cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ramz Tube (Ibn Suleyman)

"የተሰበረ ልባቸውን ጠግኑ፤ ስሜታቸውን ጠብቁ፤ ቃላት ምረጡ፤ ድርጊታችሁን አለስልሱ፤ መልካም ትድድርን አትርሱ፤ ማንንም አታቁስሉ፤ በንፅህና በቀናነት ኑሩ። ይህ የነቢያት መንገድ፣ የመልካሞች መንገድ ነው።" for any coment @ibn_suleyman01 & @Adham_Tube_inbox_bot ✍............🌺🌺🌺..............☘☘

Show more
Advertising posts
509
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Photo unavailableShow in Telegram
⌛3 ቀን ብቻ ቀረ!⌛ ኢስላምን ለመተግበር ህግጋቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። የኢስላማዊ ህግጋት ጥናት ዘርፍ ፊቅህ ይባላል። ታዋቂ ከሆኑ የፊቅህ መዝሀቦች (አስተሳሰብ ትምህርት ቤቶች) መሀከል የሆነው ፊቅህ አሻፊዒያ የመጀመሪያ ኪታብ የሆነችውን ሰፊነቱ ነጃ መማር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ብዙ ምሁራን መስክረዋል። ሰፊነቱ ነጃ ማለት የመዳኛይቱ መርከብ ማለት ሲሆን በአምልኮ ተግባራቶቻችን ስኬታማ ሆነን እንድን ዘንድ ሁነኛ ሚና ያላት ኪታብ ነች። በሀገራችንም የሀይማኖት ትምህርት ጀማሪዎች የሸሪዓ እውቀትን የሚጀምሩባት ኪታብ ነች። በኪታቧ አንድ ሙስሊም ሊያከናውናቸው የሚገቡ መሰረታዊ አምልኳዊ ተግባራት ህግጋት በግሩም ሁኔታ ቀርበዋል። እርስዎም ሀይማኖታዊ ግዴታዎትን በእውቀት ላይ ተመስርተው ያከናውኑ ዘንድ ለማገዝ አልገዛሊ አካዳሚ ይህን አድል አመቻችቶላችኋል። የትምህርት አሰጣጡ ሙሉ በሙሉ በኦንላየን የቀጥታ ስርጭት (LIVE) ሲሆን በተጨማሪም ለትምህርት አሰጣጥ ሂደቱ ውጤታማነት አጋዥ የሆኑ የትምህርት ግብአቶችን ያገኛሉ። ትምህርቱ የሚጀምረው ጁን 22/2024 ወይም ሰኔ 15/2016 ዓ ል ሲሆን ለተከታታይ 12 ሳምንታት ዘወትር ቀዳሜ ማታ 2:30–3:15 በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። በትምህርቱ ማጠናቀቂያም ፈተና የሚኖር ይሆናል። በስኬት የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ሰርተፍኬት የሚያገኙ ሲሆን ወደቀጣይ ምዕራፍ በመሸጋገር የእውቀት አድማሳቸውን የሚያሰፉበት እድል ተመቻችቷል። ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ዛሬውኑ ተመዝግበው ቦታዎትን ይያዙ። ለመመዝገብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ https://forms.gle/35MjjTBNxhkyiBH66 ለተጨማሪ መረጃ በቴሌግራም @algazaliacademyadmin ወይም በዋትስአፕ https://wa.me/251984109507 ያናግሩን
Show all...
You have a new listing for Ramz Tube (Ibn Suleyman) ID order: 2300729 Format: 1/24 Date published: Asap Publication time (UTC+3): - ➡️ You have 23 hours. During this time you need to reject or accept the application in your personal account: https://telega.io/channels Please note that the term for placing advertising materials after accepting the application is 36 hours. After this time, the project is automatically canceled and the money is returned to the advertiser.
Show all...
የ1445 ኛው አ.ሂ የኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓልን የተመለከቱ የእንኳን አደረሳችሁ መረጃዎች! ... ... የ1445 ኛው አ.ሂ የኢድ አል አድሃ ሰላት በአዲስአበባ እና በሸገር ሲቲ ጠዋት 2:30 ሲል እንደሚጀመር ሁለቱ የመጅሊስ ተቋማት በየፅቤታቸው በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። . የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉደዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸውም "የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል ለፈጣሪያችን አሏህ ፍጹም ፍቅር እና ፍጹም ታዛዥነትን የምንማርበት፣ ስንተገብረውም የምንድንበት እና አስደናቂ ታሪክ የምናወሳበት የደስታ ቀናችን ነው" ብለዋል። የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል ማካፈልን፣ አንዱ ለአንዱ መድረስን የምንተገብርበት እና ፍጹም ሰብዓዊ የኾኑ ተግባራት የሚከወኑበት የደስታ እና የአብሮነት ማሳያ በዓል ነው ብለዋል። የዘንድሮው ዒድ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ሰዎች ሊረዳዱ እና ሊተጋገዙ የሚገባቸው ወቅት ነው ያሉት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ "ይህንን በዓል ስስናከብር በየአካባቢያችን በከባድ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችንን በማሰብ፣ በማገዝ እና የምንችለውን ሁሉ ማድረግ ይገባል" ብለዋል። "በዓሉን ስናከብር ያለንን በማጋራት እና የእኛን ደስታ በማካፈል ደስታችን ሙሉ ማድረግ ይኖርብናል" ነው ያሉት። ... ¤በተመሳሳይ የሸገር ሲቲ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለኢድ አል አድሃ (አረፋ)በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እንደተለመደው በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ወገኖች ታሳቢ እንድያደርግ ጥሪ ቀርቧል። .. ¤የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል፡፡  በመግለጫውም በዓሉን በፍቅር እና በሰላም ማክበር እንደሚገባ መልዕክት አሰተላልፏል፡፡ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ጀውሃር ሙሐመድ በመልዕክታቸው በሀገር እና በውጭ ለሚገኙ ሙስሊሞች ለ1ሺህ 445ኛው ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል አድሃ ዓረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል፡፡ “ዒዱን በሰላም፣ በፍቅር፣ በመተባበር፣ በመተሳሰብ እንድናሳልፈው አደራዬን አስተላልፋለሁ” ነው ያሉት፡፡ ፧ ...
Show all...
👍 1
🛑 የአረፋ ቀን ፆም! ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦ “ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162 🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 ነው። ⚫️ ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል። ⚫️ ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል። ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው። ⚫️ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም። ⚫️በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣ 1/ ቀኑን መጾም 2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር 3/ ዱዓእ ማብዛት ⚫️ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል። 🛑 የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 2016 ነው።
Show all...
00:58
Video unavailableShow in Telegram
ፈተና እንዲቀላችሁ የሚያረግ ዱአ
Show all...
owK1wDEEIBQmJGTffIFJOWhLjZBNhEAsDBiRQj.mp410.84 MB
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
በዐስሩ ቀናት ምን እንስራ?         (ክፍል አንድ) ================ ⚀  በእነዚህ ቀናት ውስጥ ምን እናድርግ? ተውበት: ‐ በማንኛውም ጊዜ‐ ለኔ ቢጤ ኃጢኣተኛ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአላህ ባሪያ ምርጡ ተግባር ተውበት ነው። በተለይ እንዲህ ዓይነት ጊዜያትን በተውበት ስሜት ማሳለፍ ወሳኝ ነው። እውነተኛ ተውበት፣ በሙሉ ወኔ ወደ አላህ መመለስ፣ ርቀነው ወደሄድነው የጌታችን እቅፍ መጠጋት የመጀመሪያም የመጨረሻም ስራችን መሆን አለበት። በዱንያም ሆነ በአኺራ የሰው ልጅ መድህን እና ስኬት ያለው በዚህ ውስጥ ነው። ያፈረስነውን መገንባት፣ ያቆሸሽነውን ማፅዳት፣ ያበላሸነውን ማደስ… ተውበት ነው። ማን አለ ከእኛ መሀል ያላመፀ? ማናችን አለ ያላጠፋ? ማን አለ ንፁህ? ማን አለ ግፍ ያልሰራ? ማንም! ማጥፋቱን እንደተካንበት ሁሉ ያሳለፍነውን ደግሞ እንድንክስ ዘንድ የተሰጠን እድል ነው፤ ተውበት። አላህ እንዲህ ብሏል: ‐ [وَتُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ ٱلْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ] «ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡» ❷ ጊዜውን ለመጠቀም መጓጓት: ‐ እነዚህን ጊዜያት ለመጠቀም እና በመልካም ስራዎች ለማሸብረቅ መጓጓት አለብን። አላህ በሚፈልገው መልኩ በአግባቡ ጊዜውን ለመጠቀም መወሰን አለብን። አንድን ነገር ከልቡ ወስኖ የነየተን ሰው አላህ ያግዘዋል። [وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلْمُحْسِنِينَ] «እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡» https://t.me/strong_iman
Show all...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በሃገረ ሳዑዲ ዐረቢያ የወርሃ ዙል-ሒጃህ ጨረቃ ዛሬ ሐሙስ ስለታየች ነገ ጁሙዓህ ግንቦት 30, 2016 E.C. የዙል-ሒጃህ ወር የመጀመሪያው ቀን ይሆንና ወርቃማዎቹ የዙል-ሒጃህ 10 ቀናት ከነገ ይጀምራሉ። ስለሆነም ቅዳሜ ጁን 15, 2024 (ሰኔ 08, 2016 E.C.) የዕለተ ዐረፋህ ቀን ሲሆን እሁድ ጁን 16 (ሰኔ 09) ዒደ-ል-አዽሓህ ይሆናል። አላህ በሰላም ያድርሰን‼ እነዚህን ወርቃማ ቀናቶች በዒባዳህ ለማሳለፍ ከወዲሁ ዝግጅት አድርጉ። ቀናቶቹን ከምታሳልፉባቸው ዒባዳዎች መካከል፤ ጾም፣ ዚክር፣ ቁርኣን መቅራት፣ ሶደቃ፣ ለቻለ ሰው ሐጅና መሰል በጎ ተግባራትን ማከናወን ይገኙበታል። አላህ ያበርታን። ሌሎችንም አስታውሱ! The Dhul Hijjah Crescent was SIGHTED today, hence Dhul Hijah.1445 will begin tomorrow Friday, 7th June 2024.
Show all...
👏 1
የስራ ማስታወቂያ ‼️ የምንፈልገው ብዛት= 20 ፆታ = ወንድ/ ሴት የስራው አይነት=ክላይንት ማናገር የክፍያ መጠን = በአንድ ስራ 400-1200 እድሜ =ከ18-25 ለማመልከት👇👇👇👇 @Amin_Digital_Marketing_Inbox JOIN Our channel 👇👇👇👇 https://t.me/Amin_Digital_Marketing
Show all...
👍 4
ቀናት ባለፉ ቁጥር በጣም እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር፤ በዚህች ምድር ላይ የተረጋጋና የተሻለ ሕይወት እንደሚገባን ነው፡፡ ምቀኝነት የሌለበት፣ ክፋት የሌለበት፣ ሰዉን በክፉ መጠርጠር የሌለበት፣ ቅናትና የዐይን ቅላት የሌለበት፣ መጉዳትም ሆነ መጎዳት የሌለበት፤ አስረዳ፣ አብራራ፣ ምን ለማለት ፈልገህ ነው የሌለበት፣ መረበሽና ማስደንገጥ የሌለበት፣ ጥላቻና ስጋት የሌለበት፣ መጯጯህ የለሌበት፣ አዎ በቀሪው የሕይወት ዘመናችን ለኛ ጥሩ ሕይወት ይገባናል፡፡ ጁሙዓ ሙባረክ https://t.me/Ibn_Suleyman
Show all...
Ramz Tube (Ibn Suleyman)

"የተሰበረ ልባቸውን ጠግኑ፤ ስሜታቸውን ጠብቁ፤ ቃላት ምረጡ፤ ድርጊታችሁን አለስልሱ፤ መልካም ትድድርን አትርሱ፤ ማንንም አታቁስሉ፤ በንፅህና በቀናነት ኑሩ። ይህ የነቢያት መንገድ፣ የመልካሞች መንገድ ነው።" for any coment @ibn_suleyman01 & @Adham_Tube_inbox_bot ✍............🌺🌺🌺..............☘☘

👍 2
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.