cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የአሐዱ ማስታወሻ

📑 የአሐዱ ማስታወሻ 🌲"የኛስ ትውስታ ያለው በሰፊው ልባችን ውስጥ ነው። 👼"ፈጣሪ ኢትዮጵዊ እናቶች ይወዳል?!"💚💛❤ 😭#የልባችን ጥጋት ምነው ደጋግሞ ቆሰለ ስናለቅስ ስንጮህ ድምፃችን ሰለለ?!"😭 "💪በአመፃ ቀለም…🎨" #ከእለት_ሐሳብ_ማስፈር #ምሳሌ_VS_ዕንቁ commente፦ @fanus_lemastawesha

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
197
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✍ብላቴናው ሸጋ ቅዳሜ (ደመራ) 💚💛❤️ @joftdav @joftdav @joftdav
Show all...
4.94 KB
ተስፋ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ በአሉ ግርማ ተስፋ ባይኖር ኖሮ ህይወት አታጓጓም ነበር ይላል አንድን አምፖል እንዲበራ የሚያደርገው ሽቦው ነው ፡ ሽቦው ከረገፈ ጠርሙስ ይሆናል ሰውም ህይወቱ እንዲበራ የሚያደርገው በውስጡ ያለው ተስፋ ነው ። ተስፋ ከቆረጠ ውስጡ ይጨልማል አቡነ ሺኖዳ የተስፋ ህይወት በሚለው መፅሀፉቸው የሚከተለውን አስቀምጠዋል ። ተስፋ ለህይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው። ሰው ተስፋ ካጣ ሁሉንም ነገር ያጣል። ተስፋ ያጣ ሰው ደግሞ በጭንቀት ፣ በስቃይ ፣ ግራ በመጋባት ፣ ዓላማ በሌለው ጥበቃና በዛለ መንፈስ ውስጥ የወደቀ ስለሚሆን ሰይጣን በመዳፎቹ ውስጥ አስገብቶ መጫወቻ ያደርገዋልይህ በመሆኑም ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚመራው ሰይጣን ነው እንላለን ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ምንግዜም ተስፋ ስላላቸው በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው በመከራ ጊዜ ተስፋ አላቸው ፣ ነገሮች ሲወሳሰቡ ተስፋ አላቸው ፣እግዚአብሔር የዘገየ በሚመስልበት ጊዜና ነገሮች ሁሉ ጨለማ በሚመስሉበት ጊዜም ተስፋ ይኖራቸዋል ለኃጢያተኞች በንስሀ ውስጥ ተስፋ አለ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለና ለህይወቱ ወሳኝ በነበረችው ሰዓት ለወንበዴው ለፊያታዊ ዘየማን ተስፋ ነበር። በዘመኑ ቀረጥ ሰብሳቢ ለነበረውና በሰዎች ላይ ከፍተኛ በደል ያደርስ ለነበረው ለዘኬዎስ ተስፋ ነበር ሰባት አጋንንት የነበሩባትና በኀላ የጌታን ትንሳኤ ለአስራ አንዱ ሀዋሪያት ታበስር ዘንድ ለተላከችው ለመግደላዊት ማርያም ተስፋ ነበር (https://t.me/joinchat/AAAAAEkSiWw7drZxpcxk4Q) ክርስትና ለተቀጠቀጠው ሸንበቆና ለሚጨሰው ጧፍ ተስፋ ሰጥቷል። እግዚአብሔር የተቀጠቀጠ ሸንበቆን ሰብስቦ በአንድ ለማሰርና የሚጨስ ጧፍን ለማቀጣጠል አይሳነውም በክርስትና ተስፋ የተሰጠው ለሁሉም ነው ነገሮች ቢወሳሰቡና ከባድ ቢመስሉም እንኳን ተስፋችን አይላላም። ነቢዮ ዮናስ በአሳ አንባሪ ሆድ ውስጥ ሳለ ተስፋ ነበረው። በእሳት መካከል ለተወረወሩት ለሶስቱ ብላቴኖችና በተራቡ አናብስት ጉድጓድ ውስጥ ለተጣለው ዳንኤል ተስፋ ነበር ልጅ ላልወለደችው ለመካኒቱም ሴት ተስፋ ነበርሞቶ ከአራት ቀን በላይ በመቃብር በመቆየቱ እህቱ ማርታ አሁን ይሸታል ብላ እስክትናገር ድረስ በመቃብር የቆየውን አልዓዛር ለእኛ ተስፋ ይሰጠን ዘንድ ጌታ ከመቃብር አስነስቶታል የማይድን በሽታን በማዳን ውስጥ ተስፋ አለ ጌታ ዓይን ለሌላቸው ብርሃንን ሲያድል ለልምሾዎች ለሽባዎችና ለአካለ ስንኩላን ጤና አድሏል። ለ38 ዓመታት በመጠመቂያው ጉድጓድ አጠገብ ወድቆ ለነበረው መፃጉም ተስፋ ነበረው ተስፋ ያለው ሰው የሚያየው መከራዎችን ሳይሆን መከራዎችን እንዲያሸንፍ የሚያደርገውን እግዚአብሔርን ነው እያንዳንዱ የተቆለፈ በር ሺህ መክፈቻ ቁልፎች አሉት። ሁሉም ጨለማ በብርሃን ይሞላል፣ ከመራራው ጣፉጭን ከበላተኛውም የሚበላን ማውጣት የሚቻለው እግዚአብሔር ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ አለው ስለዚህ ወዳጄ ተስፋ እንዳትቆርጥ Comment @kokuha_haymanot_bot 💚 @Kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Show all...
አንድ ወዳጄ ከጠየቀቅኝ ለላንተ አስፈርኩኝ
Show all...
ፈቃደኛ ከሆናችሁ ሌሎች ወዳጆቻችሁን @lemastawesha ላይ አድር አድርጓቸው ክብረት ይስጥልኝ አመሰግናለው
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.