cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱስ ዮሴፍ እና የአሳይ ት/ቤት ግቢ ጉባኤ

የቅዱስ ዮሴፍ እና አሳይ ትምህርት ቤት ግቢ ጉባዔ ኦፊሻል ቴሌግራም ቻናል፡፡ ተቀላቅለው አብረን የእግዚአብሔርን ቃል እንማር፡፡

Show more
Advertising posts
258Subscribers
No data24 hours
-17 days
+130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ (ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ) "አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት። ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት። ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።  ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። "የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት? ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም። እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን። #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
251Loading...
02
#ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) #የዘንባባ_ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ #የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
282Loading...
03
“ፍቅርህ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” #ሊቁ_ያዕቆብ_ዘሥሩግም
292Loading...
04
#ሆሳዕና (የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት) ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ #ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡- ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ #የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ #ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡- እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡….. ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል። #መልዕክታት ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) 1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ) #ግብረ_ሐዋርያት የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ) #ምስባክ "ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3 ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡ ወይም "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2 ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡ #ወንጌል ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡
322Loading...
05
"የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
390Loading...
06
የሰውን ልጅ በሩህሩህነት አሸንፈው። ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው፤ ሁሉንም ሰው ውደድ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር። አባ እንጦንስ
490Loading...
07
“በደለኞች ወደ እርሱ መቅረብ ይችሉ ዘንድ በሥጋ ለተገለጠው ረቂቅ አምላክ ምስጋና ይሁን። ጌታችን ኃጢአተኛዋን ሴት ፈሪሳውያኑ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው እንዳሰቡት ከእርሱ አላረቃትም። ማንም ሊደርስበት ከማይችለው ሰማይ የወረደው እንደ ዘኬዎስ ያሉ አጭር ቀራጮች ይደርሱበት ዘንድ ነው። ሊይዘው የሚችል ምንም ነገር የሌለ አምላክ የሰውን ሥጋ የለበሰው ኃጢአተኛዋ ሴት እንዳደረገችው የተዳደፉ ከንፈሮች ሁሉ እግሮቹን በመሳም ይቀደሱ ዘንድ ነው” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዲያቆን አቤል ካሳሁን @KaleEgziabeher
911Loading...
08
#ሰው_እንደ_ዘር_ነው አባቶቻችን ሊቃውንት ሰው እንደ ዘር ነው ይላሉ። ሰው እንደ ዘር ነው ማለት ዘር ተዘርቶ የሚያድገው በሁለት መሠረታዊ ነገር ነው። በብርድ እና በጸሐይ። ዘር ዝናምና ጸሐይ ያስፈልገዋል። ዝናም ብቻ ከሆነ ሽባ ይሆናል ጸሐይ ብቻም ከሆነ ይደርቃል። ሰውም እንደ ዝናሙ የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል፤ እንደ ጸሐዩም መከራ ያስፈልገዋል። ዘር በዝናሙ እየለዘበ፣ በጸሐዩ እየበሰለ እንደሚያድገው ሁሉ ሰውም በመከራ እየጠነከረ በተስፋና በእግዚአብሔር ቸርነት እየተጽናና ያድጋል። ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብቻ ከሆነ የሚያስበው ሽባ ይሆናል። መከራ ባገኘው ጊዜ ወዲያው ተስፋ ይቆርጣል። ሃይማኖትን ሊክድ ይችላል። መከራ ብቻ ከሆነበት ደግሞ ወዲያው ደግሞ እንደዚሁ ተስፋ ቆርጦ ሊሠበር ይችላል። ስለዚህ ዘር ዝናምና ጸሐይ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰውም መከራና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልገዋል። #አባ_ገብረ_ኪዳን (የብሉያት እና የሐዲሳት መምህር)
600Loading...
09
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም "ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡" #ቅዱስ_ዮሃንስ_አፈወርቅ
580Loading...
10
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው.... ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡ "ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡ አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
491Loading...
11
እሺ ብትሉ… ልጆቼ! እስኪ ምላሴን ላሰናብትባችሁና እናንተም በትዕግሥት አድምጡኝ! የቤት ሠራተኛ አላችሁ እንበል፡፡ ይህቺ የቤት ሠራተኛችሁ የለበሰችውንና በወጥ፣ በአመድ እንዲሁም በሌላ ቆሻሻ እድፍ ያለ ልብሷን ትለብሱ ዘንድ ትፈቅዳላችሁን? በእርግጠኝነት አትፈቅዱም፡፡ ግን የብዙዎቻችን ሰውነት ከዚህ ልብስ በላይ መቆሸሽዋስ ታውቃላችሁን? ልጆቼ! ንግግሬ በጣም እንደሚያሳምም አውቃለሁ፤ ግን ምን ላድርግ? የተስተካከለ ሕይወት ቢኖረን እንዲህ የምናገር ይመስላችኋልን? በፍጹም! አንድ የቆሰለ የሰውነት ክፍል ቢኖራችሁ ሐኪሙ ይህን ቁስላችሁ በጣቱ ሳይነካካ ማከም ይችላልን? አይችልም! እኔም እንዲህ ቁስላችሁን ካልነካካሁት በስተቀር ማከም አልችልም፡፡ ለነገሩ ሰው ሰውነትህን አትንካ ማለት ይቻላልን አይቻልም! ታድያ እኔና እንናተ እኮ አንድ አካል ነን፡፡ በክርስቶስ አንድ ኾነን የለምን? እንግዲያውስ ንግግሬን አትጥሉት፤ ክፉ ግብራችሁን እንጂ፡፡ ችግሩ ከማን ነው ከእኛው ወይስ ከቆሻሻው? አንድ ወደ ትዕይንት (ቲያትር) ቤት የሄደ ወጣት ገላዋን ገላልጣ የምትተውን ተዋናይትን አይቶ ዝሙትን መፈጸም የማያስብ ማን ነው? ደጋግሞ የዝሙት ዘፈንን የሚሰማ ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መቋቋም እችላለሁ የሚል ማን ነው? ቀኑን ሙሉ የዝሙት ጽሑፎችን ሲያነብ የሚውል ሰው ዝሙትን ከመፈጸም መጠበቅ እችላለሁ የሚል ማን ነው? ልጆቼ! ትዕይንቱን እያየነው፣ ዘፈኑን እየዘፈንነው፣ መጽሐፉንም እያነበብነው ኾኖም ግን መፍትሔ ካላገኘንበት ችግሩ እየባሰ የሚሄድ አይደለምን? እኛ ፈቃደኞች ከኾንን ግን መፍትሔው በሥጋችን ላይ ካለው ደዌ በላይ በጣም ቀላል ነው፡፡ ምክንያቱም የሥጋችን ቁስል ሐኪም፣ መድኃኒት፣ ጊዜ ያስፈልጓል፡፡ የነፍሳችንን ቁስል ግን ፈቃድ በቂ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሕዛብ ከእኛ በላይ በንጽሕና ሲኖሩ ሳይ በጣም አፍራለሁ፡፡ እንግዲያውስ ልጆቼ እንመለስ፡፡ ያቆሸሹንን ነገሮች እንጣላቸው፤ እንቁረጣቸው፤ እናስወግዳቸው፡፡ ሰነፎች አንሁን፡፡ ውሳኔው የእኛው ነው፡፡ መጽሐፍ ሲናገር “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል” ይላል /ኢሳ.1፡19-20/፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእኛ እሺታና እምቢታ የተወሰነ ነው ማለት ነው፡፡ የምንኮነነውም የምንመሰገነውም በዚሁ መሠረት ነው ማለት ነው፡፡ መድኃኒዓለም በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር በቸርነቱ ይደምረን አሜን፡፡ ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
550Loading...
12
"ድኃ በቤትኽ ደጃፍ ይጮኻልን? ተነስተህ በደስታ የቤትህን ደጅ ክፈትለት የድኃውን ልመና ቸል አትበል፡፡ በነፍሱ የመረረው ነውና ቢረግምህ እግዚአብሔር አቤቱታውን ይሰማዋል፡፡ ስለዚህ ይረግምህ ዘንድ ምክንያት አትሁነው አዝኖ ከሆነ በመልካም መስተንግዶ ደስ አሰኘው፡፡ በኀዘን የከበደው ልቡ በአንተ ይረፍ፤ በሕይወት ዘመንህ ማጣት የሚያመጣቸውን ስቃዮች ታውቃቸዋለህና ችግረኛውን ከቤትህ ደጅ አትመልሰው፡፡" #ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶሪያዊ
951Loading...
13
#ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ በነበረው በኒቆዲሞስ የተሰየመ ሰንበት ነው፡፡ የአይሁድ አለቆች አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን “ምልክት አሳየን” እያሉ ይፈታተኑት ነበር፡፡ ስለሞቱና ትንሣኤው በምሳሌ ቢነግራቸው አልገባቸውም፡፡ ሲያስተምር ብዙዎች ያምኑ ነበር፡፡ ለአይሁድ አለቆች ግን ጭንቅ ነበር፤ የታመሙ ሲፈወሱ ሕጋችን ተሻረ ይሉ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ተአምራትና ትምህርት የአይሁድ አለቆች ክርስቶስን ለመክሰስ በሚፈልጉበት ወቅት ከአይሁድ አለቆች አንዱ ኒቆዲሞስ በቀን እንዳያደርገው አይሁድን ፈርቶ አንድም ጊዜ አላደርሰው ብሎ እንደ አይሁድ አለቆች ኢየሱስን መቃወሙን ትቶ በሌሊት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሄደ፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በነፍስ የታመሙትን በቃሉ በሥጋ የታመሙትን በተአምራቱ ሲፈውስ፤ ኒቆዲሞስ ሰምቶና ተመልክቶ “መምህር ነኝ” ብሎ በመምህርነቱ ሳይኮራ አለቅነቱን መመኪያ ሳያደርግ፡፡ በልቦናው የተሳለውን እውነትን የመፈለግ ስሜት አንግቦ ጌታው መምህሩ ዘንድ በሌሊት ገሠገሠ ዮሐ.3÷1ደርሶም ምስክርነቱን እንዲህ ሲል መስጠት ጀመረ “መምህር ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና” ዮሐ.9÷24፣ የሐዋ.ሥራ 10÷38 በማለት መመስከር ሲጀምር ጎዶሎን የሚሞላ፡፡ አላዋቂነት በአዋቂነት የሚለውጥ፡፡ ከምድራዊ እውቀት ወደ ሰማያዊ ምስጢር የሚያሸጋግር አምላክ፡፡ “ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይችልም” ዮሐ.3÷6 ,1ጴጥ.1÷23 በማለት የአይሁድ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ ቢያስተምረው ስለዳግመኛ መወለድ ከመጽሐፍ ቢያገኘውም ምስጢሩ አልተገለጠለትምና “ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅፀን ተመልሶ መግባት ይችላልን?” በማለት ጥያቄ አቅርቧል፡፡ “እውነት እውነት እልሃለሁ ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዝአበሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፡፡ ኤፌ.5÷26 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ በማለት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢያስረዳው ምስጢሩ ከአቅሙ በላይ የሆነበት ኒቆዲሞስ እንደምን ይቻላል? በማለት ጠይቋል፡፡ አበ ብዙኀን አብርሃም ከአምላኩ ሞገስን አግኝቶ፤ የሰዶምና ገሞራ ጥፋት እንዳይደርስ እያማለደ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር እንደ ነበረ፤ ኒቆዲሞስም አላዋቂነቱን አምኖ ያልገባውን ምስጢር አምላኩን የመጠየቅ ዕድል በማግኘቱ ሲጠይቅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን ነገር አታውቅምን? በምድር ያለውን ስንነግራቸው ካላመናችሁ በሰማይ ያለውን ብንነግራችሁ እንደምን ታምናላችሁ? ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ ሙሴ ምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለ የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀላል፡፡ ያመኑበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዲጠፉ አይደለም…..” ዮሐ.3÷14፡፡ እያለ ለድኅነተ ዓለም እንደ መጣ ሰው በመብል፣ አምላኩን ከድቶ ልጅነቱን ትቶ ከእግዚአብሔር ቢለይም የሰው ልጅ ያጣውን ልጅነት ለመመለስ ስመ ግብርና ሀብተ ወልድን ለመስጠት መምጣቱን አስረዳው። “ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረከ በዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው፡፡ ልቤን ፈተንከው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንከኝም ምንም አላገኘህብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው” መዝ.16÷3 እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ምስጢረ ሥጋዌን የድኅነት ምስጢር ገልጾለታል፡፡ በሌሊት ከአምላኩ ተምሮ ምስጢሩ የተገለጸለት ኒቆዲሞስ ፍርሃት ርቆለት ቀድሞ በአደባባይ ሄዶ መማርን የፈራ ምስጢሩ ሲገለጽለት አይሁድ በሰቀሉት ዕለት ሳይፈራ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር ቅዱስ ሥጋውን ገንዞ ለመቅበር በቃ “ወአልቦ ፍርሃት ውስተ ተፋቅሮትነ፡፡ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል ማቴ.27÷58፣ 1ዮሐ.4÷18 እንዲል፡፡ ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ማር.16÷16፡፡ ባለው አማናዊ ቃል ኪዳን መሠረት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አምላክነቱ አምነን ለመንግሥቱ ዜጋ እንድንሆን ለኒቆዲሞስ ምስጢሩን ጥበቡን የገለጸ አምላክ ለኛም ይግለጽልን፡፡ #የዕለቱ_የሰንበት_መዝሙር_እና_ግጻዌ #መዝሙር፦ ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኃበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ፤ ዕጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ፡፡ (ስሙ ኒቆዲሞስ የተባለው ሰው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄደ፤ መምህር ሆይ ልታስተምር ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ እንደመጣህ እናምንብሃለን አለው። የአንበሳ ደቦል ተኛህ፣ አንቀላፋህም፤ በትንሣኤህ አንሣኝ።) #መልዕክታት፦ ሮሜ 7÷1-12 "ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች።... 1ኛ ዮሐ. 4 ÷18 - ፍጻሜ ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም። ..... የሐዋ.ሥራ 5÷34 - ፍጻሜ በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ...... #ምስባክ፦ መዝ.16፥3 ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፡፡ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፡፡ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው፡፡ ትርጉም፦ በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ልቤንም ፈተንኸው÷ ፈተንኸኝ÷ ዐመፅም አልተገኘብኝም፡፡ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር #ወንጌል፦ ዮሐንስ 3፥1-12 "ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ። መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።.... #ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም [ጎሥዐ] (#ማኅበረ_ቅዱሳን_ድረ_ገጽ እና #ግጻዌ)
631Loading...
14
Media files
701Loading...
15
ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡ በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡ ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡ ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡  #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
400Loading...
16
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ ተአምሪሁ ለቅዱስ ሚካኤል ሊቀመላእክት ዘሥዑል በነደ እሳት፡፡ ዘይስእል ምሕረተ ለኵሉ ቅድመ መንበሩ ለፀባዖት፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ለሁሉ ምሕረትን የሚለምን በእሳታዊ ባሕርይ የተፈጠረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ተአምር ይህ ነው፡፡ ልመናው፣ አማላጅነቱ የጥምቀት ልጆች ሁላችንን ከክፉ ቀን ያድነን፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ በሮም አገር ስለነበረ ስለ አንድ አይሁዳዊ ሰው ተነገረ፡፡ ሰውዬውም በዚህ በኃላፊው ዓለም ሀብት እጅግ ባለጠጋ ነበር፡፡ ወርቅና ብር ብዙ ከብትም ነበረው፡፡ በአንዲት ቀንም እንደአባቶቹ ልማድ ወደሚሰግድበት ቦታ ሲሄድ በመንገድ ሳለ ከአንድ ክርስትያናዊ ሰው ጋር ተገናኘ፡፡ ያ ክርስትያናዊም ድሮ በገንዘብ እጅግ ባለጠጋ ነበር፡፡ ግን ደሀ ሆነ፤ የዕለት ምግብ፣ የዓመት ልብስም አጣ፡፡ እጅግም ተቸገረ፡፡ ከዚህ በኋላ በመከር ጊዜ የቀን ሥራ ይሠራ ዘንድ ወደእርሻ ተሠማራ፤ የሚሰጠው ቢያገኝ የዕለት ምግብ ሊያገኝ ሽቶ፤ ያ አይሁዳዊ ያን ክርስትያን ወገን አገኘው፤ እንዲህም አለው፡፡ “ና፤ ሥራ፡፡ እኔ ዐሥር ወቄት ወርቅ እሰጥሀለሁ፤ ነግደህ ታተርፍበት ዘንድ፡፡ ነገር ግን ና፤ የመላእክት አለቃ ወደሚሆን ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን እንሂድና እኔን ከድተህ ገንዘቤን እንዳታጠፋ ማልልኝ፡፡” ሁለቱም ወደ መላእክት አለቃ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ሄዱ፡፡ አይሁዳዊውም ያን ክርስትያናዊ እንደወደደ አማለው፡፡ ከዚህ በኋላ ያ አይሁዳዊ ወርቁን ወዲያውኑ ሰጠው፡፡ ያም ክርስትያናዊ ገንዘቡን ተቀብሎ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ ከአይሁዳዊውም አገር ርቆ በሄደበት አገር እየነገደ ብዙ ዘመን ቆየ፡፡ ያ ክርስትያናዊም ወደሮም አገር ከተመለሰ በኋላ በብዙ ቀን አይሁዳዊው ክርስትያናዊው እንደተመለሰ ሰማና ፈልጎ አገኘው፡፡ “ነግደህ ልታተርፍበት የሰጠሁህን ገንዘቤን ለምን አትሰጠኝም?” አለው፡፡ ክርስትያናዊውም “ለኔስ ፈጽሞ ምንም አልሰጠኸኝም፡፡” አለው፡፡ አይሁዳዊውም “ነግደህ ልታተርፍበት በትርፉም አንተ ልትጠቀምበት ዐሥር ወቄት ወርቅ አልሰጠኹህምን?” አለው፡፡ ክርስትያናዊውም “አላውቅም፤ ከገንዘብህ አንድም አላየሁም፡፡” ብሎ ካደ፡፡ ከዚህም በኋላ አይሁዳዊው እንዲህ አለው፡- “እኔ ቀድሞም ቢሆን አንተ ከሀዲ እንደሆንክ ዐውቄያለሁ፡፡ በሰጠሁህም ጊዜ ይህን ዐውቄ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ታቦት አማልኩህ፡፡ አሁንም ና፤ አልሰጠኸኝም ስትል እንደገና ማል፤ እኔም በነጻ ወደወደድከው እንድትሄድ አሰናብትሀለሁ፡፡ ነገር ግን ኃይሉን በአንተ ላይ እንደሚገልጽ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እታመነዋለሁ፡፡ እርሱ ሰውረህ የሠራኸውን ያውቃልና፡፡ አንተም ሀሰተኛ እንደሆንክ ያውቃልና፡፡ እርሱ ረቂቅ መልአክ ብርሀናዊ መልአክ ስለሆነ፡፡” ይህን ካለው በኋላ ወደመላእክት አለቃ ወደቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን አብረው ሄዱ፡፡ ያም አይሁዳዊ ወደውስጥ ሳይገባ በፊት ለፊቱ ቆመ፡፡ አእምሮ የጎደለው ልብ ያጣ ያ ክርስትያናዊ ግን የመላእክት አለቃ ወደሚሆን ወደቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን በድፍረት ገባና በታቦተ ሚካኤል በሐሰት ማለ፡፡ ያን ጊዜንም ወዲያውኑ ከቤተክርስትያን ሲወጣና ከበር ሲደርስ እጆቹ እግሮቹ ደረቁ፡፡ እንደደንጊያም ሆኑ፡፡ መንቀሳቀስም ተሳነው፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፡- “የመላእክት አለቃ፣ የቸርነትና የይቅርታ መልአክ ሆይ በደሌን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፡፡ እኔ ታላቅ በደል ሠርቻለሁና፡፡ ተደፋፍሬም ወደቤተመቅደስህ ገብቻለሁና፡፡ በፈጣሪህ በእግዚአብሔር ስምም ምያለሁና፡፡ ጌታዬ እለምንሀለሁ፤ እማልድሀለሁ፤ ይቅር ትለኝ ትምረኝ ዘንድ፤ ኃጢአቴንም በደሌንም ታስተሠርይልኝ ዘንድ፡፡ እኔ በድፍረት ወደቤተመቅደስህ ገብቻለሁና፡፡ በሐሰትም ምያለሁና፡፡ እንደሥራዬ አትክፈለኝ ፤ ኃጢአቴን በደሌን አታስብብኝ፡፡ ለሰው ወገኖች ሁሉ አማላጅ፣ ለፍጥረትም ሁሉ ምሕረትን የምትለምን አንተ ነህና፡፡ ከዚህ ደዌ ብትፈውሰኝ ግን እንዲህ ያለ ሥራ ወደ መሥራት አልመለስም፡፡ በሐሰትም አልምልም፡፡ እኔ እንደቀድሞው ጤንነቴን ባገኝ ባለ ዘመኔ ሁሉ እስከ ዕለተ ሞቴ ቤተክርስትያንህን አገለግላለሁ፡፡” ይህንንም ሲናገር መራራ እንባ ያለቅስ ነበር፡፡ ደረቱንም እየመታ በቊርጥ ሕሊና ወደ እግዚአብሔር ወደመላእክት አለቃ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ይማልድ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እንቅልፍ መጣበት፤ ተኛ፡፡ መንፈቀ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ለዚያ ለድውዩ ተገለጠለት፡፡ እንዲህም አለው፡- “አንተ ጎስቋላ ሰው ምስጉን እግዚአብሔርን ለምን አልፈራኸውም? ወደ ቤተመቅደሱ በድፍረት ገባህ፤ በሐሰትም ስሙን ጠርተህ ማልክ፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም ታጋሽ እውነተኛ ቸር ባይሆን ኖሮ ሳታስበው በቀሰፈኽ ነበር፡፡ በቅጽበትም ባጠፋህ ነበር፡፡ የተሸከመችህ ምድርም እንደ ዳታን እንደ አቤሮን በዋጠችህ ነበር፡፡ በሐሰት የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ የሚምል ሁሉ ከኃጢአት አይነጻም፡፡ መጽሐፍ “በምትምልበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም በሐሰት አትጥራ” ያለውን አልሰማህምን?” ድውዩም እንዲህ አለው፡- “ጌታዬ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አንተም በምታውቀው በድያለሁ፤ አጥፍቻለሁ፡፡ ነገር ግን ማረኝ፤ ከዚህ ደዌም ፈውሰኝ፤ ምሕረት የእግዚአብሔር ልማዱ ነውና፤ አንተም እንደፈጣሪህ እዘንልኝ፤ ሰው ወዳጅ የምሕረት አማላጅ ነህና፡፡” ያንጊዜም አዘነለት፤ እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰው፡፡ “እንግዲህ አሁን ከደዌህ ፈወስኩህ፤ ግን ከዚህ የከፋ እንዳያገኝህ ዳግመኛ አትበድል፡፡” አለው፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ይህን ብሎ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ ያንጊዜም ድውዩ ከእንቅልፉ ነቃ፤ ደዌው ለቆት አገኘ፡፡ መላ ሰውነቱ ሕማም የሌለበት ጤነኛ ሆነ፡፡ ፈጽሞ ደስ አለው፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነው፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አደነቀው፡፡ ያ አይሁዳዊ ግን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገውን ይህን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ባየ ጊዜ ያን ወርቅ ከዚያ ሰው ተቀብሎ ስእለቱን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን አምኃ አድርጎ ሰጠ፡፡ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመነ፡፡ የክርስትና ጥምቀትንም ተጠመቀ፡፡ የመንፈስ ቅዱስንም ጸጋ ተቀበለ፡፡ በረከትንም አገኘ፡፡ የሥጋውንና የነፍሱን መዳኛም አገኘ፡፡ በሃይማኖትም በመታመንም የጸና ምዕመን ሆነ፡፡ ከዚህ በኋላ አይሁዳዊውም ክርስትያናዊውም አብረው የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ቤተክርስትያን ሲያገለግሉ፣ ታላላቆቹን ተአምራትና ድንቅ ድንቅ ሥራዎቹንም ሲመሰክሩ ኖሩ፡፡ ቸርነቱንም ለሰው ሁሉ ሲነግሩ ኖሩ፡፡ ልመናው አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይኑር፡፡ የሰማነውንም ሁሉ በጽላሎተ ረድኤቱ ይሸፍነን፡፡ የበደል ሐሩር እንዳያቃጥለን፣ የኃጢአት ቊርም እንዳያጠወልገን፣ እንዳያደርቀን፡፡ የአማላጅነቱ ኃይል ይሰውረን፡፡ የጠላት ፍላጻ እንዳይወጋን፡፡ የሱን መታሰቢያ ለማድረግ የተሰበሰብነውን ምእመናን ሁሉ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
7775Loading...
17
"ትሑትን ቢሹ የትሑታን ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የዋሃንን ቢሹ የየዋሃን አብነት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ደጉን ቢመኙ የበጎ ምንጭ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወዳጅ ቢሹ የማይከዳ ባልንጀራ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መጋቢ ቢሉ የማያልቅበት ባለፀጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማረፍ ቢሹ በክንዱ የሚያቅፍ በጀርባው የሚሽከም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መድኃኒት ቢሹ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡"
550Loading...
18
አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡ ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡ ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡ ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡ ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡ ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡ ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡ እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡ "ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው" መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 86
570Loading...
19
"አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡  የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ። የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ኑ! ያለንን በማካፈል በዓለ ትንሳኤን ከነዳያንና የአብነት ተማሪዎች ጋር #በወልድያ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ካቴድራል #ከፈለገ_ሰላም_ሰንበት_ትምህርት_ቤት አብረን እናክብር።             ለፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት                        ዳሽን ባንክ           የሂሳብ ቁጥር 5033012404001 ለበለጠ መረጃ፦ ➛ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋሁን- 09 13 23 10 26 ➛ ዶክተር ሰሎሞን በላይ - 09 16 03 35 43 ➛ ሐብታሙ እንግዳው -  09 38 36 01 75 ➛ ደርቤ ካሳ - 09 42 50 75 95
520Loading...
20
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን፡፡ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፡፡ አሜን፡፡ ሚያዝያ ዐሥራ ሁለት በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው፡፡ በዚህች ቀን ክብር ምስጋና ይግባውና ልዑል እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ወደነቢዩ ኤርምያስ ልኮታልና፡፡ ንጉሡ ሴዴቅያስ አሳሥሮበት ከነበረው ከዓዘቅተ ወህኒ ቤት አወጣው፡፡ የንጉሡ ባለሟል የሠራዊቱ አለቃ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አወጣው፡፡ ያንጊዜም ኤርምያስ የኢየሩሳሌምን ጥፋት አያሳይህ፤ በመማረክ የሚመጣውንም መከራና ፈተና አያድርስብህ ብሎ መረቀው፡፡ እንደተናገረውም ሆነለት፡፡ ስድሳ ስድስት ዘመን ተኛ፤ ወይንና በለስም ይዞ ነበር፡፡ የእስራኤል ልጆችም ከጼዋዌ እስኪመለሱ ድረስም አልጠወለጉም፤ አልደረቁም፡፡ ከወይኑ ከበለሱ ፍሬ አምጥቶ ለኤርምያስ ሰጠው፡፡ ስለዚህም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ በዐሥራ ሁለት ቀን እንድናከብር የቤተክርስትያን መምህራን አዝዘውናል፡፡ አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይኑር፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
8834Loading...
21
"ልጆቼ! ከእሳተ ገሃነም እንዴት ልንተርፍ(ልንድን) እንደሚገባን እንጂ እሳተ ገሃነም የት እንዳለ ለማወቅ እጅግ የምንደክም አንኹን፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
690Loading...
22
"ወዳጄ ሆይ! በጎ ነገር አግኝተህ እንደ ኾነ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ነገር ከአንተ ጋር ጸንቶ ይኖራል፡፡ በጎ ያልኾነ ነገር ደርሶብህ እንደ ኾነም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያም በጎ ያልኾነ ነገር ወደ በጎ ነገር ይቀየራል፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
730Loading...
23
" ኃጢአት መሥራት ማለት ለእግዚአብሔር ታማኝ አለመሆን በእርሱ ላይ ማመፅና ትእዛዛቱን መተላለፍ ማለት ነው " አቡነ ሺኖዳ
680Loading...
24
ልጆቼ! የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደሆነ የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም ታስሬ አስፈትታችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ታምሜ አድናችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ተርቤ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መዓድ ሳይሆን አንዲት ዳቦ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መጠጥ ሳይሆን አንዲት ቀዝቃዛ ኩባያ ውኃ አጠጥታችሁኛልና ነው የሚለን፡፡ በጣም የሚያቀለው ደግሞ እነዚህን ቀላል ትእዛዛት በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸው አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በቃሉ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ስለሚለን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን ነው፡፡ እንግዲያውስ ድሀ ስለሆንኩ እነዚህን ማድረግ አልችልም ብለን ራሳችን ሰነፎች የምናደርግ አንሁን፡፡ ሺህ ጊዜ ደሀ ብንሆን ሁለት ሳንቲም ከሰጠችው መበለት በላይ ድሀ ልንሆን አንችልምና፡፡ ስለዚህ ስንፍናን ከእኛ እናርቅ፡፡ ልጆቼ! እነዚህን በእርሱ እርዳታ ስላደርግንስ ምን እንደምንባል ትገነዘባላችሁን? “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን!” ካላደረግንስ? “እናንተ ርጉማን ከእኔ ዘንድ ሂዱ!” እንግዲያውስ ለእኛ ሳይሆን ለሰይጣንና ለመላእክቱ የተዘጋጀውን እሳት ከሚያገኘን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለእኛ የተዘጋጀውን መንግሥት እንወርስ ዘንድ ዛሬ አብዝተን ዘይት የምንገዛ እንሁን፡፡ እንደነዚያ ሰነፍ ደናግላን እዚያ መግዛት በማይቻልበት ቦታ ሄደን ከምንጠይቅ ዛሬ ሳይመሽብን የሚበቃንን ያህል ዘይት እንግዛ፡፡ ዘይቱ የሚገዛውስ የት ነው? የታመሙት ጋር፤ እስረኞች ጋር፤ ቁርና ሀሩር በሚፈራረቅባቸው ወንድሞቻችናነ እኅቶቻችን ጋር፡፡ ልጆቼ! እንደ ነዌ እዚህ ምድር ባለጸጎች ሆነን ያኔ ከምንለምን ዛሬ አልዓዛርን ልናስበው ይገባል፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
861Loading...
25
Media files
901Loading...
26
#ገብር_ኄር (የዐቢይ ጾም 6ኛ ሳምንት) የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ በዚህ ሳምንት የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብርኄርን የሚያወሳ ነው። ማለትም ስለ ታማኝ አገልጋይ ነው፡፡ የማቴ.25፥14-25 የሚነግረን ይህን ነው፦ “አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠው አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡ ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ “ገብርኄር ወምዕመን ዘበሁድ ምዕምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ” “አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ “አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ “ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ” አለው፡፡ “አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡ ኑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ኑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” አለ ማቴ. 25፥14-25፡፡ ባለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፡፡ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡ ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ መኑ ውእቱ ገብር ኄር ወምእመን ዘይረክቦ እግዚኡ በምግባረ ሠናይ ወይሠይሞ ዲበ ኲሉ ንዋዩ ካዕበ ይቤሎ እግዚአብሔር ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ ባእ ውስተ ፍሥሐሁ ለእግዚእከ፡፡ ትርጉም፦ ጌታው በመልካም ሥራ የሚያገኘው በሐብቱ ኹሉ ላይ የሚሾመው፤ የታመነ በጎ አገልጋይ ማን ነው? ዳግመኛም እግዚአብሔር አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለኾንህ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ይለዋል፡፡ #መልዕክታት 2ኛ ጢሞ.2÷1-15 "ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ) 1ኛ ጴጥ.5÷1-11 "እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡" (ተጨማሪ ያንብቡ) #ግብረ_ሐዋርያት የሐዋ.1÷6-8 "እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።" #ምስባክ መዝ. 39÷8 "ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡" ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ #ወንጌል ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡” (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ቅዳሴ ➛ ቅዳሴ ባስልዮስ
791Loading...
27
#በስድብ_ፈንታ_አመስግኑ ብዙ ጊዜ ስንሳደብ እና መጥፎ ቋንቋ ስንጠቀም “እኔ ይህን አለማድረግ አልችልም ልማዴ ነው" እንላለን፡፡ እናም ሲጎዱን አንድ ነገር መናገር ካለብንም፣ በስድብ ፈንታ ምስጋና መናገርን እራሳችንን እናስተምር። ነገር ግን፣ ሰው እያሰቃየኝ ዝም ማለት አልችልም ትላለህ፡፡ ከመናገርም አልከለክልህም፡፡ ሆኖም ከመሳደብ ይልቅ ምስጋናን ተናገር፡፡ ከመበሳጨት ይልቅ ምስጋናህን ግለጽ፡፡ ለጌታህ መናዘዝ ትችላለህ፡፡ በጸሎትህ ውስጥ ጩኽ፤ እንዲሁ መከራህን ያቀልልሃል፣ ፈታኙም ሰይጣን በምስጋናህ ውስጥ ይሸሻል፣ የእግዚአብሔርም እርዳታ ወዳንተ ይቀርባል። ከተሳደብክ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታ ትከለክላለህ፤ እናም ፈታኙ በአንተ ላይ እንዲበረታ ታደርጋለህ፤ በዚያም እራስህን የበለጠ በህመም ውስጥ ታስገባለህ፡፡ ብታመስግን ግን የክፉ መንፈስን ጥቃት ትቃወማለህ፡፡ ነገር ግን ምላስ ብዙውን ጊዜ በልማድ ኃይል አንዳንድ መጥፎ ቃላትን ከመናገር ወደኋላ ማለት አይችልም:: ከዚያም በምትወድቅበት ጊዜ ኹሉ ቃሉ ከመናገርህ በፊት ጥርሶችህን ጠብቀው ይዘጉ፡፡ ምላስህ የደም ጠብታ ብታፈስስ ይሻላታል ፤ ከስድብም በኋላ የማያቋርጥ ቅጣት ከምትቀበል በጊዜው ሥቃይን ብትታገሥ ይሻልሃልና፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ) @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
792Loading...
28
#ወደ_ትክክለኛው_መንገድ_መቅረብ የሰው ልጅ በሚመርጠው ምርጫ ወጥነት የለውም። አንድ ጊዜ በጣም ለጋስ እና ራስን መስዋእት እስከማድረግ ድረስ ይደርሳል፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያው ሰው በስግብግብነት እና በራስ ወዳድነት ሲወድቅ እናገኘዋለን፡፡ እግዚአብሔር የመምረጥ ነፃነትን ስለሰጠን፤ ይህንን የባህሪ እንከን ለማስተካከል እጁን አላስገባም። ይህ ማለት የሰው ልጅ በተፈጥሮው ጠባዩ የክርስቶስን ህጎች መከተል አይችልም ማለት ነውን? እርሱ ከሰበከው የፍቅር መንገድ ዘውትር ይርቃልን? መልሱ አዎም አይደለምም ነው፡፡ እኛ ራሳችንን እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የምንቆጥር ከራሳችን የኃጢአት ጠባይ እንርቃለን፡፡ ይህም የሆነው በትክክል ክርስቶስን ስለምናውቀው እና ፍጽምናውን ስለምንመለከት ነው፤ የእኛንም ደካማነት ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ በራሳችንና ፍፁም ንጹህ በሆነው በክርስቶስ መካከል ያለውን ንጽጽር ማየት በራሱ ምንኛ ህመምን ይፈጥራል፡፡ ፍፁም መልካም የሆነውን የክርስቶስን መንገድ እንከተል፤ ትክክለኛውም መንገድ እርሱ ነውና። ሁልጊዜ ከፍቅር መንገድ ለመውጣት እንገፋለን፣ ከቀን ወደ ቀን የተሳሳቱ ምርጫዎችን እናደርጋለን፡፡ ኾኖም “ከመንገዱ መራቅ” የለብንም፤ አቅጣጫው እስኪጠፋብንና መንገዱ ከአይናችን እስኪሰወር መራቅ የለብንም፡፡ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር መሆን ማለት፣ ሁልጊዜ፣ በየደቂቃው፣ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆን ማለት አይደለም፤ በዚያም ለመቀጠላችን ዋስትና አይሆንም፡፡ ይልቁንም የቁርጠኝነት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መጠን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመቅረብ እና ከተሳሳትን በኋላ ዳግም ለመመለስ የምንገባው ቃል ኪዳን ነው፡፡ ይህ በራሳችን ጥንካሬ ማከናወን የምንችለውን ያህል ነው፤ በእግዚአብሔር ቸርነትም ጉዟችን ቀና እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
692Loading...
29
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም፦"ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
723Loading...
30
#የትሕትና_ማደሪያ ወደ ክብር የሚወስደው መንገድ ትህትና ነው፡፡ ይህን በጎነት ከየት እናገኘዋለን? ትህትና ወደሚኖርበት ወደ መልካም ማደሪያ መሄድ ትፈልጋለህ? በዚያም በየደረጃቸው በሀብታቸው የታወቁ፤ በኹሉም የሕይወት ዘርፍ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን እናገኛለን፡፡ በሕይወታቸውም ላይ "ትህትና" የሚለውን ቃል በብዕርና በቀለም ይጽፋሉ፡፡ የተንቆጠቆጡ አለባበሶች፤ የተንቆጠቆጡ ቤቶች ከንቱነትን ይወልዳሉና ብዙውን ጊዜ ሰዎች በትዕቢት ወጥመድ ይወድቃሉ፡፡ ኾኖም በትህትና ውስጥ የሚኖሩት እነዚህ ሰዎች ምንም ያህል አገልጋዮች ቢኖሯቸውም፤ የራሳቸውን እሳት ያቀጣጥላሉ የራሳቸውን እንጨት ይፈልጣሉ፤ የራሳቸውን ምግብ ያዘጋጃሉ በግላቸውም እንግዶቻቸውን ያስተናግዳሉ፡፡ ከእነርሱ በታች ያሉትን በስድብ ከፍ ዝቅ አያደርጉም፤ ማንም ሌላውን አይገዛም፡፡ ኹሉም በአገልግሎት ላይ ይሳተፋሉ፡፡ እያንዳንዱም ሰው የእንግዶችን እግር ያጥባል እናም እኔ አጥባለሁ እኔ በማለት ጠብን ያነሳሉ፡፡ እግሩንም የሚያጥቡለት ስው ባርያም ሆነ ባለስልጣን ግድ አይሰጣቸውም፡ በእነርሱ ፊት ማንም ትልቅም፤ ትንሽም አይደለም፡፡ ራሱን ከንቱ እንደሆነ የሚቆጠር ሰውም ከባርያ ጋር እኩል መቆጠሩ አያስከፋውም፡፡ ባሮችም የተከበሩ እንግዶች የሚቀርብላቸው ተመሳሳይ አይነት ምግብ፤ ተመሳሳይ ማረፊያ ነው፤ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያም ይቀርባሉ፡፡ ታላቅነት የሚገኘው ትሑት በመሆን ነውና፡፡ “የእኔ” እና “ያንተ" የሚሉት ሃሳቦች ከንቱ ናቸው, ማለቂያ የሌለውን የግጭት ምንጭ ይፈጥራሉ፡፡ እነርሱን የሚያስተሳስራቸው አንድ መንፈስ ኖሮ ሳለ ስለምን አገልጋዮችና ጌቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መታደማቸው ያስገርመናል? በዚህ ድህነት እና ባለጠግነት ስልጣን የላቸውም፤ ዝናና ውርደትም የለም፡፡ ስለዚህም ስንፍናና ከንቱ ውዳሴ በመካከላቸው ቦታ አያገኙም፡፡ አብርሃምም በከነዓናውያን ፊት ራሱን ዝቅ አደረገ፣ ከአፈርና ከአመድ በላይ እንዳልሆነ ያውቅ ነበር። ዳዊት ምን ያህል እንኳ የታላቅ ግዛት ንጉስ ቢሆንም ራሱን ከትል በታች ዝቅ አድርጎ ገለጸ። ታዲያ ትሑት ላለመሆናችን ምን ሰበብ ልንሰጥ እንችላለን? ከአብርሃምና ከዳዊትስ በምን ብንበልጥ ነው? (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
781Loading...
31
አንድ ሰው መፍትሔ የሌለው የሚመስል መከራ ሊገጥመው ይችላል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ መከራው የገጠመው ጥቂት ኃጢአቶችን ስለ ፈጸመ መሆኑን ከማስጠንቀቂያ ጋር ይነግረዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ቃሉ ንስሓ ከገባህ መከራው ፍጻሜ ያገኛል እያለ ውስጡን ሲመክረው ይሰማል። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ንስሓው ሲል ለሰውየው ይራራለታል። የእግዚአብሔር ድምፅ አንድ ሰው ሲታመም ወይም እርሱ የሚወደው ሌላ ሰው ሲታመም ሊመጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ እንዲጸልይ ወይም ስእለት እንዲሳል የሚመክረውን ድምፅ ከውስጡ ይሰማል ይህ ድምፅ የእግዚአብሔር ድምፅ ነው። የዮሴፍ ወድሞች እህል ሊገዙ ወደ ግብጽ ከወረዱ በኋላ በዚያ ችግር ሲገጥማቸው እርስ በእርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋግረው ነበር፦ "በእውነት ወድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።"/ዘፍ 42፥21/ ከዚህ በኋላ ለዮሴፍ እንዲህ ብለውታል፦ "ለጌታዬ ምን እንመልሳለን? ምንስ እንናገራለን? ወይስ በምን እንነጻለን? እግዚአብሔር የባሪያዎችህን ኃጢአት ገለጠ"/ዘፍ 44፥16/ ኃጢአታቸውን እንዲያስታውሱ ኋላም እንዲገሰጹ ያደረጋቸው የእግዚአብሔር ድምፅ ነው። ነቢዩ ዳዊት የጌራ ልጅ በሆነው በሳሚ ሲሰደብ የእግዚአብሔር ድምፅ ውስጡ ስላለፈ ኃጢአቱ እየወቀሰው መሆኑን አዳምጧል። ስለሆነም በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች "እግዚአብሔር ዳዊትን ስደበው ብሎታልና ይርገመኝ።" /2ኛ ሳሙ.16፥10/ በማለት በግልጽ ተናግሯል። ረሀብና የመሬት መንቀጥቀጥ በዓለም ሲደርስ የእግዚአብሔር ድምፅ በመላው ዓለም ውስጥ ይሰማል። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚናገረን "ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ።" /ሚል 3፥7/ እያለ ነው። ይህ ድምፅ በረሀቡ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት ለደረሰባቸው ሀገሮች የሚሆን የእርዳታ ጥሪ ለማሰማት ወይም ሌሎቹ ከእነርሱ ትምህርት በመውሰድ ንስሓ እንዲገቡ ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኝት ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው። ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት መከራ ውስጥ ስትገቡ ከውስጣችሁ ያለውን የእግዚአብሔር ድምፅ አድምጡት እርሱ ለእናንተ ሊነግራችሁ የሚወደው ምን እንደ ሆነ ታውቃላችሁና። #አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
501Loading...
32
#እግዚአብሔርን_መፍራት ከፍርሃታችን የሚመጡትን ጥቅሞች ታያላችሁ? ፍርሃት ባይጠቅም ኖሮ አባቶች ለልጆቻቸው ሞግዚቶችን አይቀጥሩም፤ ሕግ አውጪዎችም በከተሞች ላይ ዳኞችን አይሾሙም ነበር። ከገሃነም የበለጠ የሚያስፈራስ ምን አለ? እናም ገሃነምን ከመፍራት የበለጠ የሚጠቅም ነገር የለም:: ገሃነምን መፍራት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይመራናልና፡፡ ይህ ፍርሃት ባለበት ምቀኝነት ቦታ የለውም፤ ይህ ፍርሃት ባለበት የገንዘብ ፍቅር ቦታ የለውም፤ ቁጣ ይጠፋል፣ ክፉ ምኞቶች ይወገዳሉ፡፡ አንድ ዘብ ሁልጊዜ ነቅቶ በሚጠብቅበት ቤት ውስጥ ሌባ፣ ዘራፊ ወይም ክፉ አድራጊ ሊመጣ እንደማይችል ኹሉ ፍርሃት አዕምሯችንን ሲይዝ፣ ልቅ ምኞቶች በቀላሉ አያጠቁንም፡፡ ይልቁንም ሸሽተው በየአቅጣጫው፣ በፍርሀት ምክንያት ይባረራሉ፡፡ ነገር ግን ፍርሃት ማባረር ብቻ አይደለም ጥቅሙ፤ ክፉ ፍላጎቶቻችንን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን በጎነት ወደ ነፍሳችን ለማምጣትም ይጠቅማል፡፡ ፍርሃት ባለበት ለጋስ መሆን አለ፤ የጸሎት ብርታት፣ ትኩስ የሚደጋገም እንባ እና ለንስሃ የነቃች ነፍስ አለች። ኃጢአትን የሚሸፍን በጎነትን የሚያብበው በማያቋርጥ የፍርሃት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ነው:: ስለዚህ በፍርሃት የማይኖር ሰው ልቡ ደንድኖ የሰይጣን ባርያ እንደሚሆን ኹሉ፣ በፍርሃት የሚኖር ሰው በማያውቀው ጎዳና እንደማይጓዝ ኹሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት በትክክለኛው የጥበብ መንገድ ይወስደናል፡፡ (#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ ገጽ 20 #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ) @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
762Loading...
33
Media files
550Loading...
34
#ጾሙን_አጋመስነው_አትበሉ ብዙ ሰዎች ደስ ተሰኝተውና እርስ በእርሳቸው “ግማሹን ጾም ፈጽመናል፤ የጾሙ እኩሌታ አለፈ” ሲባባሉ ተመልክቻለሁ፡፡ እኔ ግን እነዚህ ሰዎች በዚሁ ምክንያት ደስ ሊላቸው እንደማይገባ እመክራቸዋለሁ፤ የጾሙ እኩሌታ ማለፉን ሳይኾን የኃጢአታቸው እኩሌታ መኼዱን [መወገዱን] ያስቡ፤ እንደዚያ ከኾነም ሐሴት ያድርጉ፡፡ ደስ ልንሰኝበት የተገባው ነገር ይኼ ነውና፡፡ ሊታይ የሚገባው ይኼ ነው፤ ጥንቱም እነዚህን ኹሉ ነገሮች የምናከናውናቸው ስሕተቶቻችንን እንድናስተካክል፣ ጾሙ ሲጀምር እንደ ነበርንበት ሳይኾን እንድንነጻበት፣ ክፉ ልማዶቻችንን ወደ ጎን አድርገን የተቀደሰውን በዓል [በዓለ ትንሣኤን] እንድናከብር ነውና፡፡ እንደዚህ ካልኾነ ግን ጾሙን መጨረሳችን በራሱ ለእኛ ታላቅ ጉዳትን ይዞ ከመምጣት ውጪ ሌላ ምንም ረብ ጥቅም አይሰጠንም፡፡ ስለዚህ ብዙ ጊዜ መጾማችንን ብቻ አንመልከት፤ ይህ ምንም ትልቅ ነገር አይደለምና፤ ይልቁንስ በዚህ ጾም ራሳችንን አሻሽለን እንደ ኾነ፣ ጾሙ ከተፈታ በኋላም የዚሁ ፍሬ ጎምርቶ ይታይብን እንደ ኾነ ሐሴት እናድርግ፡፡ የክረምት ጥቅሙ ይበልጥ የሚታወቀው ወራቱ ካለፈ በኋላ ነውና፡፡የዚያን ጊዜ የአበባው ማበብ፣ የአዝመራው ማፍራት፣ ሌሎች ዕፅዋትም በቅጠላቸውና በፍሬያቸው በወርሐ ክረምት ያገኙትን ጥቅም ግልጽ አድርገው ይናገራሉና! በእኛም ዘንድ ልክ እንደዚህ ይኹን፡፡ በወርሐ ክረምቱ በብዛትም በዓይነትም የተለያየ ዓይነት የዝናብ ጠብታዎችን ተቀብለናል፤ ብዙ ተከታታይ ትምህርቶችን ተምረናል፤ መንፈሳዊ አዝርእት ተዘርተዉብናል፤ የቅምጥልነት እሾኽም ቈርጠን ጥለናል፡፡ ስለዚህ ጾሙ በተፈታ ጊዜ የጾሙ ፍሬ ይከብበን ዘንድ፣ ከጾሙ የሰበሰብናቸውን መልካም ነገሮችም ጾሙን ራሱን እናስታውሰው ዘንድ የሰማነውን ነገር አጽንተን በመያዝ እንትጋ፡፡ (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #በእንተ_ሐውልታት 18፥1-2) @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
710Loading...
35
#ደብረ_ዘይት (የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት) የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡ እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት (ማቴ. 24፥3፣ ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7) #አመጣጡስ_እንዴት_ነው? ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበብ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርሃ መጋቢት ዕለት እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው የሚያውቀው የለም ይባል የለምን? ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን፤ ብዙ የመጋቢት ወር፤ ብዙ የእሑድ ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡ ሞት ለማን አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ. 3፥19 በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፏን ነቅለው ደንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደ ብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መለኸት ይነፋል፡፡ 1ኛ መቃ. 9፥8 ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ (ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት) ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደጉነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡ ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ.13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ቡሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለ ክፉ ሥራቸው (ከኔ ሂዱ) ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ፤ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ ደረት ይደቃሉ እንባቸው ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ለቅሶ የማይጠቅም ሐዘን ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡ #ምልክቱስ_ምንድን_ነው? ብለው ጌታን ሲጠይቁ ‹‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል፤ ረሃብም ቸነፈርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ.... (ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡....) #የዕለቱ_ምንባባት 1ኛ ተሰሎንቄ 4÷13-ፍጻ፡- ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡..... 2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡- አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡..... ሐዋ. 24÷1-21፡- በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡..... (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ምስባክ መዝ. 49÷2 እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡ ትርጉም፦ እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡ አምላካችንም ዝም እይልም፤ እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ #የዕለቱ_ወንጌል ማቴ. 24÷1-25፡- ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡.....” (ተጨማሪ ያንብቡ) #የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ ምንጭ፡- (የማቴዎስ ወንጌል 24፥1 ትርጓሜ፣ መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣ ግጻዌ) @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
640Loading...
36
መጋቢት - 27 መድኃኔዓለም መጋቢት ሃያ ሰባት በዚችም ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ ተሰቀለ። ፈጣሪዋ በእንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳትለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ስለ ዓለም ሁሉ ድኅነት በሥጋ ተሰቅሏልና ሞቱን በአንክሮ እናዘክር ዘንድ የልቡናችን ዐይን ወደ ቀራንዮ እናንሳ! እነሆ ክፉዎች አይሁድ ሰይጣን ልባቸውን አስቶታልና እንደ ወረንጦና እንደ ወስፌ እንደመርፌም ያለ 300 እሾህ ያለው ስረወጽ አድርገው አክሊል ሠርተው ከፍላት አግብተው በጉጠት አንስተው ‹ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ነህ ዘውድ ይገባሃል› ብለው በራሱ ላይ ደፉበት፡፡ ለአክሊለ ሦኩም 73 ስቁረት ነበረው፡፡ እራሳቸው እንደ መሮ፣ ወርዳቸው እንደ ሞረድ 4 ማዕዘን አሠርተው ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር፣ ስለታቸውን እንደ ወስፌ አድርገው 73 ችንካር ሠርተው በ73ቱ ስቁረት አግብተው በጌታችን በራሱ ላይ ቢመቱበት ሥጋ ለሥጋ ገብቶ መሐል ልቡን ወጋው፡፡ አክሊለ ሦኩን በራሱ ላይ አድርገው ሲያበቁ ከቤት ወደ አደባባይ እያመላለሱ ‹‹ንጉሥ ሆይ!...›› እያሉ ምራቃቸውን እየተፉበት ተዘባበቱበት፡፡ መስቀል አሸክመው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ እያዳፉ ሲወስዱት 136 ጊዜ በምድር ላይ ጣሉት፡፡ ከኋላ ያሉት ‹‹ፍጠን›› እያሉ ገፍትረው ይጥሉታል፣ ከፊት ያሉት ደግሞ ‹‹ምን ያስቸኩልሃል?›› እያሉ መልሰው ገፍትረው ይጥሉታል፡፡ ከዚህ በኋላ ክፉዎች አይሁድ ቁመታቸውን ክንድ ከስንዝር ስለታቸው ደግሞ እንደ ወስፌ የሆኑ 5 ችንካሮችን ሠርተው ሳዶር በሚባለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ በአላዶር ግራ እጁን፣ በዳናት ሁለት እግሮቹን፣ በአዴራ መሐል ልቡንና በሮዳስ ደረቱን ቸንክረው የአዳም ራስ ቅል ባለበት ቀራኒዮ አደባባይ ላይ ሰቅለውታል፡፡ ክፉዎች አይሁዶች መድኃኒታችንን በሁለት ግንዶች መካከል አድርገው 65 ጊዜ ከግንዱ ጋር አጋጩት፡፡ ቀያፋ በሚመረምረው ጊዜ ጌታችን ‹‹አምላክነቴን አንተው ራስህ ተናገርኽ›› ቢለው አይሁድ በእጃቸው ሲመቱት እጃቸውን ቢያማቸው ድንጋይ ጨብጠው 120 ጊዜ ፊቱን ጸፉት፡፡ አይሁድ ወደ ጲላጦስ ዘንድ ሲወስዱት ‹‹ምናልባት ጲላጦስ ባይፈርድበት እንኳ እንዳይቆጨን›› ብለው 305 ጊዜ በሽመል ደብድበውታል፡፡ በአምላክነቱ ቻለው እንጂ የአንዱ ምት ብቻ በገደለው ነበር፡፡ ሰይጣን ልባቸውን ለክፋት ያስጨከናቸው ክፉዎች አይሁድ በጲላጦስ አደባባይ የጌታችንን ፂሙን 80 ጊዜ ነጭተውታል፡፡ ጲላጦስ እንደ ሕጋቸው 41 ብቻ ገርፈው እንዲለቁት ቢያዝም ክፉዎች አይሁድ ግን ጌታችንን ሲገርፉት ‹‹አሠቃቂ ግርፋቱን አይተን ልባችን እንዳይራራ›› ብለው ሰንጠረዥ ገበጣ ሰርተው ሲጫወቱ አንዱ ተነስቶ እስከ 60 እና 70 ድረስ ይገርፍና ሲደክመው ‹‹ቆጠራችሁን?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡ ‹‹አልቆጠርንም›› ሲሉት ከድካሙ የተነሣ ‹‹እኔው ልግረፍ እንደገና እኔው ልቁጠር›› ብሎ ትቶት ሲቀመጥ ሌላኛው ይነሣና እንደዛኛው ሁሉ በተራው 60 እና 70 ይገርፈዋል፡፡ ሁሉም እንዲህ እያሳሳቱ የራሳቸውን ሕግ እየተላለፉ አይሁድ ጌታችንን ሥጋው አልቆ አጥንቱ እንደበረዶ ነጭ ሆኖ እስኪታይ ድረስ 6666 ጊዜ ጽኑ ግርፋትን ገረፉት፡፡ በእነዚህ ሁሉ ግርፋቱ ወቅት 366 ጊዜ ሥጋው ተቆርሶ መሬት ላይ ወድቋል፡፡ የመድኃኔዓለም ወገኖች ሆይ! የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ መሆኑንና የትዕግሥቱን ብዛት አይተን እናደንቅ ዘንድ ከመጻሕፍት ጠቅሰን እንነግራችኋለን፡፡ አይሁድ ጌታችን አብርሃም ሳይወለድ በፊት እርሱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን አምላክ መሆኑን ቢነግራቸው ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፡፡ እሱ ግን ጊዜው ገና ነበርና ተሰውሮአቸው በመካከላቸው አልፎ ሲሄድ በፍጹም አላዩትም ነበር፡፡ በቅዱስ ወንጌል ላይ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- ‹‹አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው። አይሁድም:- ገና ሃምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት። ኢየሱስም:- እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ ›› ዳግመኛም በዮሐንስ ወንጌል ላይ እንደተጻፈው አይሁድ መድኃኔዓለምን ሊይዙት የጦር መሣሪያቸውን ሰብስበው ወደ ጌቴሴማኒ በመጡ ጊዜ ‹‹ማንን ትፈለጋላችሁ?›› ቢላቸው ‹‹የናዝሬቱን ኢየሱስን እንፈልጋለን›› ሲሉት ‹‹እኔ ነኝ›› ቢላቸው ከአንደበቱ የወጣውን መለኮታዊ ቃል ብቻ መቋቋም አቅቷቸው መሬት ላይ ወድቀው ተዘርረዋል፡፡ (ዮሐ.18 ) እናም የጌታችን ሞቱ በፍጹም ፈቃዱ ባይሆን ኖሮ በጌቴሴማኒ ሊይዙት የመጡት ክፉዎች አይሁድን እንደመጀመሪያው ሁሉ በተሠወራቸው ነበር አሊያም ከአንደበቱ በሚወጣው አምላካዊ ቃሉ ብቻ ባጠፋቸው ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን ጌታችን ወደዚህች ምድር የመጣበትን ዓላማ ይፈጽም ዘንድ እንዲገድሉት በፈቃዱ ራሱን አሳልፎ ቢሰጣቸው ያን ሁሉ እጅግ አሠቃቂ መከራ አደረሱበትና ለመስቀል ሞት አበቁት፡፡ ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል! ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው!!! ለዚህ ባሕርይው አንክሮ ይገባል፡፡ በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ሁላችሁም ኑ መድኃኒታችን ሞቷልና ፍጥረታት ሁሉ አልቅሱ መከራን የተቀበለ ጌታችን ሞቷልና። የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ቀበሩት በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነስቷል። ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡ የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን። አሜን @KaleEgziabeher
652Loading...
37
Media files
501Loading...
38
#የጌታ_ስቅለት_በአበው "አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ “እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ ‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ ‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ ‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ›› #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም ‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ
962Loading...
39
"ሂድና ውደዳት!" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) በአንድ ወቅት አንድ ሰው ሚስቱ እንድትወደው ብዙ ነገር አድርጎ ስላልተሳካለት ሚስቱም ስላልወደደችው ተበሳጭቶ ወደሰባኪው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄዳል፡፡ "ሚስቴ እንድትወደኝ ብዙ ለፋሁ ፤ ያላደረኩት ነገር የለም ፤ምንም ልትወደኝ አልቻለችም፡፡ እንድትወደኝ ማድረግ የምችለው በምን መንገድ ነው?" ሲል በሀዘን ተሰብሮ ይጠይቀውና የሚነገረውን ጥበባዊ መንገድ በጥንቃቄ ለመረዳት እዝነልቦናውን አዘጋጅቶ የአባቱን ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ የአንደበቱን ጥኡም ቃል ይጠባበቃል፡፡ ቅ/ዮሐንስ ግን የነገሩት በአጭሩ በሁለት ቃል ብቻ የተዋቀረ ነበር፡፡ "ሂድና ውደዳት!" ሰውየው 'ያልኩትን አልተረዳኝ ይሆን እንዴ?' እያለ እያሰበ ጥያቄውን ደግሞ አቀረበ። "ሚስቴ አልወደኝ አለች ምንም ባደርግ ልትወደኝ አልቻለችም ነው ያልኩት" አለ በድጋሜ፡፡ "ሂድና ውደዳት" አለው ሰባኪው በድጋሜ፡፡ አሁንም ለሶስተኛጊዜ ሰውየው "ልትወደኝ የሚገባት ሚስቴ አልወደደችኝም ነው ያልኩዎትኮ!" አለ፡፡ ሰባኪውም መልሶ "ሂድና ውደዳት!" አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው እርሱ እንደሚወዳት ለመናገር 'እኔማ...' ብሎ ጀምሮ ራሱን መፈተሽ ጀመረ፡፡ እሱ ውስጥ ያለው፣ እርሱ የሚወደው፣ የእርሱ ፍላጎት የእርሱን የራሱን በእርሷ መወደድ እንጅ እርሷን መውደድ አልነበረም፡፡ ጊዜውን ለመወደድ በመጣር ብቻ አሳልፎታል፤ ጥረቱ ሁሉ እንድትወደው እንጅ እንዲወዳት አልነበረም፡፡ አዘነ፡፡ እርሷን መውደድ ሲገባው ራሱን በርሷ ለማስወደድ ሲጥር ኖሯል፤ አልተሳካለትም፡፡ ፍቅር የሚመጣው በራሱ በፍቅር እንጅ በሌላው ሁሉ ጥረት አይደለም፡፡ በሌላ ጥረት የሚመጣ ሰው ሰራሽ "ፍቅር" ካለ ግን ፍቅሩ ሀሰተኛ ነው፡፡ ራስን ከመውደድ አልፈን ራስን ወደማስወደድ ከመሄድ ይልቅ ሌላውን በመውደድ መወደድን አናጣውም፤ ፍቅር ሌላውን የሚወድ ከሆነ ፍቅርንማ እንደምን አይወድ! እርሷን ስትወዳት ፍቅሯን ታገኛለህ እንጅ ፍቅሯን ያለፍቅርህ አትሞክረው! አንዳንዶቻችን እኔ ላደረኩት ነገር ለምን አልተደነቅሁም ለምንስ አልተወደድኩም እንላለን። እንደዚህ ካልን ያደረግነውን ላደረግንለት ሳይሆን ለራሳችን ነው ማለት ነው ያደረግነው፤ ይህ ደግሞ የፍቅር ባህሪ አይደለም፡፡ እኛ ለሌሎች የሌለንን ፍቅርም ሌሎች ጋ ወደኛ መጠበቅ የለብንም፡፡ ለባለቤቴ ባደረኩላት ነገር ከእርሷ ምስጋናን የምሻ ከሆነና ካልተመሰገንኩ ከከፋኝ እኔ ከፍቅር የነፃሁ ምስኪን ነኝ፡፡ በርግጥ ሚስቴ ደስ ስትሰኝ ማየት ሊያስደስተኝ ይገባል፤ ይህ ማለት ግን እንደዋጋ አድርጌ ልወስደው ሳይሆን መደሰቷን ስለምመርጥላት ስለእርሷ ደስታ ስል ነው፡፡ ስለእኔ በደስታዋ መደሰት ያይደለ፡፡ "ሂድና ውደዳት!" የሁልጊዜም መርሃችን ልትሆን ይገባል፡፡ እንድትወደን ሳይሆን እንድንወዳት ስንወዳት የምር ትወደናለች፡፡ ስንወድ ከተወዳጁ በምንጠብቀው ነገር መመስረት የለብንም የፍቅራችን መሰረት መመስረት ያለበት ፍቅራችን ላይ እንጅ በሚጠበቅ በሌላ ፍቅርም ሆነ ሌላመሰረት ላይ መሆን የለበትም፡፡ አምላክ እኛን ስለወደድነው አይደለም የወደደን፤ በራሱ ፍቅር ተመስርቶ ወደደን እንጅ፡፡ እኛም በራሳችን ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ወይም ስለማይናድ በራሱ ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ይገባል፡፡ ሰው ላይ ግን መመስረቻው የሰው ፍቅር አይደለም፤ አያስተማምንም፡፡ በራስ ፍቅር መሠረት ላይ የተተከለች ፍቅር በራስ ይዞታ ላይ እንደተሰራች ቤት ናት፡፡ ማንም መጥቶ አያፈርሳትም፡፡ ወዳኝ ከምንዋደድ ወድጃት ብንዋደድ ይሻለኛል፡፡ መሰረቱን ራሴ ላይ ራሴ ብይዘው!
810Loading...
40
ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ከስድብ፣ ከውሸት፣ ከማታለል፣ ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም
772Loading...
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ (ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ) "አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት። ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት። ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።  ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። "የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት? ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም። እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን። #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
Show all...