cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የቅዱሳን በዓት

በዚህ ቻናል ፩ መዝሙሮች በጽሁፍና አውዲዮ ይለቀቃል ፪ የህለቱ ስንክሳር ይለቀቃል ፫ መንፈሳዊ ግጥሞች ይለቀቃል ፬ ስብከቶች ይለቀቃሉ ፭ ስእለ አድኖ ወዘተ ይለቀቅበታል

Show more
Advertising posts
722
Subscribers
No data24 hours
-47 days
-2030 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

+ ድንገት የተበጠሰ ገመድ + የደብረ ዳሞ ገዳም በገመድ ብቻ የሚወጣ እጅግ ጥንታዊ ገዳም ነው:: ይህንን አቡነ አረጋዊ በዘንዶ የወጡትን ታላቅ ገዳም ለመውጣት በግንባታው ወቅት በአፄ ገብረ መስቀል የተሠራ ደረጃ ነበረው:: ሆኖም አቡነ አረጋዊ ደረጃውን ዳህምሞ (አፍርሰው) ብለው በማዘዛቸው እስከ አሁን ድረስ በገመድ የሚወጣበት ገዳም ሆኖአል:: የደብረ ዳሞ መውጫ ገመድ እጅግ ወፍራም ሲሆን እስከ አሁን ድረስ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተንጠላጥለው ወጥተው ወርደውበታል:: ይህ እጅግ ወፍራም ገመድ ለዘመናት ሲያገለግል ተበጥሶ ሰው ጥሎ አያውቅም:: በታሪክ የማይዘነጋና መሃል ላይ የተበጠሰበትና ሰው የጣለበት ቀን አለ:: (የዲያቢሎስ መተናኮል ነው የሚል አለ) በዚያ ቀን በተበጠሰው ገመድ ላይ የወረደው መንገደኛ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ነበሩ:: መነኮሳቱን ተሰናብተው በዚያ ገመድ ሲወርዱ ተበጥሶ የማያውቀው ገመድ ድንገት ተበጠሰ:: ከላይ የሚያዩት አባቶች ቁልቁል እያዩ በድንጋጤ ጮኹ:: ሆኖም እግዚአብሔር ለጻድቁ የብርሃን ክንፍ ሠጥቶአቸው ከተበጠሰው ገመድ ተለይተው እንደ መልአክ በርረው ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ወርደው መሬት ላይ አረፉ:: ባረፉባት ሥፍራም ቤተ ክርስቲያን ተሠራባት:: ወዳጄ በሕይወትህ ድንገት የተበጠሰ ገመድ የለም? ሳትጠብቀው የተበጠሰ ገመድ ማንም ላይ ሳይበጠስ አንተ ላይ የጨከነ ገመድ የለም? ምን ዓይነት ገመድ አትበለኝ:: የእንጀራ ገመድ የኑሮ ገመድ የትምህርት ገመድ የፈለግኸው ገመድ በለው:: እሱን ተጠምጥመህ ይዘህ ወደ አንዳች ቦታ ለመድረስ የተማመንክበት ተስፋህን ሙሉ በሙሉ የጣልክበት ገመድ የለም? ድንገት ተበጥሶ ዙሪያው ገደል አልሆነብህም? ሰዎች ማንም ላይ ያልተበጠሰ ገመድ አንተ ላይ ሲበጠስ አይተው "ምኑ ዕድለ ቢስ ነው?" ብለው የተደነቁብህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከባሕር አደጋ ተርፎ ዕባብ የነደፈው እንዴት ኃጢአተኛ ቢሆን ነው?" ብለው በትዝብት ዓይን እንዲያዩህ ያደረገ በሕይወትህ ሳታስበው ተበጥሶ ዙሪያው ገደል የሆነ ሥፍራ ላይ የጣለህ የሕይወት ገመድ ይኖር ይሆናል:: በዕድልህ አትማረር በሕይወትህ ድንገት የሚበጠስብህ ገመድ የምትወድቅበት ሳይሆን ክንፍ አውጥተህ የምትበርበት ነው:: ፈጣሪ የተማመንክበትን የምታየውን ገመድ እንዲበጠስብህ ከፈቀደ ያላየኸውን ክንፍ ሊሠጥህ እንጂ ሊጥልህ አይደለም::  የሕይወትህን ገመድ የተበጠሰበትን ቀን "እግዚአብሔር ለመልካም አሰበው" ብለህ እንደ ዮሴፍ ታመሰግንበታለህ:: ገመድህን የሚበጥሰው ከገደል ሊጥልህ ሳይሆን በክንፍ አብቅሎ ሊተክልህ ነው:: የሚተክልህ በበረሃ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ነው:: ተራ ተክል የምትሆን እንዳይመስልህ:: የሃይማኖት ተክል (ተክለ ሃይማኖት) ትሆናለህ:: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ተክለ ወልድ ተክለ አብ ትሆናለህ:: አብ የተከለው ደግሞ አይነቀልም! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 24 2013 ዓ ም
Show all...
‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡ ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰) ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?›› ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ [email protected]
Show all...
+ ስንናደድ ለምን እንጮሃለን? + 🔥🍂🔥🍂🔥🔥🍂🔥🍂🔥 አንድ ብልህ አረጋዊ አባት በገዳም የሚኖሩ ደቀ መዛሙርትን ሰብስበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው :- "ስንናደድ ለምን እንጮሃለን? ሰዎች ሲበሳጩ ስለምን እርስ በእርሳቸው ይጯጯሀሉ?" ደቀ መዛሙርቱ ለጥቂት ደቂቃ ዝም ብለው ካሰቡ በኋላ ከመካከላቸው አንዱ ተነስቶ እንዲህ ሲል መለሰ :- "ስንናደድ መረጋጋት ስለሚያቅተን እንጮሀለን።" አረጋዊው አባትም ቀጠል አድርገው "አብሮህ ያለው ሰው ከአጠገብህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ስለምን ትጮህበታለህ? በለሰለሰ ድምፅ መነጋገር የማይቻል ነገር ነውን? ስትበሳጭ ስለምን ሌላኛው ሰው ላይ ትጮሀለህ?" ደቀ መዛሙርቱ በየተራ እየተነሱ የመሰላቸውን ኹሉ መለሱ ። ነገር ግን የአንዱም ደቀ መዝሙር ምላሽ እኚህን ብልህ አረጋዊ አባት ስላላረካቸው የራሳቸውን ጥያቄ እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ሁለት ሰዎች በሚበሳጩበት ሰዓት ልባቸው እጅግ ይራራቃል። ይህን ርቀት ለመቀነስ እና ለመደማመጥ ደግሞ የግድ መጮህ አለባቸው! አምርረው በተቆጡ መጠን በመካከላቸው ሰፊ መራራቅ ስለሚፈጠር ለመደማመጥ ይበልጡን መጮህ ግድ ይላቸዋል። ቀጠሉና አረጋዊው አባት ሌላ ጥያቄ አስከተሉ :- "ሁለት ሰዎች ሲዋደዱስ ምን ይፈጠራል? ከመጯጯህ ይልቅ በለሰለሰ ድምፅ ያነጋገራሉ። ለምን ካላችሁኝ ምክንያቱ ልባቸው በጣም ስለሚቀራረብ ነው! በመካከላቸው ያለው ርቀት ጥቂት ስለሚሆን እጅጉን እየተዋደዱ በመጡ ቁጥር ቃል ማውጣቱንም ትተው በሹክሹክታ ያወራሉ። በመጨረሻም መንሾካሾክም ሳያስፈልጋቸው ዓይን ለዓይን በመተያየት ብቻ ይግባባሉ።  እንዲህ ነው ሁለት የሚዋደዱ ሰዎች የሚቀራረቡት ።" "በምትከራከሩ ጊዜ ልባችሁ እንዲራራቅ አትፍቀዱለት፣ይበልጥ የሚያራርቃችሁንም ቃላት አትጠቀሙ! ምክንያቱም አንድ ቀን በመካከላችሁ ያለው ርቀት እጅግ ከመርዘሙ የተነሳ ዞሮ መመለሻው መንገድ ይጠፋባችኋል!" "ፍቅር ልብን የተረጋጋ እና ሕይወትን የሚሰጥ ሲያደርገው በአንጻሩ ጥላቻ ደግሞ የተረበሸ ያደርገዋል በዚህም ሌላውን የሚጠሉ ራሳቸውን ያሰቃያሉ! ከፍቅር በላይ ምን ጣፋጭ ነገር አለ?" "ለእኛ ያለህ የማይቋረጥ ፍቅርህ ከአባትም፣ ከእናትም ፣ ከሚስት እና ከባልም የሚበልጥ አቤቱ ፍቅር የሌለን ባሪያዎችህን ማረን አሜን!!!" ምንጭ :- አባ ዮሐንስ ክሮንስታት የተባሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባት እንደጻፉት ትርጉም :- ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ @menfesawigetem
Show all...
+++ አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ +++ "አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ "ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ "ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ "ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ❤) Deacon Henok Haile
Show all...
✞ ​ቡሄ_በሉ ✞ ቡሄ በሉ /2/ ሆ ልጆች ሁሉ ሆ የኛማ ጌታ ሆኦ  የዓለም ፈጣሪ ሆ የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ በደብረ ታቦር  ሆ  የተገለጠው  ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ     ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ ያዕቆብ ዮሐንስሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ አባቱም አለ  ሆ ልጄን ስሙት ሆ ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ       ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ     ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ በተዋህዶ  ሆ ወልድ የከበረው ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ   ሆ ወልደማርያም ነው ሆ ቡሄ በሉ  ሆ ቡሄ በሉ ሆ የአዳም ልጆች ሆ ብርሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ       ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት  ሆ እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት  ሆ ከአጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት  ሆ አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ       ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ ከተከመረው  ሆ ከመሶቡ ይውጣ  ሆ ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ  ሆ የተጋገረው ሆ  ሙልሙሉ ይምጣ   ሆ       ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ ባህላችሁን  ሆ ያዙ አጥብቃችሁ  ሆ ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ       ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ አባቶቻችን  ሆ  ያወረሱን ሆ የቡሄን ትርጉም  ሆ ያሳወቁን  ሆ እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን  ሆ ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን  ሆ   ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/   ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን ሆ  የሞሉብሽ ሆ በረከታቸው ሆ   ያደረብሽ ሆ ሁሌም እንግዶች ሆ  የሚያርፉብሽ ሆ ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ          ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ ለሐዋርያት ሆ  የላከ መንፈስ ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር  ሆ   እንድንታነጽ ሆ በቅን ልቦና ሆ  በጥሩ መንፈስ ሆ በረከተ ቡሄ  ሆ ለሁላችንይድረስ ሆ       ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና እንዲሁ እንዳላችሁ በምነት አይለያችሁ  በምነት ላመቱ በሰላም በምነት  ያድርሳችሁ በምነት ክርስቶስ በቀኙ በምነት  ያቁማችሁ  በምነት የመንግስቱ ወራሽ  በምነት ያድርጋችሁ  በምነት እንዲሁ እንዳለን በምነት  አይለየን  በምነት ለዓመቱ በሰላም  በምነት ያድርሰን  በምነት አማኑኤል በቀኙ  በምነት ያቁመን በምነት  የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርገን በምነት የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት በሁሉም ቤት/2/ ይግባ በረከት/2/ እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት ባህላችንን የአባቶች ትውፊት 3 #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ። ╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗ ✢    ✥ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖                                     ✥   ✢    ╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Show all...
#ቡሄ_በሉ #@mezmuredawit #@mezmuredawit
Show all...
✞ ደብረ ታቦር ✞ ደብረ ታቦር ተሞላ በግርማ ብርሃን ከበበው አሸብርቋል ረጅሙ ተራራ ክብሩ ሲያበራ ጴጥሮስና ያዕቆብ ደግሞም ዮሀንስ ክብሩ ሲያበራ ይዟቸው ተጓዘ የመረጣቸው ከፊታቸው ሳለ ድንገት ተለወጠ ኢየሱስ ሲያበራ ልባቸው ቀለጠ /አዝ===== ሙሴና ኤልያስ ከሱ ጋር ታያቸው ጴጥሮስ በተመስጦ ዳስ እንስራ አላቸው ልቡን የቀመሰ አይመችም ሌላ ክርስቶስ ነውና እውነተኛ ተድላ /አዝ===== በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነውና ስለመዳናችው ስሙት በፅሞና ሄዶ ሲመሰክር ከሰማይ ንጉሱ ከእየሱስ በቀር አላዩም ሲነሱ ተገለጠ በግርማ ሸሸ ጨለማ×፪ እንደ ፀሀይ ሲያበራ ማነው የማይፈራ×፪ ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ ሆ×፪ የተሰቀለው ሆ በክብር ይመጣል ሆ ሰማይና ምድር ሆ በቃሉ ያልፋል ሆ በማድጋችን ሆ ይቀመጥ ወይኑ ሆ ተግተን እንጠብቅ ሆ ቅርብ ነው ቀኑ ሆ ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና ×፪ የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን×፪ የቃሉን ሙልሙል ሆ እንመገበው ሆ የዜማን ችቦ ሆ እንድንለኩሰው ሆ የእምነት ደመራ ሆ ይደመርና ሆ ከርሞ እንዲያደርሰን ሆ እናመስግና ሆ ድምፅህን ሰማና በብሩ ህ ደመና ×፪ የቡሄው ብርሀን ለኛ በራልን ×፪ አመት አውደ አመት ድገምና አመት #Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ። ╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗ ✢    ✥ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖ ❖   @mezmuredawit     ❖                                     ✥   ✢    ╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝ ✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
Show all...
✞ ቡሄ_በሉ ቡሄ በሉ (፪) - - ሆ    ልጆች ሁሉ - - ሆ የኛማ ጌታ - - ሆ   የዓለም ፈጣሪ - - ሆ የሰላም አምላክ - -ሆ   ትሁት መሀሪ -ሆ በደብረ ታቦር - - ሆ   የተገለጠው -  ሆ ፊቱ እንደ ፀሐይ  - ሆ  በርቶ የታየው -ሆ ልብሱ እንደብርሃን -ሆ  ያንፀባረቀው -ሆ        ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/         የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/ ያዕቆብ ዮሐንስ-ሆ  እንዲሁም ጴጥሮስ-ሆ አምላክን አዩት - - ሆ ሙሴ ኤልያስ - ሆ አባቱም አለ - - ሆ ልጄን ስሙት - - ሆ ቃሌ ነውና - - ሆ የወለድኩት - - ሆ       ታቦር አርሞንኤም-ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው- ሆ ሰላም ሰላም - - ሆ የታቦር ተራራ - - ሆ ብርሀነ መለኮት - ሆ ባንቺ ላይ አበራ -ሆ       በተዋህዶ - - ሆ ወልድ የከበረው - ሆ የእግዚአብሔር አብ ልጅ - -  ሆ ወልደማርያም ነው -  -ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ ቡሄ በሉ - - ሆ የአዳም ልጆች - - ሆ ብርሃንን - - ሆ ተቀበሉ - -ሆ       አባቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ እናቴ ቤት - - ሆ አለኝ ለከት - - ሆ ከአጎቴም ቤት - - - ሆ አለኝ ለከት - ሆ ተከምሯል - - ሆ እንደ ኩበት - - ሆ       የዓመት ልምዳችን - - ሆ ከጥንት የመጣው - - ሆ ከተከመረው -  ሆ ከመሶቡ ይውጣ - ሆ ከደብረ ታቦር - - ሆ  ጌታ ሰለመጣ -  ሆ የተጋገረው - ሆ  ሙልሙሉ ይምጣ -  ሆ       ኢትዮጵያውያን - -ሆ  ታሪክ  ያላችሁ - ሆ ባህላችሁን -  ሆ   ያዙ አጥብቃችሁ - ሆ ችቦውን አብሩት -ሆ  እንዳባቶቻችሁ -ሆ ምስጢር ስላለው -ሆ ደስ ይበላችሁ -ሆ       አባቶቻችን - - ሆ  ያወረሱን - - ሆ የቡሄን  ትርጉም - - ሆ  ያሳወቁን - - ሆ እንድንጠብቀው - ሆ  ለእኛ የሰጡን - ሆ ይህን ነውና - - ሆ  ያስረከቡን - - ሆ       ለድንግል ማርያም ሆ  አሥራት የሆንሽ ሆ ቅዱሳን ጻድቃን - - ሆ  የሞሉብሽ - - ሆ በረከታቸው - - ሆ   ያደረብሽ - - ሆ ሁሌም እንግዶች - ሆ  የሚያርፉብሽ -ሆ ሀገረ እግዚአብሔር -ሆ  ኢትዮጵያ ነሽ ሆ       ለሐዋርያት - - ሆ  የላከ መንፈስ - - ሆ ዛሬም ለኢትዮጵያ -ሆ  ጸጋውን ያፍስስ ሆ በበጎ ምግባር -  ሆ   እንድንታነጽ - - ሆ በቅን ልቦና - ሆ  በጥሩ መንፈስ - - ሆ በረከተ ቡሄ - ሆ  ለሁላችን ይድረስ -  ሆ       ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና በጋሽዬ ቤ   ድገም እና ዓመት ድገም እና ያውርድ በረከት  ድገም እና ዓመት ድገም እና ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና       እንዲሁ እንዳላችሁ - -በፍቅር  አይለያችሁ - - በፍቅር ላመቱ በሰላም - - በፍቅር  ያድርሳችሁ - - በፍቅር ክርስቶስ በቀኙ - - በፍቅር  ያቁማችሁ - - በፍቅር የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር  ያድርጋችሁ - - በፍቅር እንዲሁ እንዳለን - - በፍቅር  አይለየን - - በፍቅር ለዓመቱ በሰላም - - በፍቅር ያድርሰን - - በፍቅር አማኑኤል በቀኙ - - በፍቅር ያቁመን - - በፍቅር የመንግስቱ ወራሽ - - በፍቅር ያድርገን - - በፍቅር የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2) እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት የአስራት አገር የአበው ቀደምት የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
Show all...
​​ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል? ተወዳጆች ሆይ ሕልመ ሌሊት ከሚከሰትብን ምክንያቶች ዋና ዋናዎችን ከዚህ በታች እናያለን፡፡ 1ኛ/ በአጋንንት ይከሰታል በጣም የሚገርመው በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) የተፈተናችሁ እስቲ ልብ በሉ፡፡ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሳትገቡ በዓለም ሳላችሁ ብዙም አይከሰትም፡፡ ቢከሰትም ለአቅመ-አዳምና ለአቅመ ሔዋን በደረስንበት ወቅት በሥጋ ባህሪያችን ይከሰታል፡፡ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ገብተን በተግባር መኖር ስንጀምር ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በተደጋጋሚ ይመታናል፡፡ በተለይ ወንዶችን ቋሚ ደንበኞች ያደርገናል፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ጸበል እንዳንጠመቅ፣ ቤተ ክርስትያን ገብተን ጸሎት እንዳናደርስ፣ ከመለኮታዊው ማዕድ እንዳንቋደስ /ቅዱስ ቁርባን እንዳንቀበል/ ከሱባኤ ዋሻ ለማስወጣት ከሚጠቀምበት ዋንኛ ማሰናከያ መፈተኛው ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ነው፡፡ አባቶቻችን ‹‹ተጻቦዖ›› ይሉታል ‹‹ተጻብዖ›› ማለት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን መጣላትን ያመለክታል፡፡ እኛ ሀገር ሰላም ብለን በተኛንበት ሰይጣን በማናየው መልኩ በሕልመ ሌሊት ስለሚጣባንና እኛ የማንፈልገውን ፈቃደ ሥጋ በማሳየት ፈትኖን ከሰውነታችን ፈሳሽ እንዲወጣ ስለሚያደርግ ‹‹ተጻብዖ›› ብለውታል፡፡ በእውነት ከዚህ በላይ ምን ጸብ አለ? ሰው የማይገላግለን፣ሰው የማይደርስልን ፣ጮኸን የማናመልጠው ጠብ፡፡ ተወዳጆች ሆይ በሱባኤ ላይ ሆነን አጋንንት በሕልመ ሌሊት ቢፈትነን ሱባኤያችን አይፋረስም፡፡ ሕልመ ሌሊት ስለመታን ሱባኤያችን አይቋረጥም፡፡ ምናልባት በዋሻ ውስጥ ሱባኤውን የያዝን ከሆንን ለአንድ ቀን ከደጅ እንሆናለን አልያም ሰውነታችንን ታጥበን ተመልሰን ልንገባ እንችላለን፡፡ ይህን የሚወስነው የገዳሙ የአባቶች ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ በሱባኤ ጊዜ በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ ብንፈተን ሊደንቀን አይገባም፡፡ ይልቁንም ከአጋንንቱ ጋር በስውርና በገሃድ እየተዋጋን ስለሆነ ደስ ሊለንና በጸሎት ልንዋጋው ይገባል፡፡ ሰይጣን ሕልመ ሌሊትን (ዝንየትን) ለጸሎት ማስታጎያነት ይጠቀምበታል፡፡ ሌሊት ጸሎት ካስለመድን ከመነሳታችን በፊት ሕልመ ሌሊት ይመታናል፡፡ ከዛ በኋላ ተነስተን መጸለይ ይከብደናል፡፡ ከሰውነታችን ፈሳሽ ስለወጣ፤ ጥሩ ስሜት ስለማይሰማን ‹‹ጠዋት ታጥቤ እጸልያለሁ›› በማለት ጸሎታችንን እናስተጓጉላለን፡፡ ለዚህ መፍትሄው በፍፁም ጸሎታችንን አለመተው ነው፡፡ በዚያ በሌሊት ሙሉ ሰውነትን መታጠብ ስለሚከብድ ከቻልን ፈሳሽ የወጣበትን እርጥበት የተሰማንን ቦታ ታጥቦ መጸለይ፡፡ ሴቶችም አንቀጸ ሥጋችሁን አሊያም እጃችሁን በመታጠብ ጸሎታችሁን መቀጠል፡፡ ሰይጣን የራሳችንን ሰውነት እየተጠየፍን ጸሎት እንድንተው ነውና የሚሻው በምንም ምክንያት ጸሎት መተው የለብንም፡፡ እንኳን በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ተመትተን ቀርቶ በጥሩ ሰዓት ማናችውንም ንፁሆች አይደለንም፡፡ የሚገርመው የማያፍረው ሰይጣን በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ቤተክርስትያን ገብቶ ይፈትነናል ማለት ሳይሆን፤ እኛ ላይ ያለው አጋንንት በስውር ለዚህ ፈተና ሊዳርገን ይችላል፡፡ ቤተ ክርስትያን ለንግሥ አዳር ስንሄድ አባቶች አትተኙ የሚሉን አንድም ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ሊመታንና ሊፈትነን ስለሚችል ነው፡፡ ለአንድ ቀን ሌሊት ቤተ-ክርስትያን ጊዜያችንን በጸሎት ብናሳልፍ ካልሆነ ማህሌቱንና ሰዓታቱን ብንሰማ ይበልጥ ጥቅም ስላለው አለመተኛቱ ይመረጣል፡፡ 2ኛ/ የዝሙት መንፈስ ካለብን ይቀጥላል ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur
Show all...