cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሕይውትን መረዳት

ሕይውትን እንዴት መረዳት እንደምቻል፣ ሕይውትን መረዳት ምን ጥቅም እንዳለውና ትክክለኛ የህይውት ትርጉም ምን እንደ ሆነ ብዙ ትምህርቶች የሚነሱበት ቻናል ነው።

Show more
Advertising posts
218
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንደበት የአይምሮ መስታወት ነው። 👉በአይምሮህ ውስጥያለውን ሀሳብ እና ፍላጎት አንደበትህ መስታወት ሆኖ ያሳይሀል። ሰው በአይምሮው ውስጥ ምንድነው ያለው የሚለውን ለማወቅ ከፈለክ አንደበቱን ተከታተለው። ወይም ደግሞ እንዲያወራ አድርገው ያኔ አይምሮ ውስጥ ምን እንዳለ ታያለህ። ምክንያቱም ሰው በአይምሮ ሞልቶ የተረፈውን ነው በአንደበቱ የሚናገረው። ስለዚህ አንደበትህን መደበቅ ከቻልክ ሰዎች በአይምሮህ ውስጥ ያለውን እቅድ አያውቁትም። እራስህን መጠበቅ ከፈለክ አንደበትህን ጠብቀው። Its Me Jonah 🙏🙏🙏
Show all...
አስተሳሰብ ሲያድግ ሰዎችን ለማሳመን ከማውራት ይልቅ ዝም ማለት በጣም የተሻለ እንደሆነ መረዳት ትጀምራለህ። ሰዎች ካላመኑኝ ብሎ የሚያስብ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርግ ፓርቲ ብቻ ነው። እኛ ግን ዓላማ አንግበናል... ዓላማ አለን። ማንም እንዲያቆመን ሳንፈቅድ ለመስራት... ሰዎች ምን አሉ አላሉም ልናዳምጥ አይገባም። ምክንያቱም የእኛ ትርፍ በሰዎች ጭብጨባ ሳይሆን የሚመጣው በሰራነው መጠን ነው። በአደረግነው ልክ እናገኛለን... አንድ ጓደኛዬ እንዲህ ይላል ለቦታው ባይመጥንም
Show all...
ተመራማሪዎች አንድን ሻርክ ለጥናትና ምርምር በትልቅ የውሃ ታንክ ውስጥ ያስገቡታል።ቀጥለውም ትንሽ አሳዎችን በውሃ ታንከሩ ውስጥ ይጨምራሉ። እንደጠበቁትም ሻርኩ የገቡትን አሳዎች ለመብላት ጊዜ አልፈጀበትም።በኋላም ንፁህ በሆነ መስታወት የውሃ ታንከሩን ለሁለት በመክፈል ሻርኩን በአንድ ክፍል አሳዎቹን በሌላኛው ክፍል እንዲለያዩ አደረጓቸው።ሻርኩ አሳዎቹን ለመብላት ሲሞክር በመሃል ካለው መስታወት ጋር ይጋጭ ጀመር።አሳዎቹን ለመብላት ከመስታወቱ ጋር ብዙ ከተጋጨ በኋላ ተስፋ ሲቆርጥ በመሃል የነበረውን መስታወት ያነሱታል። ሻርኩም በመሃላቸው መስታወቱ እንዳለ የበፊቱን እያየ አሳዎቹን የመብላት ሙከራውን አቆመ።      #በፊት የገጠሙንን መሰናክሎችና ውድቀቶች እያሰብን ተስፋ እንቆርጣለን።በህይወታችን ውስጥ ምንም እንኳን ተደራራቢ ችግሮች  ውድቀቶች ቢገጥሙን ተስፋ መቁረጥ እንደማይገባን የሚያሳይ ጥናት ነው።
Show all...
“ከተሳሳታችሁ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍሩ፡፡ እንደገና ስትጀምሩ እኮ የምትጀምሩት ከዜሮ ሳይሆን ከስህተታችሁ ትምህርትና ልምድ ካገኛችሁበት ደረጃ በመነሳት ነው - ካልታወቀ ምንጭ  👉ከትናንትናው ዛሬ አድጋችኋል፣ ተለውጣችኋል፣ በስላችኋል፣ ተሻሽላችኋል፣ ጥበብ አግኝታችኋል፣ በርትታችኋል፣ ነገሩ ገብቷችኋል . . . ፡፡ ብርቱ ናችሁ! በርቱ!💪 @yetbeb
Show all...
የልጆች ማህበራዊ እና ሀይለ-ስሜታዊ እድገት(social and emotional development) ማህበራዊ እድገት ለሰው ልጅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የእድገቶች አይነት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ማህበራዊ እድገት የሚጀምረው ልጆች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ልጆች ከተወለዱ ጊዜ ጀምሮ የምናደርግላቸው ነገሮች የልጆች ማህበራዊ እድገት ላይ የራሳቸው የሆነ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ አላቸው፡፡በዚህ መስክ ብዙ የተመራመረው ተመራማሪ ኤሪክ ኤሪክሰን ሰዎች ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ እስከ እርጅና ድረስ ያለውን የሰዎች የማህበራዊ እድገትን በስምንት ደረጃዎች ይከፍላቸዋል፡፡እነዚህ ስምንት ክፍሎች በእድሜ ክልል የተከፋፈሉ ሲሆን በአንደኛው ደረጃ ላይ ያለው የማህበራዊ እድገት ለቀጣዩ መሰረት ነው፡፡ ስምንቱን ደረጃዎች ከዚህ እንደሚከተለው እናያቸዋለን፡፡ 1.ማመን ወይም አለማመን( Trust Versus Mistrust) ይህ የእድገት ደረጃ ልጆች ከተወለዱ ጀምሮ እስከ አንድ አመት ተኩል ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡በዚህ እድሜ ላይ ያሉ ልጆች ፍላጎታቸውን የሚገልጹት በማልቀስ ነው፡፡ በዚህ ወቅት በሚደረግላቸው እንክብካቤ መጠን እና ቀጣይነት ሌሎችን ማመን ይጀምራሉ፡፡በዚህ ወቅት ላይ በአግባቡ የሚፈልጉት ነገር ከተሟላላቸው አለምን ማመን ይጀምራሉ የደህንነት ስሜትም ይሰማቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚፈልጉትን ነገር በአግባቡ እና ወጥ በሆነ መልኩ የማናሟላላቸው ከሆነ መጠራጠር እና መፍራት ይጀምራሉ፡፡በዚህም የተነሳ መጨነቅ፣ፍርሀት እና ከፍተኛ የሆነ እምነት ማጣት ሊታይባቸው ይችላል፡፡ 2. በራስ መተማመን ወይም ማፈር እና እራስን መጠራጠር( Autonomy vs. Shame and Doubt) ይህ የእድገት ደረጃ ከ አንድ አመት ተኩል እስከ ሶስት አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡በዚህ ጊዜ ውስጥ ልጆች መንቀሳቀስ የሚጀምሩ ሲሆን እቃ ማንሳት በአሻንጉሊት መጫወት ይፈልጋሉ፡፡ ምግብም እራሳቸው መመገብ ፣ልብሳቸውን እራሳቸው መልበስ….ወዘተ ይፈልጋሉ፡፡ እራሳችን እንስራ በሚሉበት ጊዜ እንዲሰሩ የምናበረታታቸው ከሆነ በራስ የመተማመን ስሜታቸውን ያዳብራሉ፡፡እራሳቸውን ችለው በዚህ አለም ላይ የመኖር ስሜት ያድርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የምንተቻቸው ከሆነ እንዳይሰሩ የምንቆጣጠራቸው ከሆነ ወይም ሁሉንም ነገር እኛ የምንሰራላቸው ከሆነ ነገሮችን ለመሞከር ሲያፍሩ ወይም እራሳቸውን ሲጠራጠሩ ይታያሉ፡፡ 3. መነሳሳት ወይም የጥፋተኝነት ስሜት መሰማት( Initiative vs. Guilt) ይህ የእድገት ደረጃ ከ ሶስት አመት እስከ ስድስት አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ልጆች በዚህ እድሜ መጫወት ይጀምራሉ፣ለሚሰሩት ስራ እቅድ ያወጣሉ፣ለጫወታ ይነሳሳሉ ሌሎችንም ያነሳሳሉ …ወዘተ ልጆች ይሄ እድል ከተፈጠረላቸው የተነሳሽነት ስሜት እና በራሳቸው ችሎታ የመተማመን ስሜት ይፈጠርባቸዋል፡፡ነገር ግን እገዳ የምንጥልባቸው ከሆነ ወይም የምንቀጣቸው ከሆነ የጥፋተኛነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ነገሮችን በራሳቸው ለመስራት ከመነሳሳት ይልቅ ሌሎችን መከተል ይመርጣሉ፡፡ 4. በሰሩት ስራ መኩራት ወይም የበታችነት ስሜት መሰማት( Industry vs. Inferiority) ይህ የእድገት ደረጃ ከ ስድስት አመት እስከ አስራአንድ አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ልጆች መደበኛ ትምህርት ይጀምራሉ፡፡ልጆች በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ በሰሩት ስራ የመኩራት ባህሪን ያሳድጋሉ፡፡ስራን ጀምረው ሲጨርሱ የኩራት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡አስተማሪዎች ልጆችን በማነሳሳት እና ያሰቡትን ግብ እንዲያሳኩ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጾ አላቸው፡፡ በዚህም ልጆች ስራን እንዲሰሩ ከተበረታቱ እና በሰሩት ስራ ሽልማት ከተበረከተላቸው በራሳቸው ስራ የመኩራትን ባህሪ ያሳድጋሉ ከዚህም በተጨማሪ ያሰቡትን ግብ እንደሚያሳኩ በራሳቸው ላይ እምነት ይኖራቸዋል፡፡ነገር ግን በወላጅ ወይም በአስተማሪ ገደብ የሚጣልባቸው ከሆነ ወይም የሚቀጡ ከሆነ እራሳቸውን ይጠራጠራሉ፣የበታችነት ስሜት ይሰማቸዋል እንዲሁም የአቅማቸው ጫፍ ላይ ላይደርሱ ይችላሉ፡፡ 5.ማንነትን መለየት ወይም ግራ መጋባት( Identity vs. Role Confusion) ይህ የእድገት ደረጃ ከ 11 አመት እስከ አስራስምንት አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ይህ ወቅት የጉርምስና ወቅት ነው፡፡ጉርምስና ልጆች ከህጻንነት ወደትልቅነት የሚተላለፉበት ድልድይ ነው ልጆች በዚህ ወቅት ላይ እራስን ችሎ መንቀሳቀስ፣ ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈለጉ መወሰን ፣ጓደኞቻቸውን መምረጥ …ወዘተ ይፈልጋሉ፡፡ልጆች በዚህ ጊዜ ላይ በዙሪያቸው ያሉ አማራጮችን ከማየታቸውም በተጨማሪ እራሳቸውን መፈለግ ይጀምራሉ በዚህም የተነሳ እኔ ማነኝ የሚለውን ጥያቄ ይመልሳሉ አካባቢያቸው ይህን ካልፈቀደላቸው ግን ግራ መጋባት ይፈጠርባቸዋል ወደፊት ምን መሆን እንደሚፈልጉም አያውቁም፡፡ 6.ግንኙነትን መፍጠር ወይም መነጠል (Intimacy vs. Isolation.) ይህ የእድገት ደረጃ ከ 18 አመት እስከ 40 አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ይህ የእድሜ ክልል ሰዎች ከቤተሰባቸው ውጪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት የሚፈጥሩበት ወቅት ነው፡፡የወደፊት የትዳር አጋራቸውንም በዚህ ወቅት ውስጥ ይለያሉ፡፡ይህ ሂደት ስኬታማ ከሆነ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ይኖራቸዋል፣ለግንኙነቱ ቁርጠኝነት ያሳያሉ፣ደህንነት ይሰማቸዋል….ወዘተ፡፡ከሰው ጋር መገናኘትን የማይፈልጉና የሚፈሩ ከሆነ ግን የመነጠል ወይም የብቸኝነት ስሜት ይሰማቸዋል በዚህ የተነሳ ድብርት ውስጥ ሊገቡም ይችላሉ፡፡ 7. ውጤታማነት ወይም ውጤታማ ያለመሆን ስሜት (Generativity vs. Stagnation) ይህ የእድገት ደረጃ ከ 40 አመት እስከ 60 አመት ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡ይህ ወቅት ሰዎች ስራ ይዘው ፣ትዳር ይዘው ልጅ ወልደው…ወዘተ የሚኖሩበት ወቅት ነው፡፡በዚህም የተነሳ ሰዎች ላሉበት ማህበረሰብ ማበርከት ስላለባቸው ነገር ያስባሉ ጥሩ አገር ተረካቢ ልጅ እንዲኖራቸው ከመፈለጋቸውም በላይ ባሉበት የስራ መስክ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ ነገር መስራትን ይፈልጋሉ፡፡በህብረተሰብ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ውስጥም ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ማሳካት ያልቻሉ ሰዎች ውድቀትና ውጤታማ ያለመሆን ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ 8.መተባበር ወይም ተስፋ መቁረጥ( Ego Integrity vs. Despair) ይህ የእድገት ደረጃ ከ60 አመት በላይ ባለው ጊዜ ውሥጥ ያለ የእድገት ደረጃ ነው፡፡ ይህ እድሜ የጡረታ እድሜ ሲሆን ሰዎች ወደኋላ ተመልሰው የመጡበትን ሁኔታ የሚቃኙበት ጊዜ ያገኛሉ፡፡ ወደኋላ ተመልሰው የመጡበትን የሂወት መንገድ ሲቃኙ የስኬታማነት ስሜት ከተሰማቸው ከቀጣዩ ትውልድ ጋር በመተባበር ያላቸውን ነገር ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ይፈልጋሉ ስኬታማ ያልሆኑ ከመሰላቸው ግን የተስፋ መቁረጥና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሁም ድብርት ሊሰማቸው ይችላል ከዚህም አለፍ ሲል ሞትን እስከ መፍራት ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ማጠቃለያ፡-
Show all...
አሁን ወስን! እንዲህ ቢሆን ኖሮ እያልክ ስለትላንት ማሰቡን አቁም! አሁን ወስን! አንድ ውሳኔ ህይወትህን እስከመጨረሻው ሊቀይረው ይችላል! ከዚህ ቅፅበት ጀምሮ የምችለውን ሁሉ አደርጋለው በልና ወስን! ቆራጥ ካልሆንክ ማንም አይፈልግህም! ለራስህ አቶን ለምትወዳቸው አቶን! የሚያመነታ ሰው ሲባክን ይኖራል! ቆራጥ መሆን አለብህ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ከፍርሀትህ ጀርባ ቁጭ ብለዋል! ወደኋላ ተመልሰህ ምንም ነገር መቀየር አትችልም፤ ከአሁን ብትጀምር ግን አጨራረስህን ማሳመር ትችላለህ፤ ከዚህ የተሻለ ሰው መሆን ይገባሀል! ወስን ወዳጄ! ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Inspire_Ethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Show all...
ወዳጄ:- በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ፣bቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ይችላሉ።:" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።: ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!
Show all...
በነፃነት መኖር! በህይወት ስንኖር አንድ ልብስ ብቻ መልበስ ቢኖርብን የምናደርገውን ጥንቃቄ አስቡት እስኪ? ያ ልብስ እንዳይቆሽሽ ስንጠነቀቅ፣ ከቆሸሸብን ደግሞ ስናጥበው እንዳይሳሳ ስንጠነቀቅ፣ እንዳይቀደድ ስንሳቀቅ ብቻ በተቻለን አቅም እኛ ሳናልቅ እሱ ቀድሞ እንዳያልቅ ዋጋ እንከፍላለን። የተሰጠን ህይወት እንደዚህ ልብስ ነው፤ ሌላ ተቀያሪ የለንም። ታዲያ ለምንድነው ግድየለሽ የምንሆነው? ሰዎች ምን ይሉኛል ብለን የማንፈልገውን የምናደርገው? አንድ አይን ያለው ሰውኮ በአይን አይቀልድም! ወዳጄ የተሰጠህን የመኖር ዕድል በነፃነት የፈለከውን ሆነህ የፈለከውን አሳክተህ መኖር አለብህ!     🖤🖤🖤💙💙💙
Show all...