cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ስንክሳር

ሁሌ ዝቅ ማለትን አብዝቶ መስማትን ገንዘብ እናድርግ። @Synaxarium "ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን" ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ

Show more
Advertising posts
771
Subscribers
No data24 hours
-17 days
+1530 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

. 🔸 ቀዳም ሥዑር 🔸 የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ስያሜዎች ❶ #ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)፦ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ ❷ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) ❸ #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) ከአይሁድ ጫጫታ ይልቅ፣ ጲላጦስን ሰላም የነሳው (አርምሞ ቤዛ ኩሉ) የክርስቶስ ዝምታ ነበር። Reposted 23/8/2013 ዓ.ም ©️ ሐዋሳ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1648232645330581&id=100004315844056
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

. የሰሙነ ሕማማት ስድስተኛው ዕለት ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ #ቀዳሚት፦ ➻ ቀዳሚት ሥዑር ትባላለች። ➻ ለምለም ቅዳሜ ትባላለች። ➻ ቅዱስ ቅዳሜ ትባላለች ። 🔥 ቀዳሚት ሥዑር ትባላለች። ዕለተ ቀዳሚት እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሔዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈባት ዕለት ናት፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት፡፡ እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈባት ‹‹ሰንበት ዐባይ›› (ታላቋ ሰንበት) ትባላለች፡፡ ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል (ዘፍ. ፩፥፫)፡፡ ዕለተ ቀዳሚት በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ዂሉ የፍጥረት ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ አምላክ በመቃብር አርፎባታል። (ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሙታን እንደሰበከላቸው በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤ (፩ጴጥ. ፫፡፲፰) እንዲል። በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት፤ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል "ቀዳሚት ሥዑር" ይባላል። ትርጓሜውም "የተሻረ" ማለት ነው። ይኸውም ቅዳሜና እሑድ ጾም የማይገባ ሆኖ ሳለ ጌታ በከርሠ መቃብር ስላደረ በዓመት አንድ ቀን በአክፍሎት ስለምትጾም ነው። ይኸውም ቅድስት ድንግል ማርያም እና ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንሥተው ብርሃነ ትንሣኤዉን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደርጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡ ከቅዱሳን ሐዋርያት በቅብብሎሽ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን፣ በመጾምና በመጸለይ ዕለቷን እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆችም የተቻላቸው ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ (ይጾማሉ)፤ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ፡፡ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም በዓለ ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡ በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቀዳሚት በቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ በኖኅ ዘመን ስለ ውኃው መጉደል ርግብ የለመለመ ቅጠል ይዛ እንደመጣች የቅዳሜ ሥዑር ዕለትም የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን አደረገ" እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን በየቤታቸውም እየዞሩ የለመለመ ቄጠማ ያድላሉ። ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም የኃጢአት ባሕር እንዲሁ ተወግዷልና። ይኸውም የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ምሥጢሩም በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ኾነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጕደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡ ቄጠማ፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነዉን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል (የሲኦል ቃጠሎ) ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡ 🔥 ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። 🔥 ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። 🔥 ቅዱስ ቅዳሜ ለ5500 በሲኦል ሲማቅቁ የነበሩ ነፍሳትን ሰላም ለሁላችሁ ይኹን ብሎ ወደ ገነት አስገብቷቸዋልና፤ ይህች ቅዳሜ ቅዱስ (የተለየች) ቅዳሜ ትባላለች፡፡ እንበለ ደዌ ወሕማም፤ እንበለ ፃማ ወድካም፤ ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም። ወስብሐት ለእግዚአብሔር መሰለ ንጋቱ ሚያዝያ 15/ 2014 ዓ.ም ሀዋሳ
Show all...
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች፦ 1➻ ሳዶር ፦ መስቀሉን ያመሳቀሉበት 2➻ አላዶር ፦ በዚህ ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 3➻ ዳናት ፦ በዚህ ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 4➻ አዴራ ፦ በዚህች ችንካር ሁለት እግሩን በአንድ አድርገው የቸነከሩበት 5➻ ሮዳስ ፦ 🅸🅽🆁🅸 ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ ብለው ጽፈው በመስቀሉ ጫፍ አያይዘውበታል። ከሥዕለ አድኅኖው ጫፍ ላይ "ኢ. ና. ን. አ" የሚለው "ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ" የሚለው በምሕፃረ ቃል ተጽፎ ነው። ከ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል ጋር የሚቆጠሩት ግን ፬ቱ ቅንዋት ናቸው። እነዚህም ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት እና አዴራ ናቸው። መስቀሉን ያመሳቀሉበት ሳዶር እያለፈ አካሉን ይወጋው ነበርና። 🔥 ሰባቱ የመስቀል ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. ተፈጸመ (ዮሐ 19፡30) ይህ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰውን መከራና ስቃይ ያስታውሰናል።
Show all...
. የሰሙነ ሕማማት አምስተኛው ዕለት ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ዕለተ ዓርብ እንደ ሌሎቹ ዕለታት ሁሉ በቤተክርስትያን የተለያዩ ምሥጥራዊ ስያሜዎች አሉት። #ዓርብ፦ ➻ የስቅለት ዓርብ ይባላል ➻ መልካሙ ዓርብ ይባላል 🔥 የስቅለት ዓርብ ይባላል ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ‹‹አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት ነበር›› (፩ኛ ቆሮ. ፩፥፲፰)፡፡ እንዳለ ይህች ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለ በደል ያለ ጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን የዓለም ሁሉ መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመልዕልተ መስቀል ላይ የሰቀሉት ዕለት ነውና #የስቅለት_ዓርብ ይባላል። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በበደለ ጊዜ ከሳሽ ዲያብሎስን በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ በማለት የገባለት ቃል መፈጸሙ ፤ ስለ ጌታ መያዝ፣ መገረፍ፣ መሰቃየትና መሰቀል ይነገራል። ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው። (ማቴ. ፳፯፥፴፭-፸፭)፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከሚደረገው ስግደት በበለጠ ነገረ መስቀሉን በማሰብ በጸሎትና በስግደት ዕለቱ ይከበራል። 🔥 መልካሙ ዓርብ ይባላል ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ሕግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። የሰው ልጆች በዘር ኀጢአት (ቁራኝነት) ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ ዓርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን አገኘን፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹መልካሙ ዓርብ›› በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡ በአይሁድ ልማድ ሕግ ሐጥያተኛና በደለኛ የሚሉት ሰው በድንጋይ ይወገር ነበር። ጌታችንን ግን የሚገረፍ እንዳይሰቀል፤ የሚሰቀል እንዳይገረፍ የሚለውን ሕጋቸውን ጥሰው የግፍ ግፍ ገረፈው በመስቀል ሰቀሉት። የመስቀል ሞት የአህዛብ የአረማዊያን በተለይም የፋሪሶችና የሮማዊያን ልማድ ስለሆነ፤ ወንጀለኛና እርኩስ ብለው የሚገድሉት በእንጨት ተሰቅሎ ነበር። በአይሁድ ዘንድ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነበር። ስለዚህ የመስቀል ሞት የመጨረሻ የውርደት ሞት ነበር ማለት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ስለ እኛ ሐጥያትና መርገም ፍቅሩን አሳየን ይህውም ለመስቀል ሞት በቃ። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ድንገተኛና ያልታወቀ አልነበረም። አስቀድሞ በትንቢት በኋላም ገና በማስተማር እንዳለ ለደቀ መዛሙርቱ ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ያስተምርና፤ ይነግራቸው ነበር። አዎ የእኛ ጌታ በዚያች በጌቴሰማኒ ጸለየ፤ በይሁዳ የመጡት ጭፍራዎች በእነሱ ኃይል ሳይሆን በራሱ ፈቃድ ተያዘ። ለአዳምና ለልጆቹ ካሣ ድኅነት ለመፈጸም ለመስቀል ሞት በቁጣ ስጎትቱት በፍቅር ተከተላቸው። በቤተ ክርስትያናችን የሚታወቁት ጌታችን መድኃኒታችን ላይ የደረሱት 13ቱ ሕማማተ መስቀል፦ 1ኛ➻ ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር) 2ኛ➻ ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ) 3ኛ➻ ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ) 4ኛ➻ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ) 5ኛ➻ ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም) 6ኛ➻ ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት) 7ኛ➻ ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ) 8ኛ➻ ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት) 9ኛ➻ አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት) 10ኛ➻ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም) 11ኛ➻ ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር) 12ኛ➻ ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይ መሰቀል) 13ኛ➻ ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት) ➦ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች፦ 1➻ ሳዶር ፦ መስቀሉን ያመሳቀሉበት 2➻ አላዶር ፦ በዚህ ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት 3➻ ዳናት ፦ በዚህ ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት 4➻ አዴራ ፦ በዚህች ችንካር ሁለት እግሩን በአንድ አድርገው የቸነከሩበት 5➻ ሮዳስ ፦ 🅸🅽🆁🅸 ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ ብለው ጽፈው በመስቀሉ ጫፍ አያይዘውበታል። ከሥዕለ አድኅኖው ጫፍ ላይ "ኢ. ና. ን. አ" የሚለው "ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ" የሚለው በምሕፃረ ቃል ተጽፎ ነው። ከ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል ጋር የሚቆጠሩት ግን ፬ቱ ቅንዋት ናቸው። እነዚህም ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት እና አዴራ ናቸው። መስቀሉን ያመሳቀሉበት ሳዶር እያለፈ አካሉን ይወጋው ነበርና። 🔥 ሰባቱ የመስቀል ቃላት 1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46) 2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34) 3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43) 4. እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27) 5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28) 6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46) 7. ተፈጸመ (ዮሐ 19፡30) ይህ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰውን መከራና ስቃይ ያስታውሰናል። በደረቁ ሐዲስ ኪዳን ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ አስቀድሞ እንዲህ ያለው ትንቢት ተፈጸመ። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ " በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። " ት ኢሳ 53፥2-7 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት በመስቀል ላይ ሳለ፦ ከ6 ስዓት እስከ 9 ስዓት. በነበረበት ጊዜ በሰማይ ሦስት በምድር አራት በጠቅላላው 7 ታምራት ተፈጽሟል። በሰማይ ➻ ፀሐይ ጨለመች፤ ➻ ጨረቃ ደም ሆነች፤ ➻ ከዋክብት ረገፉ በምድር ➻ አለቶች ተሰነጠቁ፤ ➻ መቃብሮች ተከፈቱ፤ ➻ ሙታን ተነሱ፤ ➻ የቤተ መቅደስ መጋረጃም ከሁለት ተቀደደ፤ ምድር ተናወጠች። [ማቴ ም 27፥ 32-47 ሉቃ 22፥54. ዮሐ 19፥ 16-22 ማር 14፥53. ማር 15፥ 21-32 ዮሐ 18፥22. ሉቃ 23 ፥46]
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ክርስቶስ አምላክነ ዘመጽአ ወሐመ በእንቲያነ በሕማማቲሁ ቤዘወነ። አምላካችን ከዕለቱ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን። "እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም መሰለ ንጋቱ ሚያዝያ 14/2014 ዓ.ም ሀዋሳ/ኢትዮጵያ ሰኞ 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2281791095308063&id=100004315844056 ማክሰኞ 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2282548848565621&id=100004315844056 ረቡዕ 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2282601898560316&id=100004315844056 ሐሙስ 👇 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2283702061783633&id=100004315844056
Show all...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን። ሚያዝያ 25 ቀን የከበረች ቅድስት ሣራ ከሁለት ልጆቿ ጋር በሰማዕትነት ዐረፈች፡፡ 🔥 ቅድስት ሣራ ይኽችውም የአንጾኪያዋ ቅድስት ልጆቿ ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ በማለት ጸሎት ካደረገች በኋላ የቀኙን ጡቷን በምላጭ ቆርጣ በደሟ የልጆቿን ግንባር በመስቀል ምልክት ያደረገችባቸው ሲሆን ይህም ለልጆቿ ጥምቀት ሆኖላቸው ተገኘ፡፡ ቅድስት ሣራ ሀገሯ አንጾኪያ ሲሆን ባሏ የከሃዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ መኰንን ነበር፡፡ ባሏም አስቀድሞ እንደ እርሷ ክርስቲያን ነበር ነገር ግን ንጉሡን በመፍራት ሲክድ እርሷ ግን በእምነቷ ጸናች፡፡ ባሏም ‹‹እኔ ንጉሡን ፈርቼ ነው እንጂ በልቤ ክርስቶስን አመካለሁ›› ይላት ነበር፡፡ ሁለት ልጆቿንም ስትወልድ የክርስትና ጥምቀትን ልታስጠምቃቸው አልቻለችም፡፡ ምክንያቱም በአንጾከያ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ወድመው ነበር፡፡ ወደ እስክንድርያ አባ ጴጥሮስ ጋር ሄዳ ልጆቿን ልታስጠምቃቸው አሽከሮቿን ይዛ ተነሣችና በመርከብ ተሳፈረች፡፡ በመሀል ኃይለኛ ማዕበል ተነሥቶ መርከቢቱ ልትሰጥም ሆነ፡፡ ቅድስት ሣራም ልጆቿ ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ በማለት ጸሎት ካደረገች በኋላ የቀኙን ጡቷን በምላጭ ቀዳ በደሟ የልጆቿን ግንባር በመስቀል ምልክት አደረገችባቸው፡፡ በጀርባቸውና በደረታቸውም ላይ እንዲሁ አድርጋ በባሕሩ ውስጥ አጠመቀቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ታላቅ ፀጥታ ሆነና ማዕበሉ ጠፋ፡፡ ቅድስት ሣራ እስክንድርያ አገር ደርሳ ልጆቿን ልታስጠምቅ ከአባ ጴጥሮስ ዘንድ አቀረበቻቸው፡፡ አባ ጴጥሮስም ሌሎች ብዙ ልጆችን እያጠመቀ በተራ ደግሞ የቅድስት ሣራን ልጆች ሊያጠምቅ ሲል ውኃው እየረጋበት እምቢ አለው፡፡ እስከ ሦስት ጊዜም እንዲሁ ሆነ፡፡ ምን እንደሆነ ቅድስት ሣራን ሲጠይቃት ያደረገችውን በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡ እርሷም ፈርታ ‹‹ይቅር በሉኝ›› ብላ እግራቸው ላይ ወደቀች፡፡ አባ ጴጥሮስም ‹‹አይዞሽ አትፍሪ፣ ሃይማኖትሽ ፍጹም ነው፣ አንቺ ባጠመቅሻቸው ጊዜ በመለኮታዊ እጆ ያጠመቃቸው ባለቤቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው›› አሏት፡፡ ከእጃቸውም ሥጋ ወደሙን ከነልጆቿ ተቀብላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰች፡፡ የቅድስት ሣራ ባሏ ይህን ያደረገችውን ሲሰማ ተቆጥቶ ሄዶ ለንጉሡ ከሰሳት፡፡ እርሷንም ‹‹ልታመነዝሪ ነው እስክንድርያ የሄድሽው›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹የክርስቶስ ወገን የሆኑ ክርስቲያኖች አያመነዝሩም እናንተ ጣዖት አምላኪዎች ናችሁ አመንዝራዎች›› አለችው፡፡ ከሀዲውና ጨካኙ ዲዮቅልጥያኖስም እጆቿን የኋሊት አሥሮ ሁለቱን ልጆቿን በሆዷ ላይ አድርጎ ሦስቱንም በእሳት አቃጠላቸው፡፡ ቅድስት ሣራም ሚያዝያ 25 ቀን ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ ከልጆቿ ጋር የሕይወትን አክሊል በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡ ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን። ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡ ምንጭ፡- የሚያዝያ ❷❺ ስንክሳር 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 🍃🍃🍃 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ እም እለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሒቅ እምንዑስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይፈኑ ለነ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እምይዜ ወእስከ ለዓለም አሜን። ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀይቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል። እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ። ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውንና ያጻፈውንም የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን። አሜን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖ . ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ ሚያዝያ ❷➍ ቀን 2011 ዓ.ም
Show all...