cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሃይማኖታችንስ✞?

✞የኦርቶዶክስ ቻናል✞ > የየዕለቱ ስንክሳር >ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎች ከነመልሱ > በቅርብ የጀመረው አስተማሪ ታሪኮች > መንፈሳዊ ዝማሬዎች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ > መንፈሳዊ ፊልሞች > መንፈሳዊ ትምህርቶችና የተለያዩ ፁፎች #ሁሉም_በየእለቱ

Show more
Advertising posts
959
Subscribers
No data24 hours
+27 days
-1330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

                        †                         🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊 🕊 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ 🕊 ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ ------------------------------------------------ ✞ [ ሰኞ ] - ማዕዶት ይባላል ፦ ማዕዶት ማለት መሻገር ፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከሲኦል ወደ ገነት ፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ✞ [ ማክሰኞ ] - ቶማስ ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ [ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱ ] ✞ [ ረቡዕ ] - አልአዛር ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ✞ [ ሐሙስ ]- አዳም ሐሙስ ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ✞ [ አርብ ] - ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ✞ [ ቅዳሜ ] - ቅዱሳት አንስት ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ✞ [ እሁድ ] - ዳግም ትንሣኤ ይባላል ፦ በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡ 🕊       እንኳን አደረሳችሁ        🕊 †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...
ስንሞትም ቢሆን ማድረግ ያለብን የሚለው ዝርዝር ባዶ የሚሆን አይደለም። ብዙዎቸችን ህይወታችንን የምንኖረው ሁሉንም ነገረ ማድረገ አለበኝ በሚል መርህ ይመስላል ማታ እንተኛለን ጠዋት እንነሳለን አንዝናናም ለራሳችን ጊዜ አንሰጥም ለምንወዳቸው ሰዎች፣ እንዲሁም ለ እግዚአብሔርም ጊዜ አንሰጠውም ሁሌ መስራት ያለብን ነገሮች አሉ እያልን ለራሳችን ጊዜ ስንነፍግ አንዱን ሰራን ስንል ሌላው ይተካል ሁሌም ቢሆን መደወል ያለብን ቦታ አለ መጨረስ ያለብን ነገሮች ይኖራሉ መስራት ያለብን ሥራ አለ። እንደዚህ አይኔት ዝርዝሮች ለስኬት ያስፈልጋል የሚሉ ሰዎች አሉ ምንም አይኔት ሰው ሁን ምንም አይኔት ሥራ ይኑርህ ከአንተ ና ከምትውዳቸው ሰዎች እንዲሁም ከሚወድህ እግዚአብሔር የሚበልጥ ነገረ የለም ሁሉንም ነገረ ማረግ አለብኝ የምትል ከሆነ ምቼም ቢሆን ውሳጣዊ ሰላም ልታገኝ አትችልም የምትወዳቸውንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም በፈጠረክ ጌታም ልትደሰትም ማስደሰትም አትችልም ( እህተ አላዛር ማርታ እጅግ ብዙ ሰትሰራ ጊዜ መስጠት ላለባት ነገረ ሳትሰጥ ስቀር አልተመሰገነችም እህቷ ማርያም ግን ለሁሉም እንደየአግባቡ ጊዜ ስትሰጥ ተመስግነበተአለች ለትውልዱም አርያ ሆና ስትወሳ ትኖራለች ስለዚህ ከሞትክ ብዋላ እድሜክ ለአልጋ በዳረገክ ጊዜ ፈተና በመጣ ጊዜ ጊዜ መስጠት ላለብክ ነገሮች ሳትሰጥ ቀርተክ በእርጅና ጊዜ ወዳጅን፣ በ ፈተና ጊዜ ሰላምህን፣ ረዳትህን፣ በሞትክ ጊዜ እግዚአብሔርን እንዳታጣ ተጠንቅቀከ ጊዜ መስጠት ላለብክ ጊዜ ስጥ ጊዜ ሰጥ። ስላነበብከው አመሰግናለው 👏። ጥያቄ የሞትህን ቀን አውቀሀው ከመሞትህ በፊት ምን ልታደርግ ትፈልግአለህ ? ምንስ ማስተካከል ትፈልግአለክ? ወዘተ የመሞቻ ቀን ዛሬ ነው ለመዳንም የምታስተካክልበት ቀንም ዛሬ ነው ስለዚህ ማስተካከል ያለብክን...........................ታውቃለህ
Show all...
🕊 ✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ †   ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ]  †   [ ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] 🕊  †  ሜልዮስ ሰማዕት  †   🕊 ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት ያሳለፈ : በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው:: ይሕችን ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም ለበርካታ ዓመታት ተጋድሏል:: በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሳታል:: የአባ ሜልዮስ ጸጉሩ እስከ እግሩ : ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር:: እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: ፪ቱ ቅዱሳን አምላካቸውን እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም ቅንነት አገልግለዋል:: ከቆይታ በኋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት:: ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው ደበደቡት:: ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም በሰይፍ አንገታቸውን መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ፲፭ [15] ቀናት ካሰቃዩት በኋላ በዚህች ቀን በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው ገድለውታል:: ጻድቅና ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል:: ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ ወደነርሱ መልሶባቸው ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል:: ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ በረከትን ያካፍለን:: [ † ሚያዝያ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን [ጻድቅና ሰማዕት] ፪. አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ [ ደቀ መዛሙርቱ ] ፫. ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት [ተንባላት የገደሉት] [ †  ወርኃዊ በዓላት ] ፩ ፡ አምላካችን አማኑኤል ፪ ፡ ቅዱሳን አብርሃም ፡ ይስሐቅ ፡ ወያዕቆብ ፫ ፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ ፬ ፡ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ ፭ ፡ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ፮ ፡ ቅዱሳን አባዲር ወኢራኢ ፯ ፡ ቅድስት ሶስና " ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ:: እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው:: አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ:: እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን:: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ:: " [ራዕይ.፪፥፲] (2:10) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
Show all...
Hi Stranger , Thank you for joining us!
Show all...
                       †                        🕊  💖  እንኳን  አደረሳችሁ  💖  🕊 🕊 " ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ! " 🕊 ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ " ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤ ደግሞም። ክርስቶስን አስነሥቶታል ብለን [ በገዛ ሥልጣኑ ተነሥቷል ብለን ] በእግዚአብሔር ላይ ስለ መሰከርን ሐሰተኞች የእግዚአብሔር ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፤ ሙታን ግን የማይነሡ ከሆነ እርሱን አላስነሣውም። ሙታን የማይነሡ ከሆነ ክርስቶስ አልተነሣማ ፤ ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት ፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ።" [ ፩ቆሮ.፲፭፥፲፬ ] ▬▬▬▬▬▬  †  ▬▬▬▬▬▬ 💖        ድንቅ ትምህርት        💖 [      በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ      ] 🕊       እንኳን አደረሳችሁ        🕊 †                       †                        † 💖                    🕊                     💖
Show all...