cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች Yasin Nuru "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "   የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7} ለአስተያየት👇👇 @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇 @yasin_nuru_hadis

Show more
Advertising posts
25 707Subscribers
-124 hours
+697 days
+79130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለፈገግታ😂 «ስንት ተምች አለ መሰለህ¡ አንዱ ገጠሬ ነው አሉ። ህዝቦቹ ተሰብስበው ሙሐደራ ካላደረክልን አሉት። ሚምበር ላይ ወጥቶ √ "አዩሃ ናስ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው "አናውቅም" አሉት። "እንግዲያውስ ለማያውቁ ሰዎች ማስተማር ድካም ነው።" ብሎ ወረደ! በሌላም ቀን መጥተው "እሺ ዛሬ አስተምረን" አሉት። አሁንም ሚምበር ላይ ወጥቶ √ "አዩሃ ናስ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው በአንድ ድምፅ "አዎን! እናውቃለን" አሉት። "እንግዲያውስ ለሚያውቅ ሰው መናገር ፋይዳ የለውም።" ብሎ ወረደ። ለሶስተኛ ጊዜ መጥተው "እባክህ አስተምረን" አሉት። አሁንም ሚምበሯ ላይ ወጥቶ √ "አዩሃ ናስ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው ቀድመው ተወያይተው ነበርና ግማሻቸው "አዎን" ሲሉ ግማሻቸው "አናውቅም" አሉ። "እንግዲያውስ ያወቁት ለማያቁት ያሳውቁ!" ብሏቸው እርፍ!!»😂😂 @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
🤣 122👍 35😁 24 5👏 3🥰 2👌 1🤗 1🫡 1😎 1
ወንድሜ ጥሩ ትዳር ትፈልጋለህ? ?? ከፈለክ ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል (አላህ ይዘንላቸው) ልጃቸው ሲያገባ የለገሱት ምክር እኔም አንተንም ስለሚመለክት ጆሮህን አውሰኝ! ! ☞ ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትህ መፈጸም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር፦ 1- ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት❤️❤️ 2- ሴት ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። (ባገኘከው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለጽ ወደኋላ አትበል🤗🤗 3- ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ።😡😡 ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ🥺 አንተጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር፡፡💪💪 4- ሴቶችን መልካም ንግግር፡ ውብ ገጽታ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖሩህ ጥረት አድርግ❤️❤️ 5- ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው ቤቷ ስትሆን ዙፋኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል😎😎 በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባትን ነገር እንዳትፈጽም ከንግስና ዙፋኗ ላይ ልታወርዳትም አትሞክር ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል።😍😍 ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ። 6- ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም🤷‍♂🤷‍♂ አንተን ከቤተሰቦቿ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ይህን ማድረግ ፍጻሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል። 7- ሴት ከጎንህ (ጠማማ አጥንት) መፈጠሯን አትዘንጋ ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን እወቅ።☺️☺️ ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለሁ እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ። ስብራቷ ፍቺ ነው ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች🥺🥺 በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት መካከለኛ ሰው ሁንላት። 8- ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች😭😭 (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል ነገር ግን እንዲህ አደረገች በማለት ብቻ እንዳትጠላት ይህን ባህሪዋን ባትወድላት ሌሎች የሚስቡህ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ። 9- ሴት አካላዊ ድካምና ስነልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል🥺🥺 በዚህን ወቅት አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ጾም) ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል። በዚህን ጊዜ እዘንላት ትእዛዝ አታብዛባት። 10– ሴት አንተ ዘንድ ያለች (የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ🥰🥰 ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት እዘንላት በድክመቷ (የምትፈጽመውን ስህተት) እለፋት ምርጥ የሂዎት አጋርህ . ትሆናለች፡፡ @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
👍 156 73🥰 14🔥 5👏 2👎 1
!የአላህ ስሞች እና ትርጉማቸው!!!!! 1 አላህ ፦ አምላክ 2 እራህማን ፦ በጣም አዛኝ ። 3 እረሒም ፦ በጣም ሩህሩ 4 ? አል- ወሃቡ ፦ ሰጪ ። 5 አል- ጀዋዱ ፦ ቸር ። 6 አል- ሱቡሁ ፦ ንጹህ ። 7 አል -ዋሪሱ ፦ ወራሽ ቀሪ ። 8 አል- ረቡ ፦ ጌታ ። 9 አል- አእላ ፦ ከሁሉ በላይ ። 10 አል- ኢላሁ ፦ አምላክ ። 11 👉🏼አል- መሊክ ፦ ንጉስ ። 💞12💫👉🏼አል- ቁዱስ ፦ ከጉድለት ሁሉ የጠራ ። 💞13💫👉🏼አሰላሙ ፦ የሰላም ባለቤት ። 💞14💫👉🏼አል- ሙእሚኑ ፦ ፀጥታን ደህንነትን ሠጪ ። 💞15💫👉🏼አል -ሙሀይሚኑ ፦ ባሮቹን ጠባቂ ። 💞16💫👉🏼አል- አዚዙ ፦ አሸናፊ ። 💞17💫👉🏼አል - ጀባሩ ፦ ሃያል ጠጋኝ ። 💞18💫👉🏼አል - ሙተ ከቢሩ ፦ ኩሩ ። 💞19💫👉🏼አል- ኻሊቁ ፦ ፈጣሪ ። 💞20💫👉🏼አል - ቃዲሩ ፦ ታጋሽ ። 💞21💫👉🏼 አል - ሙሰዊሩ ፦ ላሻው ነገር ያሻውን ቅርስ ሰጭ ። 💞22💫👉🏼አል - አወሉ ፦ ፊት ያለ ። 💞23💫👉🏼አል- አኺሩ ፦ ኅላ ቀር ። 💞24💫👉🏼አል ዟሂሩ ፦ ግልፅ ። 💞25💫👉🏼አል- ባጢኑ ፦ ስውር ። 💞26💫👉🏼አል - ሰሚዑ ፦ ሰሚ ። 💞27💫👉🏼አል - በሲሩ ፦ ተመልካች ። 💞28💫👉🏼አል - መውላ ፦ ወዳጅ/ረዳት ። 💞29💫👉🏼አል - ነስሩ ፦ ረዳት ። 💞30💫👉🏼አል - ዐፍው ፦ ይቅር ባይ ። 💞31💫👉🏼አል- ቀዲሩ ፦ ቻይ ። 💞32💫👉🏼አል- ለጢፍ ፦ ሩህሩህ ። 💞33💫👉🏼አል - ኸቢር ፦ ውስጥ አዋቂ ። 💞34💫👉🏼አል- ዊትሩ ፦ ብቸኛ ። 💞35💫👉🏼አል- ጀሚሉ ፦ መልካም ። 💞36💫👉🏼አል - ሀዩ ፦ አክባሪ/ትሁት ። 💞37💫👉🏼አል - ሲትር ፦ ሸፋኝ ። 💞38💫👉🏼አል - ከቢር ፦ ትልቅ ። 💞39💫👉🏼አል- ሙተአል ፦ የላቀ ። 💞40💫👉🏼አል - ዋሂድ ፦ ብቸኛው ። 💞41💫👉🏼አል - ቀሃሩ ፦ አሸናፊ ። 💞42💫👉🏼አል - ሃቁ ፦ እውነት ። 💞43💫👉🏼አል- አል ሙቢኑ ፦ ሁሉንግልጽ አድራጊ ። 💞44💫👉🏼አል - ቀዊዩ ፦ ብርቱ ። 💞45💫👉🏼አል - መቲኑ ፦ ብርቱ ። 💞46💫👉🏼አል - ሃዩ ፦ ህያው ። 💞47💫👉🏼አል - ቀዩም ፦ ራሱን ቻይ ። 💞48💫👉🏼አል - አልዩ ፦ የበላይ ። 💞49💫👉🏼አል- ዐዚሙ ፦ ታላቅ ። 💞50💫👉🏼አል - ሸኩር ፦ ውላታ መላሽ ። 💞51💫👉🏼አል- ሀሊሙ ፦ ታጋሽ ። 💞52💫👉🏼አል - ዋሲሁ ፦ ችሮታው ሰፊ ። 💞53💫👉🏼አል - አሊሙ ፦ አዋቂ ። 💞54💫👉🏼አል - ተዋቡ ፦ ፀፀትን ተቀባይ ። 💞55💫👉🏼አል - ሀኪሙ ፦ ጥበበኛ ። 💞56💫👉🏼አል - ገንዩ ፦ ሀብታም ። 💞57💫👉🏼አል - ከሪሙ ፦ ቸሩ ። 💞58💫👉🏼አል - አሃዱ ፦ ብቸኛ ። 💞59💫👉🏼አል - ሶመዱ ፦ እሱን አስጠጊ ። 💞60💫👉🏼አል -ቀሪብ ፦ ቅርብ ። 💞61💫👉🏼አል - መጂቡ ፦ ተቀባይ ። 💞62💫👉🏼አል - ገፋሩ ፦ መሀሪ ። 💞63💫👉🏼አል - ውዱዱ ፦ ወዳጅ/ወዳድ ። 💞64💫👉🏼አል - ወልዩ ፦ ውዳጅ ። 💞65💫👉🏼አል - ሐሚዱ ፦ ምስጉን ። 💞66💫👉🏼አል - ሀፊዙ ፦ ጠባቂ ። 💞67💫👉🏼አል - ሙጅድ ፦ ለጋስ ። 💞68💫👉🏼አል - ፈታሑ ፦ የሚከፈት /ድልን አጎናጻፊ ። 💞69💫👉🏼አል- ሸሂዱ ፦ አስቀዳሚ /የሚቀርብ ። 💞70💫👉🏼አል - ሙቀዲሙ ፦ አስቀዳሚ ። 💞71💫👉🏼አል - መአኪሩ ፦ አዘገይ /የሚያርቅ ። 💞72💫👉🏼አል - ሙአኪሩ ፦ የመጨረሻው ቀሪ ጌታ ። 💞73💫👉🏼አል - ሙስዒሩ ፦ ዋጋ አውጪ ። 💞74💫👉🏼አል - ቃቢዱ ፦ ሲሳይን የሚጨብጥ ። 💞75💫👉🏼አል - ባሊፋ ፦ ሲሳይን የሚዘረጋ ። 💞76💫👉🏼አል - ራዚቁ ፦ መጋቢ ። 💞77💫👉🏼አል - ቃሂሩ ፦ አሸናፊ ። 💞78💫👉🏼አል - ሐቁ ፦ በእውነት እውነተኛ ጋታ ። 💞79💫👉🏼አል - ሸኩሩ ፦ አመስጋኝ ። 💞80💫👉🏼አል - መናኑ ፦ ለጋስ /ችሮታውሰፊ /ሰጪ ። 💞81💫👉🏼አል - ቃዲር ፦ ቻይ ። 💞82💫👉🏼ማሊከል ሙልክ ፦ ሹም የዟሂሩ /የባጢ ። 💞83💫👉🏼ዙል ጀላሊ ወልኢክራም ፦ የልቅና/የልግስ ባለቤት ። 💞84💫👉🏼አል- ራዚቁ ፦ መጋቢ ። 💞85💫👉🏼አል - ወኪሉ ፦ ተወካይ ። 💞86💫👉🏼አል- ረቂቡ ፦ ተጠባባቂ ። 💞87💫👉🏼አል - ሙህሲነ ፦ ደግ ሰሪ ። 💞88💫👉🏼አል - ሀሲቡ ፦ ተሳሳቢ /ተቆጣጣሪ ። 💞89💫👉🏼አል - ሻፊ ፦ አዳኝ /ፈዋሽ ። 💞90💫👉🏼አል - ረፊቁ ፦ አዛኝ ። 💞91💫👉🏼አል - ሙዕጢ ፦ ሰጪ ። 💞92💫👉🏼አል - ሙቂቱ ፦ ቻይ ። 💞93💫👉🏼አል - ሠይዱ ፦ የበላይ ። 💞94💫👉🏼አል - ጦይቡ ፦ ጥሩ ። 💞95💫👉🏼አል - ሐከሙ ፦ ዳኛ ። 💞96 . አል - አክረሙ ፦ ሸፋኝ /ጠጋኝ ። 💞97💫👉🏼አል - በሩ ፦ ደግ ሠሪ ። 💞98💫👉🏼አል - ገፋሩ ፦ መሐሪ ። 💞99💫👉🏼አል - ረኡፍ ፦ አዛኝ 🍇 ከሙስሊሞች መሃል የገባውን የጥላቻን የምቀኝነትና የመናናቅን ነቀርሳን በሽታን ከመሀላችን ነቅለ አጥፋልን!!! አርቅልን!!! ያአላህ ያረብ♥♥♥♥♥♥♥ 🍇ያ አላህ በአለማችን ላይ ሙስሊም በመሆናቸው ብቻ እየታሰሩ፣ እየተንገላቱ፣ እየተጨቆኑ ላሉት ሁላ እዝነትህን አውርድልን፣ አውርድላቸው!!! ♥♥♥♥♥♥♥ ። ያአላህ ያረብ የተሻለ ኑሮን ፈልጎ ሕይወቴን አሻሽላለው፣ ቤተሰቤን እረዳለው ብሎ ከሀገር የተሰደዱትን {የራቁትን} ሁሉ ወደ ቤተሰቦቻቸው በሰላምና በጤና መልሳቸው♥♥♥። እንዲሁም ውድ እና ተናፋቂ የአገራችን ኡስታዟቻችንንም እንዲሁም በአለም ላይ ያሉ አሊሞችን አንተው በያሉበት ጠብቅልን!!! ሰላምና ጤናቸውንም አብዛልን!!! ለሙስሊሙ ኡማ ሉሁ ሰላምና እዝነትህን አውርድልን!!! ♥♥♥ 🍇አላህ ተውበት ካላረጉ በስተቀር ከማይምረው ወንጀል ~~>ከሽር ክም አላህ ይጠብቀን!!! ይጠብቃቹ!!! አሚን ያረብ @yasin_nuru  @yasin_nuru
Show all...
86👍 54🥰 8👏 6🔥 1
99 Names of Allah with English meaning... 1 Allah (الله) The Greatest Name 2 Ar-Rahman (الرحمن) The All-Compassionate 3 Ar-Rahim (الرحيم) The All-Merciful 4 Al-Malik (الملك) The Absolute Ruler 5 Al-Quddus (القدوس) The Pure One 6 As-Salam (السلام) The Source of Peace 7 Al-Mu'min (المؤمن) The Inspirer of Faith 8 Al-Muhaymin (المهيمن) The Guardian 9 Al-Aziz (العزيز) The Victorious 10 Al-Jabbar (الجبار) The Compeller 11 Al-Mutakabbir (المتكبر) The Greatest 12 Al-Khaliq (الخالق) The Creator 13 Al-Bari' (البارئ) The Maker of Order 14 Al-Musawwir (المصور) The Shaper of Beauty 15 Al-Ghaffar (الغفار) The Forgiving 16 Al-Qahhar (القهار) The Subduer 17 Al-Wahhab (الوهاب) The Giver of All 18 Ar-Razzaq (الرزاق) The Sustainer 19 Al-Fattah (الفتاح) The Opener 20 Al-Alim (العليم) The Knower of All 21 Al-Qabid (القابض) The Constrictor 22 Al-Basit (الباسط) The Reliever 23 Al-Khafid (الخافض) The Abaser 24 Ar-Rafi (الرافع) The Exalter 25 Al-Mu'izz (المعز) The Bestower of Honors 26 Al-Mudhill (المذل) The Humiliator 27 As-Sami (السميع) The Hearer of All 28 Al-Basir (البصير) The Seer of All 29 Al-Hakam (الحكم) The Judge 30 Al-Adl (العدل) The Just 31 Al-Latif (اللطيف) The Subtle One 32 Al-Khabir (الخبير) The All-Aware 33 Al-Halim (الحليم) The Forbearing 34 Al-Azim (العظيم) The Magnificent 35 Al-Ghafur (الغفور) The Forgiver and Hider of Faults 36 Ash-Shakur (الشكور) The Rewarder of Thankfulness 37 Al-Ali (العلى) The Highest 38 Al-Kabir (الكبير) The Greatest 39 Al-Hafiz (الحفيظ) The Preserver 40 Al-Muqit (المقيت) The Nourisher 41 Al-Hasib (الحسيب) The Accounter 42 Al-Jalil (الجليل) The Mighty 43 Al-Karim (الكريم) The Generous 44 Ar-Raqib (الرقيب) The Watchful One 45 Al-Mujib (المجيب) The Responder to Prayer 46 Al-Wasi (الواسع) The All-Comprehending 47 Al-Hakim (الحكيم) The Perfectly Wise 48 Al-Wadud (الودود) The Loving One 49 Al-Majid (المجيد) The Majestic One 50 Al-Ba'ith (الباعث) The Resurrector 51 Ash-Shahid (الشهيد) The Witness 52 Al-Haqq (الحق) The Truth 53 Al-Wakil (الوكيل) The Trustee 54 Al-Qawiyy (القوى) The Possessor of All Strength 55 Al-Matin (المتين) The Forceful One 56 Al-Waliyy (الولى) The Governor 57 Al-Hamid (الحميد) The Praised One 58 Al-Muhsi (المحصى) The Appraiser 59 Al-Mubdi' (المبدئ) The Originator 60 Al-Mu'id (المعيد) The Restorer 61 Al-Muhyi (المحيى) The Giver of Life 62 Al-Mumit (المميت) The Taker of Life 63 Al-Hayy (الحي) The Ever Living One 64 Al-Qayyum (القيوم) The Self-Existing One 65 Al-Wajid (الواجد) The Finder 66 Al-Majid (الماجد) The Glorious 67 Al-Wahid (الواحد) The One, the All Inclusive, The Indivisible 68 As-Samad (الصمد) The Satisfier of All Needs 69 Al-Qadir (القادر) The All Powerful 70 Al-Muqtadir (المقتدر) The Creator of All Power 71 Al-Muqaddim (المقدم) The Expediter 72 Al-Mu'akhkhir (المؤخر) The Delayer 73 Al-Awwal (الأول) The First 74 Al-Akhir (الأخر) The Last 75 Az-Zahir (الظاهر) The Manifest One 76 Al-Batin (الباطن) The Hidden One 77 Al-Wali (الوالي) The Protecting Friend 78 Al-Muta'ali (المتعالي) The Supreme One 79 Al-Barr (البر) The Doer of Good 80 At-Tawwab (التواب) The Guide to Repentance 81 Al-Muntaqim (المنتقم) The Avenger 82 Al-'Afuww (العفو) The Forgiver 83 Ar-Ra'uf (الرؤوف) The Clement 84 Malik-al-Mulk (مالك الملك) The Owner of All 85 Dhu-al-Jalal wa-al-Ikram (ذو الجلال و الإكرام) The Lord of Majesty and Bounty 86 Al-Muqsit (المقسط) The Equitable One 87 Al-Jami' (الجامع) The Gatherer 88 Al-Ghani (الغنى) The Rich One 89 Al-Mughni (المغنى) The Enricher 90 Al-Mani'(المانع) The Preventer of Harm 91 Ad-Darr (الضار) The Creator of The Harmful 92 An-Nafi' (النافع) The Creator of Good 93 An-Nur (النور) The Light 94 Al-Hadi (الهادي) The Guide 95 Al-Badi (البديع) The Originator 96 Al-Baqi (الباقي) The Everlasting One 97 Al-Warith (الوارث) The Inheritor of All 98 Ar-Rashid (الرشيد) The Righteous Teacher 99 As-Sabur (الصبور) The Patient One -------- Jazaakallaahu Khairan for Reading: @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
👍 88 53🥰 27😍 6👌 3👏 2
✔️  ሞትና ቀጣይ ሂደቶች   - ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣ - ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡ 1- ልብሴን ያወልቃሉ፣ 2- ያጥቡኛል፣ 3- ይከፍኑኛል፣ 4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣ 5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣ 6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣ 7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡ ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡ 8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል - ቁልፎቼ - መጽሐፎቼ - ጫማዎቼ - ልብሦቼ ….. በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ - በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣ - የዓለም  እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣ - የኢኮኖሚው  ቀውስም አልተፈጠረም፣ - በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ ይወጣል፣ - ንብረቴ የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣ - ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤ - ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል - ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤ ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! … በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ 1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ 2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣ 3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣ የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!! 1- መልክህ፣ 2- ሀብትህ፣ 4- ጤናህ፣ 5- ልጅህ፣ 6- ቪላህ፣ 7- ዝናህ፣ 8- ሚስትህ/ባልሽ ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡ እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ 1- በግዴታዎች፣ 2- በሱንና ነገሮች፣ 3- በድብቅ መፅውት፣ 4- መልካም ሥራ አብዛ፣ 5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣ ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡ መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡ አስቡ ያሄ መልእክት እናንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀዱ ለሌሎችም አጋሩ ወይም ሼር አድርጉ በናንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም እናንተ የሱ ምንዳ ተካፋይ ናችሁና። https://t.me/yasin_nuru_hadis/331 @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
Yasin nuru hadis

ቀብር ላይ ገብታቹ ሞክራችሁታል🥺 #ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ቀብር ውስጥ @yasin_nuru_hadis

😢 65👍 43 15😭 10🥰 5👎 1
# ልጄን አሳዩኝ አሳዩኝ አለች በደከመ ድምጿ ከወሊድ ስቃይዋ ገና ኡፎይ ሳትል አምጥተው ክንዷ ላይ አደረጉላት። #ህፃኑ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገለጠችው ክው ብላ ደነገጠች። ዶክተሩ ሁለት እጆቹን እንዳጣመረ በሀዘን ወደመስኮቱ ፊቱን አዙሮ ማየት ጀመረ።ተፈጥሮ ሰሰተች ጨከነች ህፃኑ ያለ ጆሮ ነበር የተወለደው። የእናት እንባ የህፃኑ ፊት ላይ ተንጠባጠበ። #ከአመታት በኋላ ምንም እንኳ ህፃኑ ሁለት የጆሮ ቅጠሎች ባይኖሩትም የልጁ የመስማት ችሎታ ጤነኛ እንደሆነ ተረጋገጠ። ይሁንና ሁልጊዜ ትምህርት ቤት ውሎ ሲመጣ እናቱ አንገት ላይ ተጠምጥሞ እያለቀሰ እማ እማ "አስፈሪው ልጅ " እያሉ ሰደቡኝ ይላታል። #ጊዜው ይሮጣል ልጁ ሁለት ጆሮ ቅጠሎች ከማጣቱ በስተቀር ውብና ደምግቡ ነበር እናት ግን ሁልጊዜ በልጇ ሁኔታ በሀዘን ትቆራፈዳለች። ጊዜው ተቀይሮ ቴክኖሎጂ መጣና አንድ የታወቀ ዶክተር ለቤተሰቦቹ እንዲህ ሲል አበሰራቸው "ሁለት የጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ፍቃደኛ ሰው ካገኛቹ መፍትሄው ቀላል ነው።" ይላቸዋል። #ፍለጋው ተጀመረ ለዚ ለጋ ወጣት ከሞት በኋላ የጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ተፈለገ…ተፈለገ…ተፈለገ። ከጥቂት ቀናት በኋላ አባት ልጁን ጠራውና ነገ ሆስፒታል እንሄዳለን ምክንያቱም ሁለት ጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ሰው ተገኝቷል ነገር ግን የሰውየው ማንነት በሚስጥር ስለሆነ አይነገርህም አለው። በንጋታው እናት እና አባቱ ልጁን ይዘው ወደ ሆስፒታል ሄዱ ፍፁም የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደረገለት አዲስ ውብ የሆነ ልጅ ሆኖ ከሆስፒታል ወጣ በቃ አለምን በድጋሚ ተቀላቀላት በራስ መተማመኑም ሲጨምር የእውቀት ብቃቱም ጨመረ ሀይስኩል እና ዩኒቨርስቲም በጥሩ ውጤት በማእረግ ተመርቆ ወጣ በጥሩ ክፍያም ስራ ተቀጠረ። #ልጅም አንድ ቀን አባቱን እንዲህ ሲል ጠየቀው ሁለት ጆሮዎቹን ለግሶ ይህንን አለሜን እንዳይ ያደረገኝን ሰው ንገረኝና ዘላለሜን ሳመሰግነው ልኑር ሲል ጠየቀው። #አባትም አይ ምንም ልታደርግለት የምትችል አይመስለኝም ሲል መለሰለት። #እናትና አባትም ይህንን ሚስጥር በሆዳቸው እንደታቀፉ ቀናቶች ከነፉ…ነጎዱ። እውነት ትቀጥን ይሆናል እንጂ አትበጠስም" ነውና ነገሩ ሚስጥሩ የሚወጣበት ቀን ደረሰ። አንድ ቀን ቤተሰቡ ተሰበሰበ አባትም ሄዶ ከእናት ጎን ቆመ ልጅም በጭንቀት ተዋጠ!! አባትም የእናትየውን ዞማ ፀጉር ቀስ ብሎ ከፍ አደረገው የእናት የጆሮ ቅጠሎች የሉም!!!! ልጅየውም የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም!! በእናቱ ጆሮ አልባ ፊት ላይ እንዳፈጠጠ የእንባ ዘለላ እንደ ጅረት አንጠባጠበ። እናትም እንዲህ አለች ልጄ ሆይ አታልቅስ ምክንያቱም የኔ ውበት ባንተ ፊት ላይ ሁሌ ስለማየው የአለማችን ደስተኛዋ እናት እኔ ነኝ በማለት ልጇን አቅፋ ሳመችው። # ክብር ፍቅር እና እውቅና የራሳቸውን አለም ትተው ስለኛ ሲሉ ለሚኖሩት እናቶቻችን። Copied @yasin_nuru  @yasin_nuru
Show all...
216👍 80😢 19🥰 17
# ልጄን አሳዩኝ አሳዩኝ አለች በደከመ ድምጿ ከወሊድ ስቃይዋ ገና ኡፎይ ሳትል አምጥተው ክንዷ ላይ አደረጉላት። #ህፃኑ የተሸፈነበትን ጨርቅ ገለጠችው ክው ብላ ደነገጠች። ዶክተሩ ሁለት እጆቹን እንዳጣመረ በሀዘን ወደመስኮቱ ፊቱን አዙሮ ማየት ጀመረ።ተፈጥሮ ሰሰተች ጨከነች ህፃኑ ያለ ጆሮ ነበር የተወለደው። የእናት እንባ የህፃኑ ፊት ላይ ተንጠባጠበ። #ከአመታት በኋላ ምንም እንኳ ህፃኑ ሁለት የጆሮ ቅጠሎች ባይኖሩትም የልጁ የመስማት ችሎታ ጤነኛ እንደሆነ ተረጋገጠ። ይሁንና ሁልጊዜ ትምህርት ቤት ውሎ ሲመጣ እናቱ አንገት ላይ ተጠምጥሞ እያለቀሰ እማ እማ "አስፈሪው ልጅ " እያሉ ሰደቡኝ ይላታል። #ጊዜው ይሮጣል ልጁ ሁለት ጆሮ ቅጠሎች ከማጣቱ በስተቀር ውብና ደምግቡ ነበር እናት ግን ሁልጊዜ በልጇ ሁኔታ በሀዘን ትቆራፈዳለች። ጊዜው ተቀይሮ ቴክኖሎጂ መጣና አንድ የታወቀ ዶክተር ለቤተሰቦቹ እንዲህ ሲል አበሰራቸው "ሁለት የጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ፍቃደኛ ሰው ካገኛቹ መፍትሄው ቀላል ነው።" ይላቸዋል። #ፍለጋው ተጀመረ ለዚ ለጋ ወጣት ከሞት በኋላ የጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ተፈለገ…ተፈለገ…ተፈለገ። ከጥቂት ቀናት በኋላ አባት ልጁን ጠራውና ነገ ሆስፒታል እንሄዳለን ምክንያቱም ሁለት ጆሮ ቅጠሎች የሚለግስ ሰው ተገኝቷል ነገር ግን የሰውየው ማንነት በሚስጥር ስለሆነ አይነገርህም አለው። በንጋታው እናት እና አባቱ ልጁን ይዘው ወደ ሆስፒታል ሄዱ ፍፁም የተሳካ ቀዶ ጥገና ተደረገለት አዲስ ውብ የሆነ ልጅ ሆኖ ከሆስፒታል ወጣ በቃ አለምን በድጋሚ ተቀላቀላት በራስ መተማመኑም ሲጨምር የእውቀት ብቃቱም ጨመረ ሀይስኩል እና ዩኒቨርስቲም በጥሩ ውጤት በማእረግ ተመርቆ ወጣ በጥሩ ክፍያም ስራ ተቀጠረ። #ልጅም አንድ ቀን አባቱን እንዲህ ሲል ጠየቀው ሁለት ጆሮዎቹን ለግሶ ይህንን አለሜን እንዳይ ያደረገኝን ሰው ንገረኝና ዘላለሜን ሳመሰግነው ልኑር ሲል ጠየቀው። #አባትም አይ ምንም ልታደርግለት የምትችል አይመስለኝም ሲል መለሰለት። #እናትና አባትም ይህንን ሚስጥር በሆዳቸው እንደታቀፉ ቀናቶች ከነፉ…ነጎዱ። እውነት ትቀጥን ይሆናል እንጂ አትበጠስም" ነውና ነገሩ ሚስጥሩ የሚወጣበት ቀን ደረሰ። አንድ ቀን ቤተሰቡ ተሰበሰበ አባትም ሄዶ ከእናት ጎን ቆመ ልጅም በጭንቀት ተዋጠ!! አባትም የእናትየውን ዞማ ፀጉር ቀስ ብሎ ከፍ አደረገው የእናት የጆሮ ቅጠሎች የሉም!!!! ልጅየውም የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም!! በእናቱ ጆሮ አልባ ፊት ላይ እንዳፈጠጠ የእንባ ዘለላ እንደ ጅረት አንጠባጠበ። እናትም እንዲህ አለች ልጄ ሆይ አታልቅስ ምክንያቱም የኔ ውበት ባንተ ፊት ላይ ሁሌ ስለማየው የአለማችን ደስተኛዋ እናት እኔ ነኝ በማለት ልጇን አቅፋ ሳመችው። # ክብር ፍቅር እና እውቅና የራሳቸውን አለም ትተው ስለኛ ሲሉ ለሚኖሩት እናቶቻችን። Copied @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
የኢራን እና የእስራኤል ነገር ግን አይገርማችሁም🤔 ኢራን ባለፈው "ምንም ጉዳት ባያመጣም" ሚሳኤል ተኩሳ ነበር። እስራኤልም እበቀላለው ብላ ዛሬ በድሮን ጥቃት አድርሳለች ተብሎ ሲነገር ነበር። ኢራኖች ደሞ በእስራኤል የተሰነዘረ ጥቃት አይደለም አሉ። ሌላውን ህዝብ ዝም ተባባሉ እንዳይል አውቀው ጉዳት የማያደርስ ጥቃት እያደረጉ ጠላት ናቸው ብሎ እንዲየስብ እያረጉ ይሆን? ደሞ እኮ እዚ ቦታ ነው ጥቃት የማደርሰው በዚ ቀን እየተባባሉ ነው የሚጠቃቁት። እውነት እስራኤል ያሁሉ ሚሳኤል የምር ተተኩሶባት ከሆነ በቀሏ ተራ ይሆን ነበር? ሃማስን ለማጥፋት ብላ ያሁሉ ሺህ ሰው ገላ ሃገሩን በሙሉ አደጋ ሊያደርስባት የሚፈልግ ሃገርን እንዴት በቀላሉ ተወቻት። እስኪ የናንተን ሃሳብ ወዲህ በሉ @yasin_nuru @yasin_nuru
Show all...
👍 74🤔 22 19👎 12
#ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት  በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል። በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው  ይበቃናል ? በፍጹም ! ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል። የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ?  - ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር - ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን - ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ - ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን - ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል። ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው። በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል። ወደፊት እንደ ሩዋንዳ እጅግ አሰፈሪ የዘር ጭፍጨፋ ሊኖር እንደሚችል ማሳያ እያየን ነው አላህ ከዚ ጥንብ ዘረኝነት ይጠብቀን። @yasin_nuru   @yasin_nuru
Show all...
👍 68👏 14 13💔 7😢 3😁 1
#ኢትዮጵያ ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት  በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል። ይህን እጅግ አሳፋሪና በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሚያሳይ ቪዲዮ ያጋሩት ደግሞ እራሳቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ናቸው። ድርጊቱ ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል። በርካቶች ስለ ነገ በማሳብ ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል። በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው  ይበቃናል ? በፍጹም ! ከዚህ በፊትም እንደምንለው በቪዲዮዎች ተቀርጾ የምናየው ምናልባትእድለኞች ሆነን ከብዙ አንዱ እንጂ ስንት ያላየነው ይኖራል። ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል። ይህን ተግባራቸውን እንደ በጎ ስራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል። የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ?  ይህ ተግባር በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነዛ ያለው የጥላቻ ስብከት ምን ያህል ስር እንደሰደደ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ነገን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል። ግልጽ የሆነ የብሄርና የግለሰቦች ጥላቻ ፣ ልብም አእምሮም በጥላቻ መሞላት፣ አይንም በጥላቻ መታወር ፦ - ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር - ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን - ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ - ለህግ እና ስርዓት ቅንጣት ታክል ደንታ እንዳይኖረን - ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን - ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል። ሰዎች ወደው ሳይሆን በስርዓት፣ በግለሰቦች፣ በአንቂዎች ፣ በሚዲያዎች... አማካኝነት ነው ጥላቻ እንዲውጣቸው እና ማገናዘብ ፣ ቆም ብሎ ማሰብ የሚባለውን መሰረታዊ ነገር እንዲያጡት የሚሆነው። ሰዎች ከመሰል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አብሮነት ፣ ፍቅር ፣ መግባባት፣ መከባበር ፣ ህግ ፣ ስርዓት፣ ወንድማማችንነትን ከማስተማር ባለፈ በህግ ማረም ፣ ነገ መዘዙ የከፋ እየሆነ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲገታ በአንድ ላይ ማውገዝ ፣ ተበዳይን መካስ ፣ እውነት ህግ የበላይ ነው የምንል ከሆነም ለራሳችን ስንል ህግን ሁሌም ማስከበር ነው። ዛሬ ላይ እንዲህ ያሉና ከዚህ ቀደምም በየሀገሪቱ ክፍሎች የሰማናቸው ፍጹም አደገኛ የሚባሉ ጉዳዮች የሳምንት አጀንዳ እየሆኑ እያለፉ ይመስለን ይሆናል ግን በእርግጠኝነት መዘዛቸው የከፋ ሊሆን ይችላል። ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው። በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል።
Show all...