cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ግጥም እና ፊልም

እግዘብሔርን በተሰጣችሁ ፀጋ አመስግኑት በገና ክራር ዋሽንት የተለያዩ መዝሙሮችን ለማግኘት @MEZMUROCHACHIN @MEZMUROCHACHIN @MEZMUROCHACHIN @MEZMUROCHACHIN @MEZMUROCHACHIN @MEZMUROCHACHIN

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
2 149
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለክርስቲያን ምኑ ነው? (በዲ/ን ሕሊና በለጠ) ቤተ ክርስቲያን በባሕርይዋ የአንድ ማኅበረሰብን ባሕል ንቃም ኾነ ተቃውማ አታውቅም። በተቻላት መጠን ማኅበረሰቡ ከነ ባሕሉ ድኅነትን ያገኝ ዘንድ ሃይማኖቷንና ሥርዓቷን አስተምራ ታስተናግደዋለች እንጂ። ከእርሷ አምልኮ በተቃራኒው የሚያመልክ የአንድን ተገዳዳሪ የእምነት ተቋም አምልኮም በማይገባ መልኩ ተችታና አኮስሳ አታውቅም፤ እውነተኛውን መንገድ ግን በተገቢው መልኩ በጥብዓት ታስተምራለች። የዚያ የእምነት ተቋም አምልኮና እምነት ስሕተት ከኾነ ሰዎች ኹሉ ይድኑ ዘንድ እውነትን ትሰብካለች፤ ወደ እውነት ትመራለች፣ ታደርሳለች። ኢሬቻ ምንድን ነው? ባሕል ነውን? መልካም፣ ባሕልስ ከኾነ ቤተ ክርስቲያን የባሕሉን አክባሪ ባሕሉን ሳይዘነጋ ይቀበላት ዘንድ አይገዳትም። እርሷም ከነ ባሕሉ ዐቅፋና ደግፋ ትቀበለዋለች። ግን ኢሬቻ ባሕል ነው? አይመስለኝም። ሰሞንኛ ተናጋሪዎችን እንዘንጋቸውና እስኪ እንዴት እንደተከበረ እንመርምር። የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች ውኃ ውስጥ ሣር እየነከሩ ወይም ዛፍን ቅቤ እየቀቡ ፈጣሪን ሲያመሰግኑ የሚያሳዩ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን ስናይ ነበር። ስለዚህ ይህ በዓል:- #1ኛ ፈጣሪ የሚመሰገንበት ነው (ይህም ተደጋግሞ በአክባሪዎቹ እየተነገረ ነው)። በፈጣሪ መኖር ማመን ደግሞ: ለሃይማኖት ህልውና የመጀመሪያው መስፈርት መኾኑን ልብ ይሏል። ስለዚህ ኢሬቻ/ዋቄፈና/ ለሃይማኖትነት ትልቁን መሥፈርት አሟልቷል ማለት እንችላለን። #2ኛ የታወቀ የምስጋና (አምልኮ?) ሥርዓት (ለምሳሌ:- ሣር ውኃ ውስጥ መንከር፣ ቅቤ መቀባት ...) አለው። ይህም እስልምናም ኾነ ክርስትና የታወቀ የአምልኮ ሥርዓት እንዳላቸው ማለት ነው። #3ኛ እስልምና መስጊድ፣ ክርስትናም ቤተ ክርስቲያን እንዳላቸው ኹሉ: ኢሬቻም /ዋቄፈናም/ ይህ ሥርዓት የሚፈጸምበት ቦታ (Sacred Place, ለምሳሌ:- ውኃና ዛፍ ያለበት ሥፍራ) አሉት። #4ኛ ሃይማኖታዊ የአምልኮ ሥርዓት በካህናት እንደሚመራ: ክብረ በዓሉን የሚመሩ የሥርዓት መሪዎች (አባ ገዳዎች?) አሉት። ስለዚህ ወይ አምልኮ ነው፣ ወይም ደግሞ ከቆይታ ብዛት ወደ ባሕልነት የተቀየረ አምልኮ ነው። #ዐቢይነጥብ - ከላይ ከጠቀስናቸው ከዐራቱ ለጊዜው አንዱን ብቻ እንምረጥ - -ፈጣሪ የሚመሰገንበት መኾኑ ይህ ብቻ "ባሕል ነው" ለሚሉት ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድድ ምክንያት ነው። ፈጣሪን ማመስገን የሚቻለው በእምነት ነው። በመጀመሪያ ይህን ፈጣሪ ማመንና በጥቂቱም ቢኾን በእምነት ማወቅ ይገባል። ቢያንስ ፈጣሪ መኾኑን በእምነት መረዳት ያሻል። ከዚያም እርሱ በሚፈልገው ሥርዓት እርሱን ማመስገን/ማምለክ ይከተላል። እርሱን ማምለኪያ ውሱን ሥርዓት የለም ቢባል እንኳን: የማመስገኛ ሥርዓቱ "ሥርዓት የለሽ በመኾን" ይገለጻል፤ (non-religiousness is my religion) እንዲል አንድ የፍልስፍና መምህር /ፈላስፋ ላለማለት ነው/)። ሙስሊሙ ፈጣሪን የሚያመሰግንበት ሥርዓትና ቦታ አለው፤ ሳምንታዊ(ጁምዓ) እና ዓመታዊ (ኢድ አል ፈጥር፣ ኢድ አልአድሃ) የበዓላት ዕለታትም አሉት። ክርስቲያኑም እንዲሁ ከሳምንታዊ ሰንበትን፣ ከዓመታዊ ልደትና ትንሣኤን የመሰሉ (ዕለታዊና ወርኃዊውን ጨምሮ) ብዙ በዓላት አሉት። ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በየበዓላቱና በየታወቀ ሥርዓቱ ፈጣሪን ያመሰግናሉ፣ ያመልካሉ። ነገር ግን ክርስቲያኑ ኢሬቻ የሚል ፈጣሪን የማመስገኛ በዓል በዚቁ (liturgical Calendar) ውስጥ የለም። ሙስሊሙም እንደዚያ። ሌላው ነጥብ: ኹሉም እምነት ፈጣሪን የተመለከተ መሠረተ-ትምህርቱ (Doctrine/Creed) ከሞላ ጎደል ይለያያል። ሙስሊሙም (ካልተሳሳትኩ) "ላ ኢላህ ኢለላህ መሐመዱር ረሱለላህ" የሚል ሸሀዳ (Creed) አለው። ይህንን አዘውትሮ ያደርሳል። ፕሮቴስታንቱ "ክርስቶስ አማላጄ" (ሎቱ ስብሃት) ይላል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ "ኹሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚኾን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን" ከሚለው ጀምሮ የክርስቶስንና የመንፈስ ቅዱስን አንድ የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ጋር መተካከል፣ የቤተ ክርስቲያንን ኲላዊነት፣ አንድነት፣ ቅድስናና ሐዋርያዊነት፣ የጥምቀትን የኃጢአት ማስተሥሪያነት፣ የትንሣኤ ሙታንን ተስፋነት የምንመሠክርበት የዘወትር ጸሎተ ሃይማኖት (Creed) አለን። እነዚህ እምነቶች ይለያያሉ ብቻም ሳይሆን ይቃረናሉ። እንዴት በአንድነት ምስጋናቸውን ለአምላክ ያደርሳሉ? እኔ አምላክ የምለውን ክርስቶስን አንዱ ከአጠገቤ "አማላጄ" እያለው እንዴት አንድነት ይኖረኛል? አንዱስ "ነቢይ" እያለው እንዴት አብረን እናመሰግናለን? የኔን አምላክ አማላጅም ፣ ነቢይም ማለት እርሱን ማሳነስ ለእኔም ንቀት ነው። ሙስሊሙም አላህን አምላክ ይላል። ኢሳን ነቢይ ይላል። እኔ ከጎኑ ቆሜ ኢየሱስ ክርስቶስን "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ስል እንዴት ይዋጥለታል? አብረን ቡና የምንጠጣ፣ አብረን ኳስ የምንጫወት፣ በንግድ የምንተባበር ሙስሊሞችና ፕሮቴስታንቶች ይኖራሉ። በጣም የምንዋደድ ጓደኛሞችና የሥራ ባልደረቦች ልንሆን እንችላለን። ግን ለአምልኮ ሙስሊሙም መስጊድ፣ ፕሮቴስታንቱም "ቸርች" እኛም ቤተ ክርስቲያን እንሔዳለን እንጂ ፈጣሪን ለማመስገን መስጊድ ወይም ቤተ ክርስቲያን በአንድነት አንሔድም። አንድ የምንኾንበትንና የማንኾንበትን እንለይ እንጂ! በኢትዮጵያዊነት አንድ ነን፤ በባሕል እንተባበራለን፤ በልማት አንድ መኾን እንችላለን፤ እንኳን በሀገር በቤተ ዘመድም በሃይማኖት መለያየት ይገጥመናል፤ ዝምድናን ጨምሮ ግን ብዙ አንድ የሚያደርጉን ጉዳዮች አሉን። ኾኖም በሃይማኖት አንድ ካልኾንን ከእናቴም ጋር ለጸሎትና ለምስጋና አልቆምም። እንኳን ከሙስሊምና ከፕሮቴስታንት ጋር ይቅርና በብሉይ ኪዳን በሃይማኖት አንድ ከነበርነው ከይሁዲውም ጋር ፈጣሪን ለማመስገን በአንድነት አንቆምም። የይሁዲው መሠረተ ሃይማኖት ( ሸማ፣ Creed) በእኛው ብሉይ ኪዳን ላይ ዘዳ.6÷4-9 ያለው ንባብ ነው። ይሁዲዎች ይህንን በእጃቸው ያሥሩታል (Teffilin)። በበራቸውም ይጽፉታል (Mezzuzah)። ንባቡ እኛም የምናምንበትና የምናነበው ነው። ነገር ግን ምንም ያኽል ብንወዳቸው ክርስቶስን ከማያምኑት ከይሁዲ እምነት (Judaism) ተከታዮች ጋር የሃይማኖት ኅብረት የለንም። ወንጌላችንም ያዘናልና "ቢቻለንስ በእኛ በኩል ከሰው ኹሉ ጋር በሰላም መኖርና ሰላምን መከታተል" የክርስትና መርሐችን ነው። (ሮሜ 12÷18፣ ዕብ. 12÷14)። ኾኖም ፈጣሪን የምናመሰግንበት የሃይማኖት ኅብረት የሚኖረን ግን ከተጠመቁት ጋር ብቻ ነው። @Manetkelfares @Manetkelfares @Manetkelfares
Show all...

ፎቶ : የመስቀል ደመራ በዓል እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝበ ክርስቲያን በተገኘበት በፍፁም ሰላም ተከብሯል። ከአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው መስቀል ደመራ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ባለፈው ዓመት እጅግ በጣም በውስን ተሳታፊዎች መከበሩ አይዘነጋም። ፎቶ : አዲስ አበባ - መስቀል አደባባይ (2014 ዓ.ም) #Share @Manetkelfares @Manetkelfares @Manetkelfares
Show all...
#ዕሌኒ ንግስት እሌኒ ንግሥት ሐሠሠት መስቀሉ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ክብሩ/4/ @Manetkelfares
Show all...
M.eleni nigest.mp37.66 KB
#እንተ ተሐንፀት እንተ ተሐንፀት በስሙ ወተቀደሰት በደሙ ቤተክርስቲያን ወተአትበት (2) በዕፀ መስቀሉ እስመ ኃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 @Manetkelfares
Show all...
እንተ ተሐንፀት.mp39.91 KB
#ወሪዶ እመስቀሉ ወሪዶ እመስቀሉ (2) እመስቀሉ አብርሃ ለኵሉ(4) @Manetkelfares
Show all...
ወሪዶ-እመስቀሉ.mp31.15 MB
#መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ /2/ ይኩነነ ቤዛ /4/ መስቀልከ ይኩነነ ቤዛ @Manetkelfares
Show all...
መስቀልከ-ይኩነነ-ቤዛ.mp31.56 MB
#ዕሌኒ ንግስት እሌኒ ንግሥት ሐሠሠት መስቀሉ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ክብሩ/4/ @Manetkelfares
Show all...
M.eleni nigest.mp37.66 KB
"የመስቀሉ ነገር በሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነው ፥ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው፡፡" ፩ኛ ቆሮ ፩፥ ፲፰ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !
Show all...