cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ወላዲተ አምላክ

Advertising posts
263
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰው ሆይ! ጻድቅ መሆንን ትወዳለህን? አዎን ትለኝ እንደሆነ፥ እንግዲያውስ ለራስህ ንፉግ ለሌላው ግን ቸር ሁን፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ @Wedasa
Show all...
እኔ አባታችሁና መምህራችሁ ነኝ፥ ሁላችሁ ልጆቼ ትእዛዜን አዳምጡ፤ በቅድስት ሥላሴ ማመንን እንድትከተሉና እንድትጸኑ እነግራችኋለሁና፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ እርስ በእርሳችሁ በእውነተኛ ፍቅር ትዋደዱ ዘንድ እለምናችኋለሁ። የተወደዳችሁ ልጆቼ በፍጹም ሰብአዊነት መልካምን አንድታደርጉ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ ዓለም እንድታታልላችሁ አትፍቀዱላት፤ በእግዚአብሔር አገልግሎት ዳተኞችና ቸልተኞች አትሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። የተወደዳችሁ ልጆቼ ያለማቋረጥ እና ያለ መታከት እንድትጸልዩ እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ መለያየትን ከሚያመጣ ንግግር አንደበታችሁን እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ። የተወደዳችሁ ልጆቼ የተጠመቃችሁባትን ቅድስቲቱን ጥምቀት እንድትጠብቋት እለምናችኋለሁ፤ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሰውነታችሁን ለጌታ ንጹሕ አድርጋችሁ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ። ልጆቼ መብራታችሁ ፈጽሞ እንዲጠፋ አትፍቀዱ ይልቅስ ብርሃንን እንዲሰጥ እንድታደርጉት እለምናችኋለሁ፤ ልጆቼ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ትእዛዝ እንድትጠብቁ እለምናችኋለሁ። ልጆቼ እግዚአብሔርን መፍራት ከእናንተ ጋር እንዲሆን እለምናችኋለሁ፤ የነገርኳችሁን ሁሉ ከጠበቃችሁ የእባቡንና የዘንዶውን ራስ ትቀጠቅጣላችሁ፤ ያልኋችሁን ካደረጋችሁ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ ብርሃናዊያን ኪሩቤል ይጠብቋችኋል፡፡ #ብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ @Wedasa
Show all...
"ክርስትና የሚጀምረው ከተግባር እንጂ ከወሬ አይደለም፡፡ ሕይወታችን በጥቅስ ተገንዞ በጥቅስ የተቀበረ ከሕይወትና ከሥራ የተለየ እንዲሆን አንፍቀድለት፡፡" ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡" አንጋረ ፈላስፋ "ራስህን ለማየት ወደ መስታወት ብትመለከት ውበትህን ወይም ጉድለትህን ያሳይሃል፡፡ ምንም ነገር እንዳታይ ታደርግ ዘንድ ከመስታወቱ መሰወር አትችልም፡፡ ማንም ሊያመልጥበት በማይችለው በፍርድ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡" አንጋረ ፈላስፋ "የአንጥረኛ ዕቃ በየቀኑ በተመታ ቁጥር የበለጠ ጽሩይ እየሆነ እንደሚሄደዉ ሁሉ ሰውነቱን ለማድከም ራሱን የሚያስገዛ ሰዉም እንዲሁ ነዉ፡፡ በየቀኑ እየተማረ፣ እየጠራ እየነጻ ከጠላት ስውር ወጥመድ እየተጠበቀ ይሄዳል፡፡" አንጋረ ፈላስፋ "ሀብትን ብታከማች ያንተ አይደለም፡፡ ብትመፀውተው ግን ታከማቸዋለህ፡፡" ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ "ስለ ወንድሙ መዳን የማይደክም ድኗል ብዬ አላምንም፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እግዚአብሔር አንድን የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ ሊሰጥህ ቢወድ ፀጋውን ልትጠብቀው ከምትችለው ከትህትና ጋር ይሰጥህ ዘንድ ለምነው አለበለዚያ ግን ከአንተ እንዲያርቀው ጠይቅ፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እዉነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፡፡ እውነተኛ ትህትና ትሩፋትን መሥራት ነዉ፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ስለ ሌሎች ሰዎች ያለማቋረጥ ፀልዩ፡፡ወደ እግዚአብሔር ይደርሱ ዘንድ የንስሐ እድል አላቸውና፡፡ ለእነርሱ ነቀፋ እናንተ ምላሻችሁ ፀሎት ይሁን፡፡" ቅዱስ አግናጥዮስ @Wedasa
Show all...
"የወንድምህን ኃጢአት መሸፈንና የእርሱን ኃጢአት እንደራስህ አድርግህ በእርሱ ፋንታ መሞት ካልቻልክ ቢያንስ ስለ ኃጢአቱ አትፍረድበት።›› ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Wedasa
Show all...
#ኢየሱስ_ክርስቶስ የማይጠልቅ #ጸሐይ ነው፡፡ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ @Wedasa
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ❖ ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች። እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡ ❖ እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡ ❖ ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡ ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡ ❖ የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡ ❖ ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡ ❖ ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እእንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም። ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች። አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡ ❖ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨ ❖ ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦ ❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡- “በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ” (በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል)  በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡ ❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦ “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡ (ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨ ❖ እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨ ❖ “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ” (በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ)  ይላል @Wedasa
Show all...
በአካለ ሥጋ የሞተን ሰው መመለስ እንደማንችል እያወቅን ከልባችን የምናለቅስ ከኾነ፥ የመዳን ተስፋ ያለውንና በነፍሱ ለሞተ (ለኃጢአተኛ) ሰው አለማልቀሳችን እንደ ምን ያለ ስንፍና ነው? @Wedasa
Show all...
ወርኃ ጽጌ - (ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡ በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡ የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡ @Wedasa
Show all...
አባቶቻችን እንዲህ አሉ.... "መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም" ቅዱስ ባስልዮስ "በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ "ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ "የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው" ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ "እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD) "ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD) ‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ "ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡ የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ @Wedasa
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.