cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/የሰ/ት/ቤ/ማ/መ/ማኅበረ ቅዱሳን አ.አ ማዕከል መርሐ ግብራት ፥ #የቅዱሳን_ታሪክ #መጽሐፍ_ትረካ #መጽሐፍ_ጥቆማ #ብሒላተ_አበው https://t.me/amstkilogbigubae በዩትዩብ ቤተሰብ እንሁን ☟☟☟https://www.youtube.com/@5kilogbigubae

Show more
Advertising posts
1 998
Subscribers
No data24 hours
+17 days
+2330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ልደቱ በገሊላ ባሕር ዳር፣ #በቤተሳይዳ ሲሆን አባቱ ከሮቤል ነገድ የሆነ ዮና የሚባል ሰው ነው። ሪዛምና በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ የነበረ ይህ ሰው የመጀመሪያ ስሙ #ስምዖን ይባላል፣ ይህም በእናቱ ነገድ ስም የወጣለት ነው። በጐልማሳነቱ እድሜም ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ በማሥገር ያሳልፍ ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀንም በገሊላ ባሕር አጠገብ ዓሳ በማጥመድ ላይ ሳሉ ጌታችን "ሰው አጥማጆች አደርጋቹ ዘንድ ተከተሉኝ" አላቸው። እነሱም መረባቸውን ትተው፣ ታንኳቸውን ጥለው ተከተሉት [ማቴ ፬ ÷ ፲፰]። በዚህ ጊዜ ስምዖን እድሜው ፶፭  ነበር። ስምዖን፣ በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን "ማን ትሉኛላችሁ?" ብሎ በጠየቀ ጊዜ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ በመመስከሩ ጌታችን አንተ #ጴጥሮስ ነህ አለው፣ ይህም በግሪክ ቋንቋ ዐለት ማለት ሲሆን፤ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል [ማቴ ፲፮ ÷ ፱፰]። ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ/የምሥጢር ሐዋርያት አንዱ ነው። ይህ ሐዋርያ «ከደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ አለው፣ እንዲሁ ሐዋርያቱንም ወክሎ ይናገር ነበርና» የሐዋርያት #አፈጉባኤ ተባለ [ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫ ፣ ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰ ]። «መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ የባሕርይ ልጁ መሆኑን መስክሯልና» #የመንግስተ_ሰማይ_ቁልፍ ተሰጠው [ማቴ ] ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። ይህም፤ በሽምግልና አባትነቱ፣ ጌታ በቂሳርያ በሰጠው ቃል ኪዳን፣ የሐዋርያት አፈ ጉባዔ ሆኖ ይናገር ስለነበር፣ በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጥኤም፣ በሶርያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ሰብኳል። እንዲሁም ሁለት መልእክታትንም ጽፏል። #ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ የኪልቂያ ዋና ከተማ በሆነች በ #ጠርሴስ፣ ከዕብራዊያን ዘር፣ ከብንያም ነገድ ተወለደ። የመጀመርያ ስሙ ሳውል ነው። በአባቱ ሮማዊም ነበር [አባቱ የሮም ሰራተኛ ሲሆን፣ ሮማውያን ደግሞ ለሚሰሩላቸው ዜግነትን ይስጡ ነበርና]። በወጣትነቱም በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገብቶ፣ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቆ ተምሯል። በዚህም በ፴ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆነ። ለኦሪት ከነበረው ቅናት ይተነሳ ክርስቲያኖቸን እጅግ አምርሮ ይጠላ፣ ያሳድዳቸውም ነበር።  በ፴፪ ዓመቱ ከሊቀ ካህናቱ እጅ ክርስቲያኖቸን ሊያጠፋ የሚያስቸለውን ደብዳቤ ተቀብሎ፣ ወደ ደማስቆ በመሄድ ሳለ በታላቅ ብርሃን ተመታ። መድኃኒታችንም በብርሃኑ መሃል ተገልጦለት "...አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ብሎ ተናገረው [ሐዋ ፱፥፩]። በዝያም የሐዋርያው ዓይኖች ማየት ስላልቻሉ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ። በሶስተኛው ቀን ሐናንያ የሚባል ደቀ መዝሙር በጌታ ትዕዛዝ ወደሱ መጥቶ ዐይኑን ፈወሰው፣ አጠመቀውም። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም ይሸከም ዘንድ የተመረጠ ዕቃ» ሆነ [ሐዋ ፱፥15]። ብረሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የኦሪትም የወንጌልም ሊቅ የነበር፣ ምድርን ሙሉ ዞሮ ወንጌልን የሰበከ፣ እስከ ሶስተኛው ሰማይ መነጠቅ የቻለ፣  ዐስራ አራት መልእክታትን የጻፈ ድንቅ ሃዋርያ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ነው። #ዕረፍት በ ፶፬ ዓ.ም ኔሮን በሮም ነገሠ። በ፷፬ ዓ.ም ይህ ንጉስ በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ነበርና ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም #ተሠይፎ ዐረፈ። ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች "አንተ ትረፍልን" ብለው ቅዱስ ጴጥሮስ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት። ቅዱስ ጴጥሮስ በመንገዱ እያዘገመ ሳለ አንድ ጐልማሳ መስቀል ተሸክሞ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ። እየቀረበ ሲመጣ ጌታችን መሆኑን ተረዳ። እርሱም "ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?" አለና ጠየቀው። "ዳግም በሮም ልሰቀል" አለው። በዚህ ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ አዘነና እንደገና ወደ ሮማ ተመለሰ። በዚያም እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት #ቁልቁል_ተሰቅሎ ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ዐርፈ። ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ ረድኤትና በረከታቸው ይደርብን🙏🏾🙏🏾
Show all...
🙏 7 6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ!!! እንኳን ለበዓለ ዕረፍታቸው አደርሳቹ !!!
የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፣ እሰከ ዘላለምም ይኖራል። ምሳ 10፥7 ፣ መዝ 112፥6
፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
4🔥 2
👏ተመራቂ ተማሪዎች ስንመጣ ጋውን ለብሰን ይሁን!
Show all...
👍 1
✝ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተመራቂዎች እንኳን አደረሳችሁ።ለዚህ ያበቃችሁ ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን🙏 ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
Show all...
23🥰 2
የሐዋርያት ስራን በሐዋርያት ጾም አጠራራቸው ካማረ ቦታ አልነበረም፣ የተጠሩትም ከንጉሳውያን ቤተሰብ አይደለም፣ የጠራቸውም አንድ በኢየሩሳሌም ጎዳና እየተመላለሰ የሚሰብክ በስጋ ላየው ጉስቁል የመሰለ እረኛ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። ይህ መለካም እረኛ እነዚያን ሰዎች ከገሊላ አውራጃ ሰበሰባቸው ፣ "ሐዋርያት" ብሎም ጠራቸው። ያእረኛ አይሁድ ሰቅለው በገደሉት በሶስተኛው ቀን ከሞት ተነሳ። ስለ ቃሉ የታመነ ነውና በተነሳ በኅምሳኛው ቀን ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱሳን ላከላቸው፣ እነሱም በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ የምስራቹን ቃል ለዓለም ሰበኩ። እኛም ዜና ስራቸውን፣ ታሪከ ገድላቸውን እያነበብን ሳምንት አለፈን። በአበው በሂል የበረታን መሸለም ወግ ነውና፣ በዚህም በመጀመሪያ ሳመንት Tg Bot ላይ የተለቀቁ ጥያቄዎችን የመለሱ እነሆ ፩ኛ @yordyteklu21 {25 birr card} ፪ኛ @habib_georgis {15 birr card} ፫ኛ #likeness {10 birr card} አሸናፊዎች በዚህ @Heban7 ያናገሩን ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ስነ ፅሁፍ ንዑስ ክፍል
Show all...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! "ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር መዝ. 118፥26 🎓🎓🎓🎓እንኳን ደስ አላችሁ።🎓🎓🎓🎓 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ማዕከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል ግቢ ጉባኤያት ማስተባበሪያ ክፍል ስር ሲማሩ የነበሩ የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ላይ ከጠዋቱ ከ2:30 - 7:00 ሰዓት ያስመርቃል። እርስዋም በዕለቱ የመርሐ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል። በዕለቱ ➡️ ጸሎተ ወንጌል ➡️ ትምህርት ወንጌል ➡️ የበገና ዝማሬ በተመራቂ ተማሪዎች ➡️ ወረብ በተመራቂ ተማሪዎች ➡️ ቅኔ በተመራቂ ተማሪዎች ➡️ የአደራ መስቀል ለተመራቂ ተማሪዎች ቦታ: ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ቀን: እሑድ ሰኔ 30 ጠዋት 2:30 ጀምሮ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን ©አራዳ ጉለሌ ወረዳ ማዕከል!
Show all...
1
#ዕቅበተ_እምነት በነገረ ቅዱሳን ላይ
ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ 1ኛ ጴጥ 3፥15
ክፍል ፩የቅዱሳን አማላጅነት : የቅዱሳን አማላጅነት ጥቅም እና በእግዚአብሔር የተወደደ ስለመሆኑ ✝  ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፊት ስለበደላችን ይለምኑልናል። ንጉስ አቤሜሌክ የነበዩን የአብርሃምን ሚስት ሊያገባት፣ ሊያውቃት በወደደ ጊዜ እግዚአብሄር ስለበደሉ መቅሰፍት አዘዘበት። ምህረት ሊያገኝ ቢወድ ግን አብርሃም እንዲጸልይለት እንዲህ ሲል አዞታል: "አሁንም ሴቲቱን ወደባልዋ መልስ እሱም ነቢይ ነውና ስላንተ ይጸልይልህ ትድናለህ"። በዚህም የተነሳ ቅዱሱ ነቢይ አብርሃም ምህረትን ከአምላክ እንዲማልድ፣ ለሀጢያተኛው ስርየት እንዲያሰጥም ሆኗል።  [ዘፍ 20÷ 1-18] ጻድቁ ቅዱስ ኢዮብም ወዳጆቹ በበደሉ ወቅት "...ባሪያዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ስንፍናችኹ እንዳላደርግባችኹ እቀበላለኹ..." [ኢዮ 42÷8] በማለት ለምህረት የፈጠነ የሆነ መሆኑን፣ በወዳጆቹ ምልጃም መማር እንደሚሻ አሳይቶናል። በእውነት ይህንንስ በእርሱ የማያምኑት እነ ፈርኦንም ሳይቀሩ እንዲህ መስክረዋል: "ፈርዖንም ሙሴንና አሮንንጉሥ ጠርቶ፦ ጓጕንቸሮቹን ከእኔ ከሕዝቤም እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ..." [ዘጸ 8፥8] ስለዚህ እንደ ፈርኦን በማመን አንካሳ የሚሆን፤ እንደ ንጉሱ አቤሜሌክ፣ እንደ ኢዮብ ወዳጆችም በኃጢያት የወደቀ ከእግዚአብሔር ምህረትን የምታሰጥ ትሩፋት እንደሌለው በማመን በትህትና የቅዱሳንን ምልጃ በመጠቀም ምህረትን ከእግዚአብሔር ያገኝ ዘንዳ አማናዊው የእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ ያዘናል። ✝ ከሕዝብ የምንቆጠር ሆነን በደል ባይኖርብን እንኳ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኙ ቅዱሳን እንዴት ከመቅሰፍት እንደሚያድኑን እንመልከት። ዳታን አቤሮን በሙሴ ፤ ደቂቀ ቆሬ በአሮን ላይ በምቀኝነት በተነሱባቸው ጊዜ እግዚአብሔር ተቆጥቶ: "ሁሉንም ባንዲት ጊዜ አጠፋለሁ" ቢላቸው። አንድ ሰው ኃጢአት ሰራ ብለህ በማህበሩ ሁሉ ላይ እባክህ አትቆጣ በማለት ቢማጸኑት እርሱ እግዚአብሔር አምላክም ዳታን አቤሮን  እና ደቂቀ ቆሬን ለይቶ ሲያጠፋ ሕዝቡን ግን በቅዱሳኑ ምልጃ ምሮታል። [ዘኁልቅ 16÷20-36] ✝ እስራኤል ጣዖትን ሰርተው ባመለኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን "ተወኝ እኒህን ሰዎች ላጥፋቸውና አንተን በሌላ ሕዝብ ልሹምህ"አለው። ሙሴም " አቤቱ ከመአት ወደ ምህረት ከቁጣ ወደ ትዕግስት ተመልሰህ ወገኖችህን ይቅር በላቸው። ልጆቻችሁን እንደ ሰማይ ኮከብ አበዛላችኋለሁ ፡ ይህችን ምድር ለዘለዓለም ይወርሷት ዘንድ ለልጆቻችሁ እሰጣለሁ ብለህ የማልክላቸው ባሮችህን አብርሃም፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን አስብ " በማለት ስለህዝቡ ዕርሱ ቅዱሱ ሙሴ የቅዱሳኑን የአብርሃምን፣ የይስሐቅን፣ የያዕቆብን ምልጃ ተጠቅሞ ህዝቡን ከጥፋት ታድጓል። ቅዱስ ዳዊትም ይህንን ሲመሰክር በመዝሙር 105 (106)÷23 " እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ" በማለት የሙሴን ምልጃ ለህዝቡ ድህነት ምክንያት መሆኑን በቅዱስ መንፈስ ተቃኝቶ ነግሮናል። ሙሴ ደግሞ መጽሐፍ እንደሚለው ቅዱሳን በአካለ ስጋ ከምድር ቢለዩ ጸጋቸው ተገፎ፣ ቅድስናቸው ጠፍቶ፣ ቃልኪዳናቸው ታጥፎ፣ እንደማይቀር በማወቅ በአጸደ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ተማጽኗል።   ቅዱስ መጽሐፍም "ከመረጥሁት ጋር ቃልኪዳኔን አደረግሁ"መዝ 88(89)፥3 "አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ ለሚወዱህና ትዕዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንንና ምህረትን የምትጠብቅ" ነህምያ 1፥4-7 በማለት ያስረዳናል። ጌታችንም  በቅዱስ ወንጌል ይህንኑ ሲያረጋግጥልን  "በሰማይ እግዚአብሔርን እንሚያገለግሉ መላዕክት ይሆናሉ"ብሎ ነግሮናል ማቴ 22÷27-30። እንዲሁም ከትንሳኤ ቀድሞ ያለው ዘመን በዓለመ ሥጋም በዓለመ ነፍስም የስራ ዘመን ስለመሆኑ "መላዕክት ሁሉ ረቂቃን ሲሆኑ የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለተልዕኮ ይላካሉ"  በማለት ቅዱስ ጳውሎስም ያስረዳናል ዕብ 1፥14። ዳግመኛም ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ሳሉ መጸለይ  እንደሚችሉ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ " ሕጉን ስለጠበቁ ስለ እግዚአብሔር ቃል የሞቱትን ሰዎች አየሁ ፥ እነሱም እውነተኛ የባህርይ አምላክ አቤቱ ደማችንን በግፍ ያፈሰሱብን ሰዎች በምድር ከሚኖሩ ሰዎች ለይተህ አትበቀላቸውምን? አትፈርድባቸውምን? እስከመቼ ድረስ ትታገሳቸዋለህ? እያሉ በታላቅ ድምጽ ጮሁ" በማለት ይነግረናል።ራዕ 6፥9-11 እኛም አባታችንን ሙሴን ሌሎችን በቅዱሳን ምልጃ የተጠቀሙ ቅዱሳንን አብነት አድርገን፣ ይልቁንም አማናዊ ዘላለማዊ የሆነውን የቅዱስ መጽሐፍን ቃል አምነን በቅዱሳን ምልጃ በነርሱም ቃልኪዳን እንታመናለን። "የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች" [ያዕቆብ 5÷ 16] "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል: ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ፣ ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንድ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋም" [ማቴ 10÷ 40-42] እንዲል በረከትን በመሻት የማጠፋ ዋጋን ለማግኘት በቅዱሳን ምልጃ እንታመናለን። ✝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋዕለ ስጋዌው በሐዋሪየቱ ምልጃ የከነናዊቷን ሴት ጩኸት ሰምቶ በጋኔን የሚሰቃይ ልጇን ምሮላታል። ማቴ 5፥21-18 ስለእህቱ ማርታ ሀዘን አልአዛርን ከሞት አስነስቶታል። [ዮሐ11፥21-24] እንኳንስ ስለከበሩት ቅዱሳን ምልጃ ጌታችን ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው ስለእናቲቱ ሀዘን ልጇን [ማር 7፥25-29] ፤ ስለአባቱ ጸሎት ልጁን [ማቴ 9፥18፤ ዮሐ 4፥46] ፤ ስለአሳዳሪው ልመና ባሪያውን [ሉቃ 7 ÷ 2] ምሯል። ✝ ስለዚህም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላክ በዓለመ መላዕክት ከመላዕክት ጋር ህብረት ያገኙትን - በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን፤ በምድር የሚኖሩ- በአጸደ ስጋ- ያሉ በገድል በትሩፋት ያሸበረቁ ቅዱሳንን ምልጃ እንደሚቀበል ህይወት የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ህያው ምስክር ይሆናል። ክፍል ፪ ይቀጥላል...... ፭ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ትምህርት ክፍል ትምህርታዊ ስነ ፅሁፍ ንዑስ ክፍል
Show all...
8👍 3
Photo unavailableShow in Telegram
በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፣ ሉቃስ 24፥45
የሐዋርያት ስራን በሐዋርያት ጾም ቀን ፯ ምዕራፍ ፱ ከምእራፍ ፱ ለተወጣጡ ጥያቄዎች ከምሽቱ 3:00 ሰአት ላይ በ Telegram Bot ይጠብቁን🙏 Tg Bot = @amst_kilo_gibi_gubae_bot
Show all...
👍 4💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.