cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖

ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559 Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia. Email- nurotekore@gmail. Com ⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Show more
Advertising posts
8 336Subscribers
+2624 hours
+1867 days
+76830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

📘 Legal Protection of Databases 👤 Mark J. Davison (Author) #️⃣ #Database 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
📘 How the Law Works — 4th Edition 👤 Gary Slapper (Author), Routledge (Publisher) #️⃣ #Beginner 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
📓 Equity and Trusts: 6th Edition 👤 Alastair Hudson (Author), Routledge-Cavendish (Publisher) #️⃣ #Equity #Trusts 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
📓 The Law of Armed Conflict: International Humanitarian Law in War 👤 Gary D. Solis (Author), Cambridge University Press (Publisher) #️⃣ #War #HumanitarianLaw 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
📘 International Human Rights Law 👤 Olivier De Schutter (Author), Cambridge University Press (Publisher) #️⃣ #HumanRights 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
👍 1
📘 Principles of Land Law: 4th Edition 👤 Martin Dixon (Author), Cavendish Publishing (Publisher) #️⃣ #LandLaw 🔗 t.me/lawbookshelf
Show all...
ሰ/መ/ቁ. 85979 - በአንድ ወቅት የአንድ ሃይማኖት ተከታይ የነበረ ሰው ከሃይማኖት ተቋሙ በተሰጠው ልዩ ፈቃድ ለስርዓተ ቀብሩ መፈጸሚያ እንዲሆነው በቅጥር ግቢ ውስጥ የመቃብር ቤት አሰርቶ ከመሞቱ በፊት ሃይማኖቱን ቢቀይር ባሰራው መቃብር ቤት “የመቀበር መብት” አይኖረውም፡፡
Show all...
👍 4🥰 1
Share Ethiopia's transitional justice policy .pdf
Show all...
👍 2
አጣሪ ጉባዔው በ19 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብ እና አቅጣጫ አስቀመጠ። -------------------------------------------------------------------------- የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ሚያዝያ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ጥናት እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት ጉዳዮች መካከል በድምሩ 19 በሆኑ የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ 15ቱ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል። በሌላ በኩል ከመሬት ይዞታ ክርክር ጋር በተያያዘ በተሰጠ ውሳኔ ላይ "ሕገ መንግሥታዊ የንብረት መብቴ ተጥሷል" በሚል በቀረበ መዝገብ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት ጉባዔው አቅጣጫ አስቀምጧል። በመጨረሻም ጉባዔው በሦስት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል በሚል ለትርጉም የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል። እነዚህ በጉባዔው ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላኩ የውሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው 3 ጉዳዮችም የመጀመሪያው ከሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 9(4) "ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የሀገሪቱ ሕግ አካል ናቸው እንዲሁም በአንቀፅ 84(4) "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦኟን ጥቅም የማይጻረሩ ዓለም አቀፍ ሕጐችና ስምምነቶችን ማክበር የሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ተጥሷል በሚል ሲሆን ሌሎች የሕገ መንግሥት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል በሚል ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላኩ የውሳኔ ሐሳብ የተሰጠባቸው 2 አቤቱታዎች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 40 የተረጋገጠው የንብረት መብት ተጥሷል በሚል የቀረቡ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል ፡፡ #CCI
Show all...
👍 7 1
የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅን በማስፈራራት ገንዘብ የተቀበሉ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅን በወንጀል ትፈለጋለህ በማለት አስፈራርተው ገንዘብ ተቀብለዋል ተብለው ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ሙስና ወንጀል የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች እስከ 13 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጡ ተወሰነ። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ የወሰነባቸው ተከሳሾች 1ኛ ጫላ መገርሳ፣ ለሊሳ በቀለ፣ ዳዊት ጉደታ፣ ዮሃንስ ደረጄ እና ብርቱካን ለታ ናቸው። የክልሉ ፍትህ ቢሮ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ ና ለ እንዲሁም የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 2 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና በአዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀጽ 29/1 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን ጠቅሶ በ2015 ዓ.ም ክስ መስርቶባቸው ነበር። በክሱ ዝርዝር ላይ እንደተመላከተው፤ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌሎች ለማስገኘት በማሰብ በመጋቢት 19 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በሸገር ከተማ ገፈርሳ ክፍለ ከተማ አካባቢ በሚገኝ የኖክ ነዳጅ ማደያ ስራ አስኪያጅ የሆነ የግል ተበዳይን የፀጥታ አካላት ነን፣ በወንጀል ትፈለጋለህ በማለት መንገድ ላይ በማስቆም ከውጭ ወደ ውስጥ እንዳይታይ አድርገው በስቲከር ሸፍነው ወደአዘጋጁት የቤት መኪና ውስጥ በማስገባት ወደ መልካ ናኖ ክ/ከ አንፎ ወደ ተባለ አካባቢ ወስደውታል። ከዚህም በኋላ የሞተ ሰው ፎቶ ለግል ተበዳዩ በማሳየትና በመሳሪያ በማስፈራራት ግማሽ ሚሊየን ብር እንዲያመጣና እንደሚለቁት በመግለጽ ገንዘቡን ካልከፈለ ደግሞ ወደ ጦር ኃይሎች እንወስድኃለን በማለት ገንዘብ እንዲከፍል መጠየቃቸውን ተከትሎ የግል ተበዳዩ በባንክ ሂሳቡ ውስጥ 100 ሺህ እንዳለው ገልጾ መልስ መስጠቱ በክሱ ተመላክቷል። በዚህም ጊዜ 1ኛ ተከሳሽ ባለቤቱ በሆነችው በ5ኛ ተከሳሽ የባንክ ሂሳብ በሞባይል ባንኪንግ የግል ተበዳዩ 100 ሺህ ብር እንዲያዘዋውር ያደረገና ቀሪውን 400 ሺህ ብር እንዲያመጣ በማስጠንቀቅ የለቀቁት መሆኑን ዐቃቤ ሕግ በክሱ ላይ የጠቀሰ ሲሆን፤ በህገወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ደግሞ 5ኛ ተከሳሽ ከአንደኛ ተከሳሽ ጋር በመሆን ምንጩን ለመደበቅ በማሰብ በተለያዩ መጠኖች ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅም ያዋሉት መሆኑ በክሱ ዝርዝር ላይ ሰፍሯል። ተከሳሾቹ ክሱ ከደረሳቸው በኋላ ድርጊቱን ክደው በመከራከራቸው ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮችን፣ አስረጂና ገላጭ የሰነድ ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርቧል። ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ቢሰጥም ተከሳሾቹ በተገቢው መከላከል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል። ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግን ቅጣት ማክበጃ አስተያየትንና የተከሳሾቹ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት በመያዝ 1ኛ ተከሳሽን በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል። ከ2ኛ እስከ 4ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾችን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ7 ዓመት ጽኑ እስራትና በ3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ የወሰነው ፍርድ ቤቱ 5ኛ ተከሳሽን በሚመለከት በ1 ዓመት እስራትና በ1 ሺህ ብር ገንዘብ እንዲቀጡ ወስኗል። በታሪክ አዱኛ ((ኤፍ ቢ ሲ)
Show all...
4👍 2