2 406
Subscribers
+124 hours
+407 days
+33730 days
Posts Archive
…………………………………………………
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ ተቀብሎ ለሚያሰለጥናቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች ምዝገባ እያካሄደ ሲሆን እርሶም በቀሩት ጥቂት ቀናቶች መተው እንዲመዘገቡ እንጋብዛለን።
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከታች የተቀመጠውን መስፈርት ለሚያሟሉ ትምህርትና ስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ ከሰኞ 16/09/2013 ዓ.ም ጀምሮ ምዝገባ የሚጀምር መሆኑን በደስታ ይገልፃል።
ፎቶ ሳይነሳ ያመለጠው አስከ ማታ
ፎቶ አላዛር ሄዶ መነሳት ይቻላል
አድራሻ: አማን ሆቴል ቁ-2 ስጋ ቤት አጠገብ።
…………………………………
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
#ኢድ_ሙባረክ
……………………………………………
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራር አባላት የእስልምና እምነት ተከታይ በሆነው የስራ ባልደረባቸው መኖርያ ቤት በመገኘት በጋራ የአፍጥር ስነ-ስርዓት ላይ በመካፈል አብሮነታቸውን አሳይተዋል።
ለ አሰልጣኝ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች::
ለመታወቂያ የሚሆን መረጃ እየተሰበሰበ ስለሆነ በየ ዲፓርትመንት እና በየስራ ክፍላችው እድትሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።
…………………………………………………
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የቴክኖሎጂና ክህሎት ውድድር ላይ ኮሌጃችንን ብሎም አስተዳደሩን ወክለው በመሳተፍና ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተቋሙን እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩን ላኮሩት አሰልጣኝ መምህራኖች እና ሰልጣኝ ተማሪዎች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ኘሮግራም በማዘጋጀት ጀግኖቹን አመስግኗል።
ተሸላሚዎችም ለተደረገላቸው እውቅናና ሽልማት በማመስገን እንዲ አይነት ማበረታቻዎች በቀጣይ በበለጠ ጠንክረው እንዲሰሩና ከዚህም የላቀ ውጤት ለማምጣት የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ገልፀዋል።
የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
#መልካም_የፋሲካ_በዓል
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
……………………
ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰናዳው የቴክኖሎጂ እና ቴክኒካል ክህሎት ውድድር ላይ ድሬዳዋን እንዲሁም ተቋማችንን በመወከል የተወዳደረው አሰልጣኝ መምህር #ስንታየሁ_ቀጭኔ በተወዳደረበት ዘርፍ(CNC) ከመላው ኢትዮጵያ ከመጡ ተወዳዳሪዎች 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ እና የ30ሺህ ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል።
በዚህም አሰልጣኝ መምህራችን ያስመዘገበው ላቅ ያለ ውጤት የተቋማችንን እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደርን ስም በክብር ያስጠራ በመሆኑ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተገኘው ድል ደስታውን እየገፀ ለአሰልጣኝ መምህር #ስንታየሁ_ቀጭኔ ላቅ ያለ ክብርና ምስጋና ያቀርባል።👏👏👏
