cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

BBC News አማርኛ ️

━━⊱✿⊰━━ እንኳን ወደ BBC News አማርኛ መጡ ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች እና ቴሌግራም ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.  ድረ-ገፅ:- https://www.bbc.com/amharic የቴሌግራም ገፅ:- https://t.me/BBC_Amharic_News1 የፌስቡክ አድራሻ:- https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/ @BBC_Amharic_News1

Show more
Japan1 937The language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
16 968
Subscribers
+1324 hours
+367 days
+11730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📌ማሳወቂያ ይህ የቴሌግራም ገፅ ለብዙሀን ተደራሽ መሆን ስላልቻለ 20ሺ አባላት እስኪደርስ ድረስ መረጃዎች እንደማንለቅ ልናሳውቅ እኖዳለን። ስለሆነም የቢቢሲ አማርኛ ዜናዎችን በእየለቱ ለማግኘት እስከዛው እነዚህን አማራጮች እንዲጠቀሙ በአክብሮት እንጠይቃለን። ድረ-ገፅ:- https://www.bbc.com/amharic የፌስቡክ አድራሻ:- https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/ @BBC_Amharic_News1
Show all...
ዜና - BBC News አማርኛ

ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ዜናዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን በየዕለቱ እናቀርባለን። ምንጊዜም ከቢቢሲ አማርኛ ከማንም ያልወገኑ፣ ሚዛናዊ፣ ተዓማኒ፣ ግልጽና እውነተኛ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚችሉ እናምናለን።

የአሜሪካ ፖለቲከኞች የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ከስምምነት ደረሱ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ልዩነት ያላቸው ሪፐብሊካን እና ዲሞክራቶች በአዲሱ መመሪያ ላይ ከስምምነት መደረሳቸው ተገለጸ። ሆኖም የምክረ ሃሳባቸው ሂደት የሚጠበቅበትን ያህል አልተጓዘም ተብሏል። ፍሎሪዳ ውስጥ በአንድ ትምህር ቤት ላይ ከተከፈተ ተኩስ የተረፉት ዴቪድ ሆግ “ምንም እንኳን ይህ ስምምነት ትንሽ ቢሆነም ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለዋል። ሌላዋ የቀድሞ ሕግ አውጪ እና እንደ አውሮፓውያኑ በ2011 በአሪዞና ግዛት ውስጥ ከተፈጸመ ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው የተረፉት ጋብሬል ጊፎርድስ ስምምነቱን “ጠቃሚ እርምጃ ነው” ብለውታል። ተቀናቃኞቹ ከስምምነት የደረሱበት አዲሱ እቅድ የጦር መሳሪያ ገዢዎች ጠንካራ ምርመራ የሚደረግባቸው ሲሆን ከ 21 ዓመት በላይ መሆን እና ከሕገ ወጥ የመሳሪያ ግዢ ጋር በተያያዘ ምረመራ ይደረገባቸዋል። ይህ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ምክረ ሀሳብ ትላንት ዕሁድ ነበር ይፋ የተደረገው። ታዲያ 10 የሪፐብሊካን አባላት ሕጉን የደገፉ ሲሆን ይህ ማለት ወደ ሕግ ለመቀየር የሚስፈልገው ቁጥር ተሟልቷል ማለት ነው። ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን ዕቅዱ በትክክለኛ መንገድ ላይ እየሄደ ነበር ያሉ ሲሆን፣ ሆኖም እሳቸውም ይሁን ሌሎች ዲሞክራቶች እንዲሆንከሚፈልጉት እጅግ የራቀ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/c1wl701nx19o @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
የአሜሪካ ፖለቲከኞች የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ላይ ከስምምነት ደረሱ

በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን በተመለከተ ልዩነት ያላቸው ሪፐብሊካን እና ዲሞክራቶች በአዲሱ መመሪያ ላይ ከስምምነት መደረሳቸው ተገለጸ። ሆኖም የምክረ ሃሳባቸው ሂደት የሚጠበቅበትን ያህል አልተጓዘም ተብሏል።

አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች ከአህጉሪቱ መሰደድ እንደሚፈልጉ ጥናት አመለከተ አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች በአገራቸውና በአህጉሪቱ ላይ ብሩህ ተስፋ እንደማይታያቸው አንድ ጥናት አመለከተ። በጥናቱ ውስጥ ከተካቱት አፍሪካውያን ወጣቶች መካከል ሁለት ሦስተኛው ስለ እራሳቸው የወደፊት ተስፋ አውንታዊ ምልከታ ቢኖራቸውም፣ አገራቸውና አህጉራቸው አፍሪካ እየሄዱበት ባለው አቅጣጫ ላይ ተስፋ ሰጪ ነገር እንደማያዩ ተናግረዋል። ‘አፍሪካን ዩዝ ሰርቬይ’ በተባለው በዚህ ጥናት ውስጥ ከ15 የአፍሪካ አገራት የተወጣጡ ከ4,000 በላይ ወጣቶች ከአጥኚዎቹ ጋር የፊት ለፊት ቃለ ምልልስ አድርገው ነው፤ ስለአገራቸውና አህጉራቸው ያለቸውን አመለካከት ለአጥኚዎች የገለጹት። https://www.bbc.com/amharic/articles/cxr67p3y0xko @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች ከአህጉሪቱ መሰደድ እንደሚፈልጉ ጥናት አመለከተ

አብዛኞቹ አፍሪካውያን ወጣቶች በአገራቸውና በአህጉሪቱ ላይ ብሩህ ተስፋ እንደማይታያቸው አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

ታዋቂው የትግርኛ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ታዋቂው ድምጻዊ ዳዊት ነጋ ትናንት እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. አመሻሹ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ወዳጆቹና ዘመዶቹ ለቢቢሲ ገለጹ። ዳዊት ነጋ ባደረበት ድንገተኛ ህመም ዓርብ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው አዲስ ህይወት ሆስፒታል መግባቱን ተናግረዋል። ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት በጉንፋን መልክ የጀመረ ህመሙ ከተባባሰ በኋላ ዓርብ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እስከ ቅዳሜ ድረስ ህክምና ሲደረግለት ቆይቷል። ትናንት እሁድ ከሰዓት በኋላ ህመሙ ሲጸናበት ወደ ጽኑ ህሙማን ክትትል ክፍል መግባቱን እና ማታ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ህይወቱ ማለፉን ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዳዊት ወደ ሆስፒታሉ ከመምጣቱ በፊት ህመሙን ለማስታገስ በቤት ውስጥ ግሉኮስ ይወስድ እንደነበረም ተነግሯል። ህመሙ ሲበረታበት ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ የስኳር መጠኑ መጨመሩን እና ህመሙ ወደ የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) መቀየሩን ተነግሮታል። በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት በተለየው የዳዊት አስከሬን ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚደረግም ሲያስታምሙት የሰነበቱት ጓደኞቹና አብሮ አደጎቹ ለቢቢሲ ገልፀዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cp9nz07x94eo @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
ታዋቂው የትግርኛ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ታዋቂው ድምጻዊ ዳዊት ነጋ ትናንት እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. አመሻሹ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የቅርብ ወዳዶቹና ዘመዶቹ ለቢቢሲ ገለጹ።

ለዩክሬን ሲዋጋ የነበረው የቀድሞ የብሪታኒያ ወታደር ተገደለ የቀድሞው የእንግሊዝ ጦር አባል የነበረው ግለሰብ ዩክሬን ውስጥ መገደሉን ቤተሰቦቹ አሳወቁ። ጆርዳን ጋትሊ ከብሪታኒያ ጦር በመውጣት ባለፈው መጋቢት ነበር በሩሲያ ከተወረረችው ዩክሬን ጎን ለመሰለፍ ወደ ጦር አውድማ ያቀናው። የወታደሩ አባት ልጄ "ጀግና" ነው ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ፅፈዋል። በምሥስራቃዊቷ የሰቨሮዶኔስክ ከተማ ውስጥ በነበረው ጦርነት ነው የተገደለው። ከተማዋ ባለፉት ጥቂት ቀናት ከበድ ያለ ጦርነት እያስተናገደች ትገኛለች። የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "ዩክሬን ውስጥ የተገለደውን ወታደር ቤተሰቦች እንደግፋለን" ብሏል። የወታደሩ አባት በፌስቡክ ገፃቸው በፃፉት መልዕክት ልጃቸው የዩክሬን ወታደሮችን እያሠለጠነ እንደነበረ ገልጠዋል። አክለው ውጊያ ላይ እያለ ክፉኛ ቆስሎ ሕይወቱ ማለፉን አርብ ዕለት እንደሰሙም ጽፈዋል። ወታደሩ ልጃቸው ወደ ዩክሬን ያቀናው ከራሱ ጋር "ብዙ ከመከረ" በኋላ እንደነበርም አባት አስታውሰዋል። የቤተሰቡ መግለጫ እንደሚያትተው ወታደሩ በዩክሬን ተወዳጅነት አትርፎ ነበር። https://www.bbc.com/amharic/articles/cv29e4w4nnyo @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
ለዩክሬን ሲዋጋ የነበረው የቀድሞ የብሪታኒያ ወታደር ተገደለ

የቀድሞው የእንግሊዝ ጦር አባል የነበረው ግለሰብ ዩክሬን ውስጥ መገደሉን ቤተሰቦቹ አሳወቁ።

ተቃዉሞን ተከለትሎ ሕንድ የበርካታ ታዋቂ ሙስሊሞችን ቤት አፈረሰች በነብዩ መሐመድ ላይ የተቃጡ ናቸው በተባሉ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ከተቀሰቀሰ ረብሻ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የበርካታ ሙስሊሞች ቤቶችን የሕንድ የፀጥታ ኃይሎች አፍረሱ። በኡታር ፕራዴሽ ግዛት የሚገኙት የቤቶቹ ባለቤቶች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ተስጥቷቸው ነበር። ሁለት የሕንድ ገዢ ፓርቲ ቢጄፒ ፓርቲ አመራሮች ፀረ እስልምና አስተያየቶችን ከሰጡ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቷል። ከሁከቱ ጋር በተያያዘ ፖሊስ ከ300 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል። እነዚህ አስተያየቶች የተሰጡት በግንቦት ወር በቲቪ ክርክር ወቅት የቢጄፒ ቃል አቀባይ በሆኑት ኑፑር ሻርማ ነው። የግለሰቧ አስተያየት አጸያፊ በመሆኑ ምክንያት ቢቢሲ ላይደግመው ወስኗል። አስተያየቱ በሕንድ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችንና በርካታ እስላማዊ መንግሥታትን አስቆጥቷል። የፓርቲው የደልሂ ሚዲያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ናቪን ኩማር ጂንዳል ይህንን አሉታዊ አስተያየት በትዊተር ገጻቸው በማጋራታቸው ተባረዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c973ej608gjo @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
ተቃውሞን ተከትሎ ሕንድ የበርካታ ታዋቂ ሙስሊሞችን ቤት አፈረሰች

በነብዩ መሐመድ ላይ የተቃጡ ናቸው በተባሉ አሉታዊ አስተያየቶች ምክንያት ከተቀሰቀሰ ረብሻ ጋር ግንኙነት አላቸው ያሏቸውን የበርካታ ሙስሊሞች ቤቶችን የሕንድ የፀጥታ ኃይሎች አፍረሱ።

ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። https://www.bbc.com/amharic/articles/cndxlne6nk9o @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት

ፕሮስቴት ካንሰር በብዛት የሚያጠቃው አፍሪካውያንን እና ጃማይካያውያንን እንደሆነ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። በዚህ ካንሰር የተጠቃ የቤተሰብ አባል ያለው ወንድ ከ40 ዓመቱ ጀምሮ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ምርመራ እንዲያደርግም ይመክራሉ።

የነዳጅ ድጎማው ሲነሳ ምን ሊያስከትል ይችላል? መንግሥት የውጭ ምንዛሬን በስስት ነው የሚያየው። እንደ ስእለት ልጅ። የዶላር ጥሪት እንደዋዛ አይቋጠርማ። በብዙ አበሳ፣ በብዙ የወጭ ንግድ፣ በብዙ ተጋድሎ ነው የሚመጣው። እንዲያም ኾኖ ጥሎበት ከአራት ቢሊዮን ዶላር አይዘልም። እሱም ቢኾን መጥቶ አይበረክትም፤ አብዛኛውን ነዳጅ ይጠጣዋል። ይሁን እንጂ፣ እስከዛሬ ድረስ ለነዳጅ የሚከፈለው ዶላር በወጭ ንግድ ከሚገኘው ዶላር በልጦ አያውቅም ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀየረ፤ ነገሩ ከፋ። ይህ በይፋ የታወቀው ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ነው። ለ2015 ነዳጅ መግዣ የሚያስፈልግህ ስንት ነው ሲባል 5.6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ። እንዲህ ያለ አሃዝ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር፤ ይህም የመርከብና የነዳጅ ዋጋ መናር ያመጣው ነው ይባላል። ታዲያ ይህ ገንዘብ ከየት ይመጣል? አንደኛ ከውጭ ንግድ እንዲህ ዓይነት ገቢ በጭራሽ ኖሮን አያውቅም። ቡናው፣ ሌጦው፣ ሰሊጡ ተረባርበው ከአገር ወጥተው እንኳ እንዲህ ዓይነት ገቢን አያመጡም። https://www.bbc.com/amharic/articles/cyd3yjlr0rgo @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
የነዳጅ ድጎማው ሲነሳ ምን ያስከትላል?

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በአጠቃላይ የምርትና አገልግሎት ዋጋ ላይ ጭማሪን ስለሚያስከትል በርካቶችን የሚያሳስብ ጉዳይ ነው። በቅርቡም መንግሥት ለዳጅ የሚያደርገውን ከፍተኛ ድጎማ ለማንሳት እየተዘጋጀ መሆኑን ተከትሎ፣ ይህ እርምጃ ያለውን የዋጋ ንረት በማባባስ ሌላ ቀውስ ይፈጥራል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። መንግሥትም በቢሊዮኖች የሚቆጠር የድጎማ ዕዳን ተሸክሞ መቀጠል እንደማይችል ይገልጻል። ድጎማውን የመንሳት ተገቢነትና ሊያስከትል የሚችለው ጫና ምንድን ነው?

━━⊱✿⊰━━ 📌 BBC News አማርኛ ቢቢሲ ከሌሎች ድረ-ገጾች እና ቴሌግራም ገጾች ለሚመጡ መረጃዎች ሀላፊነት አይወስድም.  ድረ-ገፅ:- https://www.bbc.com/amharic የቴሌግራም ገፅ:- https://t.me/BBC_Amharic_News1 የፌስቡክ አድራሻ:- https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/ @BBC_Amharic_News1
Show all...
ዜና - BBC News አማርኛ

ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ዜናዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን በየዕለቱ እናቀርባለን። ምንጊዜም ከቢቢሲ አማርኛ ከማንም ያልወገኑ፣ ሚዛናዊ፣ ተዓማኒ፣ ግልጽና እውነተኛ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚችሉ እናምናለን።

ከዩኬ ወደ ሩዋንዳ የሚደረገው የስደተኞች ጉዞ ጉዳይ ይግባኝ ሊጠየቅበት ነው የዩኬ መንግሥት ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ማጋዝ መጀመሩን የተቃወሙ ሰዎች ጉዳዩን ሰኞ ዕለት ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ይግባኝ ሊጠይቁ ነው። ከፍተኛው ፍርድ ቤት የመጀመሪያው ዙር ስደተኞችን የማጓጓዝ ሥራ እንዲካሄድ ፈቃድ መስጠቱ ተሰምቷል። 31 ሰዎች ማክሰኞ ዕለት በአውሮፕላን ተጭነው ወደ ሩዋንዳ እንደሚወሰዱ ተነግሯቸዋል። በዚህ ዓመት ተጨማሪ አውሮፕላኖች ስደተኞችን ጭነው ወደ ሩዋንዳ ይሄዳሉ። የዌልሱ ልዑል ቻርልስ በዚህ የመንግሥት ዕቅድ ደስተኛ እንዳልሆኑ የዩኬ ጋዜጦች አስነብበዋል። ልዑሉ በያዝነው ወር ወደ ምስራቅ አፍሪቃዊቷ ሃገር ንግሥቷን ወክለው እንደሚያቀኑ ታውቋል። የልዑሉ ጉዞ ዓላማ ኪጋሊ ውስጥ የኮመንዌልዝ ሃገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው። የልዑሉ ተወካይ እንደሚሉት ልዑሉ "ፖለቲካዊ አስተያየቶችን" ከመስጠት ይቆጠባሉ። አዲሱ የመንግሥት ፖሊሲ እንደሚለው በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዩኬ የገቡ ሰዎች ወደ ሩዋንዳ ተወስደው እንደ አዲስ ጥገኝነት ይጠይቃሉ። የቦሪስ ጆንሰን መንግሥት ይህን የሚያደርገው ስደተኞች በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዩኬ የሚያደርጉትን ጉዞ ለመግታት ነው። በዚህ ዓመት ብቻ ኢንግሊሽ ቻናል የተሰኘውን የባሕር መንገድ ተጠቅመው 10 ሺህ ሰዎች ድንበር አቋርጠዋል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cld26qry5nqo @BBC_Amharic_News1 @BBC_Amharic_News1
Show all...
ከዩኬ ወደ ሩዋንዳ የሚደረገው የስደተኞች ጉዞ ጉዳይ ይግባኝ ሊጠየቅበት ነው

ከዩኬ ወደ ሩዋንዳ የሚደረገው የስደተኞች ጉዞ ጉዳይ ይግባኝ ሊጠየቅበት ነው