425
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
425
#ጨክነሽ🚶♀
፧
ከእርሳስ ጋር ሆኖ ውሎዬ ቋንቋችን ስለሚግባባ፣
አንቺን ለይቶ ያውቅሻል ስስልሽ ልክ እንደአበባ፣
ጨክኜ የማላውቀውን በእርሳሴ ሳይቀር መፍረዴ፣
ቀረጭዋለሁ ሺ ግዜ በለቅሶው ሳይባባ ሆዴ፣
መች አሰብኩና ለአፍታ ድካሙን ስደመስሰው፣
በህመም ያሰመረውን ሽራፊ ላፒስ ሲገምሰው፣
መቼ ታየኝ የእርሳሴ ሲቃ ቀርጬ እንደጨረስኩት፣
አንቺን ለመኳል ስጠበብ ምናለ ያላፈረስኩት፣
ወይ ከእርሳሴ አልሆንኩኝ ወይ አልመጣሽ አንቺ፣
ወይ ደሞ የለኝም "ለክፉ ቀን" ብዬ የደበኩት ካንቺ፣
ጨክነሽ ካልመጣሽ🥹
የእርሳሴ አጥንት 'ሾህ ሆኖ እንዳይወጋሽ
ስዕልሽን እንቺ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getmk2g
425
እጠብቅሻለሁ🕴🕴🕴
አንቺን መናፈቄን በየ እለት ውሎዬ ስነግርሽ ኖሬአለው፣
ፍቅሬን ብትገፊም እመካብሻለሁ አስብልሻለሁ፣
ደግሞ ያየሁሽለት ሲነሳ ህመሜ ፣
ሳልጠግብሽ ሳልረካ ሲጠፋ ሰላሜ፣
እታመማለሁኝ እንደ አዲስ አፍቃሪ፣
ከሌላ እንዳልደርስ አድርገሺኝ ፈሪ፣
ያላንቺ አማራሪ፣
ሰው ሲያይ የቀድሞ የተለየውን ሰው፣
የጥላቻ እሳት ነው ውስጡ ሚለኮሰው፣
የኔ አጀብ ጉድ ነው ሳይሽ ነው ምሳሳው፣
ደገግሞ ዛሬ አየሁሽ ልትናፍቂኝ ነው፣
እንደ ሙሾ አድራሽ ደረቴን ስደቃ ሳነባ ላድር ነው፣
አወይ መውደድ ደጉ አወይ ማፍቀር ደጉ፣
ስለይሽ ናፍቆታት በውስጤ አደጉ፣
ሆዴ(2) ደሞ አየሁሺኝ፣
ከአይኔ ሳትርቂ ደጋግመሽ ናፈቅሺኝ፣
እኔ ያንቺ ጎጆ ኮሳሳው ደሳሳው፣
ራቅ ስትዪ ነው መኖርሽን ምረሳው፣
እኔ ያንቺ አንቀልባ ታዝለሺኝ ካልያዝሺኝ፣
የወደኩ ለታ ሁሉ ነው ሚረሳኝ፣
አዎን ውዴ(2) ፍቅሬ አልይሽ አልራቅሽ፣
ያየሁሽ የራኩሽ ለታ ነው የማጣሽ፣
አረ አጀብ ጉድ ነው ስትርቂ ሚያስከፋኝ፣
ስትቀርቢ ሚያስነባኝ፣
አቤት ጉድ መፋቀር አጀብ ነው መዋደድ፣
ቀድሞስ ምን አስኬደኝ በተረሳ መንገድ፣
ባልታወሰ ፍቅር ፡ በሔደ መቃብር፣
እየመጣሽ ጎብኚኝ እዛው ነው የምኖር፣
ኑሮዬ በዛው ነው መቃብር ሞት ጠሪ፣
እጠብቅሻለው አንቺ እንዳትቀሪ ፣
አዎ እንዳትቀሪ እጠብቅሻለው፣
ባንቺ ያገኘሁት የሰራሁት ቤቴን ላሳይሽ እሻለው፣
እጠብቅሻለው።
#ገጣሚ አቤል አለማየሁ
@getemk2g
@getemk2g
@getemk2g
425
#አፍቅሬሽ_ነበር
፧
የማይቻል የለም ቻልኩት፣
ያፈቀርኩትን ልብሽን ናኩት፣
"ለምን?" እንዳትይ እንዳጠይቂኝ፣
ስንቄን ቀምተሽ ሸኝተሽኛል እንዳጠብቂኝ፣
ጉዞዬ ፊት ነው ለመመለስም ከቶ የማይቻል፣
በየዱካዬ አሜኬላ እሾህ በቅሎ ይከማቻል፣
ልመለስ ካሰብኩ ወደኋላዬ፣
ይደማል እግሬ ይህ ነው ዕጣዬ፣
አፍቅሬሽ ነበር ከሰው ነጥዬ፣
ቆረጥሽው እንጂ እኔ ቀጥዬ፣
ልብሽ ከገፋኝ አልመለስም ካንቺ ልብ ስር፣
ስንዴ ተዘርቶ አይታጨድም በቆ'ሎ ምስር፣
በብቸኝነት ደግ መቃብር በመጎዳት ሳጥን ታሽጌ፣
አልሞትኩም አለሁ በጤና አፈሩን ገለባ አድርጌ፣
በጎረበጠው በዛሬው ፍዳ ስሬ ከሌለሽ፣
ታዲያ ያማረው ውቡ ነገ ላይ ምን ትሰሪያለሽ?
የነገን አላውቅም አልልም አልዋሽም፣
ሲጎለኝ ከሌለሽ ሲሞላ አላውቅሽም።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ቀን_ሲጥል
፧
ውጥንቅጥ ነው የአለም ጉዞ ጎርባጣ ነው አይመችም፣
አለኝ ያልኩት ቢርቀኝም መኖር ቅሉ ቢሰለችም፣
አምኖ ማጣት ድቅቅ አርጎ ቢሰልቀኝ፣
ሙሉ ተስፋ ያረኩበት እየጠፋ ቢያሳቅቀኝ፣
ቢከፋኝም ሳቅ ብዬ አለሁ በቀኝ፣
ምቱኝ ስቃለሁ እቀፉኝ ስቃለሁ፥
ጣሉኝ ስቃለሁ አንሱኝ እስቃለሁ፣
"ጥርስ" ወዳጅና ጠላት መሀከል የሚገኝ
ድልድይ ነው አውቃለሁ፣
ህይወት ካለኝ ቀን ያነሳል ቀን ይጥላል፣
መኖሬንም አላቆምም መሳቄም ይቀጥላል፣
ምክንያቱም...
ሲከፋኝ በኔ ለቅሶ ለሚያለቅሱ ወዳጆቼ፣
ለእነሱ ስል...
መከራዬን ዋጥ አርጌ እስቃለሁ ሁሉን ትቼ፣
በኔ እንባ ለሚስቁ ለሚወዱኝ ጠላቶቼ፣
ሲያምራቸው ይቅር...
ፈገግታ እንጂ እንባ አይወርድም በጉንጮቼ፣
ለምን ሲባል ልሰባበር? ቻል አርጌ ልቁም በግድ፣
በቀላሉ ይሰበራል ያልጎመራ የእፅዋት ግንድ፣
በእኩል ሚዛን ሁሉን ውድድ ሁሉን ፍቅ'ር፣
ለምን ብዬ ትናንት ላይ ቆሜ ልቅር፣
እጓዛለሁ እሄዳለሁ ካሰብኩበት እስከምደርስ፣
ህይወት ቀለበት ናት ዙር ገጥሜ እስክፈርስ፣
አጭር ነው አውቃለሁ
እስከዛ ግን እስቃለሁ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ስምሽን_ቀይሪ
፧
በፍቅር ስንቱ ራሱን አጠፋ፣
በፍቅር ስንቱስ አገኘ ተስፉ፣
በፍቅር ስንቱ ከሲኦል ተዳኘ፣
በፍቅር ስንቱ በገነት ተገኘ፣
ይህ ሁሉ በፍቅር ምክንያት
መሆኑን እየተረዱ፣
ቤተሰቦችሽ ምነው ግን
ፍቅርን በስም ነገዱ፣
ካልጠፋ የስም ግትልትል
ፍቅር ላይ "በ" ተጨምሮ፣
"በፍቅር" የሚል ሀረግን
ያገኛል የሚያይ አትኩሮ፣
ሀረጉን አረፍተነገር ለማድረግ
ስለከበደው፣
ተማሪው "በ"ን እያጠፋ "ፍቅር"
ይልሻል ሳይገደው፣
ሰው ሁሉ "ፍቅር" እያለሽ
ውዱ ቃል ስለቀለለ፣
አፍቃሪሽ አይታወቅም
በስምሽ እያታለለ፣
የወጣልሽን ተይና ቀይሪው
"ናፍቆት" በሚል ቃል፣
አፍቃሪሽ "ፍቅር" ይልሻል
ሌላው ባ'ዲሱ ይዘልቃል።
ገጣሚ✍️
#ካሳሁን_ክንፈ
#በ_ድምፅ_መስማት_የምትፈልጉ
Join👇
@getemk2g
425
#አምናለሁ
፧
እንዳላቅፍሽ ረጅም እጅ አልታደልኩም፣
እንዳላይሽ የንስር ዓይን አልተከልኩም፣
እንዳልመጣ እግር አጠረኝ ለመሮጥም፣
ወዳንቺ እንዳልጓዝ ቆሽቴ አረረ በውሃ ጥም፣
ለጥምቀት ያልሆነ...ብዬ ላንቺ ሳወጣው አደፈ፣
ሆድ ባሰኝ ስላልተሳካ እንባዬ ከዓይኔ ረገፈ፣
አንቺን እንጂ..... ያንቺን ጠረን አላወኩም፣
ማፍቀር እንጂ... ፍቅርን ማየት አልታደልኩም፣
አለቀለኩት በእንባዬ ልብሴ ከሀር አማረ፣
ጠጣሁት ቆሽቴ ራሰልኝ የጥማት ቃጠሎ ቀረ፣
እጄን እንባዬን ቀባሁት ረዘመልኝ አደገ፣
ያጠረው እግሬ ተመዞ መሮጥን ልምዱ አደረገ፣
ሀሳቤ ሙሉ ተሳክቶ ጎዶሎው እንዲሞላልኝ፣
በየቀኑ አይንሽን እንዳይ ጭንቀቴ እንዲቀልልኝ፣
ወንድ ነኝ እኔ አላለቅስም አልልም በፍቅርሽ ሞቼ፣
አልቅሼ ክንፍ ካበቀልኩ መጣለሁ ሁሉንም ትቼ፣
ስታለቅሽ አይዞሽ እንድልሽ ስትስቂ አብሬ እንድስቅ፣
የናፈቅሽኝን አቅፌ ከፍቅርሽ ጠረን እንዳ'ርቅ፣
በድምፅሽ እየተፅናናሁ ህይወቴ እንዲለመልም፣
ህይወቴ እንዲበራልኝ መኖሬን ካንቺጋ ላልም፣
መራራቅ ፍቅር ያስርባል በናፍቆት ያመነምናል፣
ተስፋ መፋቀር እስካለን ሁሉም በጊዜው ይሆናል፣
ሁሉም በቀኑ ይሆናል።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#እናቴ_ነህ
፧
ከየቱ ልነሳ?
ድሮ ከነበረው ከቆንጅዬው ፎቶ? ወይስ
እኔን ለማሳደግ እታች ላይ ስትል ፀዳልህ ተከፍቶ?
መልኬ ያንተ እኮ ነው ካንተ እየተቀዳ ለኔ እየተሰጠ፣
ያንተ እየጎደለ እኔን እየሞላ በውበት ያስጌጠ፣
መመኪያዬ ክብሬ ስኬቴን ነው እንጂ ጥቃቴን አትወድም፣
ልዩ ነህ አባቴ ስትገስፀኝ ደሞ እንደታላቅ ወንድም፣
የደከመክበትን ፍሬ እስክትበላ ይጠብቅህ ጌታ፣
ተከፍሎ ባያልቅም ጦሬህ እንዳቃልል የአንተን ውለታ፣
ለኔ መኖርህን በፍፁም አልክድም፣
አባቴ እናቴ ነህ ክፉህን አልወድም።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ዕዳ_አለብኝ
፧
የዘጠኝ ወር የቤት ኪራይ ዕዳ አለብኝ፣
አከራዬን እንዳላጣት እንቅፋትም አይንካብኝ፣
ድህነቴን ሳትፀየፍ ደህንነቴ ሁሌ ጭንቋ፣
የኔ ሰላም ሰላሟ ነው የኔ ደስታ ለሷ ሳቋ፣
አለብኝ ውዝፍ ዕዳ ተጠራቅሞ ያልከፈልኩት፣
ቢከፈልም የማይጨረስ መጠኑንም ያላወኩት፣
ደግ አከራይ መስጠት እንጂ መቀበልን የማትሻ፣
የፍቅር ጥግ ምሳሌዋ መጠለያ ናት መሸሻ፣
ሳትቀየር በጉድለቴ የምትወደኝ ሳትሰለች፣
የዘላለም ስጦታዬ ደጓ አከራይ እናቴ ነች።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join👇
@getemk2g
425
#ልቆጣሽ_ነው
፧
ልቆጣሽ ነው ዛሬስ እጅጉን ነዶኛል፣
እንዳይከፋሽ ብዬ መሳቄ ከብዶኛል፣
ሁሌ የምስቀው ሁሌ ሞልቶ አይደለም፣
እያልኩ ነው እንጂ ካንቺ ሚበልጥ የለም፣
መች ሳይከፋኝ ቀረ ሆድ ብሶኛል እኔ፣
በሳቅ ይደበቃል መከፋት ማዘኔ፣
እወቂው የኔ ዓለም ዘወትር አይሞላም፣
ያልበሰለ ፍሬ ያለቀኑ አይቀላም፣
ለሁሉም ጊዜ አለው እስኪሞላ ልሳቅ፣
በጥርሴ ከለላ ንዴቴን ልደብቅ፣
ሆድ ባህር ከሆነ ሁሉን ስለሚችል፣
ስለከፋኝ ብቻ ለቁጣም አልቸኩል፣
ሁሌ የምስቀው ሁሌ ሞልቶ አይደለም፣
እያልኩ ነው እንጂ ካንቺ የሚበልጥ የለም፣
ማን እንደዝምታ ማን ጭጭ እንደማለት፣
አስከፍቼሽ ደሞ እኔው ከምፀፀት፣
ራሴን ነው እንጂ አንቺን አልቆጣም፣
ትዕግስቴ እስኪሟጠጥ ከመሳቄ አልወጣም፣
እኔ አንቺን አልከስም ስጣላ ከራሴ፣
ሌላውን ሆድ ይፍጀው ብቻ ዕድሜ ለጥርሴ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join
👇👇👇
@getemk2g
425
#አከተመ
፧
ሁሉ ሞልቶለት የኖረ ጎሎበት ቀን ይጥለዋል፣
እንደነገሩ ሲፈታ ማጣትን የሚያውቅ ያውቀዋል፣
ሞላልኝ እያልኩ ሲጎለኝ አገኘሁ እያልኩኝ ሳጣ፣
መኖሬ እየመረረኝ ፊቴ በሀዘን ገረጣ፣
ሬት ስለበዛብኝ ማርን እላለሁ ይመራ'ል፣
የፈላ ወተት የፈጀው ቀዝቃዛ ውሃን ይፈራል፣
በነፃው ፍቅራችን መሃል የማጣሽ እመሰለኝ፣
ነገዬን ካንቺጋ ሳየው ትላንቴ እየከለለኝ፣
የሰይጣን ጆሮው ይደፈን...
ይያዘው የብርድ ቆፈን...
መለ'የት ስለማይታሰብ የፀናን ባለበት ቦታ፣
ስለሆን የአንድ ሳንቲም ውበቱ ሁለት ገፅታ፣
አንወድቅም በመለያየት የለንም ብሎ 'አከተመ'፣
ቢወድቅም አይሰበርም ተማምኖ በፍቅር የቆመ።
ገጣሚ✍
#ካሳሁን_ክንፈ
Join
👇👇👇
@getemk2g
425
#ልደቴ
፧
የታለ ስጦታ የታል ያ መወደድ?
ብርቅ አልነበረ እንዴ የእኔ መወለድ?
ያ ሁሉ ተረሳ ቤተሰቦቼም ልደቴን ዘነጉት፣
መኖር ና ጉጉት ልጅነቴን ዘጉት፣
----------------
ሲታየኝ የፊቱ ቀድሜ ስረዳው፣
ለዛ ነው በለቅሶ አይኔ የፈነዳው፣
ቢቻል ኖሮ መምረጥ መኖሬ ካልቀረ፣
ከእናቴ ሆድ ውስጥ አልወጣም ነበረ፣
---------------
አምጠው ካመጡኝ እኔ ከለመድኩት፣
ከኖርኩበት ምቾት ቀድሜ ካወኩት፣
ግድ የለም ልልመደው መኖሬ አልታቀበ፣
ልደቴን ቆጥራለሁ ሞቴ እየቀረበ።
#መልካም_ልደት_ለኔ🎂
ገጣሚ
#ካሳሁን_ክንፈ
Join
👇
@getemk2g
