cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የሚካኤል አስጨናቂ እና የዘመኑ ተጋሪ ፀሀፍት ግጥሞች!

Show more
Advertising posts
728
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ጊዜ እንዳለኝ እያሰብኩ ነበር — እንደምኖር። በመጻሕፍት መደርደሪያዬ እኔን መጠበቅ ያደከማቸው ያልተነበቡ መጻሕፍት ተገጥግጠዋል። አንድ ቀን እንደማነባቸው ተስፋ ሳደርግ ምጽዓት ደረሰ —ሀገሬ። በሲዖል ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ አይቻልም። አንደኛ ሀገሩ የእሳት ነው። በእሳት ሀገር ወረቀት ቀለም ይዞ አይቆይም። ይነዳል፥ አመድ ይሆናል። ብዙ ጩኸት አለ —ሰቆቃ። እና አይመችም። ዙሪያው ገደል ነው። ልብ ዝቅ ያደርጋል። ቀን በቀን መጻሕፍቴን እየተሰናበትኩ ነበር። ምን ትርጉም አለው? ሳልፈልግ አእምሮዬ እንደተረበሸ ከተማ ሐሳብ ይጎሎጉላል። በሥነ ሥርዓት ላጠነጥን እሞክራለሁ —መሥመር ላስይዝ። ግን አልችልም ይሳከርብኛል። አንጎሌ፥ ሰውነቴ ይሰንፋል። የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው። አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ። ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? ዳሩ ብትነቃስ ምን ታደርጋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ብትተኛ አይከፋም፥ ብትማር፥ ብትቆጥብ፥ ብታገባ፥ ብትወልድ። ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል። ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ። ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ማንንም መርዳት አትችልም። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ግን ተራው ያንተ ከሆነ ያንተ ነው። ትከሻህን ማስፋት፥ መቻል፥ መቀበል ይጠበቅብሃል። እውነት አይመስልም አይደል? ትላንት በእቅፍህ የነበረ ሰው እንደወጣ ሲቀር? ደብዛው ሲጠፋ?? ግን ይህ የብቻህ እውነት ነው። ይህ የብቻህ ሕመም ነው —ጽና። እ. . . ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በሌላ አውድ የጻፈው አንድ ግጥም አለ። ያለ ዐውዱ እዚህ ጋር እንድጠቀመው ይፈቀድልኝ፦ “...ተገልለህ ርቀህ እውነት ይተዉኛል ብለህ እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?! . . . . ተስፋ አድርገህስ ምን ልትሆን ፡ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ ? እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ።” Esubalew Nigussie
Show all...
ጭንቅላታችሁ እንደ ማግኔት ነው ➡️ በረከትን ስታስቡ በረከት ይመጣል። ➡️ ችግሮችን ካሰባችሁ ችግሮችን ትስባላችሁ። ➡️ ሁልጊዜም ጥሩ ነገሮች በውስጣችሁ አሳድጉ። ➡️ በአስተሳሰባችሁ በጎና ውጤታማነትን አስቡ፡፡ ➡️ በሂደት ወዳሰብነውና ወደተመኘነው ነገር እንሄዳለን። ➡️ ጨለምተኝነትን ካሳደግን ጨለምተኛ እንሆናለን... ➡️ ተስፋንና ውጤታማነትን በውስጣችን ካለማመድን ስኬታማ እንሆናለን፡፡ ከአዲስ አድማስ ገፅ
Show all...
መልከ ቀና አድርገኝ ህይወቴ ቢቀለኝ.. . አውለኝ በክብር ቀባኝ ሞገስ ቅባት ቀኖቼ ላይ ልንገስ በሌሎች ፍርሀት። ስጠኝ የመሪ ድምፅ አጥር የሚሻገር... መንገዴ እንዲሳለጥ እንዲሆን ገር በገር ። አልያ አልገፋትም... ይህችን ስንኩል ዕድሜ ለአይን አስቀይሜ፥ ቀልዬ ያለ ሞገስ... ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው ከሞት ደጅ የሚደርስ !! (ሚካኤል.አ)
Show all...
በማይፀፅት ትናንት ፡ በማይናፍቅ ነገ መካከል ላይ ፍቅርሽ ፡ ስለተሰነገ፣ አልማትር ወደፊት ፡ አልዞር ወደኋላ «አ...ሁን!» ነኝ ... «አ...ሁኝ!» ነሽ ፡ ከእንግዲህ በኋላ። Red 8
Show all...
የቤት አህያና የሜዳ አህያ ሲኖሩ ሲኖሩ ... መንገድ ሲያሳልጡ እቃ ከጀርባቸው ሸክፈው ሲያኖሩ፤ ሰለቸና ወጣ የሜዳ አህያ አህያ ግን ቀረ ከቤት ከገበያ። እንዲህ በአንዳንድ ቀን ሲበዛበት አደን ... ሳሩ እሳት ገብቶት ሲኖር በሰቀቀን ባልወጣሁ ምናለ? ብሎ እንባ ይዘራል የሜዳ አህያ አያውቅም እንዳለ ... ስሙን የሚያወሳ መንገድ መሻገሪያ። የሚል አለ ተረት ... የአንዱ መለየት ነው የሌላው ነፃነት ፤ ስንት እግር ተራምዷል በእንባ ቀን ወ'ቶለት። (ሚካኤል.አ)
Show all...
ሕልም ... ያለው ሕልምም ያየው ከተባለ ባለ ሕልማም ከጥሪው ነው እንጅ ከግብሩ አይሟላም ! ሕልም ታይቶት የመራ በሕልም እንደመራ ከተባለ መሪ ... ችግር ይታየናል ከዚህ የቃል ጥሪ! ስለዚህ ይወጠን ... ስለዚህ ይታሰስ... ከዚህኛው መዝገብ እስከዚያኛው ድረስ ፈልጉ.. . ፈልጉ ... ይፈለግ እንጅ ቃል ? ቀለም ቆጥሯል ብለን አዋቂ ነው ያልነው ለጠንቋይ ይሆናል። (ሚካኤል.አ)
Show all...
የልኳንዳ ቤት በር ቡችላ (በእውቀቱ ስዩም) ሰፈራችን ባለው፥ የስጋ ቤት በራፍ የገዛ ገላየን ፥እየጎተትኩኝ ሳልፍ ሁልጊዜ የማያት ፥ ሚጢጢ ቡቸላ ከስጋ ቤቱ በር ፥ ፊትለፊት ቁጭ ብላ ወደ ሱቁ መስኮት ፥ አንገቷን አስግጋ ትቁለጨለጫለች፥ ጅራቷን ከፍ አርጋ እንደ ሰላም ሰንደቅ፥ ታውለበልባለች:: ነጋዴው በጠዋት፥ መስኮቱን ይከፍታል ያቺን ግልገል ውሻ ፥ የጎሪጥ ያያታል እንዳልተፈጠረች ወድያው ይረሳታል:: ቢላዋ ሰንዝሮ ጎድን ከዳቢቱ፥ በየገጹ መትሮ በግራም በኪሎ ለየበላተኛው ሲያከፋፍል ውሎ መስኮቱን ይዘጋል ቀኑም እንደ ወትሮው ይመሻል ይነጋል:: ከዚያ በማግስቱም ይቺ መከረኛ፤ የሙት ልጅ ቡችላ የስጋ ትራፊ፤ ያጥንት ርጋፊ ቢጥልልኝ ብላ ትጠባበቃለች፤ ከስጋ ቤት በር ላይ ፥ ትቁለጨለጫለች ያ ስጋ ቸርቻሪ፥ ባይለግሳት አዝኖ ከሰው ንፍገት በላይ፥ ተስፋዋ መዝኖ ምጽዋት ይጠብቃል፤ልቧ መቸ ቦዘኖ፤ እኛም እንደዚህ ነን፥ ሰላምን መጠበቅ፥ ከጦረኛ ዘመን ከንፉግ ሰው ደጃፍ ፥ እንጀራ መለመን መቸም የማይደክመን ፥ በገፊ መንደር ውስጥ፥ የሚያቅፈን ፍለጋ እጅ የምንዘረጋ ሞኝነት ቢመስልም፥ ለሚያየው በሩቁ፥ ተግቶ መጠበቁ ከጦር ዘመን ሰላም ፤ ከንፉግ ሰው ሲሳይ አንዳንድ ቀን አለ፥ ተአምር የሚያሳይ አንዳንድ ቀን፥ አለ ፥ ተፈጥሮ ሚያስለውጥ ስራት የሚያናውጥ በዚህ ምክንያት ነው፥ ሰው ልምዶቹን ትቶ ፥ ህልሞቹን የሚያምነው::
Show all...
[ . . . ⏱ . . . ] Henock Bekele የቅርቡን ጨዋታ ፣ በሳቅ እያከሙ የሩቁን በሩቁ ፣ ምኑንም ሳይሰሙ የሕዝቡን ቀዳዳ ፣ ሲቀዱ ሲጠቅሙ የመንደሩ ሰፊ ፣ ዘንድሮስ ደከሙ። አዬ!! . እያጋቱ ኮሶ ፣ ወለምታ እያቀኑ የስንቱን ስብራት ፣ በዘበት ያዳኑ ያበጁትን ክኒን ፣ ለራሳቸው ውጠው እጆቻቸው ዝለው ፣ ከጀርባቸው ጎብጠው “ወንድ ልጅ አይደለህ?” ፣ ብለው ያጀገኑ ተፋልመው ከዘመን ፣ እንደማይሆን ሆኑ። አዬ!! . የተመካሁበት በዓለም ስፋት ሄጄ ፣ ለመንደሬ ስቀኝ እንኳንስ ሰው ሁሉ . . . በሃው ድንጋይ እንኳ ፣ አርጅቶ ጠበቀኝ። ወረት አይነካውም “አይለወጥ” ያልኩት ፣ ያመንኩት አለፈ እንኳን ፈገግታቸው ፣ ጥርሳቸው ረገፈ አይምሬ ምስለኔ በአፍላ ሌማቱ ላይ ፣ እግሮቹን ዘርግቶ ጠበቀኝ ጀግኖቹን ፣ ለሞት አስጠግቶ ቃልም ጠፋ ዜማ ዐየሁ ጥበብ ዐየሁ ደግሞም በዝግታ ደግሞም በፀጥታ ፣ ልሂቅ የደረሰው። ምን አለ ሙዚቃ? የት ይገኛል ግጥም ጊዜ በላዩ ላይ ፣ እንዳለፈበት ሰው ? ___________________
Show all...