en
Feedback
ዛሀር አካዳሚ | Zaher Academy 💡

ዛሀር አካዳሚ | Zaher Academy 💡

Open in Telegram

የዚህ ቻናል ዋና አላማው ኮምፒውተር ነክ እንዲሁም የተለያዩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ፈጠራዎችን ለማህበረሰባችን ማስተዋወቅ ብሎም ማስተማር ነው። እባክዎ ለወዳጅ ዘመዶ ይህን channel እንዲቀላቀሉ ያድርጉ! እናመሰግናለን 🙏🙏🙏 Y͙o͙u͙ ͙k͙n͙o͙w͙ ͙b͙u͙t͙ ͙y͙o͙u͙ ͙d͙o͙n͙'͙t͙ ͙k͙n͙o͙w͙ ͙w͙h͙a͙t͙ ͙y͙o͙u͙ ͙k͙n͙o͙w͙.͙

Show more
Japan43 432The category is not specified
247
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-930 days
Posts Archive
ስልክ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲሎት ይፈልጋሉ? ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች የሚከተሉት ናቸው 👉 ቴለፎኑ ለግዜው ጥሪ አይቀበልም እና 824 ያሳዉቁኝ እንዲደርሶ *21*857# ይደውሉ ። ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! 👉 ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ሲፈልጉ *21*Phone_number# በ Phone_number ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ ከዘ ወደርሶ ሲደወል ወደ ያስገባነው ቁጥር ይደዉላል። ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል 👉 ስልክዎ ሲጨናነቅ(busy) ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ 👉 ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ 👉 ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ! 👉 ኮል ዌይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮል ዌቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል 👉 ሲደውሉ ስልክ ቁጥርዎ እንዳይታይ ወይም በሌላ ቁጥር ተክተው ለመደወል ሲፈልጉ #31#"የሚደውሉት ቁጥር" ከዛ መደወል 👉 አንዳንድ ስልኮች #31# ከተደወለ በኀላ የምንደውለውን ቁጥር ስናስገባ በእኛ አገር ኔትዎርክ ላይሰራ ይችላል:: ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ጠቃሚ የቴክኖሎጂ እውቃት ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/zed_comp

ከሀገር ውጪ ሂደው መማር ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ስለ Scholarship ያለዎትን ግንዛቤ ያሳድጉ! How to Get a Scholarship to Study Abroad in 2020 https://www.mastersportal.com/articles/2850/how-to-get-a-scholarship-to-study-abroad-in-2020.html?utm_source=onetime_email_dotmailer&utm_medium=email&utm_campaign=commercial_PU_Master1_oct&dm_i=4WBC,ERUL,2FNPRW,1Q2RJ,1

🏁 ስልክዎ ላይ Application ሲጭኑ App_Not_Installed እያላችሁ ተቸግራችኋልን? ✅ብዙውን ጊዜ ይህ ችግር የሚፈጠረው ቨርዥናቸው(Version) በጣም ዝቅተኛ በሆኑ ስልኮች ላይ ነው! ሆኖም ግን በትላልቅ ስልኮችም ላይ ይሄ ችግር ይፈጠራል! እኛም መፍትሄ ይሆናሉ ብለን ያሰብናቸው ስምንት(8) አማራጮችን እንደሚከተለው አቅርበናል። 1ኛ. በአብዛኛው ጊዜ App_Not_Installed የሚለው ልትጭኑት ያሰባችሁት አፕ አይነት ተመሳሳዩ ስልካችሁ ላይ ሲኖር ነው። ለዚህም መኖር አለመኖሩን አረጋግጡ! ካለ Uninstall🚫 አድርጉት! 2ኛ. ሊጭኑት ያሰቡት አፕ አዲስ Android Version Support የሚያደርግ ሆኖ የእርስዎ ስልክ የድሮ Version ከሆነ ይሄ ችግር ሊፈጠር ይችላል። ይሄን ችግር እንዴት መቅረፍ ይቻላል? 1. 👉 Apk_Editor መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ያዉርዱ! 2. 👉 አፑን Install ካደረጋችሁ በኋላ ክፈቱትና » Select Apk From App »Common Edit 3. 👉 Install Location የሚለዉን Default አድርጉት! 4. 👉 አፑን Install እንዲሆንልን በዋናነት Version_Code መቀየር ነዉ! ኮዱን ስትቀይሩ ከስልካችሁ ጋር የሚሄድ መሆን አለበት ወይም ሌላ ስልክ ላይ መተግበሪያው Install ከሆነ ኮዱን አይታችሁ መቀየር ትችላላችሁ። 5. 👉 Save አድርጎ Install ማድረግ ነዉ። 99% ይሰራል። 3ኛ. ስልካችሁ ጊዜያዊ የሲስተም ችግር ሲያጋጥመው አዲስ አፕልኬሽን መቀበል ያቆማል። Restart በማድረግ ይስተካከላል። 4ኛ. በቀጥታ Install ማድረግ የማንችላቸው የሚከፋፈሉ መተግበሪዎች አሉ ለምሳሌ Base.Apk, ConfigArchi.Apk ✅Split Apk የሚባል አፕልኬሽን ከPlaystore በማውረድ ይጠቀሙ! አጠቃቀሙ ቀላል ነው! 5ኛ. Reset App Preferences ማድረግ። በቀጥታ ስልካችን ላይ የሚገኘው Settings ውስጥ በመግባት Apps (Apps Manager) የሚለውን በመንካት «Menu»Reset App Preferences» አድርጎ መሞከር! 6ኛ. መተግበሪያው የተቀመጠው ሚሞሪ ላይ ከሆነ ወደ InternalStorage Move አድርገው መሞከር! 7ኛ. Package_Installer ችግር ሲያጋጥመው አፕሊኬሽኖችን መቀበል ያቆማል! ይህን ችግር ለመቅረፍ Setting ውስጥ በመግባት Manage Apps Package የሚለውን በመንካት -> Installer -> Clear Data And Clear Cache አድርጎ መሞከር። 8ኛ. አፑን Install ከማድረግዎ በፊት ስልክዎ FreeSpace እንዳለው እርግጠኛ ይሁኑ። https://t.me/zed_comp

ብሉቱዝ(Bluetooth) ብሉቱዝ በአጭር ርቀት ውስጥ ምንም አይነት ገመድ ሳይጠቀም ዝቅተኛ ፓወር ራዲዮ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ስልኮች፤ ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ኔትወርክ ዲቫይሶች እንዲገናኙ( ኮሚኒኬሽን እንዲያደርጉ) ያስችላል፡፡ ብሉቱዝ ስታንደርድ IEEE 802.15.1 ሲሆን ስሙን የወሰደው 1000 ዓመት በፊት ከነበረ Harald Bluetooth ከተባለ ዴንማርክ ንጉስ ነው፡፡ ብሉቱዝ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲዛይን የተደረገው ቀላል ዋየርለስ ኔትወርክ ዲቫይሶችን፤ ስልኮችን እና ዋየርለስ ሄድሴት ሰፖርት ለማድረግ ሲሆን ዋየርለስ ሲግናል ትራንስሚትድ(የሚተላለፈው) በብሉቱዝ በአጭር ርቀት 10 ሜትር ውስጥ ነው እንዲሁም ብሉቱዝ ዲቫይሶች በአጠቃላይ ግንኙነት የሚያደርጉት 1 Mbps ያነሰ ነው፡፡ የብሉቱዝ ኔትወርክ ፒኮኔት(piconet) ወይም ፐርሰናል ኤርያ ኔትወርክ(PAN) ሲሆን ፒኮኔት ቢያንስ ቢያንስ 2 እና ከ8 ያልበለጡ ብሉቱዝ ዲቫይሶች የተገናኙበት የብሉቱዝ ኔትወርክ አይነት ነው፡፡ዲቫይሶች ግንኙነት ሲያደርጉ ፕሮቶኮል(ቐንቐ) ይጠቀማሉ ብሉቱዝ የተለያዩ ቨርዥን ሲኖሩት እነሱም 1.1, 1.2 and 2.0 ናቸው፡፡ ብሉቱዝ በተለያዩ ዲቫይሶች ላይ የምናገኘው ሲሆን ለምሳሌ፡- በኮምፒውተር፤ በስልክ፤ በጌም መጫወቻዎች፤ ሄድሴት፤ ወዘተ ብሉቱዝ ዲቫይሶች ለማገናኘት ምንም አይነት ኢንስታሌሽን ወይም ኮንፊገሬሽን (ኔትወርክ ዝርጋታ) አያስፈልግም በቀላሉ ዲቫይሱን ብሉቱዝ ኢኔብል(መክፈት) ብቻ ነው የሚያስፈልገው። t.me/zed_comp

last final 2013 pg advertisement(4).pdf7.27 KB

ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን Pdf ይመልከቱ!

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ 2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሣምንት መጨረሻ መርሐ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች 1. የትምህርት መረጃ፡- ሙለ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁሇት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶ ግራፍ 2 የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter/ 3 የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የማመልከቻ ክፊያ የ100 ብር ዯረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210 ፣ 211 እና ከዩቪርሲቲው ድህረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላል፡፡ 4 የግል አመልካቾች፡- ከሚሰሩበት መ/ቤት እንዲማሩ የተፈቀደላቸው ስለመሆኑ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ 5 በመንግስት /በድርጅት ስፖንሰርነት የሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsor ship form / ከዩቪርሲቲው ድህረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላል፡፡ የማመልከቻ፤የፈተና መስጫ፤ የውጤት ማሳወቂያ፤የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ የማመልከቻ ጊዜ ፡- ከነሐሴ 28/2012 ዓ.ም እስከ መስከረም 16/2013 ዓ.ም፤ የማመልከቻ ቦታ ፡-አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን፤ በፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- መስከረም 20/2013ዓ.ም ፤ በፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩቪርሲቲው ድህረ-ገፅ (www.amu.edu.et) መከታተል ይችላል፡፡ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 25/2013 ዓ.ም በድህረ-ምረቃ ት/ቤት ህንፃ ፈተና ይሰጣል፤ የመግቢያ ፈተና ያለፉ የሚገለጽበት እና የምዝገባ ጊዜ፡- በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡ ማሳሰብያ፡-  ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት/ Official Transcript/ በምዝገባ ወቅት ካላቀረበ መመዝገብ የማይችል መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡  በአካል ቀርባችሁ ማመልከት የማትችለ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ/ቁ 1000021480502 ብር 100 ገቢ ያደረጋችሁበትን አንድ ኮፒና ሙለ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ በማድረግ በ Email አድራሻችን admission@amu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አ/ዳ/ጽ/ቤት Tel. +251468814065 +251468814903 https://t.me/zed_comp

ትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስጀመር ሂደት በሶስት ዙር እንደሚከናወን ተገለጸ **************** የትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስጀመር ሂደት በሶስት ዙር እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ማለትም ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል። በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ደግሞ በሁሉም የዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀምሩ ነው ምክረ ሃሳብ የቀረበው። በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ባለው ውይይት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል። ውይይቱ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ለውሳኔ የቀረበ ምክረ ሃሳብ፣ የ8ኛ እና 12ኛ ከፍል ብሄራዊ ፈተናና የግል ትምህርት ቤቶችን የትምህርት አሰጣጥ ሂደት የተመለከተ ነው። የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል። ባለፉት ሁለት ቀናት ከሁሉም ክልሎች የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መካሄዱንና የውሳኔ ሃሳብም መቅረቡን አንስተዋል። የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶም ሁሉም ተፈታኞች ለፈተና እንዲቀመጡ የሚል የውሳኔ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ተገልጿል። የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው። በተመሳሳይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል። የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ለመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚወጣው መመዘኛ በግል ትምህርት ቤቶችም ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል። የግል ትምህርት ቤቶች የምዝገባ ክፍያ በ2012 ዓ.ም በነበረው መጠንና የክፍያ ስርዓት መሆን እንዳለበትም ተገልጿል። የትምህርት ቤቶች የክፍያ ስርዓት በባንክ በኩል ብቻ መፈጸም እንዳለበትም ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ የሚደረገው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ https://t.me/zed_comp

🖥⌨ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ከመግዛትዎ በፊት ሊያውቋቸው የሚገቡ 10 ነገሮች‼️ ✅ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት ስንመርጥ ብዙ ነገሮችን አስበን ነው። ከነዚህ ውስጥ የተለመዱ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ አይነቱና ዋጋው። ✅ አሁን ማንኛውም ሰው #Desktop_PC ከመግዛቱ በፊት ሊያውቃቸው የሚገባቸው ምርጥ 10 ሃሳቦችን ይዘንላችሁ ቀርበናል። 1⃣ ካገለገለ ኮምፒውተር ይልቅ አዲስ ኮምፒውተር ይምረጡ። 2⃣ #Motherboard ውስጥ PCI Express x16 slot መኖር አለበት። ይህም ሌሎች ካርዶችን ለመጨመር ይረዳዎታል። ለምሳሌ፦ ቲቪ ካርድ፣ ግራፊክስ ካርድ እና ሌሎች . . . 3⃣ ሚሞሪው ወይም #RAM ቢያንስ 4GB መሆን አለበት። ይህም ኮምፒውተርዎ እንዳይጨናነቅና ፈጣን እንዲሆን ያደርገዋል። 4⃣ ፕሮሰሰሩ ወይም #CPU Quad-core processor ቢሆን ይመረጣል። ይህም ኮምፒውተርዎ ፈጣንና ብዙ ፕሮግራሞችን በአንዴ የማስተናገድ አቅም እንዲኖረው ያደርጋል። 5⃣ ኮምፒውተሩን ለቤት ከሆነ የፈለጉት ፋኑ የማይጮህና የማይረብሽ ቢሆን ይመረጣል። 6⃣ All-in-one ወይም ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ ኮምፒውተር ይምረጡ (ሞኒተሩ #Flat እና #HDMI_Cable ማስገባት የሚችል፣ #Bluetooth እና #Wi-Fi የሚሰራ እና ሌሎችንም የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች ያሟላ) 7⃣ Single and High powered graphics card ያለው ይምረጡ። ይህም ኮምፒውተርዎ ላይ ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅምዎታል። 8⃣ የሃርድ ዲስኩ ሳይዝ 500 GB ወይም ከዛ በላይ ቢሆን ይመረጣል። ይህም ኮምፒውተርዎ ላይ ብዙ ፋይሎችን የሚያስቀምጡ ከሆነ ነው። 9⃣ ሃይል ቆጣቢና አነስተኛ ወጪ የሚያወጣ ይምረጡ። 🔟 ኮምፒውተር ሲገዙ አብረው #External_Hard_Disc ይግዙ። ይህም ኮምፒውተሩ ቢበላሽ ለFile backup (መጠባበቂያ) ያገለግላል። https://t.me/zed_comp

የዩኒቨርሲቲዎች መከፈተን በተመለከተ ዶክተር ሙሉ ነጋ (የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ) ጠይቀናቸው ተከታዩን መረጃ ሰጥተውናል ፦ - በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ። - የዩኒቨርሲቲዎች ዳግም መከፈት ውሳኔ የሚያገኘው በጤና ሚኒስቴር እና በኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል በመሆኑ የነሱ ምላሽ እየተጠበቀ ነው። - ዩኒቨርሲቲዎች እያደረጉ ያሉትን ዝግጅት በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ሆነዋል? የሚለውን ለመገምገም) ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚቀጥለው ሳምንት ሰፊ የውይይት መድረክ ሊድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው:: Addis Ababa, Ethiopia 0919743630 https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 @tikvahethiopia t.me/zed_comp

ሰላም ውድ የ Tech🌍Zoneᴱᵗʰ ቤተሰቦች ዛሬ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ድረገፆችን (Websites) እንጠቁማቹ። 🔺 የትምህርታዊ ድረገፆች ◽️ www.khanacademy.org ◽️ www.academicearths.org ◽️ www.coursera.com ◽️ www.edx.org ◽️ www.open2study.com ◽️ www.academicjournals.org ◽️ codeacademy.org 🔺የመፀሀፍት ድረገፆች ◽️ www.bookboon.com ◽️ http://ebookee.org ◽️ http://sharebookfree.com ◽️ http://m.freebooks.com ◽️ www.obooko.com ◽️ www.manybooks.net ◽️ www.epubbud.com ◽️ www.bookyards.com ◽️ www.getfreeebooks.com ◽️ freecomputerbooks.com ◽️ www.essays.se ◽️ www.sparknotes.com ◽️ www.pink.monkey.com 🔺Online ትምህርታዊ ድጋፎች ◽️ www.ocwconsortium.org ◽️ www.ocwconsortium.org ◽️ http://ocw.tufts.edu ◽️ http://ocw.upm.es ◽️ http://www.open.edu ◽️ http://ocw.usu.edu/ ◽️ http://open.umich.edu/ ◽️ http://ocw.nd.edu/ 🔺የጥያቄዎች ምላሽ ◽ www.ehow.comwww.whatis.comwww.howstuffwork.comwww.webopedia.comwww.plagtracker.comwww.answers.com 🔺መፈለጊያ (Search) ድረገፆች ◽ www.about.comwww.alltheweb.comwww.altavista.comwww.askjeeves.comwww.excite.comwww.hotbot.comwww.looksmart.comwww.lycos.comwww.dmoz.orgwww.google.comwww.mamma.comwww.webcrawler.comwww.aol.comwww.dogpile.comwww.10pht.com 🔺የአፋልጉኝ ድረገፆች ◽ www.anywho.comwww.infospace.comwww.switchboard.comwww.whitepages.comwww.whowhere.lycos.com 🔺የዜና ድረገፆች ◽ www.abcnews.comwww.cbsnews.comwww.cnn.comwww.foxnews.comwww.msnbc.comwww.nytimes.comwww.usatoday.com 🔺ስፖርታዊ መረጃዎች ◽ www.sportsmangist.comwww.sportsline.comsportsillustrated.comespn.go.comfoxsports.lycos.comwww.nbcsports.comwww.sportingnews.com 🔺የህክምና ትምህርቶች ◽ www.healthatoz.comwww.kidsdoctor.comwww.medexplorer.comwww.medicinenet.comwww.nlm.nih.govwww.planetwellness.commy.webmd.com 🔺ጋዜጦች ◽ www.indexcopernicus.comwww.ajol.infowww.doaj.org ◽️ www.sabinet.co.za ◽️ www.oajse.com ◽️ www.lub.lu.se/en.html ◽️ www.copernicus.org 💠Best websites for games and softwares 📌 PC GAMES 🔰http://oceanofgames.com/ 🔰http://www.ovagames.com/ 🔰http://fitgirl-repacks.site/ 🔰http://skidrowgamez.net/ 🔰http://full-pcgames.com/ 🔰http://www.xfullgames.com/ 🔰http://www.newgamesbox.com/ 🔰http://www.y8.com/ 📌 SOFTWARES 🔰http://getintopc.com/ 🔰https://fullstuff.co/ 🔰http://www.piratecity.net/ 🔰http://gigahax.com/en/ 🔰http://karanpc.com/ 🔰http://www.mixhax.com/ 🔰http://www.novahax.com/ 🔰http://full-pcsoftware.com/ 🔰http://dl.par30dl.com/Software/ 🔰http://s0ft4pc.com/ 🔰http://filehippo.com/ 🔰http://www.fileeagle.com/ 🔰http://softfunda.com/ 🔰https://www.freewaresys.com/ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ https://t.me/zed_comp

_________________________________ አርብ ነሃሴ 8, 2012 ሶፍትዌር ነክ ትምህርት በ እንስትራክተር ዘሀረዲን ሺፋ _________________________________ እንደምን አደራችሁ እንደምን ዋላችሁ እንደምን አመሻችሁ እንደምን ሰነበታችሁ እስቲ ዛሬ አንድ አሪፍ ነገር ላስተዋውቃችሁ። 🙏🙏🙏 =========================== የኮምፒውተር የእይታ(ድስፕሌይ) መስኮት ብርሃን አለመጨመር ወይም መቀነስ አለመቻል የሚያጋጥም ብልሽት ለማስተካከል በዊንዶ 8.1 እና 8 ዊንዶ 8.1 እና 8 አብግሬድ ወይም አብዴት ስናደርግ የስክሪን ብርሃን(Brightness) መጨመርም ሆነ መቀነስ አለመስራት ችግር የሚፈጠር ሲሆን ይሄን ብልሽት እንዴት እንደምናስተካክል ደረጃዎችን ተከትለን እናያለን፡- 1. ዊንዶ መፈለጊያ ገጽ እንክፈት(ከኪቦርድ ላይ ዊንዶ ምልክት እና ሲ ፊደልን እንጫን) 2. በመፈለጊያው ገጽ ላይ Device Manager በመፃፍ እንምረጥ 3. ዲቫይስ ማኔጀር ገጽ ላይ Display adapters እንምረጥ እና ከስሩ Intel(R) HD Graphics የሚለውን መርጠን 4. ቀኝ ክሊክ በማድረግ Update Driver Software 5. Browse my computer for driver software” manually የሚለውን እንምረጥ 6. Let me pick …..on my computer እንምረጥ 7. Microsoft Basic Display Adapter የሚለውን እንምረጥና Next የእይታ መስኮት ብርሃን መጨመሪያ እና መቀነሻ ማስተካከያ ለዊንዶ 7፣ 8፣ 8.1 እና 10 ይሰራል። Share your knowledge free for millions በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ላይክ ሼር ያድርጉ!!! የዛሬው ትምህርታችን ይህን ይመስላል በሌላ ትምህርት እስክንገናኝ መልካም ግዜ ይሁንላችሁ። 🙏 https://t.me/zed_comp

Your computer recycle bean and temp folder contains your trash files and the file shares your storage. It has great impact on the processing speed. So the best practice to make your computer faster than usual use the following tips 1. From your desktop recycle bean folder click and open it and make shift delete 🗣 warning the file are not recovered once deleted. 2. From search bar of windows type %temp% and click enter. The temp folder store temp files. Select all and make shift delete. 3. Make partition from storage . Move your personal file to none window partition. This has great advantage for your files when windows fail. Join the channel and increase your computer knowledge 🗣🗣🗣🗣🗣 subscribe YouTube https://www.youtube.com/channel/UCgCgB8bpYhbbv0LYFrj1eTw Website: https:// www.all-standard.com 🅙🅞🅘🅝 𝑡𝑒𝑙𝑒𝑔𝑟𝑎𝑚 https://t.me/allstanderdcoder

------------------------------------------------------ ማስታወቂያ ------------------------------------------------------ ለግልም ይሁን ለድርጅት መዋል የሚችል የሶፍትዌር አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በቅርበት ማግኘት ከሚችሉት All Standard ቢገዙ በብዙ አማራጭ ደምበኛዎ ጋር መድረስ ይችላሉ። 🏇 ለዳቦ ቤት ምርት፦ ግዢ እና ሽያጭ መመዝገቢያ እና ከሰራተኛ እስከ የምርት ብክነት መከላከያ ሙሉ የኮምፒውተር ሶፍትዌር እንተርኔት ሳይፈልግ በSms ሪፖርት የሚልክ። 🍎 የት/ቤት መቆጣጠሪያ ከምዝገባ እስከ ሰርተፊኬት እንዲሁም በቤት ሆነው ተማሪዎችን መፈተን ከሚያስችል አዲስ መፈተኛ ዘዴ ጋር። 👨‍💻👨‍💻 አዳዲስ በማለቅ ላይ ያሉ ስራዎች፦🤖🤖 👖👠👔 ለሱቅ እቃ መረከቢያ እና ሽያጭ መዝግቦ ባላንስ መስሪያ። ትርፍ እና ኪሳራዎን በወር ከፋፍሎ የሚነግርዎ። 👍ሌላም የሚፈልጉትን ቢያዙን መልሳችን ፈጣን ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ የሞባይል እና የኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን እንሰራለን 🌻🌻🌻የሚፈልጉት የድርጅት ማስታወቂያ ዌብሳይት ከሆነ በአንድ ሳምንት እናስረክባለን ይላል 𝙖𝙡𝙡 𝙨𝙩𝙖𝙣𝙙𝙖𝙧𝙙 🌎🌎🌎🌎 ለበለጠ መረጃ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ Join ይበሉ 👇 https://t.me/allstanderdcoder 𝙖𝙡𝙡 𝙨𝙩𝙖𝙣𝙙𝙖𝙧𝙙 🅦🅔 🅐🅛🅦🅐🅨🅢 🅒🅞🅓🅔 0923137897 Ⓜ🅤🅑🅐🅡🅘🅚 🅝🅔🅙🅐

__________________________________ 𝕄𝕖𝕥𝕙𝕠𝕕 𝟛: ℂ𝕝𝕖𝕒𝕟 𝕚𝕟𝕤𝕥𝕒𝕝𝕝 𝕎𝕚𝕟𝕕𝕠𝕨𝕤 𝟙𝟘 𝕨𝕚𝕥𝕙𝕠𝕦𝕥 𝕝𝕠𝕤𝕚𝕟𝕘 𝕕𝕒𝕥𝕒 If you prefer installing Windows 10 without losing data from USB drive or installation disc, you can also choose this method. Before you do, you need to make sure your C: drive has more than 16GB of free space. Step 1. 𝐈𝐧𝐬𝐞𝐫𝐭 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐢𝐧𝐬𝐭𝐚𝐥𝐥𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐝𝐢𝐬𝐜 and boot from it. If you do not have one, you can download the Windows Media Creation tool to create one. Step 2. When it loads, select the language and keyboard, then click "𝐍𝐞𝐱𝐭". Step 3. Click "𝐈𝐧𝐬𝐭𝐚𝐥𝐥 𝐍𝐨𝐰". Step 4. 𝐓𝐲𝐩𝐞 𝐲𝐨𝐮𝐫 𝐩𝐫𝐨𝐝𝐮𝐜𝐭 𝐤𝐞𝐲 or skip it. Step 5. Select the installation type "𝐂𝐮𝐬𝐭𝐨𝐦". Step 6. At the following screen, just select the C: drive and click Next to proceed. Then, wait patiently until the installation complete 100%. 𝐴𝑠 𝑙𝑜𝑛𝑔 𝑎𝑠 𝑦𝑜𝑢 𝑑𝑜 𝑛𝑜𝑡 𝑓𝑜𝑟𝑚𝑎𝑡 𝑡ℎ𝑒 𝐶: 𝑑𝑟𝑖𝑣𝑒 𝑖𝑛 𝑡ℎ𝑒 𝑆𝑒𝑡𝑢𝑝, 𝑦𝑜𝑢 𝑤𝑖𝑙𝑙 𝑛𝑜𝑡 𝑙𝑜𝑠𝑒 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑑𝑎𝑡𝑎, 𝑏𝑢𝑡 𝑡ℎ𝑒𝑦 𝑎𝑟𝑒 𝑚𝑜𝑣𝑒𝑑 𝑡𝑜 𝑎𝑛𝑜𝑡ℎ𝑒𝑟 𝑙𝑜𝑐𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛. 𝐴𝑓𝑡𝑒𝑟 𝑡ℎ𝑒 𝑖𝑛𝑠𝑡𝑎𝑙𝑙𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛, 𝑦𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑓𝑖𝑛𝑑 𝑎 𝑓𝑜𝑙𝑑𝑒𝑟 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠.𝑜𝑙𝑑 𝑖𝑛 𝑡ℎ𝑒 𝑟𝑜𝑜𝑡 𝑑𝑖𝑟𝑒𝑐𝑡𝑜𝑟𝑦 𝑜𝑓 𝐶: 𝑑𝑟𝑖𝑣𝑒. 𝐴𝑙𝑙 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑎𝑟𝑒 𝑠𝑎𝑣𝑒𝑑 𝑡ℎ𝑒𝑟𝑒. 𝐴𝑓𝑡𝑒𝑟 𝑐𝑜𝑝𝑦 𝑎𝑙𝑙 𝑦𝑜𝑢𝑟 𝑛𝑒𝑒𝑑𝑒𝑑 𝑓𝑖𝑙𝑒𝑠 𝑜𝑢𝑡 𝑓𝑟𝑜𝑚 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠.𝑜𝑙𝑑 𝑓𝑜𝑙𝑑𝑒𝑟, 𝑦𝑜𝑢 𝑐𝑎𝑛 𝑢𝑠𝑒 𝐷𝑖𝑠𝑘 𝐶𝑙𝑒𝑎𝑛𝑢𝑝 𝑡𝑜 𝑑𝑒𝑙𝑒𝑡𝑒 𝑡ℎ𝑒 𝑊𝑖𝑛𝑑𝑜𝑤𝑠.𝑜𝑙𝑑 𝑓𝑜𝑙𝑑𝑒𝑟 𝑡𝑜 𝑓𝑟𝑒𝑒 𝑢𝑝 𝑑𝑖𝑠𝑘 𝑠𝑝𝑎𝑐𝑒. https://t.me/zed_comp