cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍቅር እና መዝናኛ

ቴሌግራም ላይ አሉ ከተባሉ የቀልድ ቻናሎች በቀዳሚነት የሚጠራው ምርጡ ቻናል ነው comment Bey_kiyaye አስቂኝ ቀልዶች እና የፍቅር ታሪኮች No_ጭንቀት_No_tata_jest_relax_&_feta በየቀኑ 🗯ለጆሯችሁ አዳዲስ 💎👂😋 የሆኑ እና ያልተደመጡ 👌👌 ጥርስ የማያስከድኑ ሽንት አስጨራሽ ቀልዶችን ወደናተ 📲📲📲 እናደርሳለን @fikrenakeld ❌Leave❌_ማለት_አይቻልም

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
392
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​​​​. 💓❦የልቤ ትርታ❦💓 💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘 #ክፍል_3 ...🖌በክፍል ሁለት እንደምታስታውሱት መቅደስና ዮናስ ካፌ ቁጭ ብለው እያወሩ ሳለ ነበር ጌዲዮ ባጋጣሚ መጥቶ አይን ላይን የተፋጠጡት.... .......መቅደስ ከመቀመጫዋ ተነሳች ጌዲዮም በነበረበት ቆሞ እሷን እያየ ጭንቅላቱን ያዘ መቅደስ በድንጋጤ ሙክክ ብላለች እንደው አይተው ሲገምቷት ባሏ ከሌላ ወንድ ጋር የያዛትን ሴት ነው የምትመስለው ጌዲዮ ሰውነቱን እንደማንቀጥቀጥ አደረገው ይህን ጊዜ ሊያመው እንደሆነ አወቀች መቼም መቅደስ የግቢው ቅፅል ስሟ የጌዲዮ የግል ነርስ ሆኗል በፍጥነት እየተንቀጠቀጠች ቦርሳዋን ከፈተች..... ዮናስ ምንም እንዳልተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው እንኳን አላላትም ምክንያቱም ጌድዮን አይቶታል መቅደስም ቦርሳዋን ጠረንቤዛው ላይ ዘረገፈችው ይህን ጊዜ ዮናስ ብዙ ሴቶች ወደሱ እያዩ ስለነበር ሼም ያዘው ለመነሳትም አቃጣው መቅደስም በሚርበተበተው አንደበቷ ማማማ ማን ነበር ያያያ..ልከኝ...አ..ው..ዮ.ናስ.እእ..ባክህ..ክርቢት..ካካ..ለህ ይዤ ነነ.በር እ..ኮ.ጠፍኝ አለችው ዮናስም ከቦርሳዋ ከዘረገፈችው እቃ ወደ ክርቢቱ እያመለከተ ያውልሽ አላት መቅደስም ክርቢቱን ልታነሳ ስትቸኩል የብርጭቆውን ጁስ ዮናስ ላይ ደፋችበት ዮናስ በጣም ጮኸ ግን አልሰማችውም ይቅርታም ሳትለው ክርቢቱን ይዛ ወደ ጌዲዮ በረረች........ ......ከዛም ህመሙ ሳይብስበት ክርቢቱን አጫጭሳ ሰውነቱን አረጋግታ ደግፋ ከወንዶች ማደሪያ በር ላይ አድርሳው ተመለሰች ስትመለስ ዮናስም ወደማደሪያው እየሄደ ተገጣጠሙ ከዛም በጣም ይቅርታ አለችው በርግጥ በሰአቱ ስትደፋበት ብዙ ሴቶች ቢስቁም የለበሰውን ቲሸርት ሲያወልቀው ግን እንኳን ደፋችበት ያሉት በዝተዋል የዮናስ ደረት ላይን ያሳሳል ለነገሩ ምን አለበት ከትምርቱ ይልቅ ለሰውነቱ ቅርፅ ሲል እስፓርትን ነው የሚወደው እናም ይቅርታ እንዳደረገላት ነግሯት በሌላ ጊዜም ተገናኝተው እንድትክሰው ቃል አስገብቷት ተለያዩ። .......ቦርሳዋንም አስተናጋጇ አስተካክላ ስለጠበቀቻት ይዛ ወደዶርሟ ሄደች ግራ የገባት ግን የሷ መደንገጥ ሳይሆን የጌዲዮ እሷን ከሌላ ጋር ስላያት የህመሙ መቀስቀስ ነው እውነት ይወደኝ ይሆን ብላ አሰበች ደግማም አረ አይመስለኝም እያለች በሁለት ሀሳብ ተይዛ ብቻዋን ታወራ ጀመር። ......ጌዲዮም እንደልማዱ መፅሀፉን ይዞ ጋደም ብሎ በሀሳብ ተውጧል የዶርም ጓደኞቹም አንድ ላይ ቁጭ ብለው እያወሩ ነበር ጌዲዮም ከተለምዶ ውጪ ጮክ ብሎ አንድን ሴት ከሌላ ወንድ ጋር ስላየሀት ምን ያናድዳል ብሎ ጠየቃቸው ሁሉም በድንጋጤ ወደሱ ዞሩ ቀልዱን ነው እንዳይሉ ጌዲዮ እንኳን ሊቃለዳቸው የግዜር ሰላምታንም ሰቷቸው አያውቅም ከምሩንም ነው እንዳይሉ እሱ ስለሴት ከመቼ ወዲ ሲያስበው ነው ብለው ወደራሳቸው ሲመለሱ አሁንም መልሱልኛ አላቸው የሚመልሱት ጠፋቸው ከዛም አንድኛው ፎንቃ ይሆናላ አለው ጌዲዮም ምን ማለት ነው አለው ከዛም እንደምንም ተደፋፍሮ ፍቅር ይዞህ ይሆናል ታዲያ ፍቅር ያናድዳል እንዴ ሲላቸው እየውልህ ጌዲ አንተን ስለፍቅር ለማስረዳት ከሀ መጀመር አለብን ሲለው አንድኛው ጓደኛቸው እንደመሳቅ ብሎ ዝም ለማስባል በቁንጥጫ መዠለገው ልጁም ዝም አለ ጌዲዮም ወደ ሀሳቡ ተመለሰ። ........ከዛም በሌላ ቀን መቅደስን የሚያፈቅራት አስተማሪ ሆን ብሎ ጌዲዮን እንድጠላው ለማድረግ መፅሀፍ ላይ የሌለውን ስለሚጥል በሽታ አስከፊነት ጌዲዮን ምሳሌ አድርጎ ማስተማር ጀመረ። መቅደስ አበደች ክፍሉን ባንድ እግሩ አቆመችው አስተማሪው ላይ የስድብ ናዳ አወረደችበት ተማሪው ሁላ ግራ ገባው የሷ ፍቅር እስከምን ድረስ ነው.....አስተማሪው እንደሚከሳት አሳውቆ ከክፍል አስወጣት ሄዋንም አብራት ወጣች ከወጡም ቡሀላ መቅደስ ግን ምን እየሆንሽ እንደሆነ ይታወቅሻል አለቻት መቅደስም አዎ ይታወቀኛል ሲጀመር ይህ ትምርት መፅሀፍ ላይ የለም ሲቀጥል አንድን አገር አቀፍ ጎበዝ ተማሪን ምሳሌ ማድረግ የለበትም በቃ ጌዲዮን ማንም በክፉ ሲያነሳው መስማት አልፈልግም ብላ እጆቿን እያወራጨች ማልቀስ ጀመረች ሄዋንም የምትላት ግራ ገባት በቃ አሁን አስተማሪውን ይቅርታ በይና ወደክፍል ግቢ አለቻት እሷም ይቅርታ ብላ ጮኸችባት እንደውም ብቻዬን ተይኝ ብላ እያለቀሰች ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ወጣች..... .....በንጋታውም ይህ ወሬ ተባዝቶ ጌዲዮ የተኛ መስሏቸው ጓደኞቹ ሲያወሩ ሰማ። ጌዲዮም ምንም ሳይል ከመኝታው ተነስቶ ወደሴቶች ማደሪያ ሄደ በር ላይም ብርሀንን አገኛት ከዚያም መቅደስን ጥሪልኝ አላት ብርሀንም በፍርሀት እየተንቀጠቀጠች ወደ ዶርም እሮጠች በሩን በርግዳ መቅደስ መቅደስ አለቻ እሷም አቤት ስትላት እያለከለከች ጌዲዮ በር ላይ ሆኖ እየጠራሽ ነው አለቻት መቅደስም የምትገባበት ጉድጓድ ጠፋት ቁጭ ብድግ ትል ጀመር ለነገሩ እንኳን እሷ ጓደኞቿም ደንግጠዋል ከዛ እንደምንም ተረጋግታ ሄደች ገና ፊትለፊቱ ስትቆም ጌዲዮ አይኑ እንባ አቅርሮ ነበር.. .....ከዛም ጮክ ብሎ ስሚ መቅደስ ከዚህ ቡሀላ ስለኔ ምንም አይመለከትሽም ብወድቅ ምንም ብሆን አንቺ አይመለከትሽም ገባሽ መቅደስም አይኗን በንባ ሞልታ ትሰማው ጀመር ...ቀጠለ በቃ እኔ መውደቅ አዲሴ አይደለም ማንንም አልፈልግም እንኳን የበሽተኛ ምሳሌ የፈለጉትን ያርጉኝ ጌዲዮ ባይኑ የሞላው እንባ እንደጎርፍ ይወርድ ጀመር ሁሉም ተማሪ ከሩቅ ሆኖ ያያቸዋል ከዛሬ ጀምሮ ወድቄ ስነሳ አጠገቤ ባይሽ እመታሻለሁ ስለኔ እንድትጎጂ አልፈልግም ብሏት እያለቀሰ ከግቢ ወጣ መቅደስም በቆመችበት ቦታ ተቀመጠች ጓደኞቿም መጡ አቅፈውም ያባብሏት ጀመር እሷ ግን ለቅሶዋ ጨመረ ቅስሟም ተሰበረ.... አንድ የነበረኝ ሰበብ አንተን ለማየት ህመምክ ነበረ የሰጠኝ ብርታት: ፍቅሬን ባልነግርክም ቁጡነትህ ከብዶኝ መውደቅክ ነበረ መፅናኛ የሆነኝ: ዛሬ ግን ጨክነክ አትደግፊኝ አልከኝ አረ መላ በሉኝ ሰዎች ምን ይዋጠኝ:... ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ ክፍል 4 ከ60 ♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ከወደዱት ሼር ያርጉ 🙏 ━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━ @LovestoryB_wiz_H @LovestoryB_wiz_H For any comment @Romio_Bina
Show all...
❤️ 22
ዉዴ አንድ ምስኪንየመንግስት ሰራተኛ ጥሬ ስጋን ከሚናፍቀው በላይ ትናፊቅኛለሽ😍❤️
Show all...
ፎቶ ማሰራት ምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ያናግሩኝ👉👉👉👉@bey_kiyaye👈👈👈
Show all...
🦋Promise day🦋 ♥️♥️♥️♥️♥️♥️ ዛሬ የpromiss ቀን ነዉ እና ከጓደኞችህ መሀል ምትወዳችዉ ልትረሳቸዉ የማትችላቸዉ መርጠህ ለ 18ቱ ብቻ ላክ ልክ እኔ ላንተ/ቺ እንዳደረኩት ከዛን ስንት tex ተመልሶ እንደገባልህ እየዉ😍♥️♥️♥️😘😘😘😜 ቃል እገባለዉ አንተ/ቺ በህይወቴ ልረሳቸዉ ከማለችላቸዉ ጓደኞቼ መሀል 1ዱ ነህ /ነሺ ዛሬ የpromiss ቀን ነዉ ይሄንን መልዕክት በህይወታችዉ ልትረሷቸዉ ለማትችሏቸዉ ጓደኞቻችሁ ለእኔ ላኩልኝ😁 👌👌👌😍😍 @fikrenakeld @fikrenakeld For any comment @bey_kiyaye
Show all...
​​​​. 💓❦የልቤ ትርታ❦💓 💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘 #ክፍል_2 ...🖌መቅደስ ድንጋጤው ባይለቃትም አቅሟን ሰብስባ ጌድዮን ወደ ወደቀበት ስፍራ በረረች ነገር ግን በጣም እየተወራጨ ስለነበር የምታደርገው ጠፋት ከዛም አያቷ ለሚጥል በሽታ የክርቢት ጭስ ጥሩ እንደሆነ ያወሩት ትዝ አላትና ሁሉም ተማሪ ጋር እየዞረች ክብሪት ያለው ማለት ጀመረች።በሁኔታዋ እሩቅ የነበሩት ሁሉ መሰባሰብ ጀመሩ አብሮ አበድ ሳትባልም አይቀር መቅደስ በዛ ሰአት የስሟ ነገር ግድም አይሰጣትም ግን አለኝ እንቺ የሚላት አጣች ውስጥ ውስጡን ይስቁባት ይሳለቁባት ጀመር ። ከሰው እያደርኩኝ ሰው እንዴት ይናፍቀኝ ከሰው እያደርኩኝ ብርዱ እንዴት ተሰማኝ: አረ ጨከኑብኝ ተደፍቼ እያዩኝ ባላየ ባልሰማ ዝም ብለው አለፉኝ: የማን ያለህ ልበል ከንባ ጎርፍ በቀር ሰው በሰውነቱ ሲቀር ሳይከበር???? .......መቅደስ አለቀሰች እንደምንም ብላ ጭንቅላቱን ጭኖቿ ላይ አድርጋ ባፍና ባፍንጫው የሚፈልቀውን አረፋ በለበሰችው ነጠላ ትጠርግለት ጀመር አጭር ለማይባሉ ደቂቃዎች ማንቀጥቀጡ አላቆመም ነበር ከዛም ሊነቃ ሰውነቱ ሲረጋጋ ሁሉም ተበተነ መቅደስ ግን አይኖቿን ከፊቱ ላይ ተክላ መንቃቱን ትጠባበቅ ጀመር። .......ከደቂቃዎችም ቡሀላ ጌድዮ አይኖቹ ከመቅደስ አይኖች ጋር ተጋጭተው ተገለጡ የመቅደስ አይኖች ማልቀሷን ያሳብቃሉ ከንፈሮቿም ይንቀጠቀጣሉ ጉንጮቿ በንባ እርሰው ላይን ያሳሳሉ ጌዲዮ ትኩር ብሎ አያት እሷም ከመደንገጧ የተነሳ ሰውነቷን መቆጣጠር ከበዳት። ጌዲዮ ቀስ ብሎ ከግሮቿ ላይ ተነሳ አስተያየቱ ግን መልካም እንዳደረገችለት ሳይሆን ልክ እንደጠላቱ ነበር.....ከዛም ጥሏት ሄደ ትንሽ ከተጓዘም ቡሀላ ቆም ብሎ አሰበና ተመለሰ መቅደስም ከመሬት ተነሳች ......እሱም መሬት መሬቱን እያየ #አመሰግናለሁ አላትና ተመልሶ ሄደ።መቅደስ ግን ደስ አላት ፀሎቷም ሰመረ........ መቅደስ የግቢው መነጋገሪያ ዜና ሆነች ግማሹ ጎበዝ ተማሪ ስለሆነ ደግሞ እሷም ስለሆነች አዝናለት ነው ይላሉ ግማሹ ደግሞ ለዚህ አይመስለኝም.... የለ አፍቅራው ነው ...ሃሃሃሃሃሃ ጌዲዮ አሁን ምኑ ይፈቀራል ......አረ ከበሽታው በቀር ጌዲዮ ምን ይጎለዋል. ......ምን አለውና በቃ ግቢው ባንድ እግሩ ቆመ። ......መቅደስ ከሱ እንደተለየች ወደ ዶርም ነበር የሄደችው ጓደኞቿ ቀድመዋት ገብተዋል ልክ ስትገባ መቅዲ ግን ምን ታምር ነው ምን ጉድ ነው እያሉ ይነዘንዟት ጀመር ከጓደኞቿ አንዷ የሆነችው ብርሀን ቀጠለች.....እኔን ግን የገረመኝ የመቅዲ እንደዚህ መሆን ሳይሆን የሱ አለመማታት ነው።መቅደስም አረ ተረጋጉ ጌዲዮ እኮ እንደምታስቡት ክፉ አይደለም ስትል ዶርሙን በሳቅ ሞሉት ሄዋን ቀጠለች ባንድ ቀን እንደዚህ አፍሽን ሞልተሽ ስለሱ ካወራሽ ሳምንት አብረሽው ብትሆኚማ ታሪክ ትፅፊለታለሽ እያሉ መሳሳቅ ጀመሩ ።ብርሀን ተነሱ ሻይ ቡና ብለን እንም ጣ አለች ሄዋን እና ወይንሸት ተስማሙ መቅደስ ግን ማንበብ እንደምትፈልግ ነግራቸው ቀረች እነሱም ጥለዋት ሄዱ። እሷ ግን እንኳን ልታነብ በደስታ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፍቷታል።ከቆይታዎች ቡሀላ ሰአዳ በሩን ከፍታ ገባች መቅደስን ሰላም ካለቻትም ቡሃላ ፊቷ ላይ የሚነበበውን ደስታ አይታ ኢጃቧን እያወላለቀች ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ይህ ሁሉ ደስታ አለቻት መቅደስም ለጌዲዮ ያደረገችለትን ነገረቻት ሰአዳም ይህንንማ ገና ከበር ነው የሰማሁት አለቻት መቅደስም በመፍነቅነቅ አመሰግናለሁ አለኝ እኮ ስትላት ሰአዳ በሳቅ ወደቀች እንዴ እንዲህ ሲያዩሽ እኮ አመሰግናለሁ ሳይሆን አግቢኝ ያለሽ ነው የምትመስዪው ብላት መፅሀፏን ይዛ ቆጧ ላይ ወጣች። .........ጌዲዮም ከመኝታው ላይ ተጋድሞ መፅሀፉን እያነበበ ነው የዶርሙም ተማሪዎች አላስችል ብሏቸው ስለሱና ስለመቅደስ ይንሾካሾካሉ ጌድዮም ቀስ ብሎ ዝም ማለት አትችሉም አላቸው።ትንፋሽ ሳያሰሙ ዝም ብለው ከዶርም ወጡ።እውነት ለመናገር የዛሬው ገጠመኝ ለጌዲዮም ገርሞት መፅሀፉን እያየው እንጂ እያነበበው አልነበረም። ........ከዛን ጊዜ ጀምሮ ጌድዮ ወደቀ ሲባል የመቅደስ መገኘት የተለመደ ሆነ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ጌዲዮ ከ አመሰግናለሁ ውጪ ሌላ ቃል አናግሯት አያውቅም እንደውም ገና ሲነቃና ሲያያት ደሙ ይፈላል የመቅደስ እሱን ማናገር ፍላጎት የሱ መሸሽ ተደምሮ ስቃይዋን አበዛው። ከለታት አንድ ቀን ብቻዋን ካፌ ቁጭ ብላ እያለ ዮናስ የሚባል ልጅ መቶ አጠገቧ ቁጭ አለ ።ይቅርታ የኔ ወንድም ወንበሩ ሰው አለው አለችው ታዲያ ምን ችግር አለው ሲመጣ እነሳለኹ አላት እሺ አለችውና ስልኳን አውጥታ መነካካት ጀመረች ከዛም መቅዲ አላት ድንግጥ ብላ የት ታውቀኛለህ አለችው ዮናስም ሳቅ ብሎ እዚ ግቢ አንቺን የማያውቅ አለ እንዴ አላትና እኔን ካላወቅሽኝ ዮናስ እባላለሁ ግን ደስ እንዲለኝ ዮኒ በዪኝ አላት።መቅደስም ፈገግ ብላ በዝና የማውቅህ መሰለኝ በሚገባ አላት። ይቀጥላል..... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 60 ♥️VOTE አርጉ፡፡ ከወደዱት share ማረግ እንዳይረሱ ━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━ @fikrenakeld @fikrenakeld For any comment @beykiyaye
Show all...
❤️ 8
​​​​​​. 💓❦የልቤ ትርታ❦💓 💘✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼💘 #ክፍል_1 ...🖌ዛሬ ቀኑ አዲስ ነው አሮጌ አመት አልቆ ሁሉም አዲስ ሆኗል ትምህርት ቤቶችም እየተከፈቱ ነው። ዩንቨርስቲዎችም ለተማሪዎቻቸው አቀባበል እያደረጉ ነው። ጌዲዮ የሁለተኛ አመት አመት የዲግሪ ተማሪ ነው። በባለፈው አመት አገር አቀፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጣውም እሱ ነው.....ዛሬ የሁለተኛ አመቱን ትምርት ሊቀጥል ሻንጣውን ሸክፎ የጅማ ዩኒቨርሲቲን እረግጧል።እናም አቀርቅሮ በመንገድ ላይ ሳለ አንዲት ቅልብልብ ያለች ቆንጆ ፊትለፊቱ መጥታ ተጋጩ ከዚያም እያየህ አትሄድም ብላ ጮኸችበት እሱ ግን ምንም ሳይላት መንገዱን ቀጠለ ልጅቱም ይቅርትታ ባለመጠየቁ ተናዳ ተከትላ ሄዳ ልብሱን ያዘችና እያናገርኩህ አይደል አለችው ያምሀል አታስተውልም እያለች....የስድብ አይነት ታወርድበት ጀመር ጌዲዮን ግን እንኳን ይቅርታ ሊጠይቃት ቀናም አላለላት...... ብዙ ተማሪዎች ከሩቅ ሆነው በፍርሀት ነበር የሚያዩዋቸው ምክንያቱም ጌዲዮ ከባድ የሚጥል በሽታ አለበት ጊቢውን ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ ከመፅሀፍና ደብተሩ ውጪ ጓደኛው ነኝ የሚል ማንም የለም ሲበዛ ኮስታራ ዝምተኛ። ብቸኛ ነው ከትምህርቱ ውጪ ከመምህራኖቹ ጋር እንኳን አፍ ለአፍ ገጥሞ አያውቅም ማንም ሲስቅ አይቼዋለሁ የሚል የለም ከላይ ጀምሮ እስከታች ሁሉም ይፈሩታል። መቅደስ ግን አታውቀውም የመጀመሪያ አመት ትምህርቷን ለመከታተል ገና ጊቢውን መርገጧ ነው!!! ............እናም እጇቿን ከልብሱ አላቆ ግራ ይዞ መሄድ ፍሬን ከለቀቀ መኪና እራስን ለማዳን ይጠቅማል እኔ ባላይሽም አንቺ እያየሽ መሄድ ግዴታሽ ነው አላትና አመናጭቋት ሄደ። መቅደስም ሁኔታው ግገርሟት በነበረችበት ቆማ ሲሄድ ታየው ጀመረ እናም እግዜር አወጣሽ የሚሉ ቃላቶች ከብዙ ተማሪዎች ወደሷ ተወረወሩ ሁኔታው ግራ አጋባ አንድ ተማሪ ልክ እንደዛ ሲላት ምን ለማለት ፈልጎ እንደሆነ ጠየቀችው?? ልጁም እንዴ ጌዲዮ ማለት እኮ የግቢያችን አስፈሪና ጎበዝ እንዲሁም በሽተኛ ተማሪ ነው አላት። .......ከዛ ወዲ ብዙ ጊዜ ልታናግረው ፈልጋ ሳይሳካላት ቀረ እሷም የግቢው ጎበዝና ተወዳጅ ሲበዛም ተፈቃሪ ተማሪ ሆነች።ያያት ያረግድላታል እሷ ግን ሀሳቧ ትምርቷ ልቧም ጌዲዮን ጋር ነበር። ......ቀኑ ሰንበት ነው መቅደስም ከጓደኞቿ ጋር በመሆን ቤተክርስቲያን ሄዳለች ውዳሴም አድርሰው ሲጨርሱ የመቅደስ የመጨረሻ ፀሎቷ የመጀመሪያ ቀን የሰማሁትን የጌዲዮን ድምፅ አሰማኝ ነበር።ሲጨርሱም ወደ ግቢ ተመለሱ ....,..,...ግቢ ሲመለሱ ባየችው ነገር ግን በጣም ደነገጠች አንድ ወጣት መሬት ላይ ተዘርሮ ሲንፈራፈር ባፍና አፍንጫውም አረፋ ሲደፍቅ ነበር በዙሪያው ብዙ ተማሪ አለ ግን የሚረዳው አንድም ተማሪ አልታያት አለጓደኞቿም በነበሩበት ቆሙ እሷ ግን ልትሄድ እግሯን ስታነሳ ጓደኞቿ ያዙዋት መቅደስም ምን ሆናችሁ ልንረዳው ይገባል ብላ ጮኸችባቸው.....አንዷ ጓደኛዋም ጌዲዮ እኮ ሁሌ ነው የሚጥለው ደሞ ማንም ተጠግቶት አያውቅም ቢጋባብሽስ መሄድ የለብሽም ደሞ ካንድ ግቢ መምህርና ተማሪ ተለይተሽ የምትረጂው ማን ስለሆንሽ ነው እያሉ በየተራ ለፈለፉባት እሷ ግን የሰማችው ጌዲዮ ነው የሚለውን ቃል ነበር።... .......ደነገጠች ተንቀጠቀጠች በሁኔታዋ ጓደኞቿ ግራ እስኪጋቡ ድረስ ተርበተበተች ለብዙ ጊዜ በልቧ ሲመላለስ የነበረው ጌዲዮ እንዲህ ተዘርሮ ሲንፈራፈር ስታስተውል እሱ መሆኑን ስታውቅ በነበረችበት ደርቃ ቀረች.........። ከዚ ሁሉ ተመልካች ተለይታ እሷ ትረዳው ይሆን??? ይቀጥላል... ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል👉 ♥️VOTE አርጉ፡፡ክፍል 2 ከ 50 ♥️ ቡኃላ ይቀጥላል፡፡ ┄┄┉┉✽̶»̶̥🌹✿🌹»̶̥✽̶┉┉┄┄ 🌳ከወደዱት ሼር ያድርጉ🌳 @fikrenakeld @fikrenakeld For any comment @bey_kiyaye
Show all...
❤️ 9

​​​​​​​​​​​እንሆ የእናንተን የማንበብ ፍላጎት እንዲጨምር ለማድረግ እየሰራ የሚገኘው #የፍቅር_ጀማሪ 🌺 እናንተን ያስተምራል ብለን ያዘጋጀነውን #የልቤ_ትርታ የተሰኘውን 27 ክፍል ያለው ልብ አንጠልጣይ ታሪክ 50 vote❤️ ቡሀላ ለማቅረብ ዝግጅታችንን የጨረስን መሆኑን እንገልፃለን።
Show all...
❤️ 10