cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከኛ ለጊዮርጊስ

⭕ይህ ከኛ ለጊዮርጊስ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን መረጃዎች የሚቀርቡበት እና የምንሰራቸውን በጎ ተግባራት ለተከታዮቻችን የምናቀርብበት ነው። ሀሳብ አስተያየት ካሎት 👇👇 ያድርሱን✌ ✔✔ @Tsega_ze_missmar በግሩፓችን በ✔ @kegna_legiyorgis_viva ይቀላቀሉን በFacebook ፔጃችን ✔✌ከኛ ለጊዮርጊስ✌ ያገኙናል @kegnalegiyorgis @kegna_legiyorgis_viva

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
216
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ካስዬ እናታችን ጀግናችን ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑርልን 😭😭😭😭😭😭😭
Show all...
ያንድ ሠው ጤንነት የጋራ ጤና ነው ያንድ ሠው በሽታ የጋራ ህመም ነው ክፉ ቀን ሲመጣ... የሃገር ልጅ በሙሉ አንድ ቤተሠብ ነው አንድ ሃገር አንድ ቤተሠብ ኳስ ያለ ጤና ከቶ እንዴት ሊታሠብ ጊዮርጊስ ባገር ጉዳይ ቀልድ አያውቅም በሠው ህዝባዊነቱ ነው እዚህ ያደረሠው እንዳገር ሲሠራ እንዳገር ሲታሠብ ሁሉም ሠው ይሆናል እንደ አንድ ቤተሠብ አንድ ሃገር-አንድ ቤተሠብ ኳስ ያለ ጤና-ከቶ እንዴት ሊታሠብ
Show all...
እኛ የሳንጅዬ ደጋፊዎች እንደሁልጊዜ የምንታወቅበት የሰብዐዊ ድጋፍ እንቀጥላለን እናም ባለፉት 3 ቀናት እጅ ስናስታጥብ ለማህበረሰቡም ይጠቅማል ብለን ያሰብነውን ግንዛቤ ስንሰጥ ቆይተናል ይህን ተግባር ደግሞ ነገ ማለትም መጋቢት 16 2012 ለ covid-19 ቅድመ ጥንቃቄ አቅም ለሌላቸው የሚረዱ የንፅህና መጠበቂያ እቃዎችን ለማሰባሰብ ስታዲየም ዙሪያ በር ቁጥር 07 በመገኘት የቻልነውን ይዘን በመምጣት እንረዳለን ሁላችንም ለዚህ አለም ላይ አስከፊ ደረጃ ላይ ላለው ወረርሽኝ ለማጥፋት ሁላችንም የበኩላችንን እንወጣለን ከኛ ለጊዮርጊስ(ሊስትሮ ጀማ) እራሳችንን አላስፈላጊ ከሆኑ ንኪኪዎች እንቆጠብ keep your distance from other peoples Stay Home And Help Other From Getting The Virus
Show all...
ጨዋታ ተራዘመ ማለት ሳንጅዬ ከአይናችን ይጠፋል ማለት አይደለም ሁሌም ወደፊት ነው ነገ ማክሰኞ በ15/07/2012 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአየር ጤና ተገኝቶ እጅ የማስታጠብ ስራውን ያከናውናል መገኝት ሚችል እና ሚፈልግ አየር ጤና ተገኙ ለበለጠ መረጃ 0946368784 ፀጋ 0954840672 በሱ ከኛ ለጊዮርጊስ(ሊስትሮ ጀማ) 1 ጓንት ለ 1 ረዳት ምንጊዜም ጊዮርጊስ ✌️✌️
Show all...
✌️ስላም የሳንጅዬ ልጆች✌️ በቅርቡ በአለማችን በተከሰተው የ ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብዙ ህዝቦችን በሞት እያጣን እንገኛለን😢😭። ወደኛ ሀገርም መግባቱ ይታወቃል። እናም ''ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ'' ነውና ተረቱ እኛም እንደ ሌሎች ሀገር ችግሩ ሳይባባስ አስቀድመን በመጠንቀቅ እራሳችንንም ሆነ የምንወዳቸውን ሰዎች ባጠቃላይ የሀገራችንን ደህንነት እንጠብቅ🙏። እኛም የሳንጅዬ ልጆች የሚጠበቅብንን ለማድረግ እንደከዚ ቀደሙ ቀጠሮ ይዘናል። መምጣት ምትፈልጉ ቤተሰቦች ‼️የተከበረውን የክለባችንን ማሊያ በማድረግ እንዲሁም አቅሙ ካላቹ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ሳሙናዎችን፣የፊት ማስኮችን😷፣ጓንቶችን ለምንሰራው ስራ ይጠቅማሉ ምትሉትን ነገር በማምጣት አብራቹን ወገናችንን እንታደግ። የክለባችንንም መልካም ስም እናስቀጥል✌️። መምጣት ለምትፈልጉ ቤተሰቦች በ 09 46 36 87 84 ፀጋ በ 09 54 84 06 72 በሴ ይደውሉ ከ1:00 ሰዐት ጀምሮ ጦራይሎች እንገናኝ።🙏✌️✌️🙏 አስተባባሪ ✌️ከኛ ለጊዮርጊስ (የሊስትሮ ጀማ)✌️
Show all...
ሰላም የሳንጅዬ ቤተሰቦች እንደምናውቀው ኮሮናን ለመከላከል በየመንገዱ እጅ ማስታጠብ እና አንድ ጓንት ለ አንድ ረዳት በሚል መፈክር እኛ ከኛ ለጊዮርጊስ (የሊስትሮ ጀማዋች) መልካምነቱን በእለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 3 ሰዓት የጀመረ ሲሆን ይህ ተግባራችን ሰኞም ይቀጥላል ይህን በተመለከተ ዛሬ ተገናኝተን ስለምናወራ ማገዝ እና መሳተፍ የምትፈልጉ ዛሬ እሁድ ከ ቀኑ በ 8 00 ፒያሳ እንገናኝ እናም ምመጣት እና መሳተፍ ምፈልጉ ለበለጠ መረጃ 0946368784 ፀጋ 0954840672 በሱ በእነዚ ስልኮች ይደውሉ ምንጊዜም ጊዮርጊስ ✌️✌️✌️
Show all...
የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች 9 ደርሰዋል! የኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሁኔታን አስመልክቶ በጤና ሚንስቴር በተሰጠ መግለጫ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሰዋል። መጋቢት 10 ከተያዙት ውስጥ ፡- - የ44 ዓመት ጃፓናዊ (ከዚህ ቀደም ከተያዙት ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው) - የ85 ዓመት እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊ (ከውጪ ከመጡበት ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም ጀምሮ ራሳቸውን ለይተው ሲከታተሉ የነበሩ) - ሶስተኛው የ39 ዓመት ኦስትራዊ ዜጋ ሲሆን በመጋቢት 6/2012 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ተገቡ ናቸው። ሁለቱ ታማሚዎች በጥሩ ጤንነት ላይ ሲሆኑ የ85 ዓመት ዕድሜ ታማሚ ግን #ከባድ የሚባል ህመም ቢኖራቸውም አስፈላገው ክትትል እየተደረገላቸው ነው Ya all please wash ur hands every time u touched something n Pray for the world
Show all...
🔰 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቦርድ ዋና አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቪጅኖቭ እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ላይ የዕግድ ውሳኔ ማሳለፉ ተሰምቷል። 🔰 በሊጉ ካለፉት ሁለት ዓመታት አንፃር የተሻለ የውጤት ጎዳና ላይ ቢገኙም የክለቡ ደጋፊዎች ግን በተደጋጋሚ በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ሰርዳን ዝቪጅኖቭ ላይ ደስተኛ አለመሆናቸውን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የክለቡ ደጋፊዎች በሚያሰሙት ተደጋጋሚ የተቃውሞ ድምፅ መረዳት ይቻላል፡፡ 🔰 ከዚህ መነሻነት ሰሞኑን ቦርዱ ለውይይት እንደሚቀመጥ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ባደረገው ውይይት ዋና አሰልጣኙ ለጊዜው ከሥራቸው በእግድ እንዲነሱ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል። ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ለዓመታት ሲያገለግል የነበረው ዘሪሁን ሸንገታ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ዩጋንዳዊው ኤሚ ንዲዚዬም መታገዳቸውን ሰምተናል፡፡ 🔰ነገ በ17ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ከሰበታ ከተማ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ያለበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በክለቡ ተጫዋቾች ሳላሀዲን ሰዒድ እና ጌታነህ ከበደ እንዲሁም በቀድሞው የክለቡ ተጫዋቾች እየተመራ ጨዋታውን እንደሚያደርግ፤ አስቻለው ታመነም ቡድኑን በአምበልነት እንዲመራ ስለመመረጡ ከክለቡ ቅርበት ካላቸው ሰዎች አረጋግጠናል፡፡ 🔰ክለቡ እስካሁን በጉዳዩ ዙርያ ይፋ ያደረገው መረጃ የሌለ ሲሆን አዳዲስ እና ይፋ የሚወጡ መረጃዎችን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል። ©ሶከር ኢትዮጵያ
Show all...