cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Super christian tube ሱፐር ክርስቲያን ቱብ

የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ። 1ጴጥ. 4÷7 ይህ ሱፐር ክርስቲያን ቱብ ነው! # አላማችን 👉 በተግባሩና በህይወቱ የሚመሰገን በመንፈስ የጋለ ንቁ ክርስቲያን መፍጠር ነው። በተጨማሪ በዩቱብ https://www.youtube.com/channel/UC1JucyFEfBP0lXDNcsO11MQ?sub_confirmation=1

Show more
Advertising posts
15 178Subscribers
+324 hours
+2417 days
+1 92530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከማያምን ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት አትጀምሩ። 📛📛 ዛሬ የማይታይ ዝገት ⛔️⛔️ 👱‍♀"አንድ ልጅ አለ በጣም አስተዋይ ሰው ነው ግን በጌታ አይደለም እና እንዳገባው ጠየቀኝ ከዛ...." 👱" የምወዳት ልጅ አማኝ አይደለችም ግን ከብዙ ክርስቲያን ነን ባይ ሴቶች የተሻለ ምግባር አላት....." 👩" ይኸው ላለፉት ስምንት አመታት ከብዙ ክርስቲያን ወንዶች ጋር ግንኙነት ፈጥሬ አውቃለሁ ግን ከሶስት ወር በፊት ያወኩት አህዛብ ልጅ ግን ሁሉንም ያስንቃል...." ከላይ ያሉትና የመሳሰሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይጠየቃሉ፡፡ 👉 በወርቃማ ቅብ ያማረ ብረትን ጌጥ ብለህ በእጅህ ላይ ብታስረው ምናልባት እንደጌጥ ሊያገለግልህና ኮራ ብለህ በሰዎች ፊት ልታሳየው የምትችለው በጣም ውስን ለሆነ ጊዜ ነው፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የምትኮራበት ያ ጌጥ እራሱ የምታፍርበት መሆኑ አያጠራጥርም ፡፡ ምክንያቱም በእጅህ ላይ ያሰርከው በወርቃማ ቀለም የተሸፈነ ብረት እንጂ ወርቅ አይደለምና በላዩ የተቀባውን ቀለም አሸንፎ ዝገቱን ያጋልጣል ፡፡ የዛገን ነገር እንደጌጥ መጠቀም ማን ይመርጣል❓ ከላይ ተቀንጭበው የተጠቀሱት ታሪኮችም በወርቃማ ቀለም ከተሸፈነው ብረት የተለየ ሁኔታ የላቸውም ፡፡ ▶️ "በጣም ጥሩ ሰው ነው" ፣ " ፀባዩ አንደኛ ነው" ፣ " እጅግ አስተዋይ ናት " እና የመሳሰሉት ወርቃማ ቀለሞች ምናልባት ለጊዜው በእውቀትና በእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን በስሜት እንድንገዛ ሊጎትቱን ይችሉ ይሆናል፡፡ ጊዜያዊ ስሜታችንም እሰኪበርድ ድረስ ጥልቅ ፍስሃ ይሰጡ ይሆናል፡፡ 💠ነገርግን ያ የሚያምረው ወርቃማ ቀለም ሲደበዝዝ ከታች ያለው ማለትም እንደ "ግን በጌታ አይደለም" ፣ "ግን አማኝ አይደለም " እና የመሳሰሉ ዝገቶች "ሙታን" በሚለው መፅሀፍቅዱሳዊ ቃል ማህተም ታትመው ራሳቸውን መግለጥ ሲጀምሩ ትላንት የፈጠሩትን ደስታ የሚያስረሳ ሃዘን ይዘው ይከሰታሉ፡፡ 🗣 ለዚህ ምስክር ይሆን ዘንድ በስህተት ካላመኑ ሰዎች ጋር በትዳር ከተጠመዱ ሰዎች አንደበት የሚወጡ የፀፀት እና የምሬት ቃሎችን መስማት በቂ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እግዚአብሔር እስራኤላውያን የጋብቻ ሕይወት እንዳይመሰርቱ የነገራቸው ነበሩ እነሱም #ሞዓባውያን፤ #አሞናውያን፤ #ኤዶማውያን፤ #ሲዶናውያን፤ #ኬጢያዊውን ነበሩ። እግዚአብሔር ልባችሁን ወደ አምልክታቸው ይመልሱታልና ከእነርሱ ጋር መጋባት የለባችሁም ብሎ ነበር። ግን አንድ ቀን ንጉሥ ሰለሞን ከእነዚህ ጋር የፍቅር ግንኘነት ጀመረ። ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ሴቶች ንጉሥ ሰለሞንን ወደ ጣኦት አምልኳቸው መለሱት። 1ኛ ነገሥት 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² እግዚአብሔር የእስራኤልን ልጆች፦ አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፥ እነርሱም ወደ እናንተ አይግቡ ካላቸው ከአሕዛብ፥ ከእነዚህ ጋር ሰሎሞን በፍቅር ተጣበቀ። ³ ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ ሰባት መቶ ሚስቶች ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት። ⁴ ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት፤ የአባቱ የዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም እንደ ነበረ የሰሎሞን ልቡ እንዲሁ አልነበረም። ⁵ ሰሎሞንም የሲዶናውያንን አምላክ አስታሮትን፥ የአሞናውያንንም ርኵሰት ሚልኮምን፥ ተከተለ። ⁶ ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፥ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም። 👉ለስሜት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ የአስተዋይ ሰው ምርጫ ነው፡፡    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ 👉 inbox me @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Show all...
👍 23 18🥰 8👏 8
የማትጸልዩ ሰዎች እንዴት ነው ግን ሕይወት የምገፈላችሁ በጌታ?
Show all...
👍 44😢 19🤔 8 3🥰 3🕊 2
አንድ ጊዜ የወንጌል አርበኛው ቢሊ ግርሃምን አንዲት የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ለጠየቀቻቸው ጥያቄዎች የሰጡት መልስ ሁሌም ይደቀኛል ነገሩ እንዲህ ነበር👇 👱‍♀ ጋዜጠኛዋ ፦ ❝ አሁን ሁሉን ነገሮችን እንደ አዲስ የመሥራት ዕድል ቢሰጦዎት ምን የሚለውጡት ነገር አለ? ❞ 👨‍🦳 ቢሊ ግርሃምን እንዲህ ሲል መልሷል፦ 🗣 ❝ ከብዙ ጉዞና አገልግሎት ይልቅ ከጌታ ጋር በጸሎትና በጽሞና አሳልፍ ነበር። ❞ 👱‍♀ ጋዜጠኛዋ ፦ ❝ ለወጣቷ ሰባኪያን ምን ይመክራሉ ❞ 👨‍🦳 ቢሊ ግርሃምን እንዲህ ሲል መልሷል፦ 🗣 ❝ ብዙ ጸልዩ ብዙ አንብቡ ጥቂት አገልግሉ ነው የምላችሁ። ጥቅት አገልግሉ ስሉ አብዛኛውን ሰዓት ለአገልግሎት እየሰጣችሁ ከጸሎት አትራቁ ማለታቸው ነው። በዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያን #ሀብት አለጠችም። #የሕዝብ ቁጥርም ሆነ የአገልግሎት ዘርፎችን አለጠችም። #ነገር ግን ያጣችሁ ብቻኛ ነገር የምጸልይ ትውልድን ነው። አብዛኛው ትውልድ ሁሉም ባይሆንም ትኩረት የምሰጠው መድረክ ላይ ቆሞ ለሚያገለግለው አገልገሎት እንጂ ለጸሎት አይደለም። በጸሎት busy ከመሆን ይልቅ በመድረክ አገልግሎት busy መሆን ይፈልጋል። ነገር ግን እግዚአብሔር በአገልግሎት ከምንወጠር ጊዜ ይልቅ በጸሎት ከእርሱ ጋር የምናሳልፈውን ጊዜ ይፈልጋል። #በኳየር፤ #በስነፅሁፍ፤ #በአምልኮ_ህብረት ሆነ በሌሎች የቤተክርስቲያን ዘርፎች ላይ የሚያገለግሉ ልጆች ሁሉም ባይሆኑም አብዛኞቹ ትኩረታቸው ለጸሎት ሳይሆን ለመድረክ አገልግሎት ነው። የጸሎት ሕይወት ግን ባዶ ይሄ ደግሞ በፍጹም እግዚአብሔርን ደስ አያሰኝም። የጸሎት ሕይወት የሌለው አገልግሎት ከሙቀት ያለፈ ምንም ትርጉም የሌላ ነው። በአገልግሎት ፍሬያማ መሆን የምንችለው የጸሎት ሕይወት ስኖረን ብቻ ነው። እናንተዬ ቤተክርስቲያን ከተባረከችም አይቀር መባረክ ያለባት በምጸልዩ ትውልዶች መሆን አለባት። ❞ እናንተዬ ጸሎት ከጌታ ጋር ህብረት የማድረጊያ ትልቁ መንገድ ነው። ብዙ የሚጸልይ በጣም ብዙን ፍሬ ያፈራል። ስለዚህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ጸሎት እንደተቋሙ አደራ🙏🙏 የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ። 1ጴጥ4፥7 ጸሎት፦ ጌታ ሆይ አንተ ከምንም ነገር ይልቅ በአንተ ፊት በጸሎት የምናሳልፈውን ጊዜ ትፈልጋለህና ወደ ጸሎት ሕይወት አስገባን። በእኛ ሕይወት ላይ ውድ ነው የምንለውን የትኛውንም ነገር ቢሆን አንተ ውሰድ ሁሌም ከፊትህ አንታጣ በኢየሱስ ስም አሜን🙏🙏    👤ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👤 🙏ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ❤❤ 👉 inbox me @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @superchristiantube7 @superchristiantube7 @superchristiantube7 sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
Show all...
33👍 22🥰 8🔥 4
👍 49 22🥰 5👌 4👏 3🔥 2
17👍 6🥰 2🤔 1
12👍 7🔥 2🥰 2