cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍልስፍና

"ይህ ቻናል መግቢያም ሆነ አጥር የለውም እንደ ሰው ለሚያስብ ብቻ ተከፍቷል!" ጲላጦስ

Show more
Advertising posts
672
Subscribers
No data24 hours
-27 days
-1430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሲኦራን (ክፍል 2)  አንድን ካላየህ ተመለስ¡ የሲኦራን መፅሀፍ እና ሀሳቦች በጥልቁ ለተገነዘበ "ትንሽ" የሚለው ቃል ብቻ ሳይሆን ስር መሰረት ያለው ጽለመታዊ አመለካከት መውረሱ አይቀሬ ነው።ሲኦራን ተወልዶ እስካረፈበት እ.አ.አ 1995 ድረስ አለም ጥሩ መልክ ያልነበራት የክፋት እና ተንኮል ያደረሰውን ውድመት እና ስቃይ ማሰለፏ ለሲኦራን የህይወት ምልከታን አቅጣጫ ቀያሪ አድርጎለታል።አንደኛውም ሆነ ሁለተኛ የአለም ጦርነት ላይ ቆሞ ብርሀናማ ነገሮችን ለማሰብ አስቸጋሪ በነበረት ወቅት የእነ ሲኦራን ፍልስፍና የገሀዱ አለም እውነታ ከመሆን የዘለለ እንደነ አፍላጦም ሆነ አርስጣጣሊስ ስለsubjective አለም ማውራት ከቅንጦትም በላይ ንቀት ነበር ምክንያቱም ጊዜ የህላዌ ፍልስፍና (Existentialism) መድረክ ነበራ። ትንሽ ፍላጎት ደግሞ አድሮብህ ፍልስፍናውን ዘለቅ ብለህ ስትገባ የሞትና የህይወት መለያ መስመሩ የት እንደሆን ይጠፋሀል።እስቲ በትንሽ ዳሰሳ ላሳይህ ተረጋጋ! 𝑜𝑛 𝑡ℎ𝑒 ℎ𝑒𝑖𝑔ℎ𝑡𝑠 𝑜𝑓 𝑑𝑒𝑠𝑝𝑎𝑖𝑟 ሲኦራን የፍልስፍና ``ዋና`` መገኛ መጣጥፉ ነው ብዬ አስባለሁ።መፅሀፉ ባለፈው እንዳልኩህ በአጫጭር ርዕሶች የተሞላ ሲሆን ከራሳችን ተነስቷ ራሳችን ላይ ያልቃል።መፅሀፉ ውስጥ በተደጋጋሚ ለመነገር የተፈለጉ መልእክቶች ብዙ ቢሆኑም ``የህይወት ፍሬ ከርሲስ``ነት ዋንኛ መዳረሻው ነው። ሲኦራን በመፅሀፉ ውስጥ እንዲህ ይላል``From a grave perspective, every step in life is a step into death and memory is only the sign of nothingness...(ጽልመታዊ እይታ አንፃር እያንዳንዱ ወደ ህይወት የሚደረግ እርምጃ አብሮ ወደ ሞት የሚመስድ እንዲሁ ትውስታዎች እንደአመድ ብናኝ የሚጠፉ ናቸው)``። በሌላኛው የመፅሀፉ ክፍል(the Double and His Art ርዕስ ስር ማለት ነው) ላይ ደግሞ ስለ የህይወትን እውነታዎች መረዳት ላይ እንዲህ ብሏል ``The more you know, the less you want to know. He who has not suffered from knowledge has never known anything...(ብዙ ባወክ እና በተረዳህ ቁጥር፤ትንሽ መረዳት ትፈልጋለህ።በእውቀት ስቃይ ስር ካልወደክ ምንም አታውቅም ማለት ነው..) የእውቀትን ጉዳይ ካነሳን በስነህላውያን ዘንድ ብዙ ማወቅ ትርፉ ወለፈንዲ የሆነችውን ህይወት የምታቀርብልህን የክብር ስጦታ የሆነውን ሞት ይበልጥ መለማመድ ነው(Memento mori ልብ ይሏል)።ነገርን ነገር ያነሳዋል ወለፈንዲ ስል የሀሳቡ ባለቤት አልበርት ካሙ ትዝ አለኝ፤ ሲኦራን በአንድ ቃለምልልሱ ላይ በአንድ ወቅት አልበርት ካሙ ጋር ተገናኝተው በካሙ ``Absurdism`` ፍልስፍና ላይ ተጨዋውተው እንደነበር አንስቷል። የካሙን የሲሲፈስ መንገድ አዋጭ አድርጓ አያየውም(ድሮስ ሁለት ፈላስፎች ተስማምተው የት ያቁና¡)። እንዲሁ በሌላው ርዕስ ስር ስለሰው ልጅ እንቅልፍ እጦት ሲያነሳ ``The loss of hope comes with the loss of sleep. The difference between paradise and hell: you can always sleep in paradise, never in hell. God punished man by taking away sleep and giving him knowledge....(የተስፋ እጦት ከእንቅልፍ እጦትየሚመነጭ ነው፤በገነት እና በሲኦል መካከል ያለው ልዩነት በገነት ሁሌም መተኛት  ይቻላል ነገርግን በሲኦል ውስጥ አይታሰብም።እግዚአብሔር የሰውን ልጅ እንቅልፍም ወስዶ እውቀት በመስጠት ነው...)       1.1 𝑛𝑖ℎ𝑖𝑙𝑖𝑠𝑚 (ጽልመተኝነት) በመፅሀፉ ውስጥ ጥግ የያዘ ጽልመተኝነት ይስተዋላል።ለህይወት የሰጠው ዋጋ አነስተኛ አድርጎ እንዲሁም "ሞት" በሚለው ቃል ውስጥ የተሸከመውን እንቅስቃሴ በስጋ ለመግለጥ የቻለ አይነት ፅሁፍ ነው።``At this moment I do not believe in anything and I have no hope. All forms and expressions that give life its charm seem to me meaningless. I have no feeling either for the future or for the past, while the present seems to me poison...(በዚህ ጊዜ በምንም ነገር አላምንም እንዲሁም ምንም አይነት ተስፋ የለኝም።ለሕይወት ውበት የሚሰጡ ቅርፆች እና አገላለፆች ለእኔ ትርጉም የላቸውም፣ ለወደፊቱም ሆነ ላለፉቱ ጊዜያት ምንም አይነት ስሜት የለኝም እንደውም አሁን ያለው ጊዜ እንደመርዝ ይመስለኛል.....) በማለት ጨለምተኛ የሆነ እይታውን ይነግረናል።       1.2 𝑘𝑛𝑜𝑤𝑙𝑒𝑑𝑔𝑒 𝑢𝑛𝑑𝑒𝑟 𝑟𝑒𝑎𝑙𝑖𝑡𝑦 𝑎𝑛𝑑 𝑐𝑜𝑛𝑐𝑠𝑖𝑜𝑢𝑠𝑛𝑒𝑠𝑠 ሌላው መፅሀፉን ስትዳስሱ(ከዚህ በፊት ዳሳችሁ ሊሆን ይችላል) በእውነታው እና በንቃተ ህሊናችን መካከል ስላለው እውቀት መፅሀፉ ይነግረናል። ሲኦራን እውቀት እንደቅጣት እንጂ እንደ ሌሎች ፈላስፎች(እንደነ ስር ፍራንሲስ ቤከን ያሉ) እውቀትን አይመለከተውም።ስለእውቀት አንድ የሚለን ነገር ቢኖር ``knowledge having irritated and stimulated our appetite for power.will lead us inexorable to our ruin...``(እውቀት እያናደደን እና ለ' ኃይል' ያለንን ፍላጎት በመቀስቀስ በማያዳግም ሁኔታ ወደ ጥፋት ይመራናል).... ቀረ የምለው ካለ በComment section ላይ እፅፋለሁ! ተፃፈ በይሁዳ @Wisdom_wisdom @Wisdom_wisdom
Show all...
👍 3🔥 1
ይሄ የነቢዩ ዳዊት ምስል ነው ብትባሉ ምን ያህል ታምናላችሁ? ዘመነ ትንሳኤ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና ያቆጠቆጠበት ወቅት ነው፡፡ ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ማለት ከቢሆንና ከምናብ ዓለም ወጥቶ በምድር ላይ ያለውን እውነታ እንዳለ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የ‹‹እውናዊነት (Realism)›› ፍልስፍና በነሚካኤል አንጀሎ አርትና በማኪያቬሊ የፖለቲካ ፍልስፍና ውስጥ ተንፀባርቋል፡፡ በዘመነ ትንሳኤ የነበሩ ሰዓሊያንና ቀራፂያን (ሊኦናርዶ ዳቬንቺ፣ ሚካኤል አንጀሎ፣ ራፋኤልና ሌሎችም) የሥዕልና የቅርፃ ቅርፅ ሥራዎች እውነታውን በማስመሰል ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በርካታ ሥራዎቻቸው ዓለማዊነትን (Secularism) የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የምታዩት የመፅሐፍ ቅዱሱ የዳዊት Sculpture ይገኝበታል፡፡ ይሄ Sculpture የተሰራው ከ1501–1504 በሚካኤል አንጀሎ ነው ምስሉ በብዙ ባለሙያዎች ዘንድ ‹‹a masterpiece of Renaissance and world art›› ተብሎ ይወደሳል፡፡ ምንም እንኳ የመፅሐፍ ቅዱሱ ዳዊት የምናውቀው በመንፈሳዊነቱ ቢሆንም፣ ሚካኤል አንጀሎ ግን ጡንቻማ የግሪክ አትሌት አስመስሎ ሰርቶታል፡፡ በመካከለኛው ዘመን ቢሆን ሰው እንደዚህ ራቁቱን ሆኖ (ያውም ከነ ብልቱ) አይሳልም፣ አይቀረፅም፡፡ ‹‹ርቃን አካል ያልተገራና ያልሰለጠነ ሰው-ነት›› ተደርጎ ስለሚቆጠር በአደባባይ እንዲታይ አይደረግም፤ በጣም ነውር ነው!! በዘመነ ትንሳኤ ግን ይሄ ተጀመረ፡፡ አንዳንዶች ይሄንን ምስል የ‹‹Christian Humanism›› መገለጫ ይሉታል፡፡
Show all...
👍 2🔥 1🤔 1
ዶስቶቭስኪ እግዚአብሔር እንደሞተ ከኒቼ ሲሰማ be like..😂
Show all...
`` እናንተ ወደ እግዚአብሔር ስትናገሩ እየፀለያችሁ ነው፤ እግዚአብሔር መልሶ እናንተን ሲያናግር ግን የአእምሮ ታማሚ (𝑠𝑐ℎ𝑖𝑧𝑜𝑝ℎ𝑟𝑒𝑛𝑖𝑎) ናችሁ። ሞታን እናንተን ሲያናግሩ እናንተ መንፈሳዊ ናችሁ፤ ግን እናንተ ሞታንን ስታናግሩ የአእምሮ ህመም ተጠቂ ናችሁ! `` 𝑡ℎ𝑜𝑚𝑎𝑠 𝑠𝑧𝑎𝑠𝑧 𝑓𝑟𝑜𝑚 ℎ𝑖𝑠 𝑏𝑜𝑜𝑘 "𝑡ℎ𝑒 𝑚𝑦𝑡ℎ𝑠 𝑜𝑓 𝑚𝑒𝑛𝑡𝑎𝑙 𝑖𝑙𝑙𝑛𝑒𝑠𝑠"
Show all...
ሶስቱ ነብያት | | 1. ኒቼ 2. ካርል ዩንግ 3. ዶስቶቪስኪ | የነብይነት ጸጋ ነበራቸው። የኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጸሀፎቻቸውን ደፍራ ከቅዱሳት መጸሀፍቷ ብትቀላቅል ብዙ ትጠቀማለች። | | 1. ኒቼ በተቋማዊው ክርስትና ላይ የበረታ ሒስ በመሰንዘር ይታወቃል። " የመጨረሻው ክርስትያን መስቀል ላይ ሞቷል" እስከማለት የደረሰ ጭፍለቃው ስነጽሁፋዊ ግነት እንጂ literall(አማናዊ) ትርጉም አይደለም። የdetail አቅሙን ያየ ሌጣውን ትርጉም አይወስድም። ኒቼ cult ተሰርቶበታል። ፈጣሪን በአኗኗራቸው ክደውት በአንደበታቸው እግዜር አለ የሚሉት ቅዘናሞች አፍ ማስቲካ ሆኗል። | " እግዜር ሙቷል" የምትል ሀረጉን መዘው ፍዳውን ያሳዩታል። እስቲ ሙሉውን..... | " እግዜር ሙቷል። አዎ ሞቶ ይቀራል። ደሞ እኛ ነን የገደልነው። ከግድያም ታላቁን ግድያ የፈጸምን እኛ ሰዎች ሊመቸን ኖሯል? ምድሪቱ ያላትን ቅዱስ እና ታላቁን ሀይል በቢላችን ደሙ አፍስሰናል! ይሔን ደም ከእጃችን የሚያጥብልን ማነው? የቱ ፌሽታ ካሳ ሊሆን? የቱ አስደንጋጭ ጫወታ ሊያረሳሳን? እውነት? ኤግዜር ለእኛ ካደረገልን በላይ ለራሳችን ማድረግ እንችላለን? ይሔን ለራሳችን በማድረግ አማልክት መሆን ምን ሊረባን?" | | ቃል በቃል አልተረጎምኩም። ፍረዱኝስቲ ይሔ ወንጌል አይደለም ወይ? ስነጽሁፋዊ ውበቱ ከጀርመንኛ ወደ እንግሊዘኛ ሲሔድ ከእንግሊዘኛም ወደ አማርኛ ስመልሰው ተዳክሟል። "በራሳችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፣ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ያጠፋታል፣ ደሙ በልጅ ልጆቻችን ይሁን" የሚሉ የመጸሀፍ ቅዱስ ንግግሮች ከላይ ባለው የኒቼ ሀተታ ካልተፈቱ ግራ ናቸው። በተሰቀለው ኢየሱስ ላይ ሰው ሁሉ አንድ ነው ባይ ነው። መሲሁ የትኛውም ዘመን ላይ ቢመጣ አገዳደሉ ይለያይ እንጂ ሟች ነው። "እኔ ይሔን አላደርግም" ያለ ምእመን እንደ ጴጥሮስ ሊክድ የተዘጋጀ ነው። 📍 የተነሳውን ኢየሱስ በማመን/በመሆን ግን ልዩነት አለ ይላል። ኒቸ በስልጣን እንጂ በጨዋነት አያምንም። ትንሳኤ ስልጣን ነው ይላል the will to power መጸሀፉ ላይ። እንደ መጀመሪያው ሟች አቤል ትሁት ሆኖ ሞቶ መቅረት ወይስ እንደ መጨረሻዉ ሟች ኢየሱስ እውነት ተናግሮ ሞቶ መነሳት? | | 2. ካርል ዩንግ | የሲግመን ፍሮይድ ተማሪ ነበር። ከፍሩይድ ይበረታል ይሉታል። አባቱ ፓስተር ነው። በሙሉ ስሙ ካርል ጉስታቭ ጁንግ(ዩንግ) ይባላል። ይሔም እንደ ኒቼ ጀርመናዊ ሲሆን psychiatrist, psychoanalys እና ሳይንቲስት ነው። ድርሳኖቹን ያነበበ ከ 149 አመት በፊት አለም እንዲህ አይነት ደፋር ነበራት ወይ ማለቱ አይቀርም! | ታዋቂ መጸሀፉ the red book ይሰኛል። ከዲያቢሎስ ጋር በመንፈሱ ተገናኝቶ የጻፈው ነው። ከዚህ ገጠመኙ ተነስቶ የግል ሰይጣናችንን መገናኘት አለብን ይላል። በባህል እና ሀይማኖት የተወገዘ ድብቅ ፍላጎታች የሚፈጥረው Shadow አለ። ስንቆጣ ልጆቻችንን እስከመግደል የደረሰ ቅጣት የሚቀጣቸው በዚህ Shadow ውስጥ የሚገለጠው ሰይጣን ነው። " ተቆጡ በቁጣችሁ ላይ ጸሀይ አይግባ" ካለ በሗላ "ለዲያቢሎስም እድል ፈንታ አትሰጡት" ይላል። አጅሬ ሹልክ ትላለች ሲለን ነው። | ሴጦ እየተገለጠ ልጆቻችንን ይቆጋል፣ ወዳጆች bully ያደርጋል፤ ስራችሁን ብታጡስ እያለ ያቦካል። ለኛ አይታይም! ባለቤቱ ፍሬውን እያየ የራሴ ጠላት እራሴ ነኝ ብሎ የታገለ አንድ ቀን እንደ ዩንግ ይገናኘዋል። ክስተቱ shadow encounter ይባላል። የኛ ሰይጣን ከዋናው ሰይጣን ይለይልናል። በውጣችን ሆኖ ማስጠቃቱን ያቆማል። " እባብም እርግብም ሁኑ የሚለው ትዕዛዝ ይፈጸማል" ነው መደምደሚያው! | ኒቸ እግዜርን የገደለ ሰው እረፍት የለውም ሲል ዩንግ ተቀብሎ እግዜር በውስጡ የተነሳለትን ያሳያል። ሰው ሰይጣንን ፊት ለፊት ካገኘው በሗላ 3 stage አለው ይላል።( በቀጣይ ጽሁፍመጣበታለሁ) | | 3. ዶስቶቪስኪ ሩስያዊ ነው። ከ105 አመት በፊት የተገኘ ደራሲና ጋዜጠኛ። የኒቸ literatural prophecy ደርሶበታል። ተቋማት ደግፈው ያቆሙት የስነምግባር ሰው የፈረሱበት እለት ሊሆን የሚችለውን ዶቶቪስኪ ሆኖት ጻፈው። | ኒቼን አምኖ በዩንግ መንገድ ያልሔደ ሰው ዶቶቪስኪን ይመስላል። የስርቻውን ሰው ይሆናል። the underground man ይለዋል። ፍርፋሪ እና ልጆች መኖር ያስቀጥሉት የነበረው የተለመደው ሰው ከ existential (ህልውናዊ) ጥያቄዎቹ ፊት ስላልቆመ የስነ-ምግባር ሰው ይመስላል ባይ ነው። | ዶቶቪስኪ በስሜት ሆኖት ያሳየናል። ከ Red bookም በላይ እጅግ የምፈራው መጸሀፍ ነው። ፍርሀት እንደ አይጥ ስርቻ ለስርቻ የሚያርመጠምጠኝ ነበርኩና የሚለውን ሳነብ ያ ቦታዬ ያልዳነ ያህል ያመኛል። ልቤን ስውር እያደረገኝ ስንቴ አስቀመጥኩት? | በስራ እና በልጅ ላመልጣት የነበረች ክፉ ጥረት ነበረች። በሁለቱም የተሳካልኝ ሰው አይደለሁምና ህልውናዊ ጥያቄዎቼ ፈጠው አላላውስ አሉኝ። ዛሬ የተወለድኩ ያህል "ከየት መጣሁ? ወዴት ልሒድ? ማነኝ?" ምናምን አልኩ። ሰውነቴ እስር ቤት ሆኖብኝ መተንፈስ ተቸግሬአለሁ። በየአመቱ ይሔን መጸሀፍ ጀምሮ ያለመጨረስ እቅድ አለኝ። ዘንድሮም እሱ ላይ ነኝ። በጨዋታ፣ በፌ.ቡ፣ በበርጫ፣ በጨብሲ፣ በኢየሱስ፣ በወንጌል፣ በታማልዳለች አታማልድም፣ በጨላ አጫብለን የረሳነውን አማናዊ ጥያቄ እና ፍላጎታችንን ያፈጣል። | ሶስቱ ተባብረው የሚሉት ይሔን ነው። " በስነ-ምግባር አታመልጡም! ለጊዜው የጸጥታ ተቋማት ከሌቦች ጋር ስላልሰሩ አትሰርቁም፤ አማኝ የመሰላችሁት የሀይማኖት ተቋማት ብሔር ስላልገባቸው ነው" . ባጠቃላይ #የሰላም_ዘመን_አልፎ_የጽድቅ_ዘመን_ይመጣል እያሉን ነበር። ፦ Behailu_mulugeta @rasnflega
Show all...
``ከልክ ያለፈ እውቀት እኮ በውኑ በሽታ ነው: ሊያምኑ ጥሉ በሽታ.. `` Dostoyevsky የስርቻው መጣጥፍ ትርጉም በፋሲል ይትባረክ
Show all...
የእስረኞቹ እንቆቅልሽ አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ። አማራጭ አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡ አማራጭ ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ። አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡ አማራጭ አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ። በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ? መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ  የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው᎓᎓በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል። ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል? እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል። እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡ ምንጭ- ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ ዝግጅት-ፍሉይ አለም
Show all...
  ``በዚህ ጊዜ: ወንድ በሁለት ቡድን መካከል  በአንዱ ወድቋል በነፃነት ውስጥ አልያ በባርነት።  ማንም ሰው ሁለት-ሶስተኛው የሚሆነው ቀኑን ለራሱ ካልሆነ: እርሱ ባርያ ነው።ምናልባትም እሱ የቢዝነስ ሰው አልያ የመንግስት ሰራተኛ ወይም የአገር መሪ እንዲሁም ምሁር ሊሆን ይችላል።``      ፍሬድሪክ ኒቼ"Human, All Too Human"
Show all...