en
Feedback
ዛሀር አካዳሚ | Zaher Academy 💡

ዛሀር አካዳሚ | Zaher Academy 💡

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማው ኮምፒውተር ነክ እንዲሁም የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ፈጠራዎችን ለማህበረሰባችን ማስተዋወቅ ብሎም ማስተማር ነው። እባክዎ ለወዳጅ ዘመዶ ይህን channel እንዲቀላቀሉ ያድርጉ! እናመሰግናለን 🙏🙏🙏 Y͙o͙u͙ ͙k͙n͙o͙w͙ ͙b͙u͙t͙ ͙y͙o͙u͙ ͙d͙o͙n͙'͙t͙ ͙k͙n͙o͙w͙ ͙w͙h͙a͙t͙ ͙y͙o͙u͙ ͙k͙n͙o͙w͙.͙

Show more
Japan43 432The category is not specified
247
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-930 days
Posts Archive
__________________________________ 𝕄𝕖𝕥𝕙𝕠𝕕 𝟚: 𝔽𝕣𝕖𝕤𝕙 𝕚𝕟𝕤𝕥𝕒𝕝𝕝 𝕎𝕚𝕟𝕕𝕠𝕨𝕤 𝟙𝟘 𝕨𝕚𝕥𝕙𝕠𝕦𝕥 𝕝𝕠𝕤𝕚𝕟𝕘 𝕕𝕒𝕥𝕒 Windows 10 provides the feature "Reset this PC" to help you solve system problems by reinstalling Windows 10. During the process, you can choose whether to keep your personal files or not. To use the feature, you can go to 𝐒𝐞𝐭𝐭𝐢𝐧𝐠𝐬 > 𝐔𝐩𝐝𝐚𝐭𝐞 & 𝐒𝐞𝐜𝐮𝐫𝐢𝐭𝐲 > 𝐑𝐞𝐜𝐨𝐯𝐞𝐫𝐲 > 𝐑𝐞𝐬𝐞𝐭 𝐭𝐡𝐢𝐬 𝐏𝐂, then you will have two options, "𝐊𝐞𝐞𝐩 𝐦𝐲 𝐟𝐢𝐥𝐞𝐬" and "𝐑𝐞𝐦𝐨𝐯𝐞 𝐞𝐯𝐞𝐫𝐲𝐭𝐡𝐢𝐧𝐠", select one of them and follow the on-screen instruction. 𝒀𝒐𝒖 𝒄𝒂𝒏 𝒂𝒍𝒔𝒐 𝒓𝒆𝒔𝒆𝒕 𝑾𝒊𝒏𝒅𝒐𝒘𝒔 10 𝒇𝒓𝒐𝒎 𝒄𝒐𝒎𝒎𝒂𝒏𝒅 𝒍𝒊𝒏𝒆. 𝑻𝒉𝒆 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒔𝒔 𝒂𝒓𝒆 𝒔𝒉𝒐𝒘𝒏 𝒃𝒆𝒍𝒐𝒘: Step 1. Type “🅲🅼🅳” in the search box and press Enter. Step 2. In the listed results, right click on the Command Prompt and select "𝐑𝐮𝐧 𝐚𝐬 𝐀𝐝𝐦𝐢𝐧𝐢𝐬𝐭𝐫𝐚𝐭𝐨𝐫". Step 3. Type “𝐬𝐲𝐬𝐭𝐞𝐦𝐫𝐞𝐬𝐞𝐭” (without quotes) in the command prompt window and press Enter. If you need to reinstall Windows 10 and install new updates, you can run command “𝐬𝐲𝐬𝐭𝐞𝐦𝐫𝐞𝐬𝐞𝐭 -𝐜𝐥𝐞𝐚𝐧𝐩𝐜”. 𝐼𝑓 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑠𝑦𝑠𝑡𝑒𝑚 𝑐𝑎𝑛𝑛𝑜𝑡 𝑏𝑜𝑜𝑡, 𝑦𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑏𝑜𝑜𝑡 𝑖𝑛𝑡𝑜 𝑟𝑒𝑐𝑜𝑣𝑒𝑟𝑦 𝑚𝑜𝑑𝑒 𝑎𝑛𝑑 𝑓𝑟𝑜𝑚 𝑡ℎ𝑒𝑟𝑒, 𝑦𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑟𝑒𝑠𝑒𝑡 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑃𝐶. 𝑌𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑏𝑜𝑜𝑡 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑃𝐶 𝑓𝑟𝑜𝑚 𝑎 𝑟𝑒𝑐𝑜𝑣𝑒𝑟𝑦 𝑑𝑟𝑖𝑣𝑒 𝑡𝑜 𝑟𝑒𝑠𝑒𝑡 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 10. https://t.me/zed_comp

𝗛𝗼𝘄 𝘁𝗼 𝗥𝗲𝗶𝗻𝘀𝘁𝗮𝗹𝗹 𝗪𝗶𝗻𝗱𝗼𝘄𝘀 𝟭𝟬 𝘄𝗶𝘁𝗵𝗼𝘂𝘁 𝗟𝗼𝘀𝗶𝗻𝗴 𝗗𝗮𝘁𝗮 (𝟯 𝗪𝗮𝘆𝘀)? 🅼🅾🅽🅳🅰🆈 🅹🆄🅽 22, 2020 🅲🅾🅼🅿🆄🆃🅴🆁 🆁🅴🅻🅰🆃🅴🅳 🆃🆄🆃🅾🆁🅸🅰🅻 🅱🆈 🅸🅽🆂🆃🆁🆄🅲🆃🅾🆁 🆉🅰🅷🅴🆁🅴🅳🅸🅽 🆂🅷🅸🅵🅰. 𝐼𝑓 𝑦𝑜𝑢 𝑎𝑟𝑒 𝑐𝑒𝑟𝑡𝑎𝑖𝑛 𝑡ℎ𝑎𝑡 𝑎𝑙𝑙 𝑎𝑝𝑝𝑙𝑖𝑐𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛𝑠 𝑎𝑟𝑒 𝑟𝑢𝑛𝑛𝑖𝑛𝑔 𝑤𝑒𝑙𝑙 𝑎𝑛𝑑 𝑡ℎ𝑒 𝑝𝑟𝑜𝑏𝑙𝑒𝑚 𝑦𝑜𝑢 𝑎𝑟𝑒 𝑓𝑎𝑐𝑖𝑛𝑔 𝑖𝑠 𝑛𝑜𝑡 𝑐𝑎𝑢𝑠𝑒𝑑 𝑏𝑦 𝑎𝑛𝑦 𝑖𝑛𝑠𝑡𝑎𝑙𝑙𝑒𝑑 𝑝𝑟𝑜𝑔𝑟𝑎𝑚𝑠, 𝑡ℎ𝑒𝑛 𝑦𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑐ℎ𝑜𝑜𝑠𝑒 𝑡𝑜 𝑟𝑒𝑖𝑛𝑠𝑡𝑎𝑙𝑙 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 10 𝑤𝑖𝑡ℎ𝑜𝑢𝑡 𝑙𝑜𝑠𝑖𝑛𝑔 𝑝𝑟𝑜𝑔𝑟𝑎𝑚𝑠. 𝐼𝑛 𝑜𝑟𝑑𝑒𝑟 𝑡𝑜 𝑘𝑒𝑒𝑝 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑜𝑟 𝑎𝑝𝑝𝑠, 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 𝑤𝑖𝑙𝑙 𝑠𝑐𝑎𝑛 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝐶: 𝑑𝑟𝑖𝑣𝑒 𝑎𝑛𝑑 𝑝𝑙𝑎𝑐𝑒 𝑎𝑙𝑙 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑝𝑒𝑟𝑠𝑜𝑛𝑎𝑙 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑎𝑠𝑖𝑑𝑒. 𝑊ℎ𝑒𝑛 𝑡ℎ𝑒 𝑖𝑛𝑠𝑡𝑎𝑙𝑙𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛 𝑐𝑜𝑚𝑝𝑙𝑒𝑡𝑒, 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 𝑤𝑖𝑙𝑙 𝑝𝑢𝑡 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑝𝑒𝑟𝑠𝑜𝑛𝑎𝑙 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑎𝑛𝑑 𝑠𝑒𝑡𝑡𝑖𝑛𝑔𝑠 𝑏𝑎𝑐𝑘 𝑡𝑜 𝑡ℎ𝑒 𝑜𝑟𝑖𝑔𝑖𝑛𝑎𝑙 𝑙𝑜𝑐𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛. 𝐼𝑓 𝑦𝑜𝑢 𝑎𝑟𝑒 𝑢𝑠𝑖𝑛𝑔 𝑎 𝑔𝑒𝑛𝑢𝑖𝑛𝑒 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 10, 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠 10 𝑤𝑖𝑙𝑙 𝑎𝑢𝑡𝑜𝑚𝑎𝑡𝑖𝑐𝑎𝑙𝑙𝑦 𝑔𝑒𝑡 𝑎𝑐𝑡𝑖𝑣𝑎𝑡𝑒𝑑 𝑎𝑓𝑡𝑒𝑟 𝑡ℎ𝑒 𝑟𝑒𝑖𝑛𝑠𝑡𝑎𝑙𝑙𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛. 𝑸𝒖𝒊𝒄𝒌 𝒏𝒂𝒗𝒊𝒈𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒇𝒐𝒓 𝑾𝒊𝒏𝒅𝒐𝒘𝒔 10 𝒓𝒆𝒊𝒏𝒔𝒕𝒂𝒍𝒍𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒎𝒆𝒕𝒉𝒐𝒅𝒔: 👇 __________________________________ 👉 𝕄𝕖𝕥𝕙𝕠𝕕 𝟙: ℝ𝕖𝕡𝕒𝕚𝕣 𝕚𝕟𝕤𝕥𝕒𝕝𝕝 𝕎𝕚𝕟𝕕𝕠𝕨𝕤 𝟙𝟘 𝕨𝕚𝕥𝕙𝕠𝕦𝕥 𝕝𝕠𝕤𝕚𝕟𝕘 𝕒𝕟𝕪 𝕕𝕒𝕥𝕒. If your Windows 10 can boot and you believe all the installed programs are fine, then you can use this method to reinstall Windows 10 without losing files and programs. If one or more of your program are damaged, you'd better keep personal files only. Step 1. Download the latest Windows 10 installation ISO file. You can also use 𝐖𝐢𝐧𝐝𝐨𝐰𝐬 𝐌𝐞𝐝𝐢𝐚 𝐂𝐫𝐞𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐭𝐨𝐨𝐥 to create an installation ISO. Step 2. Double click to 𝐦𝐨𝐮𝐧𝐭 𝐭𝐡𝐞 𝐈𝐒𝐎 𝐟𝐢𝐥𝐞 (for Windows 7, you need to use other tools to mount it). At the root directory, double-click to 𝐫𝐮𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐒𝐞𝐭𝐮𝐩.𝐞𝐱𝐞 𝐟𝐢𝐥𝐞. Step 3. When the Windows 10 Setup is ready, you can whether to 𝐝𝐨𝐰𝐧𝐥𝐨𝐚𝐝 𝐮𝐩𝐝𝐚𝐭𝐞𝐬 or not based on your needs. Step 4. In the screen, click "𝐂𝐡𝐚𝐧𝐠𝐞 𝐰𝐡𝐚𝐭 𝐭𝐨 𝐤𝐞𝐞𝐩". Step 5. From there. You can select "𝐊𝐞𝐞𝐩 𝐩𝐞𝐫𝐬𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐟𝐢𝐥𝐞𝐬, 𝐚𝐩𝐩𝐬, 𝐚𝐧𝐝 𝐖𝐢𝐧𝐝𝐨𝐰𝐬 𝐬𝐞𝐭𝐭𝐢𝐧𝐠𝐬" or "𝐊𝐞𝐞𝐩 𝐩𝐞𝐫𝐬𝐨𝐧𝐚𝐥 𝐟𝐢𝐥𝐞𝐬 𝐨𝐧𝐥𝐲". Step 6. Click 𝐍𝐞𝐱𝐭 to install Windows 10. 𝑇ℎ𝑖𝑠 𝑚𝑎𝑦 𝑡𝑎𝑘𝑒 𝑎 𝑤ℎ𝑖𝑙𝑒 𝑏𝑒𝑐𝑎𝑢𝑠𝑒 𝑖𝑡 𝑤𝑖𝑙𝑙 𝑠𝑝𝑒𝑛𝑑 𝑒𝑥𝑡𝑟𝑎 𝑡𝑖𝑚𝑒 𝑠𝑐𝑎𝑛𝑛𝑖𝑛𝑔 𝑦𝑜𝑢𝑟 ℎ𝑎𝑟𝑑 𝑑𝑟𝑖𝑣𝑒 𝑎𝑛𝑑 𝑚𝑜𝑣𝑖𝑛𝑔 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠. 𝐼𝑓 𝑦𝑜𝑢 𝑗𝑢𝑠𝑡 𝑤𝑎𝑛𝑡 𝑡𝑜 𝑘𝑒𝑒𝑝 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑤ℎ𝑒𝑟𝑒 𝑡ℎ𝑒𝑦 𝑎𝑟𝑒, 𝑡ℎ𝑒𝑛 𝑡𝑟𝑦 𝑡ℎ𝑒 𝑛𝑒𝑥𝑡 𝑚𝑒𝑡ℎ𝑜𝑑. https://t.me/zed_comp

============================ ዝምተኛው መካሪ(ሞት) ============================ ስሙን ስንሰማ ብርክ የሚይዘን ስለሱ ስናስብ ፍርሃት ሚውጠን ስሙ እኮ ያስፈራል፣ እይታው ያበረግጋል ጨክኖ ከመጣ፣ ማን ሰው ያመልጠዋል ኮስታራ እኮ ነው፣ ቀልድ እንኯ የማያውቅ ስራውን ለመስራት፣ ምንም አይል ፈቀቅ እዝነትም የለውም፣ ትንሽ ይቆይ አይል የመጣበትን ጉዳይ፣ ሁሉን ይፈፅማል ለቀልድ ቦታ የለው፣አይደንቀውም ምንም ገና መጀመሪያ አልፈጠረበትም ወጣትን ይደፋል፣ ጉልበተኛን ይገነድሳል አባሮ ይይዛል፣ እሮጦ ይቀድማል ለንጉስ እጅ አያነሳም፣ለቆንጆ አይደነግጥ ህይወት ያለውን ሁሉ፣ ያስገባል ከመሬት ውስጥ ደሃን አይጠየፍ፣ ለሃብታም አይሽቆጠቆጥም ለህፃን አያዝን፣ለባለ ዝና አይደገድግም ጉድ ነው የሱ ነገር፣ ታሪኩ ቡዙ ነው ይነገር ቢባልም፣ መቼም ማያልቅ ነው ዝም ማለቱን አይተን፣ ችላ እንዳንለው ከጀርባችን አለ፣ ይዘነው ነው ምንዞረው አሁኑኑ እንመለስ፣ ወደ አላህ እንዙር ከወንጀል እንራቅ፣ ከይርን እናዘወትር የተያዝን ግዜ፣ እንዳንደናበር እሩቅ መስሎ ታይቶን፣ እንዳንዘነጋው መጥቶ ይይዘናል፣ ቅርባችን ነው ያለው:: ያአላህ መጨረሻችንን አሳምረው! አሚን! ኣሚን! ኣሚን! https://t.me/zed_comp

በስልክዎ የከፈቱት የቴሌግራም አካውንት ያለምንም password የሚከፍት ከሆነ ቴሌግራምዎ የመጠለፍ እድሉ ከፍተኛ ነው። ይህንን ለማድረግ የሚከተሉትን ሂደቶችን ተከትሎ ነው። ይህ አጭር ቪድዮ ከዚህ ችግር እንዴት መከላከል እንደሚችሉም ጭምር ያሳያል።በ All Standard የሚሰሩ ቪድዮዎች ቶሎ እንዲደርስዎ በዪትዩብ Subscribe ያድርጉ የቴሌግራም ቻናሉንም Join ይበሉ! https://www.youtube.com/watch?v=pRHmNSr3240

የኮምፒውተር ተጠቃሚ ከሆኑ አሁን ከእንቅልፍ ተነስተው የሚሰማዎትን አይነት የእረፍት ስሜት ለኮምፒዩተሩ እንዲሰማው ይፈልጋሉ ? የሚከተለውን ያድርጉ 1. Save your current work if you are on using the computer now. 2. Shutdown for 5 minutes 3. open it and wait till finish everything. 4. On windows 10 search tab type %temp% 5. Click enter and open the folder. How many file are there? This is your previous work history and it uses a RAM 6. Delete this trash file. አሁኑኑ ይሞክሩት! ይህ መልእክት ከ All standard ነው Join link All Standard በዚህ ቻናል ከትናንሽ የኮምፕዩተር ኮድና ትሪክ እስከ ሙሉ ፕሮጀክት የምናጋራበት የጋራ መማሪያ ቤታችን። 🌴🌴🌴Only computer and computer related posts🌿🌿🌿 🌿Join the Telegram channel And subscribe my YouTube channel https://www.youtube.com/channel/UCgCgB8bpYhbbv0LYFrj1eTw wed: all-standard.com https://t.me/allstanderdcoder Share share please for more

የፀሐይ ግርዶሽ እና ዓይናችን ★★★★★★★★★★★★ (ዶ/ር ጸደቀ አሳምነው ፤ የዓይን ሐኪም፣ የቪትሮ-ሬቲና ድህረ-ስፔሻሊስት) *************************** **** በሰኔ 14, 2012 ዓ.ም የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ እንደሚታይ ከመዘገቡ ጋር ተያይዞ የፀሐይ ግርዶሹን ለማየት ሲባል ቀጥታ ወደ ፀሐይ ማየት ስለሚያስከትለው ጕዳትና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ማብራሪያ ለመስጠት እሞክራለሁ። በፀሐይ ጨረር የሚመጣ የሬቲና(የብርሃን መቀበያ) ጉዳት በእንግሊዝኛ, solar retinopathy, photic retinopathy, faveomacular retinitis, solar retinitis, and eclipse retinopathy ይባላል። ይኽ ጉዳት የሚከሰተው በቀጥታ ፀሐይን ወይም የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ሲሞከር የሚከሰት ችግር ሲሆን የብርሃን መቀበያችን (ሬቲና) ላይ ጉዳት በማድረስ ዕይታችንን ይቀንሳል፡፡ ጨረሩን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ያዩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በዚህ ምክኒያት የሚከሰተው ጉዳት ለመዳን ከ3-6 ወር ሊፈጅ ይችላል። እንደዛም ሆኖ ግን ወደ ቀድሞው የዕይታ አቅም ሳይመለስ ዘለቄታዊ የዕይታ መቀነስ ሊያስከትል ይችላል። የዚህ ችግር ዋና መንስዔ ከፀሐይ የሚወጣው ጨረር ቢሆንም በብረት ብየዳ ጊዜ ከሚወጣ ጨረር ፣ ከትክክለኛው ኃይል በላይ የሚለቀቁ ሌሎች የብርሃንና የሌዘር ምንጮችም ሊከሰት ይችላል። ጨረሩን (በተለይ ልዕለ ሐምራዊ-ለ Ultraviolet-B ) በቀጥታ የብርሃን መቀበያና መጋቢ ህዋሳት ላይ ኬማካዊ ለውጥ በመፍጠር ጉዳት ያስከትላል። ---------------------------------------------------------- አጋላጭ ሁኔታዎች፡- - ህጻናትና ወጣቶች የተፈጥሮ ሌንሳቸው ሞራ ያልጀመረው ስለሚሆን በቀጥታ ፀሐይን ሲያዩ ሊጐዱ ይችላሉ፡፡ - ባንጻራዊነት እድሜያቸው የገፋ ሰዎች ላይ ሞራ ስለሚጀምር ወደ ዓይን የሚገባው ጨረር ይቀንሳል፡፡ - ሆኖም የሞራ ቀዶ ጥገና አድርገው አርቲፊሻል ሌንስ የገባላቸው ሰዎች ወደ ፀሐይ ቀጥታ ማየት የለባቸውም። - የአዕምሮ ህመም ወይም ውስንነት ያላቸው ሰዎች በብዛት ወደፀሐይ ቀጥታ ሊያዩ ስለሚችሉ ጥንቃቄና እርዳታ ያሻቸዋል፡፡ - ወንዶች ከሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው - ነጮች ከጥቁሮች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው - በብየዳ ጊዜ ተገቢውን መነጽርና የፊት ጋሻ አለመጠቀም ለተመሳሳይ ጉዳት ይደርጋል። ---------------------------------------------------------- ምልክቶቹ፦ በዚህ ችግር የተጠቁ ሰዎች ለጨረሩ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ብዙ ጊዜ በሁለቱም ዓይን ላይ፦ - የዕይታ መቀነስ - በዕይታ አድማስ ውስጥ የሚታይ ጥላ - የዕይታ ቅርጽ መዛባት (የሚያዩት ነገር የተጣመመ ፣ በመጠን ያነሰ ወይም የተለቀ መምሰል) - በተጨማሪም በግንባርና በጭንቅላት ጐን አካባቢ ራስ ምታት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህን ችግር መከሰቱን ለማወቅ የዓይን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። በማይክሮስኮፕ በማየት ወይም ሬቲናውን ፎቶ በማንሳት ወይም OCT በሚባል መሳሪያ በማየት ችግሩ መከሰቱን ማረጋገጥ ይቻላል። ---------------------------------------------------------- ህክምናው፦ ምንም እንኳን ይህን ችግር ለማከም የተለያዩ መድኃኒቶች(ስቴሮይድን ጨምሮ)ቢሞክሩም አጥጋቢ ውጤት አላመጡም፡፡ስለዚህ ዋነኛው ነገር ችግሩ እንዳይከሰት አስቀድሞ መከላከል ነው ። ---------------------------------------------------------- መከላከያ መንገዶች፦ ፀሐይን ፣ ፀሐይ ግርዶሽን ፣ የብየዳ ጨረርና ሌሎች ኃይለኛ ብርሃን የሚረጩ ነገሮችን በቀጥታ አለማየት ፣ በፀሐይ ግርዶሽ በዓመታት አንዴ የሚታይ በመሆኑና ብርሃኑም የቀነሰ ስለሚመስለን ለማየት ሊያጓጓን ይችላል... ሆኖም በፍጹም በቀጥታ ማየት የለብንም። ህጻናት፣ የአዕምሮ ህመምና ውስንነት ያለባቸውን ሰዎች ወደ ፀሐይ እንዳያዩ መከላከል ፣ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ መርዳት የፀሐይ ግርዶሽን ለማየት ዓላማ የተሰሩ ISO እና CE ሰርቲፊኬት ያላቸው ልዕለሐምራዊ (UV) ንዑሰ - ቀይ (Infrared) ጨረሮችን 99 - 1ዐዐ% የሚከላከሉ ጥቁረታቸው (shade no 12) የሆኑ መነጽሮችን ብቻ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም እንደነዚህ ዓይነት መነጽሮች በሀገራችን ስለመግባታቸው እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ቱሪስቶች ወደ እኛ ሀገር ሲመጡ ይዘው ይመጡ ይሆናል፡፡ ---------------------------------------------------------- የተለመዱትን የፀሐይ መነጽሮች ማድረግ ይቻላል? በፍጹም! ምንም እንኳን የፀሐይ መነጽሮች ጐጂ ጨረሮችን መቀነስ ቢችሉም በቀጥታ ወደ ፀሐይ ለማየት ተብሎ ስላልተሰሩ ተጨማሪ ጨረሮችን ወደ ዓይን ያስተላልፋሉና በፍጹም እነዚህን መነጽሮች ተማምነው ወደ ፀሐይ/ ፀሐይ ግርዶሽ ማየት የለብዎትም፡፡ ጥቁር መነጽር መሆኑ ብቻ ጨረሮቹን ይከላከላል ማለት አይደለም። ጥላሸት የተቀባ መነጽር፣ የራጅ ፊልም፣ የተለመደ የፀሐይ መነጽር፣ ካሜራዎች ወዘተ የሚታዩ የብርሃን ጨረሮችን ቢቀንሱም አደገኛ የሆኑትን ልዕለሐምራዊና ንዑስቀይ ጨረሮችን መከላከል አቅም ስለሌላቸው በነሱ መተማመን አይገባም፡፡ መንግስት ይኽን አጋጣሚ ተጠቅመው ጥራታቸው ያልተረጋገጠ መነጽሮች እንዳይሸጡ ቁጥጥር ማድረግ ይገባዋል። ከ "𝑨𝒉𝒎𝒆𝒅𝒊𝒏 𝑱𝒆𝒃𝒆𝒍 𝒐𝒇𝒇𝒊𝒄𝒊𝒂𝒍 - አህመዲን ጀበል" ፌስቡክ ማህደር የተወሰደ https://t.me/zed_comp

_____________________________________ እሮብ ሰኔ 10, 2012 ሶፍትዌር ነክ ትምህርት በ እንስትራክተር ዘሀረዲን ሺፋ _____________________________________ እንደምን አደራችሁ እንደምን ዋላችሁ እንደምን አመሻችሁ እንደምን ሰነበታችሁ እስቲ ዛሬ አንድ አሪፍ ነገር ላስተዋውቃችሁ። 🙏🙏🙏 Dell Laptop computer እየጋለ አስቸግረዎታል? እንግዲያው መፍትሄውን ልንገሮት አብራቹኝ ቆዩ። አብዝሃኛው የ Dell Laptop ተጠቃሚ ይህ ችግር ያገጥማቸዋል። Dell Laptop በሚግልበት ግዜ ከራሱ አልፎ ኮምፒውተሩ የተቀመጠበትን ቦታ ሳይቀር በእጃችን ለመንካት እስከማንችል ድረስ እንዲያቃጥል ያደርገዋል። Latest Latitude, Inspiron, Vostro Series የመሳሰሉ የ Dell Laptop ምርቶች ለገበያ ተመርተው ሲቀርቡ በተፈጥሮ የመጋል ባህሪ አላቸው። ይህ Dell Computer የተለያዩ ጌሞችን በምንጫወትበት ግዜም በከፍተኛ ሁኔታ ግለቱ ይጨምራል። አሁን እኔ እማሳያችሁ እንዴት አድርገን Dell Computer Overheated እንዳይሆን ማድረግ እንችላለን የሚለውን ይሆናል። Step 1: Install Prerequisite Software ኮምፒውተራችን እንዳይግል የሚረዳንን Dell Feature Enhancement Pack Software ከመጫናችን በፊት .NET Framework (ዶትኔት ፌሬምዎርክ) መጫን ይኖርብናል። ምክንያቱም ይህ .NET ፍሬምዎርክ main dell cooling software በአግባቡ ስራውን እንዲሰራ ያደርግልናል። Step 2: Install Dell Feature Enhancement Pack ይህ Software ኮምፒውተራችን እንዳይግል የሚያደርግ ዋና መሳሪያ ነው። ይህን Software ከ Google ዳውንሎድ አድርገን ኮምፒውተራችን ላይ እንጭነዋለን። Step 3: Dell Feature Enhancement Pack የተባለውን Software በአግባቡ ከጫንን ቡኋላ ከኮምፒውተራችን ግርጌ በቀኝ በኩል ወዳለው የባትሪ ምልክት(Battery Icon) እንሄድና በምልክቱ ላይ Right Click አድርገን Cool Power Plan የሚለውን እንመርጣለን። ይህን ካደረግን የ Dell ኮምፒውተራችን በከፍተኛ ሁኔታ መጋሉን ይቀንሳል። Like, Share ያድርጉ 🙏🙏🙏😷😷😷 ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቴሌግራም ቻናሌ ላይ መከታተል ትችላላችሁ። https://t.me/zed_comp የዛሬው ትምህርታችን ይህን ይመስላል በሌላ ትምህርት እስክንገናኝ መልካም ግዜ ይሁንላችሁ። 🙏

______________________________ ማክሰኞ ሰኔ 9, 2012 ሶፍትዌር ነክ ትምህርት በ እንስትራክተር ዘሀረዲን ሺፋ ______________________________ እንደምን አደራችሁ እንደምን ዋላችሁ እንደምን አመሻችሁ እንደምን ሰነበታችሁ እስቲ ዛሬ ጠቃሚ ነገር አብረን እንማር። 🙏🙏🙏 የኮምፒውተሮን የይለፍ ቃል(Password) ረስተዋሉ? እንግዲያው አይጨነቁ መፍትሄውን ይሀው ብለናል። አብዛኞቻችን ኮምፒውተራችንን ከኛ ፍቃድ ዉጪ ሰዎች access እንዳይደርጉት ብለን በይለፍ ቃል እንቆልፋለን። ይሁንና በተለያየ አጋጣሚ የኮምፒውተራችንን ይለፍ ቃል(Password) ልንረሳው እንችላለን። በዚህን ግዜ ቡዙ ሰው የሚዮስደው እርምጃ የኮምፒውተሩን ኦፕሬቲን ሲስተም መቀየር ነው። ከዚህ መንገድ ሌላ የተሻለ አማራጭ ስላለ የተሻለዉን መንገድ መጠቀሙ ይመከራል። ይህ ቱቶሪያል የረሳነውን የ window 10/ 8/ 7 የይለፍ ቃል በቀላሉ Reset ማድረግ ምንችልበትን መንገድ ያሳያል። የመጀመሪያ ስራችን የሚሆነው ሌላ ከ internet ጋር የተገናኘ ኮምፒውተር ፈልገን በቀጥታ ከ Google ላይ PcUnlocker ZIP file ብለን ዳውንሎድ እናደርጋለን። በመቀጠል ዳውንሎድ በተደረገው ZIP ፋይል ላይ Right click አድርገን Extract እናደርገዋለን። Extract አድርገን ሲንጨርስ ከታች በፎቶ 1 እንደምትመለከቱት ከውስጡ pcunlocker.iso የሚል setup እናገኛለን። በመቀጠል ባዶ CD ወይም ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን በማገናኘት pcunlocker.iso ፋይሉን Boot እናደርጋለን። ማስታወሻ:- Boot ለማድረግ አሁንም ከ Google ላይ ሌላ ISO2Disc ወይም Rufus የተባለ Boot ማድረጊያ software ዳውንሎድ እናደርጋለን። እኔ ማሳያቹ ከታች በፎቶ 2 የምትመለከቱትን ISO2Disc የሚለውን Boot ማድረጊያ Software በመጠቀም ይሆናል። ISO2Disc የሚለውን Boot ማድረጊያ software ዳውንሎድ ባረግንበት ኮምፒውተር ላይ በመሆን እንከፍተዋለን። ከታች ባለው ፎቶ 2 እንደምትመለከቱት ISO Image: ከሚለው ፅሁፍ በቀኝ በኩሉ Browse የሚለዉን በተን ተጭናቹ መጀመሪያ Extract ወዳረጋችሁት ፋይል ሂዳቹ pcunlocker.iso የሚለውን ትመርጣላችሁ። በማስከተል የተጠቀምነው CD ከሆነ Burn to CD/DVD የሚለውን እንመርጣለን(በፎቶዎ እንደተመረጠው ማለቴ ነው)። USB ዲስክ ከሆነ ደግሞ Burn to CD/DVD የሚለውን ትተን Burn to USB Flash Drive የሚለውን በመምረጥ ከስር Start Burn የሚለውን button በመጫን Boot አርጎ እስኪጨርስ እንጠብቀዋለን። በፎቶ 2 እንዳያችሁት የተጠቀመው CD ስለሆነ ከተወሰነ ደቂቃ ቡኋላ Boot አርጎ ሲጨርስ ሲዲዉን ነቅለን የይለፍ ቃሉ(password) ወደተረሳው ኮምፒውተር እናስገባዋለን። እናንተ የተጠቀማችሁት CD ሳይሆን USB Flash ዲስክ ከሆነም መመሪያው ተመሳሳይ ይሆናል። የይለፍ ቃሉን reset ለማድረግ የፈለግነውን ኮምፒውተር Shot down እናደርግና መልሰን በ BIOS system እናስጀምረዋለን። ኮምፒውተራችት BIOS system ውስጥ እንደገባ BOOT menu ወደሚለው እንሄድና CD/DVD የሚለውን ወደ መጀመሪያ (First priority) እናመጠዋለን። ይህ ማለት ኮምፒውተራችን ሲነሳ ከ CD/DVD እንዲጀምር ማድረግ ማለት ነው። CD/DVD የሚለውን አማራጭ ወደ መጀመሪያ ካመጣን ቡኋላ BIOS ሲቲንጉን Save አድርገን ኮምፒውተራችንን Restart እናደርገዋለን። ከዛ በቀጥታ ወደ PcUnlocker CD ይገባል። ከታች በፎቶ 3 እንደምትመለከቱት ከ CD Boot ሲያደርግ PcUnlocker በቀጥታ የኮምፒውተራችንን ኦፕሬቲን ሲስተም ያገኘዋል። ከተዘረዘሩት user account ውስጥ የይለፍ ቃሉን reset ለማድረግ ያሰባችሁትን መምረጥ። ልክ እዚሁ DAVID የሚለው አካውንት እንደተመረጠው። በመጨረሻም Reset password የሚለውን በተን መንካት። Reset Password የሚለውን እንደነካን ከታች በፎቶ 4 እንደምትመለከቱት Change password ወደሚል Dialogue box ዮስደናል። አዲስ የይለፍ ቃል እንድናስገባ ይጠይቀናል ከፈለግን አዲሱን የይለፍ ቃል እናስገባለን ካልፈለግን ባዶዉን ትተን OK የሚለውን በተን እንጫናለን። ከዚህ ቡኋላ ኮምፒውተራችንን Reboot አድርገን CD/DVD የሚለውን አማራጭ ከ First priority ቀድሞ ወደ ነበረበት እንመልሳለን። በመጨረሻም የይለፍ ቃሉን reset ወዳደረግነው window በቀላሉ መግባት እንችላለን። Like, Share ያድርጉ 🙏🙏🙏😷😷😷 ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ቴሌግራም ቻናሌ ላይ መከታተል ትችላላችሁ። https://t.me/zed_comp የዛሬው ትምህርታችን ይህን ይመስላል በሌላ ትምህርት እስክንገናኝ መልካም ግዜ ይሁንላችሁ። 🙏🙏🙏

______________________________ ማክሰኞ ሰኔ 9, 2012 ሶፍትዌር ነክ ትምህርት በ እንስትራክተር ዘሀረዲን ሺፋ __________________________ እንደምን አደራችሁ እንደምን ዋላችሁ እንደምን አመሻችሁ እንደምን ሰነበታችሁ እስቲ ዛሬ አንድ ሶፍትዌር ላስተዋውቃችሁ። 🙏🙏🙏 👉 Sdata tool software ምንድነው? ይህ ሶፍትዌር Pen drive ወይንም በምናውቀው ቋንቋ ፍላሽ ብለን የምንለውን ሚሞሪ መጠኑን(Size) ከነበረበት ለማሳደግ የሚጠቅም ሶፍትዌር ነው። እናም ይህን ሶፍትዌር በቀላሉ ከGoogle ላይ Download በማድረግ መጠቀም ይቻላል ይህ ሶፍትዌር በZip ፎርም ስለሆነ Download ከተደረገ ቡሃላ extract ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም ማለት Right Click አድርገን extract All የሚለውን መምረጥ ማለት ነው። እናም ይህን ካደረግን ቡሃላ sdata tool.exe የሚለው ላይ right Click በማድረግ Run as administrator የሚለውን መምረጥ። በመቀጠል choose your data to compress የሚለውን በመንካት መጠኑን ከፍ ለማድረግ ያሰብነውን ፍላሽ ስም መምረጥ በመቀጠል compress To: የሚለው ጋር በመሄድ ልንቀይረው ያሰብነውን መጠን መምረጥና በመጨረሻ E-Compress NOW የሚለውን በመንካት የፍላሻችንን መጠን ከነበረበት መጨመር እንችላለን። ይህን ስላቹ አንድ ነገር ማወቅ ይኖርባችኋል ለምሳሌ ሚሞሪያችን 2GB ነው እንበል እና ማሳደግ የፈለግነው ወደ 16GB ከሆነ መጀመሪያ ወደ 4GB ከዛ ወደ 8GB ከዛ ወደ 16GB እያልን ነው ማሳደግ ያለብን። ባንዴ ከ 2GB ወደ 16GB ማሳደግ አይቻልም። በሌላ ትምህርት እስክንገናኝ መልካም ግዜ ይሁንላችሁ። 🙏🙏🙏