cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሥርአተ ተዋህዶ✅

ስለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አናውቅበታለን እንማማራለን ! ሼር በማረግ ተባበሩን .! ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች መዝሙሮች ምክረ አበው ትምህርቶች እና ሁሉም አለ። @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል @Ortodox1221 ለማንኛውም አስተያየት @Dengl_mariyam21 @Sreatetewahdoobot እናመሰግናለን !

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
489
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🌻ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው በሰንበተ ክርስቲያን እሑድ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና ሰባተኛ ክፍል።🌻 ጸጋን የተመላሽ ኾይ ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ለአንቺ ይገባሻል። አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ።ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኚ ነሽ። ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን። እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። 🌿🌹ቅድስት ሆይ ለምኝልን🌿
Show all...
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵 ሥርዓተ ማኅሌት ዘሐምሌ ጴጥሮስ ወጳውሎስ "ሐምሌ ፭" 🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵 ስቡህ @seratebetekrstiyan ሥርዓተ ነግሥ:- ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለቃልክሙ መታሬ እሳት ነዳዲ: ሥሉስ ቅዱስ ንዋያተ ዕፁብ ነጋዲ: አመ በንስሐ ተወልዱ እምጸጋክሙ ወላዲ: ተወፈየ መርኆ ሰማይ የማነ #ጴጥሮስ ከሐዲ: ወመምህረ ወንጌል ኮነ ጳውሎስ ሰዳዲ። ዚቅ ጸጋ ዘአብ ኂሩት ዘወልድ: ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ: ተውህቦሙ ለሐዋርያት። @seratebetekrstiyan ነግሥ ሰላም ለመልክዕክሙ እመልክዐ አዳም ዘተቶስሐ: እግዚአብሔር መሐሪ ዘኮነክሙ መርሐ: ፲ወ፪ እለ ሰበክሙ ቃለ ንስሐ: ሥረዩ ኃጢአትየ ወጌጋይየ ብዙኀ: በእንተ ማርያም ድንግል በህሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ። ዚቅ ሐዋርያተ ሰላም ክቡራነ ስም: ሥረዩ ኃጢአተ ዓለም: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ወበእንተ ድንግል እም። መልክዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰላም ለመቃብሪከ በመካነ ሐዋዝ ሃሌሉያ፡ ወለትንሣኤከ ድኅረ ዘይከውን በዕለተ ምርያ፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሞተከ ታብዕል ኢትዮጵያ፡ ለጴጥሮስ በዓለ መርኆ ወለጳውሎስ ሐዋርያ፡ ከመ ተዝካሮሙ ታብዕል ሮምያ። ዚቅ ንግበር ተዝካሮሙ ለእለ ኃረዮሙ ዓጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለዝክረ ስምክሙ ዘአልባስጥሮስ አፈው: ወለሥዕርትክሙ ጸሊም ዘድላሌሁ ፍትው: ምቱረ ክሣድ ጳውሎስ ወጴጥሮስ ቅንው: ተራወጸ ውስተ ልብየ ምስል መዓዛሁ ቅድው: ደመ ስምክሙ ሐዋርያ ዘኅብሩ ከዋው። ዚቅ ሃሌ ሉያ: ከዋው እገሪሆሙ: ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ: ዘእግዚአብሔር ፈነዎ: ቃለ እግዚአብሔር ይነግር። አመላለስ ሃሌ ሉያ/፪/ ከዋው እገሪሆሙ/፪/ @seratebetekrstiyan ወረብ ከዋው እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ዜና ሠናየ ለእለ ይዜንዉ/፪/ ዘእግዚአብሔር ፈነዎ ይነግር ቃለ እግዚአብሔር/፪/ @seratebetekrstiyan መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለአዕዛኒክሙ ለሰሚዓ ወንጌል ዘተሰብሐ: ወለመላትሒክሙ ቀይሐት እምነ ሮማን ዘቄሃ: መሥዋዕተ አምልኮት ኩኑ ወዘመሃይምናን ምክሐ: ደምከ ጴጥሮስ ወልደ ዮና በጽዋዓ መስቀል ተቀድሐ: ወደመ ጳውሎስ ሐዋርያ ሰማያተ ጸርሐ። @seratebetekrstiyan ዚቅ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም እንተ ትቀትሎሙ ለነቢያቲሃ: ወትዌግሮሙ ለሐዋርያቲሃ: ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ: እምደመ ጳውሎስ ሐዋርያ: እስከ ደመ ጴጥሮስ ወልደ ዮና። ዓዲ እግዚአብሔር : እንተ ተሰመይኪ ገነተ: ደሞሙ ለሰማዕታትኪ ውኅዘ ከመ ማይ: ድምፀ ነጎድጓዶሙ በጽሐ እስከ ሰማይ። ወረብ ሚ መጠን ዘተክዕወ ዲቤሃ ለኢየሩሳሌም/፪/ እምደመ ጳውሎስ ሐዋርያ እስከ ደመ ጴጥሮስ ወልደ/፪/ መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ለዘባናቲክሙ በምኲራባት እለ ተቀሥፋ: ወለእንግድዓክሙ ዘሰፍሐ መልዕልተ ጠበብት ወፈላስፋ: በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተጸፍአ ቅድመ ቀያፋ: ሀበኒ ጴጥሮስ መስቀለከ ይኲነኒ ተስፋ: ወጳውሎስ ዉቅየተከ እንተ ደም ለከፋ። @seratebetekrstiyan ዚቅ እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ: ዘተሠውጠ ላዕለ ኲሎሙ ሐዋርያት: በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት: ይኲነኒ አክሊለ መዊዕ ወተስፋ: በረከቶሙ ለሳውል ወኬፋ። ወረብ እስመ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘተሰውጠ ላዕለ ሐዋርያት/፪/ በመንፈስ ቅዱስ ነበቡ በነገረ ኲሉ በሐውርት/፪/ መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ሰላም ዕብል ብርሃናተ ፪ኤተ: በዓውደ ንጉሥ ኔሮን እለ ፈጸሙ ሩጸተ: ጳውሎስ ወጴጥሮስ ዘያጸንዑ ፀበርተ: አሐዱ በመስቀል ተሰቅለ ቊልቊሊተ: ወካልዑ ተመትረ ክሣዱ ክብርተ። ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: ብርሃናተ ዓለም ሐዋርያተ ሰላም ሱቱፋነ ሕማም: አሥራበ ምሕረት ከዓዉ እምአርያም። @seratebetekrstiyan ወረብ ሐዋርያተ ሰላም "ብርሃናተ ዓለም"/፪/ አሥራበ ምሕረት ከዓዉ ከዓዉ እምአርያም/፪/ መልክዐ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተዘኪረከ ክርስቶስ ዘሐዋርያት ኲሎሙ: ህየንተ ክቡር ደምከ እለ ከዓዉ ደሞሙ: አክሊለ ስምዕ ሀበኒ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ: ወደምስስ ለአጽራርየ እመጽሐፈ ህይወት ዝክሮሙ: ከመ ለይሁዳ ረሲዕ ተደምሰሰ ስሙ። ዚቅ ስምዖን ጴጥሮስ ወአኃዊሁ ሱቱፋነ ሕማምከ: እለ ከዓዉ ደሞሙ ህየንተ ደምከ: ከመ ይኩን ተውሳከ ለሴጠ አሕዛብ በስብከተ ወንጌልከ: በከመ ተቶስሐ መዓዛ ክህነትከ በክህነቶሙ: ቶስሕ ስእለተነ በስእለቶሙ: ጸግወነ ሎሙ ከመ ንድኃን ቦሙ። @seratebetekrstiyan ወረብ ስምዖን ጴጥሮስ ወአኃዊሁ "ሱቱፋነ ሕማምከ"/፪//፪/ እለ ከዓዉ ደሞሙ ደሞሙ ህየንተ ደምከ/፪/ መልክዐ ኢየሱስ ሰላም ለእራኅከ መክፈልተ ሕማማት ሱቱፍ: ወቅንዋቲሁ እኤምሕ በአፍ: ኢየሱስ_ክርስቶስ በላዕለ ቅዱሳን ዕሩፍ: ይፀነስ ውስተ ከርሥየ ዘርአ ቃልከ መጽሐፍ: ጸዳለ እምጸዳል ከመ ትፀንስ ዖፍ። ዚቅ እግዚአ ውእቱ ለሰንበት ውእቱ: አቡሃ ለምሕረት ውእቱ: ኃያል ወብዙኅ ሣህል ውእቱ: ዘባሕቲቱ በቅዱሳኒሁ ዕሩፍ። ምልጣን ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ ወኢትናፍቅ እምዝ ዳግመ ኢንመውት ዳግመ ወእምዝ ዳግመ ኢንመውት። ወረብ ይቤሎ ጴጥሮስ ለጳውሎስ ጥባዕኬ እኁየ ጳውሎስ እኁየ/፪/ ወኢትናፍቅ ዳግመ እምዝ ዳግመ ኢንመውት/፪/ @seratebetekrstiyan እስመ ለዓለም ሕዝብ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን: አርድዕት ልዑላን አዕማደ ቤተክርስቲያን: ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ: ወኲሎሙ ሐዋርያት: ፈድፋደ ቦሙ ሞገሰ በኀበ ኲሎሙ ሕዝብ። አመላለስ ሕዝበ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡራን አዕማደ ቤተክርስቲያን/፪/ ሰመየ ስሞሙ ደቂቀ ብርሃን ጴጥሮስ ወጳውሎስ/፪ @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan
Show all...
«በሚያልፍ ዓለም ውስጥ የማያልፈውን አምላክ ተስፋህም፣ መከታህም አድርገው!!» ❀︵♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡︵❀ : ♡አቤቱ ጌታዬ ሆይ፥ ፡ ➊.በጥበቤ እንዳልመካ ➡ ጥበቤ ይዘነጋኛል፣ ፡ ➋.በጉልበቴ እንዳልመካ ➡ ጉልበቴ ይከዳኛል፣ ፡ ➌.በሀብቴ እንዳልመካ ➡ ሀብቴ እንደ በረዶ ይሟሟል፣ ፡ ➍.በዝናዬ እንዳልመካ ➡ ተረኛ ዝነኛ ይነጥቀኛል፣ ፡ ➎.በኃይሌ እንዳልመካ ➡ ኃይሌ ይዝልብኛል፣ ፡ ➏.በሰራዊት እንዳልመካ ➡ ይበተንብኛል፣ ፡ ➐.በውበቴ እንዳልመካ ➡ ውበቴ ይበላሽብኛል፣ ፡ ➑.በፍቅሬ እንዳልመካ ➡ ፍቅሬ በጥላቻ ይለወጣል፣ ፡ ➒.በአገልግሎቴ እንዳልመካ ➡ የገነባሁትን ላፈርሰው እችላለሁ፣ ፡ ➓.በወዳጅ እንዳልመካ ➡ ከስፍራው አጣዋለሁ፣ ፡ ➊➊.በትላንት እንዳልመካ ➡ አልፎ ተረት ይሆንብኛል፣ ፡ ➊➋.በዛሬ እንዳልመካ ➡ ባሰብሁበት መዋል ያቅተኛል፣ ፡ ➊➌.በነገ እንዳልመካ ➡ ቀን የሚያመጣውን ማወቅ ያቅተኛል፣ : ➊➍.በቅድስናዬ እንዳልመካ ➡ አንዱን ስደፍን አንዱ ያፈስብኛል። ፡ ↪የምመካበት ያሳፈረኝን የምመካበትን የፈራሁትን፣ የምመካበት ያጣሁትን እኔን ልጅህን ትምክሕት የሆንከኝ ጌታዬ ሆይ ተመስገን። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ፥ ፡ ➊.ጽድቅ ለሌለኝ ጽድቅ ፣ ቅድስና ለሌለኝ ቅድስና ፣ ጥበብ ለሌለኝ ጥበብ የሆንከኝ አንተ ነህ። ፡ ➋.ቤዛ ማቅረብ ለማልችል ቤዛ የሆንከኝ ፣ ከሞትም ያዳንከኝ ፈጣሪዬ ሆይ ምስጋናዬ ይድረስህ። ፡ ➌.ከሚያባርረኝ ጠላት ፣ ከሚያሳድድ ሕሊና የተማጸንሁብህ የደኅንነቴ ቀንድ አንተ ነህ። ፡ ➍.የማትደፈር ምሽግ ሁነህ ከሁሉ የምታድነኝ አንተ ነህ። ፡ ➎.የዘራሁት ሲመክን ፍሬን የምትሰጠኝ ፣ የሠራሁት ሲፈርስ አዲስ ገንብተህ የምታኖረኝ አንተ ነህ። ፡ ➏.አንተ ትምክሕቴ ነህ። የደኅንነቴም ራስ ነህ። ለሚያልፈው ዓለም ብቻ ሳይሆን ለማያልፈው ዓለምም እሻሃለሁ። ፡ ➐.አንተ ካላቅኸኝ የሚያሳንሰኝ ፣ አንተ ከወደድከኝ ከንቱ የሚለኝ ማንም የለም። ቢኖርም ሐሰተኛ ነው። ፡ ↪ዛሬን ያየሁብህ ትምክሕቴ ሆይ ተመስገን። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ፥ ፡ ➊.በአንተ ላይ እደገፋለሁ፣ በአንተ ላይ እደላደላለሁ፣ የማትነቃነቅ ምሰሶዬ አንተ ነህ። ፡ ➋.ከስፍራህ አትታጣም። ስደገፍህ የማትሰበር ምርኩዜ አንተ ነህ። ፡ ➌.ስጠጋህ የማትሸሸኝ ወዳጄ አንተ ነህ። ፡ ➍.ከፍ የምልብህ ደብሬ አንተ ነህ። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ፡ ↪ካንተ አግኝቻለሁና ከሰው አጣሁ ብዬ አላዝንም። ባንተ ተክሻለሁና ከሰርሁ ብዬ አላጉረመርምም። : ➊.የቤቴ ብርሃን ፣ የትዳሬም ዘውድ አንተ ነህ። ፡ ➋.በረታው ሲደክም፣ የተሾመው ሲሻር አንተ ግን በዘመናት ያው ሁነህ አይሃለሁ። ፡ ➌.ያለመድኩት ጠባይህ፣ ይህ ብቻ ነው ብዬ ያልገለጥሁት ማንነትህ የተመሰገነ ይሁን። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ ጌታዬ ሆይ፥ ፡ ↪አንተ ልዑል ስትሆን የምረገጥ ጭቃ የሆንሁት እኔ አመሰግንህ ዘንድ መፍቀድህ በእውነት በመደነቅ እንዳመሰግንህ ያደርገኛል። ፡ ➊.የገዛ አቅሜ ሲከዳኝ በእርጅናዬ የማትጥለኝ ጓዴ አንተ ነህ። ፡ ➋.እስከ ማታ ይቆያል ያሉት በጥዋቱ ሲያልቅ አንተ ግን እንደ በዛህ ትኖራለህ። : ➌.በክፉ ቀን ይቆምልኛል የምለው ራሱ ክፉ ቀን ሲሆን አንተ ግን በፍቅር ቅላፄ ታናግረኛለህ። : ➍.ያየኸው እንጂ የገላመጥኸው ማንም የለም። ፊትህን ስትመልስ እደነግጣለሁ ፣ ስምህን ስጠራ ወዲያው አይዞህ ትለኛለህ። ፡ ➎.ደስታዬን ፈውሰህ ባንተ እንድደሰት ስለረዳኸኝ ፣ ነፍሴ ከእውቀት ተራቁታ እንዳታስቸግረኝ በብዙ ትምህርት የደገፍከኝ አንተ እንደሆንህ አውቃለሁ። : ➏.በዚህ ዘመን ስላስነሣሃቸው አባቶችና ካህናት ምስጋና አቀርብልሃለሁ። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ፡ ➊.በሚክዱት መሐል አማኝ ለመሆን የበቃነው ባንተ ቸርነት ነው። : ➋.መሠረቴ አንተ ነህ። ከመነቃነቅ ከመነቀል ትጠብቀኛለህ። ፡ ➌.ነፋሱ እንዳይጥለኝ ሥር ሁነህ የያዝኸኝ ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ የደገፍከኝ አንተ ነህ። ፡ ➍.የዓለቱ መሠረት ጸንተህ የምታጸናው ሆይ ተመስገን። : ┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈ : ♡አቤቱ ጌታዬ ሆይ፥ ፡ ➊.የሰው ልጆች መናወጥ በዝቷልና። ብዙ ኑሮም በጭካኔ ይፈርሳልና ለምን ዝም አልከን። እባክህ ተለመነን። ፡ ➋.አንተ ከጨከንህብን የሚራራልን ፣ አንተ ካለፍከን የሚያየን ማንም የለም። በሰፊ አገር ላይ የታሰርን እስረኞች እንዳንሆንብህ እባክህ አስበን። ፡ ➌.ለምን ዓይነት ቀን እየተዘጋጀን እንደሆነ አናውቀውም። ጊዜ ከተገኘ ሁሉም ገዳይ ነውና እባክህን መልሰን። ፡ ➍.የምንሠራውን አሳውቀን። ፡ ➎.ሰው ለሰው ደስታው እንጂ ኀዘኑ አይሁን። ፡ ➏.ባንተ ከታመንሁ ምን እፈራለሁ? የምፈራው ራሱ ካንተ የተነሣ ይፈራል። እምነቴም ድፍረቴም አንተ ሁንልኝ። ፡ ➐.ፍጹም ፍቅር ከፍርሃት ያድናልና ፍጹም ፍቅር ስጠኝ። ፡ ➑.ማመኔን እስከ መጨረሻው ባንተ አድርግልኝ። ፡ ↪በማይፈጸም ዘመን ለዘላለሙ አሜን። ፡ ↪የሚሰማ ሁሉ በልቡ ያክብርህ ፣ በአንደበቱ ይዘምርልህ ፣ በጉልበቱ ይስገድልህ። ፡ ♡┈┈┈••✦✿✦••┈┈┈♡ : ♡አምላክ፦ ፡ ↪ክፋትን ከልባችን ያርቅልን!(አሜን) : ↪ማስተዋሉን ለሁላችንም አብዝቶ ያድለን! (አሜን) : «ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ» : "በቸር ያቆየን" :
Show all...
አረሳት ኢትዮጵያን በእርፍ መስቀል አባ ተክለ ሀይማኖት ሰባኪ ወንጌል @seratebetekrstiyan
Show all...
#ገድሉ_ተአምራቱ ገድሉ ተአምራቱ እጅግ ብዙ ነው ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው የተዋህዶ ኮከብ ተክለ ሀዋርያ አባ ተክለ ሀይማኖት ዘኢትዮጵያ አዝ፡፡፡፡፡፡፡ ዳግማዊ ይሗንስ ጠፈር የታጠቀ ንፁህ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ የፀጋ ዘአብ ፍሬዛፍ ሁኖ በቀለ በደብረ ሊባኖስ መናኝ አስከተለ አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡ ደካማ መስሏቸው ባንድ እግሩ ሲዩት ባለ ስድስት ክንፋ ተክልየ የኛ አባት እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ ለጊዮን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ አዝ፡፡፡፡፡ ከካህናት መካከል ህሩይ ነህ ተክልየ መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብየ ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አባ ተክለሀይማኖት ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቱን ቀደስሀት አዝ፡፡፡፡፡፡፡፡ የባረከው ውሀ የረገጥኸው መሬት ጥላህ ያረፈበት ሁኗል ፀበል እምነት ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ ይሰብካል ተክልየ ዛሬም እንደጥንቱ @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan
Show all...
††† ✝✝እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝ †††✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ ††† ✝በዓለ ሕንጸታ✝ ††† ††† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ) /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: (ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::) ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ:: ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው:: እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል:: ¤ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን:: ††† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን:: ††† ሰኔ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 3.ቅዱሳን ሐዋርያት 4.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ 4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና 6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት ††† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† ""ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን""::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ @seratebetekrstiyan
Show all...
††† ✝✝እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ (ሕንጸታ) በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††✝ †††✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!✝ ††† ✝በዓለ ሕንጸታ✝ ††† ††† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" (አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ) /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል:: የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው:: ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: (ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::) ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ:: በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ:: ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው:: እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል:: ¤ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን:: ††† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን:: ††† ሰኔ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 2.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 3.ቅዱሳን ሐዋርያት 4.ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ (ዕረፍቱ) ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት (ሰማዕት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር 3.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ 4.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ) 5.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና 6.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት ††† "በድካም: አብዝቼ በመገረፍ: አብዝቼ በመታሠር: አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" ††† (፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር ††† ""ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን""::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/ https://t.me/@ortodoxmezmur21
Show all...
#ዘማሪ እንግዳ ወርቅ ደጀ ጠናው ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን ተፅናነሁኝ እረሳሁ ሃዘኔን የአምላክ እናት እመቤታችን ሞገስ ሁኝኝ ቀሪው ዘመኔን (2) @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan @seratebetekrstiyan
Show all...