cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጉባኤ አፈወርቅ ወአፈበረከት🕯

ይህ ጉባኤ ቤት(ቻናል)፦ አፈ በረከት የሆኑ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ተግሳጻትን፣ መንፈሳዊ የሆኑ አነቃቂ ስብከቶችን እንዲሁም አጫጭር የሆኑ ፊልሞችን የምናቀርብበትና የምንዘክርበት ጉባኤ ቤት ነው✞ ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት @God_Listen

Show more
Advertising posts
2 863
Subscribers
No data24 hours
-137 days
-8130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤ የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል? በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡ የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡ እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ! ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤ የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ መናገር ያምረኛል፡፡... ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች። ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ 𝚓𝚘𝚒𝚗 👉 @Gubaye_Afe_Werk💡
Show all...
26👍 7
"የልቤን ኃዘን ለማን እነግረው ይሆን"። 🕯 ልብኪ የዋህ እመቤቴ ማርያም ሆይኃጥእን ለጥፋት የማይመኝ ቂም በቀልን የማያውቅ ልብሽ ፍጹም ነው እኮን፤ ድንግል እመቤቴ ሆይስለዚህ ይቅርታ ልማድሽ ነውና ይቅር በይኝ፤በልቤ ውስጥ ያለውን ምኑን ስንቱን እነግርሻለው? ኀዘኔን ጭንቀቴንም አንቺ ታውቂያለሽና። 🕯 ንዒ ማርያም እመቤቴ ማርያም ሆይለእውራን ብርሃናቸው፣ለተጠሙትም የወይን ምንጫቸው ሆይ፤ ወደኔ ፈጥነሽ ነይ። ድንግል እመቤቴ ሆይኦ ወዮ ትተይኝ ይሆን? ኦ ወዮ ትንቂኝ ይሆን? እንግዲያ የልቤን ኃዘን ለማን እነግረው ይሆን። መልክዐ ኤዶም
Show all...
27👍 7
የጨለማ ኀይል ተሰደደ፤የሕይወት ተስፋ በሰማያት ተሠራ፤ ዛሬ በሰንበት በዚህ ዕለት ሞትን አሸንፎ ተነሥቷልና" ድጓ ዘፋሲካ ቅዱስ ያሬድ
Show all...
10👏 2
በተመስጦ ሕሊናዬ ከድንግል ማርያም ጋር ነበር፤ከመስቀሉ ሥር ቆማ ስታለቅስ ታየችኝ፤ያን ጊዜ እርስዋ እንዳለቀሰችው እኔም ባለቀስኩ ብዬ እመኛለሁ። The saying of the desert fathers
Show all...
10
"በክርስቶስ የተወደዳችኹ ሆይ ኑ! ወዲህ ቅረቡ፣ በዚህች ዕለት በዳዊት ከተማ የሆነውን አብረን እንይ! በተስፋው ቃል ሲጠበቁ የነበሩት የተመረጡት የአብርሃም ዘሮች ዛሬ ምን እንዳደረጉ እንመልከት! ጌታ ሆይ ረዥሙን ሥቃይህን ማን ሊገልጸው ይችላል? ቅዱስ ኤፍሬም
Show all...
18👍 3
እንደልማድሽ ሁሉን ወደሚችለው ልጅሽ እንዲህ በይ..የማትበቀል ርህሩህ ሆይ ሣይ የሳለውን ሥዕል በከንቱ ያጠፋዋልን? የቀድሞ ስራህ አዳምን አስብ ብለሽ አማልጂኝ። መልክዐ ሕማማት ዘነግህ
Show all...
11
መድኃኔ ዓለም በመስቀል ላይ ያሳየንን ነፍሱን እስከ መስጠት ድረስ የደረሰ ፍቅር በመርሳታችንና ያደረገልንን ባለማስተዋላችን በጥልቅ የኃጢአት ባህር ውስጥ እየዋኘን፤ እርስ በእርሳችን በጥላቻ እየተሰቃየን ነው። ሕማማት ገጽ 17
Show all...
15
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወስ ኲሉ ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአነ ምድር፡፡ ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበ አዕላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት እስመ ገባሬ ሕይወት ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት፡፡ ትርጉም:- ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማያትና የምድር ኃይላት ሁሉ ይናወጣሉ። ያን ጊዜ በምድር ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለቅሳሉ አላቸው፡፡ ጌታችንም ከባሕርይ አባቱ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ በመለከት ድምፅ ከአእላፍ መላእክት ጋር በግርማ መለኮቱ ከሰማይ ወደ ምድር ይወርደል፡፡ መዝሙር ዘደብረ ዘይት ቅዱስ ያሬድ
Show all...