cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Merawi Preparatory School ~ Colonel Tadese Muluneh Fentie Senior SS

Show more
Ethiopia4 140Amharic3 866The category is not specified
Advertising posts
1 845
Subscribers
No data24 hours
-117 days
-2930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
Ethio Matric Grade 12 Entrance - Apps on Google Play

ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና በብቃት ለመስራት የሚያዘጋጅ Ethiopian app

"የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል":- ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶችና ከክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችጋር ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱም የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ሃምሌ ወር ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡ ፈተናው ልክ እንደባለፈው ዓመት በኹለት ዙር የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመጀመሪያው ዙር የነበሩ የፈተና ችግሮችን ዘርዝረው ለቀጣዩ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ2015 ዓ.ም ፈተናን ለማስፈፀም ልዩ ልዩ መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆኑንና የተፈታኞች መረጃ በአግባቡ እየተደራጀ መሆኑን አብራርተዋል። ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍና አመለካከቱን ለመቀየር፣ ብቁና አገር ተረካቢ ትዉልድ ለመፍጠር አሁን ያለው ባለድርሻ አካል ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም በ2016 የሚካሄደው ፈተና እንደአካባቢው ሁኔታ ኦን ላይን እንደሚሆን ገልጸው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡
Show all...
Repost from Amhara Bank
Photo unavailableShow in Telegram
ባንካችን በ2014 ዓ.ም በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ምዘና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 በላይ እንዲሁም በማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ500 በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የትምህርት ወጪያችሁን እንደሚሸፍን መግለፁ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሰውን ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ስለቀረበልን፣ አቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች የትምህርት ማስረጃችሁን እና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ይዛችሁ በመቅረብ እንድታመለክቱ እንጠይቃለን፡፡ አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር! የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች Website: https://amharabank.com.et/ Facebook: www.Facebook.com/amharabanksc1 Telegram: https://t.me/Amhara_Banksc Instagram: https://instagram.com/amhara_bank Twitter: https://twitter.com/Amharabanksc LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/amharabank/ YouTube: https://youtube.com/channel/UC73x9uuGYV0Uxw0EkpVZN8g #አማራባንክ #AmharaBank
Show all...
1. የተማሪዎች አማካይ ውጤት በየትምህርት አይነቱ፤ አጠቃላይ መረጃ፡-  ፈተና የተፈተኑ ብዛት-----908,256 ናቸው፡፡   አማራ………..30.37%   ኦሮሚያ…..…27.96%   ደቡብ………..28.17%   ሀረሪ…………32.88%   አዲስ አበባ----38.46%   ደሬደዋ--------31.42%   ሲዳማ---------28.34% 2. ከ50% እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ከተፈተኑት መካከል እንደ ሀገር ያለፉ 29,909 (3.3%) ናቸው   አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 ((3.6%)   ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)   ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)   ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)   አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)   ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)   ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%) 3. ተፈጥሮ ሳይንስ  ከ600 እና በላይ እንደ ሀገር 263 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ   አማራ………70 ተማሪዎች   ኦሮሚያ…..…51 ተማሪዎች   ደቡብ………..10 ተማሪዎች   ሀረሪ…………1 ተማሪዎች   አዲስ አበባ----117 ተማሪዎች   ደሬደዋ-------- 2 ተማሪዎች   ሲዳማ---------8 ተማሪዎች 4. ማህበራዊ ሳይንስ  ከ500 እና በላይ እንደሀገር 10 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ   አማራ………1ተማሪ   አዲስ አበባ----8 ተማሪዎች   ደሬደዋ-------- 1 ተማሪ 5. ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች 7 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ   ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት   ባሕር ዳር ስቲም ት/ቤት   ጎንደር ኮሙኒቲ ስኩል   ወላይታ ሶዶ ሊቃ ት/ ቤት   አዳማ ኦዳ አዳሪ ት/ ቤት ናቸው። 6. ከፍተኛ ውጤት (የዓመቱ ሰቃይ)  ከአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ ሚኪያስ አዳነ 666 በማምጣት የአመቱ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።
Show all...
🙏አማራ ባንክ በሀገር አቀፍ ፈተና ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ወጭ እንደሚሸፍን አስታወቀ‼️ 👉 "አማራ ባንክ ከባንክ ባሻገር ሲል በምክንያት ነው" ሲሉ የገለፁት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ #ሄኖክ_ከበደ፤ የአማራ ባንክ የማህበረሰባዊ አገልግሎት በመስጠት እየተገበረ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን፤ በዚህም ባንኩ ማህበረሰባዊ አገልግሎቱን ለማስፋት በማሰብ በዘንድሮው ዓመት በሀገር አቀፍ ፈተና በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር አስታውቀዋል። በዚህ አጋጣሚ፦ ============ በሀገር አቀፍ ደረጃ አጠቃላይ ፈተናውን የተፈተኑት የተማሪዎች ብዛት 908,256 ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥም፦ 1ኛ - እንደ ሀገር #በተፈጥሮ_ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የተማሪዎች ብዛት 263 ተማሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ፦ 🔜 አዲስ አበባ ---117 ተማሪዎች 🔜 አማራ ………70 ተማሪዎች 🔜 ኦሮሚያ …..…51 ተማሪዎች 🔜 ደቡብ ………..10 ተማሪዎች 🔜 ሲዳማ ---------8 ተማሪዎች 🔜 ድሬደዋ -------- 2 ተማሪዎች 🔜 ሀረሪ …………1 ተማሪ መሆናቸውንና እንዲሁም 2ኛ - እንደ ሀገር #በማህበራዊ_ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የተማሪዎች ብዛት 10 ተማሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ፦ 🔜 አዲስ አበባ ---- 8 ተማሪዎች 🔜 አማራ ………1ተማሪ 🔜 ድሬደዋ -------- 1 ተማሪ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር በትላንትናው ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ ማሳወቁ ይታወሳል። 🔜 ለፈተና ከቀረቡ 908,256 ተማሪዎች መሀከልም እንደ ሀገር ወደ ዩኒቨርስቲ ያለፉ አጠቃላይ የተማሪዎች ቁጥር 29,909 (3.3%) ብቻ ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ተማሪዎቾ ውስጥም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው የደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው #ሚኪያስ_አዳነ እንደሆነና ያስመዘገበው አጠቃላይ ውጤትም 666 መሆኑ ይታወቃል።
Show all...
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም  በቴሌግራም   https://t.me/eaesbot  ማየት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል፡፡
Show all...
EAES 🇪🇹 Result bot

EAES: Educational Assessment and Examination Service Official Bot. Use this bot to check your Result.

Photo unavailableShow in Telegram
ነፃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መማሪያ ገፅ የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ነፃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማሪያ ያለምንም ክፍያ አቅርቦሎታል። ልጆችዎ ይማራሉ - እርስዎም የእንግሊዝኛ ቋንቋዎን ያሻሽሉበታል። የትም ሆነው ይማሩ የቋንቋ ክህሎትዎን ያዳብሩ! አገልግሎቱን ለማግኘት ከታች የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ https://learn-english.moe.gov.et/
Show all...