ፡፡ ‹‹ለምን ይደብራታል?›› ‹‹ወደ እስልምና እንድትመለስ ልንሰብክህ መስሏት ምናምን?›› ‹‹እና አይደለም እንዴ?›› ሳቅኩኝ፡፡ ‹‹አዝግ ነገር ነህ!›› ሳቄ ተጋባባት፡፡ ‹‹የምር ግን ሚቾ ልቧ በጣም ንፁህ ነው፡፡ እንደምወዳት ታውቃለች፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ፈጣሪ ጉዳዬ እንዳልሆነም በደንብ ትረዳለች፡፡ ስለዚህ አትሰጋም፡፡›› ‹‹ትዳር የማንበጠብጥ ከሆነ መልካም ነው፡፡ የመረዳት ፕሮጀክታችን አካል ነህ! ሐይማኖትህን መቀየርህ ምንም አይነት ኢስላማዊ እውቀት ያልነበረውና ከትክክለኛ ሙስሊሞች ጋር ያልተገጣጠመ ሰው እንደመሆንህ የሚጠበቅ ይመስለኛል፡፡ ሐይማኖትህን በተመለከተ ልንጫንህ አንፈልግም …… አንተ ትልቅ ነህ፡፡ ወደፊት ላንተም ለሚቾም የሚሻለውን ተመራምረህ ትደርስበታለህ ብዬ አስባለሁ፡፡›› ‹‹እሺ መልካም እና የመረዳት ፕሮጀክት ማለት ምን ማለት ነው?›› ‹‹አንተ በልጅነትህ ስለእስልምና በስርዓቱ ብታውቅ ባሳለፍካቸው የመከራ ጊዜያት ሁሉ ትልቅ ስንቅ ይሆንህ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ትምህርቱን አላገኘህም …. እንደነገርከኝ ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህ አንተ በጣም ትፈልጋቸው የነበሩ ግን ያጣሀቸውን ነገሮች መረዳት የምናግዛቸውን ቤተሰቦች ለመርዳት በጣም ይጠቅመናል፡፡›› ‹‹እናንተ እንኳን ተረድታችሁታል ….›› ትንሽ ዝም ካለች በኋላ ትንሽዬ ማስታወሻ ደብተሯን ገልጣ እያየች ‹‹ኢብሮዬ ባለፈው ከተለያየን በኋላ ብዙ ጥያቄዎች ተፈጥረውብኝ ነበር ….. ልጠይቅህ?››› አለች፡፡ ‹‹ይቻላል ….›› ‹‹ጓደኛህና እህትህ እንዴት ተጋቡ?›› ‹‹በጣም ቅርርብ ነበረን፡፡ ወንድሜ ብዬ ነው የማስበው! ኢንቱ የአዕምሮ ህመም የገጠማት ጊዜ የምትቀርበን እኔን፣ እሱንና ሚቾን ብቻ ነበር፡፡ እሱ ደግሞ ከድሮም በጣም ይወዳታል፡፡ በጣም ያስብላታል …. ይረዳታልም፡፡ እሷም ይኼን ነገሩን በጣም ትወድለታለች፡፡ እኔና ሚቾ ከተጋባንና እሱ የሚቾ አባት ወሳኝ ጉዳይ አስፈፃሚ ከሆነ በኋላ ከአንፎ ለቅቆ ቤተል ቤት ተከራየ፡፡ እናቱ ወዲያው ስለሞተች ከአባቱ ጋር ቤቱ በጣም ሰፋው፡፡ እና የዚያን ጊዜ የልቡ እውነተኛ ፍላጎት ምን እንደሆነ ማሰብ ጀመረ፡፡ በመጨረሻም ኢንቱዬ ገና እያገገመች እያለ ሀሳቡን አካፈለኝ፡፡ መጀመሪያ በጣም ደነገጥኩ፡፡ አንደኛ በእድሜ እኔ እንኳን እሱን በአንድ አመት እበልጠዋለሁ፡፡ኢንቱዬ ደግሞ በጣም ታላቁ ነበረች፡፡ በሰባት አመት ምናምን መሰለኝ የምትበልጠው! እና እንዴት ይሆናል አልኩት፡፡ አንተ ለወደድካት ልጅ ሐይማኖትህን ቀይረህ እኔ ላይ እንዴት እድሜ እንቅፋት ይሆናል ሲል ሞገተኝ፡፡ ውሳኔውን ለሷ እንድንተወው ግን በደንብ እስከሚሻላት ሀሳቡን ላናቀርብላት ተስማማን፡፡ በደንብ ሲሻላት ነገርናት፡፡ ኢቦዬ ከፈቀደ አልቃወምም አለች፡፡ ያው እሺ ማለቷ ነው እንግዲህ በግሪክኛ! ድሮም እንደሚዋደዱ ስለማውቅ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እህቴን አስረከብኩት፡፡ አሁን ድረስ እንደሁለቱ መጋባት የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ አብዱኬ ተዛመደኝ፡፡ ደግሞ ቶሎ ቶሎ ወለዱ፡፡ ሁለት ልጅ አላቸው፡፡ በጣም የምወዳቸው ሁለት ሰዎች ተጣምረው እንደማየት ለእኔ ደስ የሚል ነገር የለም፡፡›› ‹‹ይቅርታ ይረብሽህ ከሆነ አላውቅም ግን አሰሪዋን ምንም አላልከውም?›› መረበሽ አለመረበሼን ከፊቴ ላይ ለማንበብ ሞከረች፡፡ ፈገግ አልኩኝ፡፡ ‹‹ታውቂያለሽ ዲያሪውን እንዳነበብኩ ሀሳቤ ሙሉ ንብረቱን ለማውደም ነበር፡፡ ውስጤ በጥላቻ ተሞልቶ ነበር፡፡ ከአብዱኬ ጋር ሆነን ስለሰውየው አጣራን፡፡ ባለትዳር ነው፡፡ ልጆችም ነበሩት፡፡ በመሀል ግን ማህሌት አወቀችብን፡፡ መጀመሪያ ተባባሪ መስላ ሁሉንም እንቅስቃሴያችንን አወቀች፡፡ ከዚያ ግን በአጭር ንግግር ረታችን፡፡ ‹‹የሱን ንብረት አውድማችሁ ወይም እሱን ጎድታችሁ ልጆቹ እናንተ የማቀቃችሁበትን አይነት ህይወት እንዲኖሩ ትፈልጋላችሁ ወይ?›› አለችን፡፡ ስናስበው ልክ ነበረች፡፡ እሱ ለኛ መጥፎ ቢሆንም ለልጆቹ ግን አባት ነው፡፡ እናም በጣም እየከበደኝ ይቅርታ አደረግኩለት፡፡ ያኔ ሁሉም ነገር ቀለለኝ፡፡›› ‹‹እህትህ ዲያሪ ለምንድን ነበር የምትፅፈው?›› ‹‹ያኔ ህመሟን የምታዋየው ሰው ስላልነበረ ይመስለኛል፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ያሳለፍነውን ታሪክ ሁሉ ለእኔ ልታሳውቅ ስለምትፈልግም ነው፡፡ እሷ አሁንም ዲያሪዋን እንዳነበብኩ አታውቅም፡፡ ሁሌም ከተመረቅኩ በኋላ እንደምትሰጠኝ ትነግረኛለች፡፡›› አንፎ ባጃጅ ተራው ጋር ስንደርስ መኪናዬን አቆምኩ፡፡ ‹‹ምነው?›› አለችኝ፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ መንገዱ መኪና ይጎዳል!›› ሳቀች! ከሳቋ ሳታባራ ‹‹አንተ እውነትም ከመጣህ በጣም ቆይተሀል! ተራራው ድረስ እኮ መንገድ ተሰርቷል፡፡›› አለች፡፡ መኪናዬን አስነስቼ በፒስታው መንገድ ላይ በዝግታ እያዘገምኩ ወደ ተራራው መሄድ ጀመርን፡፡ ተራራው ጋር ስንደርስ የልብ ምቴ ፍጥነት ጨመረ፡፡ ከዚህ ተራራ ስር የእናቴን እና የአባቴን ሬሳ በተለያየ ጊዜ አንዲት አሮጌ ፒካፕ መኪና ላይ ጭነናል፡፡ ድርጊቱ ሁሉ አሁን እየሆነ ያለ ያህል ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ፡፡ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ መሪው ላይ ተደፍቼ ተንሰቀሰቅኩ፡፡ ‹‹አይዞን ኢብሮ ….. አይዞን!›› ሀፍሷ ልታፅናናኝ ትሞክራለች፡፡ አንብቼ ሲወጣልኝ ይቅርታ ጠየቅኳት፡፡ ሌሎች መኪናዎች ከኋላችን መጥተው ሲቆሙ ከመኪናችን ወረድን፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከሀፍሷ መኪና ወርዶ ሀፍሷ የለበሰችው አይነት ፒፕስ ሰጠኝ፡፡ ከኋላ ከነበረችው አሮጌ ታክሲ ላይ ለወር አስቤዛ የተሸመተውን ተሸክመን ወደምንጠይቀው ቤተሰብ ሄድን፡፡ ተራራውን ትንሽ እንደወጣን ህፃናት እየተሯሯጡ እየመጡ ያቅፉን ጀመር፡፡ የምናልፍበት ቤት ሰው ሁሉ ሰላምታ ይሰጠናል፡፡ አንዲት ደከም ያለች ጎጆ ጋ ስንደርስ ህፃናቱ ‹‹ኡሚዎች መጡ …… ኡሚዎች መጡ ….›› እያሉ ወደኛ መሮጥ ጀመሩ፡፡ ሀፍሷና አብረውን የነበሩ ወጣቶች ህፃናቶቹን አቅፈዋቸው ወደ ቤት ገባን፡፡ አንዲት ህመም ከአልጋ ላይ የጣላት እናት በፈገግታ ተቀበለችን፡፡ ቤቱ ውስጥ አረፍ እንዳልን አባላቱ ስለጤናዋ መጠያየቅ ጀመሩ፡፡ ‹‹አቡኪዬ ና እስኪ የቀራኸውን አሰማኝ!›› ሀፍሷ ከመካከላቸው አንዱን ህፃን በእጇ እየጎተተች አቀፈችው፡፡ ቀይዋን ትንሽዬ ቁርዓን ከፍቶ በሚገርም ፍጥነት ማንበብ ጀመረ፡፡ ሌሎቹም በተራ በተራ አሰሟቸው፡፡ በግርምት እንደተዋጥኩ ፈገግ ብዬ ተመለከትኳቸው፡፡ ሀፍሷ የቆሸሹ ልብሶቻቸውን ሰብስባ አወጥታ ማጠብ ጀመረች፡፡ ሌሎቹ ምግብ ለማብሰል ከሰል ማያያዝ ጀመሩ፡፡ ምግብ መስራቱ ላይ ተሳተፍኩ፡፡ የህፃናቱን ገላ አጥበንና ቤቱን አፀዳድተን ግማሽ ቀን ያህል እየሰራንና ከልጆቹ ጋር እየተጫወ
Show all...
በስፒከር ነው መሰለኛ የምታወራው?›› ‹‹አዎ›› ‹‹ሀፍሳ ካንተ ጋር ናት?›› ‹‹አጠገቤ ተቀምጣለች፡፡›› ‹‹ሀፊዬ ኧረ በእሁዱ ብቻዬን አታስውዪኝ ባሌን መልሺ!›› ሁላችንም ሳቅን፡፡ እየመጣን እንደሆነ ነግሬያት ተሰነባበትን፡፡ ስልኩ እንደተዘጋ ሀፍሳ ፈገግ ለማለት እየሞከረች ‹‹Trust level መቶ ከመቶ›› አለች፡፡ ቤተል ቢሯቸው ጋር ላወርዳቸው ስል ሀፍሷ ትክዝ እያለች ‹‹please ኢብሮ ከቻልክ ታሪክህን ፃፈው!›› አለችኝ፡፡ በጣም ከፍቷታል፡፡ ፈገግ ብዬ መልስ ሳልሰጥ ተሰናበትኳት፡፡ መኪናዬን በቤተል አደባባይ በኩል አዙሬ አርባ ሜትሩን እየዠለጥኩ ወደ ልቤ ንግስት …. ወደ ደግነት ሀውልት ….. ወደ ውዷ ሚስቴ ከነፍኩ፡፡ . ተፈፀመ!!! .
Show all...
ሉ ይርቃታል፡፡›› ‹‹hey come on አብርሽ! እና ሁሌ እንደታመመች ትኑር እንዴ? ሰዉ ከፈለገ የፈለገውን ይበል! ከፈለገ ‹‹በቃ ለቀቀች›› ይበል! No አልበቃም ታክማ ትድናለች ማለት ያለብህ አንተ ነህ! በተግባር ማለት ነው! Use your brain men!›› ተቆጣች፡፡ ‹‹ታውቂያለሽ …… እሱ ሁሉ ጠፍቶኝ አይደለም! ግን ኢንቱዬ ታማለች ብዬ ማመን አልፈልግም! …… እኔንጃ ሚቾ …… አይሻላትም ቢሉኝስ ብዬ እፈራለሁ፡፡ አይሻላትም ያሉኝ ቀን ሰው የምሆን አይመስለኝም፡፡ ህልምን ፈርቶ ሳይተኙ እንደማደር ነው የሆነብኝ! አይቻልም አይደል?›› እንባዬ አይኔን ሞላው! መነፋረቅ ጀመርኩ፡፡ ቀራኒዮ ደርሰን ስለነበር መኪናውን አቁማ አቅፋ ታባብለኝ ጀመረች፡፡ አቤላ የመኪናውን በር ቀስ ብሎ ከፍቶ ወረደ፡፡ እጇን ፊቴ ላይ ስታርመሰምሰው ነዘረኝ፡፡ ከዚህ በፊት እንደዚህ ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ ‹‹ምጷ›› የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ በሀፍረት አቀረቀረች፡፡ አንገቴን ሰበርኩ፡፡ መኪናዋን አስነስታ ወደኛ ቤት ነዳችው፡፡ እጇ ሲንቀጠቀጥ ይታየኛል፡፡ አንገቴን በስሱ ወደሷ አዙሬ እየተመለከትኩ ‹‹ይቅርታ ……›› አልኩ፡፡ ‹‹it’s okay …… it’s fine›› ፊቷ በድንጋጤ ቀልቷል፡፡ መኪናዋን ጥበቃ ያለበት ቦታ አቁመን ወደ ቤት ማዝገም ጀመርን፡፡ ዳገቱ ሲከብዳት እንደቀድሞው ልትይዘኝ ትልና ትተወዋለች፡፡ ባልሳምኳት ብዬ ተፀፀትኩ፡፡ ውለታዋን ያረከስኩ መሰለኝ፡፡ ሀሳቧን ለማስቀየር ጥያቄ ሰነዘርኩ፡፡ ‹‹ሚቾዬ …… ብዙ የሀብታም ልጆች ቤት ቁጥጥር ይበዛባቸዋል፡፡ አንቺ እኛ ጋ ስታድሪ አባትሽ ምንም አይልሽም?›› ‹‹ልመለስ? መምጣቴ ደበረህ?›› አኮረፈች፡፡ ‹‹እኔ እንደዛ አላልኩም እኮ …… እኔ የሚደብረኝ አንቺ ሳትኖሪ ነው፡፡›› ሳቀችና ‹‹ሚስትነትን ልለማመድ ብዬ እኮ ነው!›› አለችኝ፡፡ በደስታ አቀፍኳት፡፡ ‹‹አሁን መልሱን ልመልስልህ ወይስ እንደዚሁ እንደጨመቅከኝ ልንቆም ነው?›› እጄን ትከሻዋ ላይ ጥዬ መሄድ ጀመርን፡፡ ‹‹ታውቃለህ …. ቤት ስሆን ብቸኝነት ይሰማኛል፡፡ dad በጣም ስለሚያምንብኝና ስሜቴን ስለሚረዳ የት እንደሆንኩ ይወቅ እንጂ ምንም አይለኝም፡፡ So ምንም አይለኝም ነው መልሱ!›› ተቃቅፈን ወደ ቤት ስንገባ አብዱኬ ኢንቱን እያባበለ ምግብ እያጎረሳት ነበር፡፡ ቤት ውስጥ ተቃቅፈን ስንቆም ግራ በመጋባት አፍጥጦ ተመለከተንና ‹‹አዲስ level unlock አስደረጋችሁ እንዴ?›› አለ፡፡ አነጋገሩ አስቆን መሳቅ ስንጀምር ኢንቱም ሳቀች፡፡ ገብቷት ይሁን አይሁን ግን አላውቅም፡፡ ‹‹level unlock ምናምን …… ደግሞ ከመች ጀምሮ ነው ጌም ተጫዋች የሆንከው?›› ‹‹እና አራቱን ቀን ከኢንቱ ጋር ምን ስንሰራ የምንውል ይመስልሀል?›› እያለ ያሳሰረችውን ስልክ አሳየኝ፡፡ ኢንቱዬን ስመን እንደተቀመጥን አብዱኬ ማህሌትን እያየ ‹‹የምር የምር ግን ምንም ለውጥ የለም?›› አለ፡፡ ሚቾ አቀረቀረች፡፡ አብዱኬ እየሳቀ ‹‹እንግዲህ ያጣፍጥላችሁ!›› አለ፡፡ እራት ለወጉ እየቀማመስን ማህሌት ህክምናውን በተመለከተ አብዱኬን አማከረችው፡፡ እሱም እያሰበበት እንደነበረ ነግሯት በነጋታው ሀኪም ቤት ለመሄድ ተስማማን፡፡ ‹‹ከአምስት አመታት በኋላ›› ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ ከመኪናዬ ወርጄ መራመድ ስጀምር የክላክስ ድምፅ ሰማሁ፡፡ ዞር ብዬ ስመለከት አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ሂጃቧን እያስተካከለች ከመኪናዋ ወረደች፡፡ ቀጠሮዬ ከእርሷ ጋር ነበር፡፡ ከብዙ ቀናት ጭቅጭቅ በኋላ ዛሬ የምትለውን ልሰማት ፈቅጃለሁ፡፡ አጠገቤ ደርሳ ‹‹ኢብሮዬ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኩም፡፡›› አለችኝ፡፡ ረዘም ብላ ቀላ ያለች ቆንጅዬ ልጅ ናት፡፡ ሙስሊሞች የሚለብሱትን ጥቁር አባያ ለብሳለች፡፡ ኮስተር እንዳልኩ ‹‹ለምን ተጠራጠርሽ?›› አልኳት፡፡ ‹‹ብዙ ሰው እሺ አይልሽም ብሎኝ ስለነበር ነው፡፡ እና መኪና ውስጥ እናውራ ወይስ ሻይ ቡና እያልን እናውራ?›› ‹‹ደስ እንዳለሽ …›› መኪናዋ ውስጥ ገብተን በመኪናዬ አጠገብ ስናልፍ ‹‹ይኼ መኪና አንድ ነጥብ ምናምን ነዋ የሚሸጠው?›› አለች፡፡ አንገቴን በአዎንታ እየነቀነቅኩ ‹‹መኪናሽ በጣም ታምራለች! ለምን Cheat ታደርጊባታለሽ?›› አልኩ፡፡ በግርምት አየችኝ፡፡ ‹‹ምነው?›› ‹‹ቀልድ የምታውቅ አይመስለኝም ነበር፡፡›› ‹‹ገምቻለሁ፡፡›› ‹‹ለምንድነው ሰው እንዲቀርብህ የማትፈልገው?›› ‹‹ብዙ የሚቀርቡኝ ሰዎች አሉ፡፡›› ‹‹ማለቴ እኔ የማውቃቸው ብዙ ልጆች በስራ ካልሆነ አሊያም ስንቸገር ካላየ በቀር ዞር ብሎ እንኳን አያየንም ነው የሚሉኝ!›› ‹‹ሙስሊሞችን ማለትሽ ነው?›› ‹‹አዎ ብዙዎቹ ሙስሊሞች …… ግን ሌሎችም አሉ፡፡›› ‹‹ሙስሊሞች ላይ ነው እንጂ ሌሎቹ ላይ እንኳን ብዙም አልኮሳተርም፡፡›› ‹‹እኮ ምንድነው ምክንያትህ?›› ‹‹ለዚህ ነው የፈለግሽኝ?!›› ተቀያየርኩባት፡፡ ‹‹ይቅርታ …… ተረጋጋ በቃ›› ደንግጣለች፡፡ በመካከላችን ለረዥም ደቂቃዎች ዝምታ ነገሰ፡፡ ከሚገባው በላይ የተንጠባረርኩባት መሰለኝ፡፡ በምን መልኩ ንግግራችንን ማስቀጠል እንዳለብኝ ማውጠንጠን ጀመርኩ፡፡ አይኖቼ መኪናው ውስጥ ሲቃብዙ መስታወቱ ላይ የተለጠፈ ጥቅስ ተመለከትኩ፡፡ ‹‹ከመርዳት መረዳት ይቅደም!›› ይላል፡፡ ከጥቅሱ ስር ‹‹ኡሚ የየቲሞች ልማትና መረዳጃ እድር›› የምትል ፅሁፍ አለች፡፡ ጥቅሱ ቀልቤን ስቦታል፡፡ ወደ ጥቅሱ እየጠቆምኩ ‹‹ይኼን …… ገዝተሽው ነው ወይስ?›› አልኳት፡፡ ‹‹አይ እኛ ነን ያሰራነው!›› ‹‹አባባሏን ወድጃታለሁ ማነው የፃፋት?›› ‹‹ፕሬዝዳንታችን ነው፡፡ ሁሌም ችግርን ከመቅረፍ በፊት የችግሩን ምንነት መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ የምናግዛቸውን ቤተሰቦች ህመም ስንረዳ እነሱን ለማገዝ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት የመስመር እድሉ ሰፊ ነው ይላል፡፡›› ‹‹ምንድነው የምትሰሩት?›› ‹‹ገንዘብ ከአባላቶቻችን እያሰባሰብን በቋሚነት በአቅም የደከሙ ቤተሰቦችን እናግዛለን፡፡ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ፍቅር በመስጠትም ማለት ነው፡፡ ቤተሰብ እንከፋፈልና የልጆቹን የጥናት ሁኔታ እንከታተላለን …… ኢስላማዊ ትምህርቶችንም እየከፈልንላቸው እንዲማሩ እናደርጋለን፡፡ ሁሌ የሰው እጅ እንዳይጠብቁ ደግሞ ስራ የመስራት አቅም ያላቸውን በተወሰነ ካፒታል ስራ እናስጀምራቸዋለን፡፡ ቤታቸውን እናድሳለን፡፡ በቃ በአጭሩ ቤተሰብ እንሆናቸዋለን፡፡›› ‹‹ይገርማል …… ቢሮ ምናምን አላችሁ ወይስ?›› ‹‹አለን ቤተል ነው፡፡ ቤተልን ታውቀዋለህ?›› ‹‹እየቀለድሽ ነው?›› ‹‹ኧረ አልቀለድኩም!›› በጥያቄ አይን ተመለከተችኝ፡፡ ‹‹ሰፈሬ እኮ ነው፡፡›› ‹‹አትቀልድ!?›› ‹‹የምሬን ነው …… ቆይ የት ሰፈር ያሉ ናቸው የምታግዟቸው? ማለቴ ቤተል ብዙ እንደዚህ አይነት ችግር ያለ ስላልመሰለኝ ነው፡፡›› ‹‹አንፎ፣ ቀራንዮ፣ ገመቹ፣ ካራ፣ ምናምን ከብዙ ቦታ ነው ሰዉ የሚመጣው! ደግሞ ቤተልም አይጠፋም!›› አንፎ ስትል ደነገጥኩ፡፡ ፈጠን ብዬ አንፎ ሄዳ ታውቅ እንደሆነ ጠየቅኳት፡፡ በብዛት እንደምትሄድ ነገረችኝ፡፡ አንፎ ላይ እሷ እየሄደች የምትከታተላቸውን ቤተሰቦች ስም ጠየቅኳት፡፡ የማውቃቸውን ሰዎች ጠራችልኝ፡፡ ለልጅቷ የነበረኝ እይታ ተቀየረ፡፡ ነፃ ሆኜ ማውራት ጀመርኩ፡፡ ‹‹ቅድም ምንድን ነበር የጠየቅሽኝ?›› ‹‹ለምንድነው ሰው የማትቀርበው ነበር ያልኩህ!›› ‹‹ስለራሴ ማብራራት ስለሚደክመኝ ነው፡፡ በተለይ ሙስሊሞችን መቅረብ የሚደብረኝ ለዚያ ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን አንቺ ስለኔ ጭንቅላትሽ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እስ
Show all...
› ‹‹ግቢ ውስጥ ነኝ እኮ!›› ‹‹ና ልብስ ቀይራ መኝታ ቤት ነን!›› ወደ መኝታ ቤት ስገባ ሚቾና ኢንቱዬ ልጃችንን እያለበሱ ነበር፡፡ ሶስቱንም ስሜ ልብሴን ቀያየርኩ፡፡ ተዘገጃጅተን እንደጨረስን ሚቾ ‹‹እስኪ dad አንተን ካላየ ከዛ ክፍል አይወጣም …… please ሂድና እንደጨረስን ንገረው!›› አለችኝ፡፡ ወደ ቢሮው ሄጄ በሩን ከፈትኩትና ‹‹ክቡር አቶ በየነ ትወጣለህ ወይስ በግድ ጎትተን እናስወጣህ?›› አልኩት፡፡ እየሳቀ ከወንበሩ ላይ ተነስቶ ተከተለኝ፡፡ ማህሌት ነጭ ሙሉ ቀሚስ …… ኢንቱዬ ደግሞ ነጭ ሂጃብና ሙሉ አረንጓዴ ቀሚስ ለብሰዋል፡፡ ወደ በረንዳው ስንወጣ ሁሉም በጭብጨባ ተቀበሉን፡፡ የበየነ ጓደኞችም ከቤተሰባቸው ጋር ተገኝተዋል፡፡ ሰዉ በልቶ እንደጨረሰ የኬክ መቁረሻው ሰዓት ሲደርስ እኔና ሚቾ ልጃችን ትንሳኤን አቅፈን ወደ ኬክ መቁረሻው ቦታ ቀረብን፡፡ ኬኩ ላይ አንድ ቁጥር ሻማ ተሰክታለች፡፡ አብዱኬ አቤላን በቪዲዮ አስገብቶ ዝግጅቱን በቀጥታ እያሳየው ነው፡፡ ኬኩ እንደተቆረሰ አቶ በየነ ፀሎት አድርገው ንግግራቸውን ከፈቱ፡፡ ‹‹የዛሬ አመት ጌታ ይህችን የመሰለች ቆንጅዬ ልጅ አሳቅፎናል፡፡ ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን!›› ‹‹አሜን!›› የታዳሚው ድምፅ አስተጋባ፡፡ ‹‹እናም ዛሬ ጌታ እኛን የባረከበት ቀን ነውና ይህን አስመልክቼ ለሁለቱ ውድ ልጆቼ የማበረክተው አንድ ስጦታ ይኖራል፡፡›› አብዱኬ ልጁን እንዳቀፈ በእጁ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ትልቅ ፍሬም አቀበላቸው፡፡ ሁሉም በአንድነት እያጨበጨበ ስጦታውን ተቀበልን፡፡ ‹‹ይከፈት …… ይከፈት!›› የሚል ድምፅ ተስተጋባ፡፡ ሚቾና እኔ በአንድነት ሆነን ስጦታውን ከፈትነው፡፡ ያየነውን ማመን አልቻልንም፡፡ ‹‹ትንሳኤ ሆስፒታል›› የሚል ፅሁፍ በትልቁ ሰፍሮበታል፡፡ በዮካን አቅፈነው በደስታ አነባን፡፡ በዮካ እንዳቀፈን ‹‹እንግዲህ ሆስፒታሉ በሁለቱ ልጆቼ ስም እየተገነባ ያለ ነው፡፡ ሁለቱም የህክምና ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ቀስ በቀስ ሙሉ ለሙሉ ተረክበው ያስተዳድሩታል፡፡ ስራው ለስጋም ለነፍስም አትራፊ ነው፡፡ ጌታ ደግሞ እንዲባርክላችሁ ፀሎቴ ነው፡፡›› አለ፡፡ መሰናዶው ተጠናቆ ቤተሰብና የፌሎው ልጆች ብቻ ቀረን፡፡ ኢንቱዬ እንባ እየተናነቃት ‹‹በእናንተ ሆስፒታል ግን መታከም አቅቶት የሚሞት አይኖርም አይደል?›› አለችን፡፡ ሚቾዬ እየተፍለቀለቀች ‹‹በፍፁም!›› አለች፡፡ እንደተሰበሰብን አቤላን በቪዲዮ አስገብተነው ማውራት ጀመርን፡፡ ኢንቱ እየሳቀች ‹‹የጅማው …… እንዴት ነው ሀገሩ? ›› አለች፡፡ አቤላ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ደርሶት የህክምና ትምህርቱን እየተከታተለ ነው፡፡ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እናሟላለታለን፡፡ እየሳቀ ‹‹ጅማ ቀሽትዬ ናት …… እናንተ ናፈቃችሁኝ እንጂ!›› አለ፡፡ እየተወራ በመሀል አቤላ ‹‹ሚቾ ግን ምን እግር ጥሎሽ ነበር የዛን ቀን ላይብረሪ ኢቦዬ ጋ የመጣሽው?›› አለ፡፡ ‹‹እኔስ ባሌ እንደሚሆን ታውቆኝ ይሆናል፡፡ አንተ ምን ሆነህ ነበር አጠገብህ ስቀመጥ ያመናጨቅከኝ?›› ሳቀች፡፡ ‹‹እኔማ የሀብታም ልጅ አጠገቤ ሲቀመጥ ይጨንቀኝ ነበር፡፡ የምሸታቸው ምናምን ይመስለኝ ነበር፡፡ ከዚያ በፊት ሙድ ይዘውብኝ ያውቃሉ፡፡ ለዚያ ነው፡፡›› ‹‹እሱማ ትሸታለህ እኮ!›› አልኩ፡፡ ሁላችንም በአንድነት ሳቅን! ‹‹ቆይ ልምጣላችሁ ብቻ!›› ዛተብን፡፡ እየተጫወትን መሸ፡፡ ሁሉም ሄደው አብዱኬና ኢንቱ ከልጆቻቸው ጋር ቀሩ፡፡ አብዱኬ ‹‹ጋሼ እንዳይደብረው ቶሎ እንሂድ!›› ብሎ ተነሳ፡፡ ከኢንቱዬ ጋር ተያይዘው ወጡ፡፡ መኪናቸው ከበር እስኪወጣ ድረስ ሸኝተናቸው ተመለስን፡፡ የአብዱኬ እናት አልፈዋል፡፡ እነአብዱኬ ቤተል ላይ ቆንጅዬ ቪላ ቤት ተከራይተው ይኖራሉ፡፡ እኔና ሚቾ ወደ መኝታ ክፍላችን ገብተን መጫወት ጀመርን፡፡ ‹‹ስሚማ ሚቾዬ ዛሬ አንዲት የክፍላችንን ልጅ ተዋውቄ ……›› ‹‹አምስት አመት ሙሉ ሳትተዋወቃት ……… እሺ?›› ‹‹አንቺ ታውቂያታለሽ እኮ መሰለኝ ሀፍሷ ምናምን ነው ስሟ!›› ‹‹አዎ አውቃታለሁ፡፡›› ሚቾ ለመውለድ ብላ ትምህርት ስላቋረጠች ከኛ አንድ አመት ትዘግይ እንጂ አንድ ባች ነበርን፡፡ ‹‹እነሱ እዚህ ቤተል ቢሮ አላቸው ………›› የነገረችኝን ሁሉ ተረክኩላት፡፡ አብረን ለመሄድ ተስማማን፡፡ ሀፍሷ ጋር ደውዬ ቅዳሜ እንደሚመቸን ነገርኳት፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ከነገረችኝ በኋላ ቢሯቸውን የማየት ፍላጎቴ ጨምሯል፡፡ ቅዳሜ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ገደማ ከሚቾዬ ጋር ትንሳኤን እንደያዝን ወደ ቤተል አደባባይ አቀናን፡፡ ሀፍሷ ቤተል አደባባዩ ጋር እየጠበቀችን ነበር፡፡ ቤተል አልመሻን ህንፃ ፓርኪንግ ውስጥ መኪናችንን አቁመን የህንፃው መግቢያ ጋር ቆማ እየጠበቀችን ወደነበረችው ሀፍሷ ሄድን፡፡ ሀፍሷ ሚቾን ስማ እኔ ትንሳኤን እንዳቀፍኩ ወደ ፎቅ መውጣት ጀመርን፡፡ ሶስተኛው ፎቅ ላይ ደርሰን ወደ ግራ ታጠፍንና በትልቁ ‹‹ኡሚ›› የሚል ፅሁፍ ወዳለበት ቢሮ ገባን፡፡ ሚቾዬ በትናንሽ የውሀ መጠጫዎች ላይ የተነቀሰውን የተቋሙን መሪ ቃል አስነበበችኝ፡፡ ‹‹ለበጎነት መስፈርት የለውም!›› ይላል፡፡ ፈገግ አልኩ፡፡ ፕሬዝዳንቱ መጥቶ በትህትና ከተዋወቀን በኋላ ስለሚሰሯቸው ስራዎች እና ስለሚደግፏቸው ቤተሰቦች ችግር በደንብ አስረዳን፡፡ በልቤ እውነትም ችግሩን ተረድተውታል ብዬ አሰብኩ፡፡ ኖሬ ስላየሁት ከማንም በላይ ችግሩን አውቀዋለሁ፡፡ ሚቾ የአባልነት ፎርም እየሞላች ሀፍሷ ወደ ሌላኛው ክፍል ወስዳ ህፃናትን በጎነት ለማለማመድ የቀረፁትን ፕሮጀክት ታሳየኝ ጀመረች፡፡ ኮምፒዩተር ከፍታ ከዚህ ቀደም የሰሯቸውን ስራዎች በፎቶ አስጎበኘችኝ፡፡ እነሚቾ ወዳሉበት ክፍል ስንመለስ ፕሬዝዳንቱ ትህትና ተላብሶ ‹‹ነገ ከቻላችሁ አንፎ ቤተሰቦችን ልናይ ስለምንሄድ ብትመጡ ደስ ይለናል፡፡›› አለ፡፡ ሚቾ ዞር ብላ ተመለከተችኝ፡፡ አንገቴን በአሉታ ወዘወዝኩ፡፡ ‹‹አንፎ ምንም አያደርግህም …… ሂድና ፍርሀትህን አሸንፈው፡፡›› አፈጠጠችብኝ፡፡ ውሳኔያችንን እንደምናሳውቃቸው ተነጋግረን ተመለስን፡፡ ለሊቱን ሙሉ ልሂድ አልሂድ የሚለውን ሳስብ ቆየሁ፡፡ ፍርሀቴን የማሸንፍበት ጉልበት ፈለግኩ፡፡ ሚቾ እንድሄድ ለማድረግ የቻለችውን ያህል ጣረች፡፡ ተሳካላት፡፡ እየቀፈፈኝም ቢሆን እናትና አባቴ ወደ ሞቱበት ሰፈር ለመሄድ ተስማማሁ፡፡ . ይቀጥላል …. . የመጨረሻው ክፍል ነገ ይቀጥላል 🖤
Show all...
ከተራራው ላይ ክፍል አስራአራት (ፉአድ ሙና) . ‹‹በፍቅርሽ እሳት፣ ባንቺው ሱባዔ፣ ጨለማው ነጋ፣ መጣ ትንሳኤ! እሳት ያበራል?›› . ፈገግ ስል ድፍረት አገኘች መሰል ውትወታዋን ቀጠለች፡፡ ‹‹በላ ንገረኝ!›› በጉጉት ትመለከተኛለች፡፡ ታሪኬን ዘና ለማለት እየሞከርኩ አጫወትኳት፡፡ ምናልባት ለሚሰሩት ስራ ይጠቅማቸው ይሆናል ብዬ አስቤያለሁ፡፡ ማኪያቶዋን እየማገች ‹‹ግን እኮ አሁንም ለምን ሐይማኖቱን ቀየረ የሚለውን ጥያቄ አልመለስክልኝም!›› አለች፡፡ በረዥሙ ተንፍሼ ማብራራት ጀመርኩ፡፡ ‹‹እንደነገርኩሽ ሙስሊም ልባል እንጂ ስለእስልምና ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ድሀ እንደመሆኔ ልማር የምችልበት ቀላል መንገድም አልነበረም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ የመከራ አይነት ያለማቋረጥ ይዘንብብን ነበር፡፡ በመከራችን ጊዜ ሁሉ ከጎናችን ሆነው ያላቸውን ያካፈሉን ደግሞ ሙስሊሞች ሳይሆኑ እነማህሌት ነበሩ፡፡›› ‹‹ሚቾ የኛ ግቢዋን ነው?›› አንገቴን በአዎንታ ነቅንቄ ቀጠልኩ፡፡ ‹‹እና ከእኔ ምንም ሳይፈልጉ …… የተረጂነት መንፈስም እንዳይሰማኝ ጓደኛ ሆነው ያገዙኝ እነሱ ነበሩ፡፡ በሂደት ደግሞ ከማህሌት ጋር የነበረን ግንኙነት ወደ ፍቅር ተቀየረ፡፡ እኔ እልም ያልኩ ድሀ …… እሷ የናጠጠ ሀብታም ልጅ! ግን የኪስ ብቻ ሀብታም አልነበሩም፡፡ አባቷ እንዴት ከደሀ ጋር ተፋቀርሽ አላላትም፡፡ መሰናክል የሆነብን የሀይማኖቱ ጉዳይ ብቻ ነበር፡፡ እሷ ስለሀይማኖቷ በደንብ ታውቃለች፡፡ እኔ ደግሞ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ፍቅረኛ በሆንን ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አባቷ ጠርቶ አናገረኝ፡፡ እንደልጁ እያየ የሐይማኖቱ ጉዳይ እንዳሳሰበውና ምን መፍትሔ ልናበጅለት እንደምንችል ጠየቀኝ፡፡ ምንም ሳላመነታ ሐዋርያት እሆናለሁ አልኩት፡፡ በጣም ደስ አለው፡፡ ከዚህ በኋላ ልጁ እንደሆንኩ ነገረኝ፡፡ ከህመምተኛ እህቴ ጋር ተቀብሎን በቤቱ እንድንኖር አደረገ፡፡›› ‹‹ስለሀይማኖቱ ሚቾ የነገረችህ ነገር ነበር? አምነህበት ነው ወይስ?›› ‹‹ስለሐዋርያት እንኳን ስለእስልምና ከማውቀው ያነሰ ባውቅ ነው፡፡ ሐይማኖት ያኔም ሆነ አሁን ጉዳዬ አይደለም፡፡ ያመንኩት ማህሌትን ነው፡፡ ፈጣሪ ካለ እንኳን ያለ የሚመስለኝ ማህሌት ላይ ነው፡፡ የደስታዬ …… የእረፍቴ ሁሉ ምንጭ እሷ ነበረች፡፡ እሷን ሳይ ደስታን የማይ ይመስለኛል፡፡ ተያይዘን ወደ ገሀነም እንግባ ብትለኝ እንቢ አልልም፡፡ ገሀነምን ገነት የማድረግ አቅም ያለው ደግነት እንዳላት ይሰማኛል፡፡ እንደዚያ ተርቤ በእጇ የበላሁትን አልረሳም፡፡ በየአንዳንዱ አዲስ ቀን እንደ አዲስ የማስታውሰው ጨጓራዬ ሲነድ ማህሌት ያጎረሰችኝን ጉርሻ ነው፡፡ ሙስሊሞችን ሳይ ……… በተለይ ሙስሊም ሀብታሞችን ሳይ በጣም እናደዳለሁ፡፡ እኛ ስንራብ እነሱ ከቤተሰባቸው ጋር በምቾት ሲደሰቱ ነበር፡፡ እዚያ የመከራ መሸሸጊያ ተራራ ላይ ስናነባ አንዳቸው እንኳን አለንላችሁ አላሉንም፡፡ እህቴ ሀይማኖቷን መማር ፈልጋ ገንዘብ ስለሌላት መማር አልቻለችም፡፡ አንዳንዱ በራሱ ጫማ እየለካን ስለእህቴ ቀሚስ መወጣጠር ሊወቅሰን ይፈልጋል፡፡ እሷ እኮ እሱን እንኳን በስርዓቱ ለመማር ፈልጋ ገንዘብ የላትምና አልቻለችም፡፡ እኔን ከሴት ጋር በነበረኝ ግንኙነት ሊተቹኝ ይፈልጋሉ፡፡ እኔ መጀመሪያ እምነቱን ሳውቅ ነው እኮ እንደነሱ ሊያሳስበኝ የሚችለው አይደል እንዴ? መጥፎ ነገር መፈለግ ብቻ! ስትሳሳቺ አሉ! ሲርብሽ ግን የሉም! በሰዎች ደግነት ተማርከሽ ሀይማኖትሽን ስትቀይሪ በዘይት አታለሏቸው እያሉ ያሙሻል፡፡›› እንባዋ አይኗን ሞልቶ ለመውረድ እየታገለ ሳግ ባጠረው ድምፅ ‹‹ግን እኮ ሐይማኖቱ እንደዚያ አይደለም ……›› አለች፡፡ ‹‹እኔ ሐይማኖቱን ሳይሆን ሐይማኖተኞቹን ነበር ያገኘሁት! ወሬ ሳይሆን ተግባር ነው የሚታየው!›› ‹‹እህትህስ? እሷስ እንዴት ሆነች?›› ‹‹ህክምናዋን ተከታትላ …… አሁን ባለ ትዳርና የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡›› ‹‹እሷም ሀይማኖቷን ቀየረች?›› ‹‹አልቀየረችም!›› ‹‹ሙስሊም ነው ያገባችው?›› ‹‹አዎ!›› ልጅቷ እየተንሰቀሰቀች ማልቀስ ጀመረች፡፡ አቅፌ ላባብላት አልኩና ሙስሊም መሆኗ ትዝ ሲለኝ እጄን ሰበሰብኩ፡፡ እንድትረጋጋ በማሰብ ‹‹ሰፈርሽ የት ነው?›› ብዬ ጠየቅኳት፡፡ እንባዋን እየጠራረገች ‹‹አየርጤና ……›› አለች፡፡ ሰዓቴን ስመለከተው የትምህርት ሰዓታችን እየደረሰ ነበር፡፡ እንድንመለስ ጠየቅኳት፡፡ ሂሳብ ለመክፈል ከተጨቃጨቅን በኋላ እሷ ከፍላ ወደ መኪናዋ ተመለስን፡፡ ወደ ጥቁር አንበሳ እየነዳች ዋናውን መንገድ እንደያዝን ‹‹ከዚያ በኋላ ወደ ድሮ ሰፈርህ ሄደህ ታውቃለህ?›› አለችኝ፡፡ ‹‹አላውቅም! የሰፈሩ ስም ሲጠራ ትዝ የሚለኝ ያሳለፍነው መከራ ነው፡፡ አባቴም እናቴም የሞቱበት ሰፈር ነው፡፡ ብሄድ እዚያው የምቀር …… ድጋሚ ድሀ የምሆን የምሆን ይመስለኛል፡፡ ድርሽ ብዬ አላውቅም፡፡›› ‹‹በአቅምህ የድሮ ሰፈርህ ላይ የነበሩ ሰዎችን ለመርዳት አልሞከርክም?›› ‹‹እኔ አልሂድ እንጂ እነማህሌት አሁንም ይሄዳሉ፡፡ ኢንቱዬም ትሄዳለች፡፡›› ልጅቷ መረበሿን ላለማሳየት እየጣረች ‹‹ድፍረት አይሁንብኝና ድጋሚ ብንገናኝ ደስ ይለኛል፡፡ እዚህ ሳይሆን እዚያው ሰፈርህ ማለት ነው፡፡ ቢሯችንን ባሳይህ …… ፕሬዝዳንታችንን ባስተዋውቅህ ደስ ይለኛል፡፡›› አለች፡፡ ‹‹ችግር የለውም፡፡ ስራችሁ ተመችቶኛል ቀኑን ንገሪኝና ከሚቾ ጋር እንመጣለን፡፡›› ‹‹ሲመችህ!›› ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ገብተን መኪናዋን ቦታ ፈልገን ካቆምን በኋላ ወደ ክፍል ገባን፡፡ የተቀመጥነው አብረን ነበር፡፡ ትምህርቱ እንዳለቀ ተማሪው በግርምት ይመለከተን ጀመር፡፡ በፍፁም ይሆናል ብለው ያላሰቡትን ነገር ያዩ ይመስላሉ፡፡ በእርግጥ ከሙስሊም ተማሪ ጋር አብሬ ስቀመጥ የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ከወትሮው በተለየም ፊቴ ላይ ፈገግታ ነበር፡፡ ልጅቷ አስገድዳኝም ቢሆን ስላወራሁ ደስ ብሎኛል፡፡ ‹‹ስምሽ ግን ማነው?›› አምስት አመት አብረን ተምረን ስሟን አለማወቄ አሳፍሮኛል፡፡ በግርምት እያየችኝ ‹‹የምርህን ነው? ማለቴ አታውቀውም?›› አለች፡፡ አንገቴን በአዎንታ ነቀነቅኩ፡፡ እየሳቀች ‹‹ሀፍሷ እባላለሁ፡፡›› አለችኝ፡፡ ከሀፍሷ ጋር እስከ መኪናዬ እያወራን ከሄድን በኋላ ተሰነባበትን፡፡ ከእሷ ጋር እንደተሰነባበትን ማህሌት ደወለች፡፡ ‹‹ሚቾዬ የኔ ቆንጆ ……›› ‹‹አብርሽዬ ማር ……›› ‹‹ወዬ ምን ልታዘዝ?›› ‹‹ከclass ወጣችሁ አይደል?›› ‹‹አዎ አሁን መኪናዬ ውስጥ ገባሁ፡፡ እየመጣሁ ነው፡፡›› ‹‹በቃ አፍጥነው ሁሉም ሰው መጥቷል አንተ ነህ የቀረኸው! One last thing ርችት ረስቻለሁ፡፡ ይዘህ ና!›› ‹‹ሰምቻለሁ ክቡርነትዎ! በመቶ ሰማንያ ነው እየነዳሁ የምመጣው!›› ‹‹ስርዓት ያዝ!›› ሳቅኩኝ፡፡ ተሰነባብተን ወደ ቤት መንዳት ጀመርኩ፡፡ ያዘዘችኝን ገዛዝቼ ቤት ደረስኩ፡፡ ግቢው ውስጥ ድንኳን ተጥሎ ምግቡ ሁሉ በአይነት በአይነቱ ተዘጋጅቷል፡፡ ገና ስገባ ምህረት እየሳቀች ‹‹በልጅህ ልደት ቀን እንኳን Class የማትቀጣ ጉድ!›› አለችኝ፡፡ እየሳቅኩ አቅፌያት ወደ ድንኳኑ ተጠጋሁ፡፡ የፌሎው ልጆች በሙሉ አሉ፡፡ አብዱኬ ልጁን አቅፎ እንደቆመ ‹‹እሺ አባትየው …… ለልጅህ ልደት እንኳን ቀድመህ አትገኝም አይደል? …… ምነው ግን እኔ ካልገባሁ የአስተማሪው ልብ አይመታም አልክ?›› አለኝ፡፡ የሚያምር እርሳስ ቀለም ያለው ሱፍ ለብሷል፡፡ እየሳቅኩ ተጠመጠምኩበት፡፡ ምህረት ርችቱን ተቀብላኝ ሄደች፡፡ ሁሉንም እየዞርኩ ሰላም ካልኩ በኋላ ማህሌት ደወለችልኝ፡፡ ‹‹አልደረስክም እንዴ?›
Show all...
ከተራራው ላይ ክፍል አስራሁለት (ፉአድ ሙና) . ‹‹ጥርሴን አልስቅበት፣ መች አርፌ ከእንባ፣ እጠቀመው መስሎት፣ ይኸው ጥርሴ አነባ! የጥርስ እንባ እንዴት ነው?›› *** የመጀመሪያውን ገፅ ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… ለእኔ ከሁሉም በላይ ሽንፈት አንተ ገንዘብ እንደሌለኝ ማወቅህ ነው፡፡ ግን ንገሪኝ ካልከኝ ምን አደርጋለሁ? እነግርሀለሁ፡፡ የነገርኩህ ግን በአንድ ሳምንት ሁሉም ስለሚስተካከል ነው፡፡ ዳግም ሆዳችንን የሚርበው አይመስለኝም፡፡ ሁለት ወዶ አይሆንም አይደል የሚባለው?›› ፅሁፉ ቅኔ ሆነብኝ፡፡ ባለፈው ገንዘብ እንደሌላት ስለነገረችኝ በጣም ከፍቷታል ማለት ነው? ወደ ቀጣዩ ገፅ ተሻገርኩ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… አብዱኬ እንደታሰረ ስሰማ በጣም አለቀስኩ፡፡ ለምን የተሰረቀ ሞባይል ማሻሻጥ እንደፈለገ አልገባሽ ብሎኛል? ገንዘብ ቸግሮት ነው እንዳልል ቢቸግረው ይነግረኝ ነበር፡፡ ተጨማሪ ፍራንክ አመጣለሁ ብሎ የባሰ የጋሼና የአባይዬን ጉሮሮ ዘጋ፡፡ እስከ ሰኞ ድረስ የምንበላውን አብዱኬ መሸፈኑ አይቀርም ብዬ አስቤ ነበር፡፡ በእርግጥ ባይታሰር አይርበንም፡፡ እሱንስ እየደበደቡት ይሆን ወይ ብዬ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡ እማዬን ግን ከዚህ በላይ እንዲርባት አልፈቅድም፡፡ ቢያንስ ደህና ምግብ በልታ መሞት አለባት፡፡ …… ቀኑ አልፈጥን ብሎኛል፡፡›› ኢንቱ አብዱኬ ሞባይሉን ያመጣው በእኔ ምክንያት እንደሆነ ብታውቅ ምን ትለኝ ይሆን? ፀፀት ተሰማኝ፡፡ አብዱኬ በእኔ ሰበብ ለዚህ ሁሉ በመብቃቱ ራሴን ወቀስኩ፡፡ ደብተሩን ገልጬ የመጨረሻውን ፅሁፍ አየሁት፡፡ ትንሽ ረዘም ይላል፡፡ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… በህይወቴ እንደዚህ እየቀፈፈኝ የፃፍኩበት ቀን ያለ አይመስለኝም፡፡ አዎ የለም! ከልጅነቴ አዕምሮዬ ላይ የተቀረፀ ነገር አለ፡፡ ክብርን መጠበቅ! ማንም ሰው ያለ ፍላጎቴ ምንም እንዲያደርገኝ አለመፍቀድ! …… ጥቅምን ፍለጋ ራሴን የምሸጥ አይነት ሴትም አይደለሁም፡፡ ብሆን ኖሮ ድሮ ድሮ የሀብታም ቅምጥ ሆኜ ነበር፡፡ ግን ስለማልፈልግ ጫናውን ሁሉ ተቋቁሜ እዚህ ደርሻለሁ፡፡ ይኼ መድረሻ ይሁን መነሻ አላውቅም፡፡ ግን የአንዱ ምዕራፍ መደምደሚያ የሌላኛው መጀመሪያ ይመስለኛል፡፡ ጥሩ አይደለም አውቃለሁ፡፡ እንደዚያም እያልኩ አመታትን በአቋሜ ፀንቻለሁ፡፡ አሁን ግን አንተና እማዬ ተራባችሁብኝ፡፡ ከሁሉም በላይ እማዬን ከዚያ ህመሟ ጋር በረሀብ ስትቆላ መመልከት አልቻልኩም፡፡ ለእናቴ ብዬ ክብሬን ብረግጠው ፀፀቱ ብዙ አይመስለኝም፡፡ ኢቦዬ …… ባለፈው ሳምንት ያለኝ ገንዘብ እያለቀ ሲመጣና ከስራውም ተስፋ ስቆርጥ የቀድሞው አሰሪዬ ጋር ደወልኩለት፡፡ ፀባዬን እንደማስተካክልና መልሶ እንዲቀጥረኝ ለመንኩት፡፡ ግን ለቅሶዬ ግድ አልሰጠውም፡፡ በአጭሩ ‹‹የምፈልገውን ታውቂያለሽ ……… እሱን እሺ ካልሽ እንደሰራተኛ ሳይሆን እንደአሰሪ ትኖሪያለሽ!›› አለኝ፡፡ ከዚህ በላይ የቀድሞዋን ኢንቲሳር መሆን አልቻልኩም፡፡ ተስማማሁ፡፡ ቅዳሜ ይዞኝ ወደ አዳማ እንደሚሄድና አድረን እንደምንመለስ ነገረኝ፡፡ ቀድሞ ትንሽ ብር ሊሰጠኝ ይችል እንደሆነ ጠየቅኩት፡፡ ‹‹ሳልነካሽ አላምንሽም …… በኋላ ሀሳብሽን ብትቀይሪስ?›› አለኝ፡፡ ያለሁበትን ሁኔታ ላስረዳው ሞከርኩ፡፡ ግን ‹‹ፀባይሽ አይያዝም ከሰጠሁሽ በኋላ እምቢ ትይኛለሽ!›› አለኝ፡፡ ያለኝ አማራጭ ቅዳሜ ከእሱ ጋር ሄጄ ድንግልናዬን ማስረከብ ነው፡፡ እንደዚያ ካደረግኩ በፈለግኩት ሰዓት የምፈልገውን ያህል ገንዘብ ይሰጠኛል፡፡ እንደተስማማሁ ነገርኩት፡፡ ሰፈር ድረስ መጥቶ እንደሚያነሳኝ ነገረኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ሆዳችንን አይርበውም፡፡ በረሀብ እንቅልፍ አጥተን አናድርም! ኢቦዬ ይኼ ማንም በእኔ ቦታ የቆመ ሰው የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ የቻልኩትን ያህል ታግሻለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን በቃ! ሴትነቴን ለአሰሪዬ ማስረከብና እሱን ማስደሰት አለብኝ፡፡ እሱን ሳስደስት እናንተ ሳይርባችሁ የተሻለ ኑሮ ትኖራላችሁ፡፡ ከመሞት …… መሰንበት ይሻላል!›› በደመነብስ ማስታወሻ ደብተሩን ወደ ቦታው ወርውሬ ከቤት ወጣሁ፡፡ እየሮጥኩ ከሰፈራችን ወጥቼ ባጃጅ ተራ ደረስኩ፡፡ ለምን እንደወጣሁ …… ለምን እንደምሮጥ …… ወዴት እንደምሄድ አላውቅም፡፡ ባጃጅ ተራ ስደርስ ከብዥታዬ መንቃት ጀመርኩ፡፡ ከአይኔ የእንባ ዘለላዎች መንታ መንታ እየሆኑ ይፈሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ምንም ፈጥሬ እንደማላተርፋት ገባኝ፡፡ እየተመለስኩ ያገኘኋት ድንጋይ ላይ ተቀምጬ ለረዥም ሰዓት አለቀስኩ፡፡ እማዬ ቁርስ አለመብላቷ ትዝ ሲለኝ እንባዬን ጠራርጌ ወደ ቤት መመለስ ጀመርኩ፡፡ የቤታችን ቅያስ ጋር ስደርስ የጩኸት ድምፅ ተሰማኝ፡፡ ቁልቁለቷን ወርጄ ቤታችን ጋር ስደርስ የሰፈራችን ሰዎች እየጮኹ እያለቀሱ ተመለከትኩ፡፡ ምን እንደተፈጠረ ለማየት በመሀል እየሰነጠቅኩ በር ጋር ደረስኩ፡፡ ጋሼ በር ላይ ቆሞ ያለቅሳል፡፡ መምጣቴን ሲመለከት አቅፎኝ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ‹‹ጋሼ ምንድነው? ምንድነው?›› እያልኩ ከእቅፉ ወጥቼ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ ወንዶቹ እማዬን ከበው እየተነሱና እየፈረጡ የሚያለቅሱትን ሴቶች ለመያዝ ይሞክራሉ፡፡ የሆነ ሰው መስኮቱን ሲከፍተው ብርሀኑ እማዬ ላይ አረፈ፡፡ አይኖቿ ፈጠዋል፡፡ ግራ ተጋባሁ፡፡ ቅድም ስቀሰቅሳት እንዲህ ሆና ነበር? ከራሴ ጋር ተወዛገብኩ፡፡ ሰውነቴ ከድቶኝ ተዝለፍልፌ ልወድቅ ስል ጠንካራ እጆች ደግፈው አስቀመጡኝ፡፡ በሰላም የወጣሁበት ቤት በሰዓታት ውስጥ ለቅሶ ቤት ሆኖ ሲጠብቀኝ በእውነት ይሁን በቅዠት አለም ያለሁት ማወቅ ተሳነኝ፡፡ ትንሽ ቆይቼ ‹‹ትናንት እኮ ከእነምህረት ጋር ስታወራ …… ስትመርቃቸው ነበር!›› አልኩ፡፡ ጋሼ አቅፈው ሊያረጋጉኝ ሞከሩ፡፡ ‹‹አንተ ወንድ ነህ! ጠንከር በል! አንተ ካልጠነከርክ እህትህን ማጠንከር አትችልም!›› ጋሼ ትከሻዬን እየወዘወዙ ሊያበረቱኝ ይሞክራሉ፡፡ ትንሽ ካለቀስኩ በኋላ ወደ እማዬ ተጠግቼ ግንባሯን …… እጆቿን …… እግሯን ሳምኩኝ፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅ ትከሻቸው ላይ አቡጀዴ አጣፍተው ሲመጡ ሳይ የእናቴ መሞት እውነት መሆኑ ገባኝ፡፡ አባቴ ሲሞትም ያጠቡት እርሳቸው ነበሩ፡፡ አሁን በጣም አርጅተዋል፡፡ ሆኖም ከሰፈሩ ሙስሊም ቤት ውስጥ የሞተ ሲኖር ለማጠብ የሚጠሩት እሳቸው ናቸው፡፡ ወደ ቤት እየገቡ ‹‹በሉ ግርግር አያስፈልግም! አልቅሳችሁ ልትመልሷት ነው?!›› አሉ፡፡ የለቀስተኛው ድምፅ ረገበ፡፡ የሰፈራችን ሰዉ ሁሌ ሞት ሲኖር ስለሚመጡ የሞት መልዓክ አድርጎ ያስባቸዋል መሰል ይፈራቸዋል፡፡ ሰዉ ራቅ እንዲል ተደርጎ ትንሽዬዋ የሬሳ ማጠቢያ የብረት አልጋ በራችን ፊት ለፊት ተዘረጋች፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅ አጥበው እስኪጨርሱ ከቤተሰብ በቀር ሁሉም እንዲርቅ ተናገሩ፡፡ ሁሉም ሰው ደጃፋችንን ለቅቆ ትጥበቱን በማይመለከትበትና ጋሽ አብዱረዛቅ በማይመለከቱት ቦታ ሰፈረ፡፡ ከጋሽ አብዱረዛቅ ጋር የቀረነው እኔ፣ ጋሼና ሀሚዱ ብቻ ነበርን፡፡ ሀሚዱ ሰውነቱ ግዙፍ ስለሆነ ጋሽ አብዱረዛቅ ለቅሶ ባለ ቁጥር ሬሳውን በመሸከም እንዲያስተካክልላቸው ይዘውት ይዞራሉ፡፡ አሁን ከእሳቸው እኩል ስርዓቱን በደንብ ያውቃል ይባላል፡፡ ሀሚዱ እማዬን ከአንድ ቀን በላይ ልትተኛበት ካልታደለችበት አዲሱ ፍራሿ ላይ እንደህፃን ታቅፎ ወደ ቃሬዛ ካሻገራት በኋላ ከጋሼ ጋር ተሸክመው ይዘዋት ወጡ፡፡ ከኋላቸው እየተከተልኩ የሚያደርጉትን አያለሁ፡፡ ማጠቢያው ላይ አስተኝተዋት ማጠብ ሲጀምሩ ደጃፋችን ላይ ያለችዋ ድንጋይ ላይ ተቀምጬ እያለቀስኩ መመልከት ጀመርኩ፡፡ አሁን በድን ሆና የማጠቢያ አልጋው ላይ የተኛችው ሴት ከአመታት በፊት ዘመደ-ብዙ ነበረ
Show all...
ች፡፡ ልክ እንደአባቴ ስስት የማያውቃት …… ቤቷ የገባን ሁሉ አጥግባ የምትሸኝ ቸር ነበረች፡፡ የዚህችን እናት ጡት ጠብቼ አድጌያለሁ፡፡ በድሎቱም በችግሩም ጊዜ ከህመሟም ጋር እየታገለች በፈገግታዋ ልታክመን ሞክራለች፡፡ ይህቺ ሴት የማጠቢያ አልጋው ላይ አስተኝተው የሚያገላብጧት …… ለእኔና ለኢንቱ የአባታችን ማስታወሻ ብቸኛ ዋርካችን ነበረች፡፡ አንዳንዴ ወደ ሰማይ ቀና ብዬ ‹‹ግን የምታደርገው ነገር ልክ ነው? …… ድሀ ላይ መበርታትህ ፍትህ ነው?›› እያልኩ ፈጣሪን መሞገት ያሰኘኛል፡፡ መከራን ሁሉ እኛ ላይ …… ድሎትን ሁሉ ሌላ ላይ ያደረገበት ምክንያት አይገባኝም፡፡ አሁን እናትም አባትም የለኝም፡፡ እናቴን መከፈን ሲጀምሩ ሳይ አምርሬ አለቀስኩ፡፡ ይኼ ከፈን የስንብት ልብስ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አባቴ ለብሶት አይቻለሁ፡፡ እሱን ልብስ ከለበሰ በኋላ ተመልሶ አልመጣም፡፡ እማዬ ተከፍና ቃሬዛው ላይ ተደረገች፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅ ‹‹በሉ በሉ ሬሳ ማቆየት አይወደድም! ቶሎ ቤተሰቦቿ ይሰናበቷትና እንሸኛት፡፡›› አሉ፡፡ ጋሽ አብራር ግራ እየተጋቡ ‹‹ኢቦዬ ኢንቲሳሬ የታለች?›› አሉኝ፡፡ ራሴን ለማረጋጋት ሞክሬ ልደውልላት ስልኬን መነካካት ስጀምር ለቀስተኛው ድምፁን ከፍ አድርጎ ሲያለቅስ መሰማት ጀመረ፡፡ ሁላችንም ምን ተፈጥሮ ነው በሚል ወደ ቅያሱ አፈጠጥን፡፡ የአይኔ ማረፊያ በእጇ የተጠቀለለ ፖስታ ይዛ ብቅ አለች፡፡ ከጀርባዋ የሰፈራችን ልጆች ሰሚራና ሙሀባ ይከተሏታል፡፡ እያለቀሰች አልነበረም፡፡ እየሆነ ያለውን በቅጡ የተረዳች አትመስልም፡፡ ቃሬዛው ላይ በአቡጀዴ የተጠቀለለ ሰው ስታይ ፊቷ ወደ ፍምነት እየተለወጠ ተጠጋች፡፡ የእማዬ ፊት ክፍት ነበር፡፡ እሷ መሆኗን እንዳረጋገጠች ተዝለፍልፋ ወደቀች፡፡ ሙሀባ አፈፍ አድርጎ ከጎኔ አስቀመጣት፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅም ማንባት ጀመሩ፡፡ ሰሚራ ሰውነቷ ላይ ውሀ አድርጋላት ስትነቃ መለፍለፍ ጀመረች፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… እየው እየው ብር እኮ አግኝቻለሁ፡፡ ሀኪም ቤት ውሰዷት እሺ!?›› ፖስታውን ከፍታ አሳየችኝ፡፡ እየተንሰቀሰቅኩ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ደሞ ለምንድነው ነጭ የምታለብሷት? ቆንጆ ልብስ አልብሷት እንጂ! ግን ለምንድነው እናንተ ያለበሳችኋት? የእኔ እናት አይደለች እንዴ? ምን አገባችሁ? ……›› አቅፌያት መንሰቅሰቅ ጀመርኩ፡፡ ኢንቱ ጮክ ብላ ትስቃለች፡፡ ‹‹ሸወድኳችሁ …… ሸወድኳችሁ፡፡›› አለችና ወደ እማዬ ተጠግታ ‹‹እማ ተነሽ በቃ ቤት እንግባ እዚህ ይበርድሻል፡፡ ይበርደኛል ትይኝ አልነበር እንዴ?!›› አለች፡፡ አቅፌ ወደ ድንጋዩ ይዣት ተመለስኩ፡፡ ‹‹ለምን የሚበላ ገዝተህላት አትመጣም?›› ትዘባርቃለች፡፡ ጋሽ አብራር እናቴን እንድሰናበት ጠሩኝ፡፡ ወደ ሬሳዋ ሄጄ ግንባሯን ሳምኳት፡፡ ኢንቱዬም ተከትላኝ ግንባሯን ሳመቻትና ‹‹ካንተ በላይ ነው የሳምኳት!›› አለችኝ፡፡ አንዳንዴ እማዬን በደንብ በሳመ እንፎካከር ነበር፡፡ አሁንም እየተጫወትን ሳይመስላት አይቀርም፡፡ ሀሚዱ፣ ፈረጃ፣ ከድርና ሚስባህ በአራቱ የቃሬዛው መሸከሚያ ጎኖች በኩል ቆመው፤ ቃሬዛውን በጋሽ አብዱረዛቅ ትዕዛዝ ሰጪነት ተሸከሙ፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅ ከፊት እየመሩ እማዬን ይዘዋት መውጣት ሲጀምሩ ኢንቱ መንገድ ዘጋችባቸው፡፡ ‹‹እናቴን ወዴት ልትወስዷት ነው?›› ጮኸች፡፡ ጋሽ አብድረዛቅ ከፊት ለፊታቸው ቆማ የምታንባርቅባቸውን ኢንቲሳርን እየተመለከቱ አለቀሱ፡፡ ‹‹እርሶ ጋሽ አብዱረዛቅ የሚባሉ ሰውዬ ግን አላበዙትም እንዴ? አሁን ባለፈው የሸረፋን እናት እንደዚህ ወስደው መች መለሷትና ነው የኛን እናት የሚወስዱት? …… እናቴን አስቀምጡ! አስቀምጡ! አንተ ኢቦ አስቀምጧት በላቸው እንጂ!›› እየተንሰቀሰቀች ማልቀስ ጀመረች፡፡ አማራጭ ስላልነበራቸው በጉልበት ወደ ቤት እንድትገባ አደረጉ፡፡ ጋሽ አብዱረዛቅና ጋሽ አብራር ሴቶቹ ኢንቲሳርን እንዲጠብቁ አደራ ብለው ወንዶቹ በሙሉ ሬሳውን ተከትለን ወጣን፡፡ ከሰፈራችን ስንወጣ ያቺ ከኋላ ክፍት የጃጀች ፒክአፕ መኪና ቆማ እየጠበቀችን አገኘናት፡፡ ሸምገል ሸምገል ያሉት መኪናዋ ውስጥ ገቡ፡፡ እነሀሚዶ እማዬን ከኋላ ጭነው ጠርዙ ላይ ዙሪያውን የቻለውን ያህል ሰው ጭነን ወደ አለምባንክ መስጂድ ሄድን፡፡ የቻሉ በባጃጅ እንዲከተሉን …… ያልቻሉ ደግሞ ቀብር ቦታ እንዲጠብቁን ጋሽ አብዱረዛቅ አሳሰቡ፡፡ አለምባንክ መስጂድ ስንገባ አስር ሰዓት ደርሶ ስለነበር ሰጋጁ ወደ መስጂዱ ብቅ ማለት ጀመረ፡፡ እኔ ከነፈረጃ ጋር ተጣጥቤ ወደ ውስጥ ገባሁ፡፡ የአስር ሰላት እንደተሰገደ ኢማሙ የሞተ ሰው መኖሩን በመናገር ሰጋጁ እንዳይወጣ አሳሰቡ፡፡ እነሀሚዱ እማዬን ተሸክመው ከኢማሙ ፊት አስቀመጧት፡፡ ኢማሙ ወገቧ ጋር ቆመው በሟች ላይ የሚሰገደውን ስግደት ምዕመኑን አስከትለው ፈፀሙ፡፡ ወደ አንፎ መቃብር ስንመለስ አብዛኛው ሰው ቀድሞን ደርሶ እየጠበቀን ነበር፡፡ አባዬም የተቀበረው እዚህ ነው፡፡ መስጂድ መምጣት ያልቻሉት እዚያው ከሰገዱባት በኋላ ወደተቆፈረላት ጉድጓድ ተወሰደች፡፡ ልክ እንደዚሁ አባቴም ተመሳሳይ ጥልቀትና ስፋት ባለው ጉድጓድ ውስጥ ተቀብሯል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ቤት አልተመለሰም፡፡ ለቀስተኛው በአንድ ድምጽ ቁርዓን ያነበንባል፡፡ ሀሚዱና የቀብር ቆፋሪው ጉድጓዱ ውስጥ ገቡ፡፡ ሌሎቹ እማዬን ከቃሬዛው ላይ አንስተው አቀበሏቸው፡፡ ከውስጥ ያሉት እማዬን መሬቱ ላይ አደላድለው ካስተኟት በኋላ እርሷን ያስገቡበት የቀብሩ የጎን ኪስ በብሎኬትና በጭቃ ተመረገ፡፡ እኔ እየተንሰቀሰቅኩ አለቅሳለሁ፡፡ ሌላው በአንድ ድምፅ ቁርዓኑን እያነበነበ ወደ ጉድጓዱ አፈር ይመልሳል፡፡ መንሰቅሰቄ በረታ! እውነታውን አውቀዋለሁ፡፡ እናቴን ከዚህ በኋላ ማየት አልችልም፡፡ አባቴም እናቴም ባዶ ቤት ትተውን ሄዱ፡፡ ልፋቷ ሁሉ መና ከቀረባት አንድ እህቴ ጋር ብቻችንን መቅረታችን ነው፡፡ ጉድጓዱ በአፈር ተሞልቶ ቀብርተኛው ቦታውን ለቅቆ መሄድ ጀመረ፡፡ እኔ ቆሜ አያታለሁ፡፡ ‹‹ከዚህና ከኛ ቤት የቱ ይመቻል?›› ብዬ ልጠይቃት እከጅላለሁ፡፡ ጋሽ አብራር እጄን ይዘውኝ መመለስ ጀመርን፡፡ ቤት ስንደርስ በጣም ብዙ ለቀስተኛ ተሰብስቦ ጠበቀን፡፡ በራችን ላይ ሸራ ተወጥሮ አግዳሚ ወንበር ተደርድሯል፡፡ ሰዉ በሀዘን ድባብ ተውጦ ሰፈራችን ፀልማለች፡፡ ሴቶቹ ያዘጋጁትን ምግብ ለለቀስተኛው ያቀርባሉ፡፡ ሁሉም በየተራ ከአጠገቤ እየተቀመጠ ሊያፅናናኝ ይሞክራል፡፡ አመሻሹን አቤላ መጣ፡፡ እንዴት እንደሰማ አላውቅም፡፡ እሱን ሳይ እንባዬ አገረሸ፡፡ አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርኩ፡፡ ከቀብር ከተመለስኩበት ሰዓት ጀምሮ ኢንቱዬን አንዴ እንኳን አላየኋትም፡፡ እሷም በሴቶቹ ተከብባ ቤት ውስጥ ተቀምጣ እንደሚሆን ገምቻለሁ፡፡ ግርግሩ ጥሩ ነው፡፡ ለጊዜውም ቢሆን የመከራውን ህመም ከመጋፈጥ ያዘገያል፡፡ እናቴ የሌለችበትን ቤት የማየትን ህመም …… ዘወትር የምትተኛበትን ቦታ ባዶ ሆኖ የመመልክትን ህመም …… የአባዬን ማስታወሻ የማጣትን ህመም …… ‹‹አባቴ ቢሞትም እናቴ በህይወት አለች፡፡›› ብሎ የአባትን ሞት መሸንገያ የማጣትን ህመም …… ለጊዜውም ቢሆን በግርግሩ ተውጠን እናመልጠዋለን፡፡ ሰው ያለን ሰው ያለን ይመስለናል፡፡ ግን እንሸሸው ይሆናል እንጂ አናመልጠውም፡፡ ምክንያቱም ቀናት መቁጠራቸውን አያቆሙም! . ይቀጥላል …… . :¨·.·¨: ❀ ·. ┈┈••◉❖◉●••┈
Show all...
ከተራራው ላይ ክፍል አስራሶስት (ፉአድ ሙና) . ‹‹ከመራራው ስር፣ የማር ጠብታ፣ መፆም አልቻልኩም፣ ልቤ ተረታ፡፡ ይቅርታ!›› . ግርግሩ ቀስ በቀስ መስከን ጀመረ፡፡ ሆኖም ኢንቱዬ ወደ ቀድሞ ማንነቷ መመለስ አልቻለችም፡፡ አንዳንዴ ወደ እኔ ትመጣና ‹‹ለአንድ ቀን እማዬን መጠበቅ አቃተህ!?›› እያለች ትጮህብኛለች፡፡ አንዳንዴ ‹‹ጋሽ አብዱረዛቅ ለምን እማዬን አይመልሱልንም? ለምንድነው የሰው እናት የሚወስዱት?›› ትላለች፡፡ ሲላት ብቻዋን ትስቃለች፡፡ ሲያሻት ማስታወሻ ደብተሯን አቅፋ ታለቅሳለች፡፡ የሆነ ሰዓት ላይ ደግሞ ወደ ራሷ ትመለስና ‹‹ኢቦዬ …… ራበህ እንዴ? ብር እኮ አለን! እየውማ እየውማ!›› እያለች ፖስታውን ታሳየኛለች፡፡ አሁን አሁን ከእማዬ ሞት ህመም በላይ እየጎዳኝ ያለው የኢንቱ ሁኔታ ነው፡፡ የሚመጣው ለቀስተኛ ሁሉ ‹‹ውይ ለቀቀች!›› እያለ ከንፈሩን ይመጣል፡፡ አብዱኬ በቀጠሮው መሰረት ፍርድ ቤት ቀርቦ በድጋሚ የሰባት ቀን ቀነ-ቀጠሮ ተጠይቆበታል፡፡ ሳምንቱ ሲያልፍ ቤታችን ወደ ቀድሞው ድባቡ ተመለሰ፡፡ ከቤታችን የማይጠፉት አቤላ፣ ማህሌትና ጥቂት የሰፈራችን ልጆች ናቸው፡፡ የፌሎው ልጆች እስካሁን ሶስት ጊዜ ያህል መጥተው ጠይቀውኛል፡፡ ኢንቱዬ ማህሌትን ስታይ ደስ ይላታል፡፡ ማህሌት የምታድር ጊዜ አቅፋት ትተኛለች፡፡ እሷ ከሌለች ከኔ ጋር ካልሆነ በፍፁም አትተኛም፡፡ የአብዱኬ ቀጠሮ ሲደርስ ማህሌት በዚህኛው መቅረት የለብንም ብላ ወተወተችን፡፡ በእርግጥ ሀሳቧ ከቀጠሮው በላይ እኛን ማናፈስ ነበር፡፡ እኔ፣ ማህሌት፣ ኢንቱ፣ አቤላና ጋሼ ሆነን በማህሌት መኪና ወደ ኮልፌ ሄድን፡፡ አብዱኬ የእማዬን መሞት አውቋል፡፡ ሲገባ ቆመን ሲያየን ፈገግ ለማለት እየሞከረ እጁን አውለበለበልን፡፡ ጉስቁልቁል ብሏል፡፡ በጣም ከስቷል፡፡ ጋሼ ሲያዩት አይናቸው እንባ ሞላ፡፡ ኢንቱ ግቢው ውስጥ እየለፈለፈች ስታስቸግረን ከማህሌት ጋር መኪና ውስጥ እንድትቆይ አደረግን፡፡ ትንሿ የችሎት አዳራሽ ውስጥ ተሰይመን የፍርድ ሂደቱን መከታተል ጀመርን፡፡ የአብዱኬ ተራ ደርሶ ፖሊስ መከራከሪያውን አቅርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠየቀ፡፡አብዱኬም ወንጀሉን አለመፈፀሙንና ከዚህ በፊትም ምንም አይነት የወንጀል ታሪክ እንደሌለው በመጥቀስ ተከራከረ፡፡ በስተመጨረሻ ዳኛዋ አብዱኬ በአምስት ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቅ ወሰነች፡፡ በደስታ ሰጠምን፡፡ አብዱኬ ከችሎቱ በረዥሙ እየተነፈሰ ወጣ፡፡ ቀስ እያልን ችሎቱን ለቀን ወጣን፡፡ መዝገብ ቤት ሄደን መዝገቡ እስኪመጣ ከጠበቅንና ወረቀት ከተቀበልን በኋላ ክፍያውን ሞቢል አካባቢ ከፍለን እንድንመለስ አዘዙን፡፡ ከማህሌት ጋር ሄደን ከፈልን፡፡ ከከሰዓት በኋላ አብዱኬ ተለቀቀ፡፡ በደስታ ተቃቀፍን፡፡ ማህሌት የደስ ደስ ካልጋበዝኳችሁ ብላ ወደ አንድ ሬስቶራንት ወሰደችን፡፡ ኢንቱዬ አብዱኬን እየደጋገመች አቅፋ ትስመዋለች፡፡ ሁኔታዋ ግራ አጋብቶት በአይኑ ምን ሆና እንደሆነ ሊጠይቀን ይሞክራል፡፡ አዕምሮዋ መነካቱን ሲያውቅ ራሱን መቆጣጠር አልቻለም፡፡ እየተንሰቀሰቀ ማልቀስ ጀመረ፡፡ አብዱኬ ተፈትቶ ስራ ከጀመረ በኋላ ማህሌት ትኩረቴን ወደ ንባብ እንዳደርግ ለማድረግ የቻለችውን ያህል ጥራለች፡፡ ኢንቱ እንዲህ ታምማ ባለችበት ሁኔታ ወደ ቤተ-መፅሀፍት ሄጄ ማንበብ ባልችልም የቻልኩትን ያህል ቤት ውስጥ ለማንበብ እሞክራለሁ፡፡ ኢንቱዬ ብቻዬን ሆኜም ሆነ ከማህሌት ጋር ቤት ውስጥ ስናነብ ስታይ ደስ ይላታል፡፡ ማስታወሻ ደብተሯን አቅፋ እየሳቀች ታየናለች፡፡ ኢንቱና ማህሌት ንፋስ ለመቀበል ወጣ ሲሉ በዚህ ወር የተፈጠሩትን ነገራቶች ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡ ኢንቱ ያመጣችውን ፖስታ ከፍቼ ተመለከትኩት፡፡ ውስጡ ሰላሳ ሺህ ብር ነበረው፡፡ አሁን እኛ ሰላሳ ሺህ ብር ምን ያደርግልናል? ምናልባትም ማህሌት ያለችው ልክ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ሰው ይርባል፡፡ እማዬ ትናፍቃለች፡፡ ያቺ ኢንቲሳር ትናፍቃለች፡፡ አሁን ይኼ ገንዘብ ምን ይጠቅማል? ድሮ ልጅ ሆኜ የአማርኛ መፅሀፋችን ላይ ያነበብኩት የከበደ ሚካኤል ግጥም ትዝ አለኝ፡፡ ፅጌረዳና ደመና የሚል አርዕስት ያለው ግጥም ነበር፡፡ ‹‹የፀሐዩ ንዳድ ያጠቃት በብዙ፣ ጠውልጎ የሚታይ የቅጠልዋ ወዙ። አንዲት ጽጌረዳ ቃልዋን አስተዛዝና፣ እንዲህ ተናገረች ለሰማይ ደመና። "ድርቀት በጣም ጎድቶኝ እየኝ ስንገላታ፣ እባክህ ጣልልኝ የዝናብ ጠብታ። ቶሎ ካላራስኸኝ ጉልበቴ እንዲጥናና፣ ምንም ተስፋ የለኝ መሞቴ ነውና።" "አሁን መሄዴ ነው ለትልቅ ጉዳይ፣ ስመለስ መጥቼ ሳልፍ ባንቺ ላይ። አዘንምልሻለሁ ጠብቂኝ" እያለ፣ ምንም ሳይጥልላት መንገዱን ቀጠለ። ጉዳዩን ጨርሶ ቆይቶ ሲመጣ፣ ያቺ ጽጌረዳ ስሯ ውሃ ያጣ፣ እንደዚያ አስተዛዝና ጭንቋን ያዋየችው፣ የፀሐዩ ንዳድ አድርቋት ቆየችው። እስኪጎርፍ ድረስ የወንዝ ውሃ ሙላት፣ ወዲያው እንደመጣ ዝናቡን ጣለላት፣ ግን ደርቃለችና አልቻለም ሊያድናት። "ሳልደርስላት ቀረሁ አዬ ጉድ" እያለ፣ ደመናም ወደፊት ጉዞውን ቀጠለ። ሰውም እንደዚሁ ጭንቁን እያዋየ፣ በችግሩ ብዛት እየተሠቀየ። ብዙ ጊዜ ኖሮ ቆይቶ ሲጉላላ፣ የሚረዳው አጥቶ ከሞተ በኋላ። ዘመድ ወዳጆቹ እንባ እያፈሰሱ፣ ተዝካር ቢያወጡለት አርባ ቢደግሱ፣ ይህ ሁሉ ከንቱ ነው አይጠቅመውም ለሱ። እውነት ከወደደው ሲቸገር ሲጎዳ፣ በሕይወቱ ሳለ ሰው ወዳጁን ይርዳ።›› ገንዘቡን ያገኘነው በፈለግነው ሰዓት ሳይሆን ከረፈደ ነው፡፡ ይኼ ገንዘብ እማዬን አይመልስም፡፡ ሰው ከምንም በላይ ዋጋ እንዳለው ተሰማኝ፡፡ በዙሪያዬ ያሉ እኔ ዘንድ ትልቅ ዋጋ ያላቸውን ሰዎች አሰብኩ፡፡ የኢንቱን ስልክ አንስቼ ተመለከትኩት፡፡ ከመቶ በላይ ያልተመለሱ ጥሪዎች ነበሩት፡፡ ስልኩን ከፍቼ የፅሁፍ መልዕክቶችን ካነበብኩ በኋላ የአሰሪ ተብዬውን ስልክ ወሰድኩ፡፡ የእኔና የማህሌት ግንኙነት ስሙ ምን እንደሚባል አላውቅም፡፡ ሰላም የሚሰማኝ እሷ ስትኖር ነው፡፡ ሁሌም ከጎኔ አለች፡፡ ይኼን የመከራ ጊዜ ያለሷ በፍፁም የማልፈው አይመስለኝም፡፡ ሞዴል ተፈትነን የዋናው ፈተና ቀን ደረሰ፡፡ ኢንቲሳር ከእኔ፣ ከማህሌት አሊያም ከአብዱኬ ጋር ካልሆነ ተረጋግታ መቀመጥ አትችልም፡፡ ትረበሻለች፡፡ ሞዴል ስፈተን አብዱኬ ለተከታታይ ቀናት ስራ አቋርጦ ሲጠብቃት ነበር፡፡ ለዋናው ፈተናም አብዱኬን ስራ ከማስፈታት ውጪ አማራጭ አልነበረንም፡፡ ፈተናው ተጠናቅቆ በመጨረሻው ቀን የፌሎው ልጆች የምህረት ቤተሰቦች ቤት ልዩ ግብዣ አዘጋጁ፡፡ ግብዣው ላይ ከአቤላና ከማህሌት ጋር ተካፍለን ወጣን፡፡ ማህሌት መኪናዋን አቤላን ለመሸኘት ወደ ቀራኒዮ እያሽከረከረች ‹‹አብርሽዬ ኢንቱዬ medical care ማግኘት ያለባት አይመስልህም?›› አለችኝ፡፡ ‹‹ማለት?›› ‹‹I mean የአዕምሮ ህክምና ምናምን ……›› ‹‹የእብድ ሀኪም ቤት?›› ፊቴ ተቀያየረ፡፡ ‹‹calm down አብርሽዬ …… የአዕምሮ ህመም እኮ just እንደሌላው ህመም ሁሉ በህክምና የሚድን ነው፡፡›› ‹‹እና አማኑኤል ትግባ ማለትሽ ነው?›› ከዚህ ቀደም ስለ እብድ ሀኪም ቤት የሰማሁትም ሆነ በፊልም ያየሁት ነገር የሚደብር ነው፡፡ ኢንቱዬን ደግሞ ደፍሬ እንደዚህ ያሉ ቦታዎች ላስገባት አልችልም፡፡ ‹‹ኢንቱዬን Where ever it is የአእምሮ ሀኪም ያለበት ቦታ እንውሰዳት፡፡ በአንድ ኪኒን እኮ በቀላሉ control ሊደረግ የሚችል ሊሆን ይችላል፡፡ ደግሞ በግድ ቀምተው ሆስፒታል ትቆይ አይሉህም፡፡›› ‹‹እብድ ናት ተብሎ ሰው ያገላታል፡፡ አሁን እንኳን በቃ ለቀቀች እያሉ ያልሆነ አስተያየት ነው የሚያዩዋት …… አስበሽዋል እዛ ከወሰድናት ደግሞ እብድ ናት ብሎ ሰው ሁ
Show all...
ላ ……›› ብዬ ቀና አልኩ፡፡ ከአቤል ኋላ ማህሌት …… ምህረት …… ቤተልሔም ……… ሁሉም የፌሎው ልጆች በእጆቻቸው ለመያዝ የከበዳቸውን ያህል በኩርቱ ፌስታል ተሸክመዋል፡፡ ሁለት ትልልቅ ፍራሾች መሬቱ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ የተጠቀለለ ወለልም የቤታችንን ግርግዳ ተደግፎ ቆሟል፡፡ ‹‹Surprise!›› አሉ በአንድነት! እንባዬ አይኔን ሞላው፡፡ ‹‹አቤላ ምንድነው?›› አልኩት፡፡ የማየውን ማመን ከብዶኛል፡፡ እንባዬ ከአይኔ አመለጠ፡፡ ማህሌት ተጠመጠመችብኝ፡፡ አቅፋኝ ‹‹ስልክህን ያላነሳነው Surprise ልናደርግህ ፈልገን ነው፡፡›› አለችኝ፡፡ ‹‹ሰው ናቸው መልዓክ?›› ማመን አቃተኝ፡፡ ‹‹ተቃቅፋችሁ ትቆማላችሁ ወይስ ታስገቡናላችሁ?›› አቤላ እየሳቀ ያየናል፡፡ በሩን በደንብ ከፍትኩትና ከማህሌት ጋር ወደ ውስጥ ገባን፡፡ ሁሉም በተራ በተራ ገቡ፡፡ ብርድ ልብሱን አጣጥፌ አነሳሳሁት፡፡ መስኮቱን ስከፍተው ቤቱ በብርሀን ተሞላ፡፡ ሁሉም ደረታቸው ላይ በትንሹ የቤተ-ክርስቲያናቸው አርማ ያለበት ነጭ ቲሸርት ለብሰዋል፡፡ ሆዳቸው አካባቢ በትልቁ ‹‹Together …… we can!›› እና ‹‹በአንድነት እንችላለን!›› የሚሉ ፅሁፎች ከላይና ከታች ተፅፈዋል፡፡ ከስር ደግሞ ሴቶቹ ጥቁር ሰማያዊ ቀሚስ …… ወንዶቹ ጥቁር ሰማያዊ ጂንስ ሱሪ ለብሰዋል፡፡ እማዬን ሰላም ብለዋት ተቀመጡ፡፡ ማህሌት ፍራሹ ላይ እየተቀመጠች ‹‹አብርሽዬ …… ለመገዛዛት ስንዞር ምሳ አልበላንም! I am hungry! Please እንብላ!›› አለች፡፡ አቤላ ያመጡትን ምግብ በሁለት ምድብ ከፍሎ ማቀራረብ ጀመረ፡፡ ምህረት ከእናቴ ጋር ታወራለች፡፡ የምግቡ ሽታ ሆዴን አላወሰው፡፡ እኔ፣ እማዬ፣ ማህሌት፣ አቤላ፣ ምህረትና ሁለቱ ወንዶች በአንድ ቡድን …… የተቀሩት ደግሞ በሌላ ሆነው መብላት ጀመርን፡፡ ሚቾዬና ምህረት እማዬን በላይ በላዩ ያጎርሷታል፡፡ በጣም ርቦኝ ስለነበር አንድ እንኳን ሳላወራ ለእነሱ ንግግር አንገቴን ብቻ እየወዘወዝኩ ወጠቅኩ፡፡ የምግቡ አይነት ምን እንደሆነ መለየት የጀመርኩት ስጠግብ አካባቢ ነው፡፡ በልተን እንደጨረስን ማህሌት ኮዳዋን አንስታ ውሀ እየተጎነጨች ‹‹Guys! Let us change this house! ኢንቲሳር ስትመጣ totally ሌላ ቤት የገባች እንዲመስላት ነው የምናደርገው!›› አለች፡፡ እማዬን አዝዬ እነአብዱኬ ቤት አስገብቻት ተመለስኩ፡፡ ሙሉ የቤታችንን ኮተት ከቤት ውጪ አወጣነው፡፡ የውስጡን የተሰነጣጠቀ ግድግዳ ክሬም ቀለም ቀባነው፡፡ አቤላ ልምድ ስለነበረው ብዙ ጊዜ አልወሰደብንም፡፡ አዲሱ ሰማያዊ ወለል ተዘረጋ፡፡ በጣም ያምር ነበር፡፡ አዳዲሶቹ ፍራሾች ቀለም እንዳይነካቸው ከግድግዳው ፈቀቅ እየተደረጉ ተዘረጉ፡፡ በጣም ከፍታ አላቸው፡፡ ብርድ ልብሶቻችንን ፍራሾቹ ላይ አነጠፍን፡፡ ቤቱ ቀለል አለ፡፡ ትራሶቹን በስርዓቱ ደረደርን፡፡ አዲስ ቤት ይመስል ነበር፡፡ ማህሌት አንድ ፍሬም ከተጠቀለለበት ማሸጊያ አውጥታ ከፊት ለፊት ግድግዳው ላይ ሰቀለችው፡፡ ፍሬሙ ውስጥ ያለው ፅሁፍ ‹‹ሁሉም ቀን የራሱ መልካም ስጦታ አለው!›› ይላል፡፡ ‹‹ቢያንስ ሁሌ ከእንቅልፍህ ስትነሳ ይኼን ስታይ positive positive side እያሰብክ እንድትውል ይረዳሀል!›› አለች፡፡ ፈገግ አልኩላት፡፡ ያመጡትን አስቤዛ በአይነት በአይነቱ ጥግ ላይ ደረደሩት፡፡ ቢያንስ ለአንድ ወር ምግብ የሚያሳስበን አይመስለኝም፡፡ ከጨረስን በኋላ ሴቶቹ እራት ሳንሰራላችሁ አንሄድም ብለው ግግም አሉ፡፡ ከሰሉን አቀጣጥዬ መክተፊያና ድስቱን ሰጠኋቸው፡፡ እየመሸ ነበር፡፡ እማዬን ይዣት ወደ ቤት ስገባ ያየችውን ማመን ከበዳት፡፡ እያለቀሰች መረቀቻቸው፡፡ ወጡን ሰራርተው ሲጨርሱ፤ እማዬ እንዲሻላት ፀልየውላት ለመሄድ ተነሱ፡፡ አብረን እየተጫወትን እስከመኪናቸው ድረስ ሸኘኋቸው፡፡ ልንለያይ ስንል ሁሉንም ከልብ አመሰገንኳቸው፡፡ ማህሌት ከቦርሳዋ ውስጥ የተጠቀለለ አስር ሺህ ብር አውጥታ እየሰጠችኝ ‹‹ይኼ ደግሞ ለአስፈላጊ ነገር ይጠቅማችኋል!›› አለችኝ፡፡ ‹‹ሚቾ ……›› ‹‹Come on አብርሽ! ይኼን እኮ ነው Social responsibility የምንለው! አንተ ደግሞ አሮጌውን ፍራሾች ካንተ በላይ ለሚያስፈልገው ሰው ስጥ! አንተ ስታስረዳን እንቢ ብለናል እንዴ? አላልንም! አንተ እውቀት አለህ ባለህ እውቀት አገዝከን! እኛ ደግሞ just ለእንደዚህ አይነት purpose ባጠራቀምነው ብር Surprise አደረግንህ! Just take it! It is normal! We are friends!›› ‹‹ባለፈው ፈጣሪ ላንተ የሰጠህ ጥሩ ነገር ብለሽ ስትቆጥሪ ግን እኔን ማለት ረስተሻል!›› ሳቀች፡፡ ገንዘቡን ተቀብዬ አቀፍኳት፡፡ ሁሉንም አቅፌ አመሰገንኳቸው፡፡ ማህሌት ‹‹ሁሌም ከጎንህ ነን! ደግሞ አብዱኬን next days ሄደን እንጠይቀዋለን፡፡ እሺ?›› ብላ ጉንጬን ስማ ወደ መኪናዋ ገባች፡፡ ስለአብዱኬ አቤላ እንደነገራት ገባኝ፡፡ መኪናዎቻቸው ከአይኔ እይታ እስኪሰወሩ ድረስ ቆሜ ተመለከትኳቸው፡፡ ለኢንቱዬ ደውዬ ልነግራት ፈለግኩና ስትመጣ አይታው ብትደመም ይሻላል ብዬ ተውኩት፡፡ ወደ ቤት ስገባ እማዬ ተኝታለች፡፡ አስተካክዬ አለበስኳት፡፡ ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ይላል፡፡ ኢንቱዬን ማደር አለማደሯን ልጠይቃት አሰብኩና ወጥቼ ካርድ ገዝቼ ተመለስኩ፡፡ ስደውል ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሶስት ሰዓት ተኩል ሲሆን እንደምታድር ገምቼ ራት አቀራረብኩና እማዬን ቀስቅሻት በላን፡፡ አራት ሰዓት አካባቢ ተመቻችቼ ተኛሁ፡፡ እንቅልፍ የበላ ሰው ይወዳል መሰለኝ ይዞኝ ነጎደ፡፡ ጠዋት ከእንቅልፌ ተነስቼ ውጪ ላይ ስፖርት ሰራሁና ቤት ገብቼ ለቁርሳችን ሻይ ማፍላት ጀመርኩ፡፡ ሻይ እያፈላሁ የኢንቱን ስልክ ደጋሜ ሞከርኩ፡፡ አይሰራም፡፡ ጭንቅ ጭንቅ አለኝ፡፡ የያስሚን ስልክ ስለነበረኝ እሷ ጋር ደወልኩኝ፡፡ የሷ ስልክ ይሰራል፡፡ ያስሚን ስልኩን አንስታ ‹‹ወዬ ኢንቱ ……›› አለች፡፡ ኢንቱ ካርድ ሲያልቃት ብዙ ጊዜ በእኔ ስልክ ትደውልላት ነበር፡፡ ትንሽ ግራ ገባኝ፡፡ ‹‹ያስሚን …… ኢንቱ አይደለሁም …… ወንድሟ ኢብራሂም ነኝ፡፡›› ‹‹ኢቦ እንዴት ነህ? እሷ መስላኝ እኮ ነው፡፡›› ‹‹ኢንቱ አንቺ ጋር አልመጣችም እንዴ?›› የልቤ አመታት ሲፈጥን ተሰማኝ፡፡ ‹‹አዎ ኢቦዬ እኔ ጋር አይደለችም፡፡ ስልኳ እንቢ ብሎህ ነው?›› ‹‹ሰርግ የለም እናንተ ጋር?›› ግራ ተጋባሁ፡፡ ‹‹ኢቦ ደግሞ የምን ሰርግ ነው? ምንድነው ኢንቱ ደህና አይደለችም እንዴ?›› ‹‹ደህና ናት!›› በአጭሩ ተሰናብቼ ስልኩን ዘጋሁት፡፡ አዎ ደህና ናት ከሚለው ውጪ ምንም መስማትም መናገርም አልፈልግም፡፡ ስልኳን ያለእረፍት ደጋግሜ ሞከርኩት አይሰራም፡፡ እማዬን ቁርስ እንድትበላ ልቀሰቅሳት ብሞክር አትነሳም፡፡ ማታ እንቅልፍ አጥታ ይሆናል ብዬ ቁርሱን አቀራርቤ እስክትነሳ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ሰዓቱ ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ይሆናል፡፡ የኢንቱን ስልክ ደጋግሜ እየሞከርኩ ቀና ስል የኢንቱን ማስታወሻ ደብተር ተመለከትኩ፡፡ ምናልባት የፃፈችው ነገር ካለ ብዬ ደብተሩን ለመክፈት መርፌ ቁልፌን መፈለግ ጀመርኩ፡፡ መርፌ ቁልፌ ጠፍታ ነበር፡፡ መርፌ ቁልፍ ገዝቼ ተመለስኩና ደብተሯን ከፈትኳት፡፡ ከባለፈው በኋላ የፃፈችው ካለ እየገለጥኩ መፈለግ ጀመርኩ፡፡ መጨረሻ ላይ ያላነበብኳቸውን ሶስት ገፆች አገኘሁ፡፡ . ይቀጥላል … . :¨·.·¨: ❀ ·. ┈┈••◉❖◉●••┈
Show all...
ከተራራው ላይ ክፍል አስር (ፉአድ ሙና) . ‹‹ከሰማይ በላይ ያለኸው ፣ ነፍሴን ለስቃይ ፈጥረኸው፣ ለአፍታ ሊያርፍ ቢደገፍ፣ ምነው ምርኩዙን ቀማኸው፣ በሱም ቀናህ?›› *** እራት ከተበላ በኋላ አብዱኬ ትንሽ ተጫውቶ ሄደ፡፡ ትንሿ ጎጇችን ውስጥ ሶስታችን ብቻ ቀረን፡፡ እማዬ ተኝታለች፡፡ ከኢንቱዬ ፊት ለፊት ተቀምጬ አይን አይኗን እያየሁ እስክትነግረኝ መጠባበቅ ጀመርኩ፡፡ ፊቷ ላይ መከፋት ይነበባል፡፡ መከፋቷን በውሸት ፈገግታ ልትሸፍነው እየሞከረች ‹‹ምንድነው የምትቁለጨለጨው?›› አለችኝ፡፡ አይኖቼን ፊቷ ላይ እንደተከልኩ ‹‹ንገሪኛ!›› አልኩ፡፡ እንባዋ አይኗን ሞልቶ ለመፍሰስ መታገል ጀመረ፡፡ ሳግ ባጠረው ድምፅ ‹‹እነግርሀለሁ ……›› አለች፡፡ ፍራሹ ላይ ከጎኗ ተቀምጬ አቀፍኳት፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ እያለቀሰች ‹‹ኢቦዬ አልቻልኩም …… ሁሉም ከቁጥጥሬ ውጪ ሆነ!›› አለችኝ፡፡ በእጄ ፀጉሯን እየዳበስኩ በዝምታ እስክትቀጥልልኝ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ‹‹ኢቦዬ …… እጄ ላይ ምንም ገንዘብ የለም፡፡ ነገ እንኳን ለምሳ የምቋጥርልህ ነገር የለኝም! ከስራ ተባርሬያለሁ፡፡ በቻልኩት አቅም ለመሸፈን ሞክሬያለሁ፡፡ ግን አሁን ከአቅሜ በላይ ሆነ፡፡ አታፍርብኝም አይደል?›› ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት፡፡ ‹‹ግን አይዞህ እሺ …… ብንራብም ይኼን ሳምንት ብቻ ነው፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ገንዘብ አገኛለሁ፡፡ እሺ?›› እንባዋን እየጠረገች ‹‹እሺ ኢቦዬ?›› አለች፡፡ ግንባሯን ሳምኳት፡፡ ‹‹ኢንቱዬ …… እንደዚህ በግልፅ ስትነግሪኝ እኮ ላንቺም ለእኔም ይቀላል፡፡ አትጨነቂ …… ደግሞ ለዚህ ሳምንት መፍትሔ አናጣም!›› ተንሰቀሰቀች፡፡ አቅፌ ላረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ‹‹ኢንቱዬ …… እኔን እኮ ከረሀቡ በላይ የሚያመኝ አንቺ ከፍቶሽ ሳይ ነው፡፡ እኛ ለረሀብ አዲስ ነን እንዴ? ረሀቡንም መከራውንም መቋቋም የቻልኩት ግን አንቺን በማየት ነው፡፡ አንቺን ማየት …… ደስ ብሎሽ ማየት ከሁሉም በላይ ያጠነክረኛል፡፡ ኢንቱዬ በጣም እወድሻለሁ፡፡ በጣም! አትዘኚ! አብረን እናልፈዋን እሺ?!›› እንባዋን እየጠረገች ‹‹እሺ!›› አለች፡፡ ‹‹ፈገግ በያ!›› ‹‹እሺ›› ፈገግ ለማለት ሞከረች! ጎኗን እየነካሁ ስኮረኩራት መሳቅ ጀመረች፡፡ መኝታችንን አነጣጠፍኩና ተቃቅፈን ተኛን፡፡ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ በእኔና በኢንቱ መካከል ትራስ ገብቷል፡፡ ኢንቱ ተዘርራ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ሰጥማለች፡፡ በመካከላችን ያለው ትራስ የእማዬ ፍራሽ ላይ የነበረ ነው፡፡ ግራ ግብት አለኝ፡፡ ማታ ተቃቅፈን እንደተኛን ትዝ ይለኛል፡፡ ተነስቼ ለትናንትና አቅጄው የነበረውን ለመጨረስ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ትንሽ ቆይታ ኢንቱዬ ነቃች፡፡ እየሳቀች መሀከላችን በነበረው ትራስ መታችኝ፡፡ ሳቋ እየተጋባብኝ ‹‹ይኼ ከየት መጥቶ ነው?›› አልኳት፡፡ ‹‹ፍቅረኛ ምናምን ጀምረሀላ!?›› በአይኖቿ ልታወጣጣኝ ሞከረች፡፡ ሳቅኩኝ! ‹‹ተናገራ የምሬን እኮ ነው፡፡›› ‹‹ኧረ ወፍ የለም!›› ‹‹እሺ ትናንት የተመቸችህ…… የሳምካት ወይም ብስማት ምናምን ያልካት ሴት የለችም?›› ‹‹ባይሆን የሚያምር ከንፈር አይቻለሁ፡፡ ግን ማንንም አልሳምኩም፡፡›› ‹‹ወረኛ አሳሳምህማ ልምድ ያለው ሰው አሳሳም ነበር!›› ‹‹የምን አሳሳም ነው?›› ግራ አጋባችኝ፡፡ ‹‹ማታ በእንቅልፍ ልብህ ስትስመኝ ነበር …… ለዛ ነው ትራሱን መሀል ላይ ያደረግኩት!›› ‹‹ማን እኔ? ምንሽን?›› ‹‹ከንፈሬን ነዋ! የሆነ ሰዓት ስባንን አይንህን ዘግተህ ……›› ሳቀች፡፡ ‹‹ቆይ እንዴት ይሆናል? ማለቴ እንዴት ከንፈርሽን አገኘሁት?›› ‹‹ብዙም ሩቅ አልነበረም …… ፊት ለፊትህ ነበር እኮ!›› ሳቀች፡፡ ‹‹ደግሞ አቅፈኸኝ ስለነበር በደመ-ነብስም አይጠፋህም!›› አፈርኩ! እሷ ትስቃለች፡፡ በትራስ እየመታች ሙድ ትይዝብኛለች፡፡ ‹‹ባይሆን እውነቱን ተናገር! ስመህ አታውቅም ማንንም?›› ‹‹ኢንቱዬ …… ማንንም አልኩሽ እኮ! ማንንም!›› ተነስቼ መለባበስ ጀመርኩ፡፡ ከቻልኩ ስልኩን ዛሬ እንደምንም ለመሸጥ አስቤያለሁ፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ስዘገጃጅ አብዱኬ መጣ፡፡ እጁ ላይ ሁለት ፓስቲ ይዟል፡፡ እንደሌላው ጊዜ ምድጃው ላይ የተጣደ ነገር ሲያጣ ‹‹ሻይ የለም እንዴ?›› አለ፡፡ ኢንቱዬ ፈገግ ብላ እያየችው ‹‹ዛሬ ሻይ ፎርፈናል!›› አለች፡፡ ‹‹አትነግሪኝም እንዴ!›› አኮረፈ! ‹‹በቃ እኛ ውጪ ‘ሚቀማመስ እንፈላልጋለን! ለእናንተ ስሪ!›› ከኪሱ ሀምሳ ብር አውጥቶ ሰጣት፡፡ ‹‹ኧረ አብዱኬ ……›› ኢንቱዬ በሀፍረት አንገቷን ሰበረች፡፡ ‹‹ምን ልትዪ ነው ደግሞ …… ወንድምሽ አይደለሁ እንዴ!?›› ‹‹እሱማ ነህ …… አበዛሁት ብዬ እኮ ነው፡፡ አላህ ይስጥልኝ …… መቼስ ምን እልሀለሁ ……›› ፓስቲውን ከሰጣት በኋላ ተሰናብተናቸው ወጣን፡፡ መንገድ ላይ እየሄድን አብዱኬን ከሌላው ጊዜ በተለየ ተመለከትኩት፡፡ መልዓክ መልዓክ መሰለኝ፡፡ በስስት እየተመለከትኩት ‹‹አብዱኬ ……›› አልኩት፡፡ ‹‹ኧ›› ‹‹ታውቃለህ ትምህርት ቤት ስማር ሁሉም በጣም Smart እንደሆንኩ ይነግሩኛል፡፡ ለእኔ ግን በጣም smart ማን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ‹‹ማነው?›› ‹‹አንተ ነህ!›› ‹‹ምን ቀላቅለህ ቅመህ ነው?›› ‹‹ቀልዴን አይደለም አብዱኬ! እኔን Smart የሚሉኝ በሚታወቅ ቀመር ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ደግሞ በሽምደዳም ቢሆን ሌሎቹን ትምህርቶች በደንብ መረዳትና መስራት ስለምችል ነው፡፡ ይኼ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ጥረት እንጂ ልዩ ጥበብ አይጠይቅም፡፡ ልዩ ጥበብ የሚጠይቀው ያልተፃፈን ነገር መረዳት ነው፡፡ የሰውን ልጅ መረዳት! የሰውን ጭንቀት ያለምንም ንግግር መረዳት! ከጭንቀቱ መፈወስ! ህይወትን መረዳት! ተቋቁሞ መኖር መቻል! ብዙ ሰው እኔን መሆን ይፈልጋል፤ እኔ ግን የምፈልገው አንተን መሆን ነው!›› ‹‹የእኔን Smart ልንገርህ?›› ‹‹ንገረኝ ……›› ‹‹የእኔ Smart ኢንቲሳር ናት፡፡ ለራስ ሳይጨነቁ ለሌላ ሰው የመኖር ምሳሌዬ ናት፡፡ ድሮ ስራ ስጀምር ገንዘብ እንዴት መጠቀም እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ ሁሉንም ያስተማረችኝ እሷ ናት፡፡ የከፋኝ ቀን የምሄደው ወደሷ ነው፡፡ ከባድ የመሰለኝን አቅልላ ታሳየኛለች፡፡ ያጣሁ ጊዜ ያላትን በአቅሚቲ ታካፍለኛለች፡፡ አንዳንዴ ምናለ ከእሷ ጋር ከአንድ መሀፀን በወጣን …… የስጋም እህቴ በሆነች ብዬ እመኛለሁ፡፡ ኢቦዬ እህትህ በጣም በጣም ልዩ ሰው ናት!›› ‹‹እሷስ ልክ ነህ ልዩ ናት!›› ባጃጅ ተራ ደርሰን አንድ ሻይ ቤት ገባንና ፓስቲ በሻይ በላን፡፡ አለምባንክ ደርሰን ከአብዱኬ ጋር ልንለያይ ስንል እጄን ይዞ ‹‹ይኸውልሽ ኢቦ …… ችግር ሁሌም ያጋጥመናል፡፡ ግን ደግሞ ያልፋል፡፡ ገባሻ! ዛሬ ቢቸግረን ነገ እናገኛለን፡፡ አትጨነቅ!›› አለኝ፡፡ አሁን አሁን አብዱኬን በአንድ አመት እንደምበልጠው መርሳት ጀምሬያለሁ፡፡ ታላቅ ወንድሜ …… ታላቅ ወንድሜ ይመስለኛል፡፡ ከአብዱኬ ጋር ተለያይተን ወደ ትምህርት ቤት ገባሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ በቻልኩት መጠን ስልኩን ለመሸጥ ለብዙ ተማሪዎች ሳሳይ ዋልኩ፡፡ በርካሽ ስምንት ሺህ ድረስ ልሸጥላቸው ብዙዎችን አጠያየቅኩ፡፡ የሚደፍር አልተገኘም፡፡ ባዶ እጄን ወደ ቤት መግባት ቀፈፈኝ፡፡ ማህሌትን ላስቸግራት አሰብኩና ወደ ማታ ደወልኩላት፡፡ ስልኳ ዝግ ነበር፡፡ ማታ ቤተል ቤተ-መፅሀፍት ከአቤላ ጋር ተቀምጬ አብዱኬ ስለዘገየብኝ ለመደወል ሞከርኩ፡፡ ስልኬ ካርድ አልነበረውም፡፡ በአቤላ ስልክ ደወልን፡፡ ስልኩ ዝግ ነው፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ትንሽ ጠብቄው ሲቆይ ወደ ቤት ሄድኩ፡፡ ለብቻዬ ስለሆንኩ ነው መሰል መንገዱ በጣም ረዥም
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.