cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አርከለዲስ | Arkeledis Media

√ ይህ የደብረ ይድራስ ሽማጎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካውንት ነው። 1000057909769 ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ እያላችሁ የቻላችሁትን አበርክቱ። 🔗 https://www.youtube.com/@Arkeledis_21 🔗 https://www.facebook.com/Arkeledis21 @Arkeledis_21

Show more
Advertising posts
1 422
Subscribers
-124 hours
-27 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

*_++ የእናቶችን ቀን ባሰብኹ ጊዜ +++_* መጽሐፍ ማርያምን "የኢየሱስ እናት" እያለ ሲጠራት ምን ይሰማህ ይሆን? ብዬ እጠይቃለኹ። ☞ የዚህ ዓለም መሪዎችን ሚስቶች እየተንቀጠቀጥህ:- "ቀዳማዊት እመቤት - First lady" እያልክ በክብር ትጠራለህ የክርስቶስን እናት ድንግል ማርያምን እመቤቴ ለማለት ግን ይተናነቅሃል። ☞ ወላጅ እናትህን ከነፍስህ በላይ ትወዳለኽ እናትህ መልካም ብትሆን አጋንነህ÷ ባትሆን ፈጥረህ ሳትደክም ባገኘኽው አጋጣሚ ሁሉ ትናገራለህ። "እናትህን አክብር።" ብሎ ያዘዘ ደግነትን ከርኅራሄ አስተባብራ ስለ ያዘች በታላቁ መልአክ፦ “ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ።” (ሉቃ 1፥28) ተብሎ ስለተመሰከረላት፤ "ጌታ ብዬ አምኜዋለሁ" ስላልከው ስለ ክርስቶስ እናት ስለ ድንግል ማርያም መልካምነት መናገር ግን እንደ ቋጥኝ ይከብድሃል። ☞ አንተ ስለ እናትህ መልካም ነገር ሲነገር ደስ ይልሃል። "ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል።" ብላ እንድትናገር ሀብተ ትንቢት የሰጣት ክርስቶስ ስለ እርሷ ክብር (አንተ? ክርስቶስን ከመውለድ በላይ ምን ክብር አለ?) ብትናገር ንጽሕት: ክብርት: ብፅዕት እያልክ ብታመሰግናት ቅር የሚለው ይመስልሃልን? ☞ አንተ ክርስቶስን "አምላኬ ጌታዬ በማለቴ ዕድለኛ ነኝ" ትላለህ። ድንግል ማርያም ግን "ጌታዬ አምላኬ" ብቻ ሳይሆን "ልጄ" እንደምትለው ግን ትዘነጋለህ። እግዚአብሔርን "ፈጣሪዬም ልጄም" የሚል ከእርሷ ሌላ ማን አለ? ☞ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ደጋግሞ "የኢየሱስ እናት" እያለ ሲጠራት ምን ይሰማህ ይሆን? ነገሩ የእርሱ ጌትነት: የባሕርይ አምላክነት: ሳይገባህ እርሷ "የኢየሱስ እናት" ስትባል ምን ሊሰማህ ይችላል? ☞ በልጇ ጌትነት የእርሷ ቃል የማይገልጠው ክብር እንደገባቸው አበው ቀደምት አንተም ሲገባህ "ሌሎች ሴቶችን ጻድቃንን ሰማዕታትን ወለዱ ብለን እናከብራቸዋለን: እርሷን ግን አምላክን ወለደች ብለን እናከብራታለን።" እያልክ ትዘምራለለህ። ለዚያ ያብቃህ!! ክርስቶስ ሆይ የእናትህን ፍቅሯን በልቡናችን: ጣዕሟን በአንደበታችን አሳድርብን!!! ☞ የአምላክ እናት ሆይ እናትነትሽ አይለየን!! ቢትወደድ ወርቁ የእናቶች ቀን
Show all...
ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Show all...
*_<<በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ>>_* "ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡" *(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)* "በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው" *(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)*
Show all...
ፎቶ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Show all...
⛪የኪዳን ትምህርት ኅቡአት አንድምታ ትርጓሜ* 🎥መምህር ነቅዓጥበብ ከፍያለው ♥️ኪዳን እና ድምጠው
Show all...
የ ኪዳንና ትምህርተ ኅቡአት አንድምታ ትርጓሜ ክፍል አንድ በ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው

በሰሙነ ሕማማት የሚተረጐም የኪዳንና ትምህርተ ኅቡአት ትርጓሜ ሲሆን ይህ ትርጓሜ በ 2015 ዓ.ም መካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የተተረጎመ ነው

ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Show all...
ኦዲዮ ከአድነኒ እግዚኦ እመ ብእሴ እኩይ
Show all...
_*13ቱ ሕማማተ መስቀል*_ 1. አክሊለ ሦክ (ወደ 70 የሚደርስ ራስ ቅሉ ላይ የተተከለ የብረት እሾኽ የያዘ ዘውድ ወይም አክሊል) 2. ተኰርዖተ ርእስ (ራሱን በዘንግ ወይም በዱላ መመታቱ/መቀጥቀጡ) 3. ተጸፍኦ መልታሕት (ጉንጩን ወይም ፊቱን በጥፊና በቦክስ መመታቱ) 4. ሰትየ ሐሞት (ተጠማሁ ብሎ ስለ ውሃ ፋንታ መራራ ሐሞትን መጠጣቱ) 5. ወሪቀ ምራቅ (በፊቱ በአካሉ ላይ በንቀትና በጥላቻ በመሳለቅ በመዘባበት ፊቱ ላይ ምራቅ መትፋታቸው) 6. ተቀስፎ ዘባን (6,666 ጊዜ የሾለ አጥንትና ብረት በታሰረበት ጅራፍ መገረፉ) 7. ተአስሮ ድኅሪት (የፍጥኝ ወደኋላ መታሰሩ ...በአፍ ጢሙ መደፋቱ) 8. ፀዊረ ጒንደ ዕፀ መስቀል (የሚሰቀልበትን የእንጨት መስቀል መሸከሙ) 9. ሳዶር (ቀኝ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 10. አላዶር (ግራ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 11. ዳናት (ቀኝ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 12. አዴራ (ግራ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር) 13. ሮዳስ (ደረቱ ከመስቀሉ ጋር እንዲጣበቅ ከታሰረበት ሽቦ ጋር ልቡ ላይ የተቸነከረ...) አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እሊህ ናቸው ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በመቁጠር መናገር ነው እንጂ የመከራው ብዛት የስቃዩ ጽናት በቁጥር የሚገለጽ ሆኖ አይደለም!!! ጌታ ሆይ! ሕማምህ ይፈውሰን ዘንድ ቁስልህ እንዲሰማን ማስተዋልን ስጠን እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም አሜን! መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል ምንጭ ፦ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ
Show all...