cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

only Et News ኦንሊ ኢት ዜና

ትኩስ፡ አጭር እና ወሳኝ መረጃዎች ይደርሶታል ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ መረጃዎች ➠ የስፓርት እና መዝናኛ መረጃዎች ➠ጠቃሚ ጥቆማዎች በአጭሩ ሳይሰላችዎ ይደርሶታል። አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን። ለማንኛውም መረጃ ➥#ልዩ_እቃዎች | #ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ PROMOTION 🎬 "ተመራጭ የእቃ ምርጫች" ለ አስተያዬቶ @abuke100

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
DailyZena መተግበርያን በስልኮ ላይ በመጫን አዳዲስ ዜናዎች እና ጠቃሚ መረጃዎችን ያግኙ። እንዲሁም ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉንም የሀገር ውስጥ የሬድዮ 📻 ጣብያዎች ያለ Earphone 🎧 ማድመጥ ይችላሉ።
Show all...
👉 አውርደው ይሞክሩት 👈
Photo unavailableShow in Telegram
#Update ትግራይ ክልል እያስተዳደረ ከሚገኘው " ህወሓት " በኩል ምላሽ ተሰጠ። ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገልጿል። ህወሓት ይህን ያለው የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው። ህወሓት ባወጣው መግለጫ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል። በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ መሆኑን አብስሯል። የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲደርስ ከባዶ ቃልኪዳን በመውጣት ተጨባጭ የሆኑ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል። " ፖለቲካዊ እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማገናኘትም ተቀባይነት አይኖራቸውም " ያለው ህወሓት ፤ የትግራይ መንግሥት እና ሕዝብ ለሰላም እድል ለመስጠት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ብሏል። ትላንትና የፌዴራል መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ያሳለፈው ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡ እና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ መጠየቁ ይታወቃል፤ ህወሓት በዚህ ላይ ያለው ነገር የለም::
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#Ethiopia #Sudan በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ላይ በምትገኘው በረከት ከተማ እና አካባቢዋ በኢትዮጵያ መንግስት ጦር እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁለት አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል። ነዋሪዎቹ ለበከፍተኛ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት መከፈቱንና ተኩስ መስማታቸውን ተናግረዋል ፤ ከሁመራ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በረከት ተኩስ መሰማት ከጀመረ አራት ቀናት መቆጠሩን ነው ያመለከቱት። ጦርነቱን የተቀሰቀሰው በሱዳን ግዛት ውስጥ በሚገኙት የሃምዳይት እና የሉግዲ አካባቢዎች እንደሆነ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ፤ " ጦርነቱ የተጀመረው ሱዳን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ነው " ያሉ ሲሆን ከዚህ በፊት ከሁመራ ወደ ሱዳን ተሰደው የነበሩ ዜጎች አሁን ላይ በሱዳን ግዛት ሆነው ጦርነት መክፈታቸውን አስረድተዋል። ከበረከት በተጨማሪም በሁመራ ከተማ በሚገኘው ዲማ የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ ጦርነት እንዳለ ገልፀዋል። ጦርነት እንደተቀሰቀሰበት የተገለጸው ዲማ የሚባለው የፍተሻ ጣቢያ በሁመራ በኩል ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚዋሰኑበት ድንበር ነው፡፡ ጦርነቱ በሱዳን ግዛት በኩል በመቅሰቀሱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ እና ሱዳን እንደሆነ የሚገልጹ አካላት ያሉ ቢሆንም ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። አሁን ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያ መንግስት ጥምር ጦር እና ሱዳን በሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች መካከል መሆኑን ነዋሪዎች ማስረዳታቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል። የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ያለው ነገርም ሆነ ያወጣው መግለጫ የለም።
Show all...
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና የሚያጣራ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን ዛሬ አስታወቀ። የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሎ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ብሏል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱን ገልጾ በአሁን ሰዓት ፦ 👉 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች ፣ 👉 ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ፣ 👉 ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፣ 👉 ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን አሳውቋል።
Show all...
ጥቆማ ፦ አብዛኞቻችን እንደምናውቀው የዋጋ ንረት እያየለ መጥቶዐል በብዙ ምክንያት ከሀገር ጦርነት እስከ ማእቀብ በቅርቡ ደግሞ የራሺያ-ዩክሬን ጦርነት ሀገራችንን ንረቱ እያጠቃት ይገኛል የዘይት ፣ቤንዚል እና መሰል ነገሮች ደግሞ ከእጥረት እስከ ስግብግብነት አይለዋል ይህ ደግሞ አስከፊነቱ ከህዝብ እስከ መንግስት እንደሚደር የቅርብ የሱዳን(በዳቦ ጭማሪ) ትውስታ ነው፡፡ይህ ብቻ አይደለም አለምን አሁን ጉድ ያስባለችው ራሺያ የስልጣን መንበር እንዳንቀጠቀጠ የታሪክ ትውስታ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል መንግስት ለዋጋ ንረት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል
Show all...
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጫካ ያሉ ታጣቂዎች ፤ ትጥቃቸውን በሚፈቱበት አካሄድ ላይ ከተወካዮቻቸው ጋር ውይይት ሊደረግ መሆኑ ታውቋል። የክልሉ መንግስት የተሃድሶ ስልጠና ሃሳቡን ያቀረበው፤ ከጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ታጣቂዎች ጋር ትላንት ቅዳሜ መጋቢት 10 ቀን 2014 በይፋ ዕርቅ መፈጸሙን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። በጉሙዝ ባህል መሰረት የተከናወነው የዕርቅ ስነ ስርዓት የተካሄደው በካማሺ ዞን፤ ካማሺ ከተማ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽና በካማሺ ወንዝ ዳርቻ ነው። በዕርቅ ስነ ስርዓቱ ላይ የምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ የክልሉ ም/ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ ይባስ እና የጉህዴን ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉደታ ተገኝተው ነበር። በካማሺ ከተማ የስብሰባ አዳራሽ በተከናወነው ዕርቅ ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ነበር። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት እና በጉህዴን አመራሮች መካከል ዕርቅ መውረድ ተከትሎ፤ በጫካ የነበሩ አማጽያን ከእነ ትጥቃቸው ወደ ካማሺ ከተማ ሲገቡ መመልከታቸውን አንድ የከተማውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ ድረገፁ አስነብቧል። የታጣቂዎቹን ወደ ከተማ መግባት የካማሺ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ቦካ አቦሴም አረጋግጠዋል። ታጣቂዎቹ ለጊዜው የካማሺ ዞን ባዘጋጀላቸው ማረፊያ እንደሚቆዩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊው ገልፀው ፤ በየትኛው የከተማው አካባቢ እንደሚቆዩ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ያንብቡ ፦ telegra.ph/Ethiopia-Insider-03-20 Credit - Ethiopia Insder
Show all...
05/7/2014 E.c በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 609 የብሬን ጥይትና ሌሎችን ህገ ወጥ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። " ኮድ 3 B38052 AA " የሆነ የጭነት አይሱዙ ቢሲቲማ ከተማ ኬላን በመጣስ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በ02 ቀበሌ ሃራ መገጠያ አካባቢ ከሌቱ 10:00 አካቢቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የመኪና አሽከርካሪ የተሰወረ ሲሆን 3 ተጠርጣሪዎችና መኪናው በቁጥጥር ስር መዋሉም የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል። ምንጭ ፦ ኢዜአ ቲክቫ አጠናቅሯል
Show all...
05/7/2014 E.c በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 609 የብሬን ጥይትና ሌሎችን ህገ ወጥ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። " ኮድ 3 B38052 AA " የሆነ የጭነት አይሱዙ ቢሲቲማ ከተማ ኬላን በመጣስ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በ02 ቀበሌ ሃራ መገጠያ አካባቢ ከሌቱ 10:00 አካቢቢ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የመኪና አሽከርካሪ የተሰወረ ሲሆን 3 ተጠርጣሪዎችና መኪናው በቁጥጥር ስር መዋሉም የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል። @tikvahethiopia
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.